July 13, 2009

ስብሰባው ያለምንም ውሳኔ ተበተነ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 13/2009)
ዛሬ ጠዋት የጀመረውና አቡነ ጳውሎስን “ሲለምንና ሲማጸን” የዋለው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ያልምንም ውሳኔ፣ የፓትርያርኩ ዉሳኔም ሳይቀለበስ መበተኑን የደጀ ሰላም ሪፖርተሮች ከሥፍራው አስታውቀዋል።
ገና ከጠዋቱ ሕገ ቤተ ክርስቲያንና የስብሰባ ደንብ ያልነበረው ጉባዔው “እርስዎ መሰብሰብ አይችሉም” ማለት ሲገባው ያንን ሳያደርግ በመቅረቱ ሲታመስ ውሎ ንፋስ እንደገባው አቧራ ተበትኖ አድሯል። ከ45 ያላነሱ ቅ/ሲኖዶስ አባላት የተገኙበት ይህ ጉባዔ በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣን በይፋ ለፓትርያርኩ በማስረከብ “ቅዱስ ሲኖዶስን ያፈረሰ ጉባዔ ተብሎ ሊጠቀስ ይገባዋል” የሚሉ አሉ።
በነገሩ የተበሳጩት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ስብሰባውን ጥለው ሲወጡ እነ አቡነ ገብርኤል ደግሞ ለቅዱስነታቸው የሥልጣን ዘመን መርዘም ሲከራከሩ ተሰምተዋል። ባለፈው ሳምንት የስብሰባ ሒደት የፓትርያርኩ”ደጋፊ” ተብለው የተፈረጁት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከሌሎቹ በተሻለ ሕግንና የስብሰባ ሥርዓትን ለማስጠበቅ ሲሞክሩ ውለዋል ተብሏል።
ነገሩ በዚሁ ስላለቀ፣ ነገ ማክሰኞም የአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ በዓለ ንግስ በመሆኑ ስብሰባው ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም።
ደጀ ሰላም በበኩሏ “ምንም የማይሳነው፣ ታሪክን መለወጥ የሚችለውን አምላክ ተስፋ እናድርግ፣ ቸር ወሬ ያሰማን” ትላለች ።

ደጀ ሰላም በበኩሏ “ኢታርዕየነ ሙስናሃ ለቤተ ክርስቲያን - የቤተ ክርስቲያንን ጥፋት አታሳየን፤ ምንም የማይሳነው፣ ታሪክን መለወጥ የሚችለውን አምላክ ተስፋ እናድርግ፣ ቸር ወሬ ያሰማን” ትላለች ።

6 comments:

Anonymous said...

ስብሰባው ያለምንም ውሳኔ ተበተነ አላችሁ? እውነት ነው ምንም ቁም ነገርና መልካም ስራ ባሁኑ ዘመን ከማንም መጠበቅ አያስፈልግምና ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያናችን ለእውነት የቆመና አላማ ያለው አበት የላትምና ይህንን ስል ግን በጣም እያዘንኩና እራሴንም እየወቀስኩ ነው። እያንድነዱ ሊቀ ጳጳስ ዛሬ የሚናገሩትና ነገ የሚናገሩት በጣም የተለያየና አሳፋሪ በመሆኑ ለሁሉም ግን ለአባቶቻችንም መልካም ስራ ሰርተው ቤተ ክርስቲያኗንና መንጋውን በቅንነት አገልግለው እንዲያልፉ እኛንም ከመፍረድና እንዲህ ተባለ እንዲህ ሆነ ከማለት ይጠብቀን። ግን ይህ ሁሉ የእኛ ሃጢአት ብዛት ነው አበው ምን ይላሉ መሰላችሁ የሰዎች ሃ ጢአት ሲበዛ "...እግዚአብሔር ሕዝቡን ሊቀጣ ሲያስብ እግዚአብሔርን የማያውቅ ጨካኝ ገዥ ያስነሳል።" ይላሉ እናም እግዚአብሄር ለቤተ ክርስቲያነችን መልካሙን ነገር ያድርግልን ከውጭ ጠላት ሳይሆን ከውስጥ ጠላት ይጠብቅልን። አሜን

Yiferdal said...

Thank you deje selam for update information.I really disappointed by the Holy sinod members. are they our representative? i have no word to say any thing. Every churh members GOd can change with in a mimit please pray.

ኃ/ሚ said...

ቤተ ክርስቲያን ሆይ ደጆችሽ አይዘጉ
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዛሬ በዙሪያዋ ስንት ችግሮች ተጋርጠውባትና ከበዋት ባለችበት ሁኔታ ውስጣችን እንዲህ መሆኑ አሳዛኝ የትውልድ ታሪክ ነው። ይህንን ስብራት ባለቤቱ ራሱ ይታደጋት።
ቸር ያሰማን

Anonymous said...

ስለዚች ቤተክርስቲያን ሰላም እባላችሁ በያለንበት እንፀልይ በየአብያተክርስቲናቱ በየገዳማቱ ምህላ ፀሎት ይድረስ ወደ ሰው ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር እንጩኽ ለሰባት ቀን እናልቅስ ቤተክርስቲንን የምትወዱ ሰዎች እባካችሁ አልቅሱላት በአንድነት በሕብረት አናልቅስ በእውነት ለሰባት ቀን በያለንበት እንጸልይ ዳዊት እንድገም በትረድንግል ነኝ ወላዲተአምላክ መፍትሄውን ትስጠን አሜን

Unknown said...

Hello Deje Selam,
I have been following ur news and it was giving me a clue about what is going on in our church.But today's news is different from what Awramba times published it.
Awramba times published that Abune Paulos has been forced to leave his power. Please Check it on EMF and tell us the truth.
Either u r conveying a wrong message or Awramba is doing it.

Anonymous said...

Deje-selam's news corresponds with today's VOA news. Addisu said "No agenda found a resolution" and many of the fathers are not willing to talk to him on the phone.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)