July 25, 2009

አቡነ ቄርሎስ የቤተ ክህነት ግቢን ለቀቁ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 25/2009)
በማፊያ ቡድን አባሎችና ወረበሎች መኖሪያቸው የተሰባበረባቸውና በሕይወታቸው ላይ አደጋ የተቃጣባቸው አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ለደህንነታቸው በመስጋት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢን ለቅቀው እንደወጡ የቅርብ ምንጮች ገለፁ።

የቅዱስ ሲኖዶስ የበላይነት አልቀበልም ብለው በማስፈራራትና በሀይል ጭምር አጀንዳውን ጠምዝዘው ጊዜያዊ እፎይታ ካገኙት ፓትርያርክ ጋር በገቡት አለመግባባት የግል ቂም ተይዞባቸው አደጋ የተጣለባቸው ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ሰሞኑን የጠቅላይ ቤተ ክህነትን ግቢ ለቅቀው የወጡ ሲሆን አንዳንዶች ወደ ሀገረ ስብከታቸው ወደ ወሎ መሄዳቸውን ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ እዚያው አዲስ አበባ ከሰዎች ዘንድ ማረፋቸውን ተናግረዋል።

“ለሕይወቴ ደህንነት አይሰማኝም” እንዳሉ የተጠቆመው ብፁዕነታቸው ዕቃቸውን ጠቅልለው ሲወጡ መታየታቸው ሲዘገብ ሌሎች አባቶችም ቢሆኑ በተመሳሳይ የደህንነት ስጋት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። የደጀ ሰላም ምንጮች ጨምረው እንደተናገሩት የፓትርያርኩ ወዳጆች የተባሉት ሳይቀሩ በፍርሃት መያዛቸው ሲነገር ፓትርያርኩ ይቃወመኛል የሚሉት ላይ አደጋ ከማስጣል አይመለሱም የሚለው ጉዳይ እያደገ መምጣቱ ታውቋል።

28 comments:

Anonymous said...

PAtriyariku, before doing something or getting worst let do something .my comment ,we have to start collecting petition abut this situation and send to Ethiopia embassy and sister churches. What do you think? I don't know what we have to do.
God bless you Deje selamsl

Anonymous said...

ሌሎቹም ያን ግቢ ለቀው ቢወጡ ነው
የሚሻለው የሰው ጅቦች ነግሰውበታልና

zemecha said...

አሌ ለክሙ ፍሩሃን ጳጳሳት
“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሄርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጰጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ”ሥራ20፣ 28

ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ የተሾማችሁ ብጹዓን አባቶች ስልጣናችሁ ረቂቅ እውቀታችሁ ምጡቅ መሆኑን አውቃለሁ ውሃም አሻቅቦ አይፈስም ነው የሚባለው በዘመናችን ግን ሰዎች ቴክኖሎጂውን ተጠቅመው ሽቅብ እንዲፈስ ሲያደርጉት እናስተውላለን እኔንም እንደ እግር ውስጥ እሳት የሚያንገበግበኝ የቤተ ክርስቲያን ነገር ወደ ላይ አሻቅቤ እንድመለከት ግድ አለኝ እናንተም የማነው ደፋር እንደማትሉኝ ተስፋ አለኝ “ለአባቶች አይጠቅሱም ለአንበሳ አይመትሩም” ካልተባለ በስተቀር የቤተ ክርስቲያን የአጥቢያ ኮከብ የሆነው ሀዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩ ጢሞቴዎስን “ማናም ታናሽነትህን አይናቀው” ብሎትስ የለ ስለዚህ በታናሽነቴ ምክንያት የማስተላልፈውን መልእክት እንደማትንቁትና ቸል እንደማትሉት እርግጠኛ ነኝ ፡፡ይህ ወቅት ለቤተ ክርስቲያናችን ፈታኝ ወቅት ነው እናንተም ካላችሁ ስልጣንና ክብር ወርዳችሁ ቤተ ክርስቲያንም የጠላቶችዋ መሳለቂያ እየሆነች ነው ከዚህ ባለፈ የባሰ ከመሆኑ በፊት ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ አበው ዛሬ እውነታውን የምንነጋገርበት እናንተም በእውነት ያለፍርሃት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሽንጣችሁን ገትራችሁ የምትሙዋገቱበት ወቅት፣ ካስፈለገም መስዋእትነትን የምትከፍሉበት ወቅት ነውና ከወዲሁ በልጅነት መንፈስ ለአባቶቼ ለእናንተ ይህን መልእክት ልጽፍ ልቤን አተጋሁ

በጥምቀት ወልዳ፣ በትምህርት አሳድጋ፣ ማዕረገ ክህነትን ሰጥታ አሁን ላላችሁበት ታላቅ መንፈሳዊ ክብር ያበቃቻችሁ እምነ ቤተ ክርስቲያን አሁን ያለችበትን ሁኔታ መቼም ላልሰማ በግልባጭ ለማሰማት ካልሆነ በስተቀር ለእናንተ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ይሆንብኛል በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ “የጥንትዋ ቤተ ክርስቲያን ሞዴል”እየተባለች እንዳልተጠራች ዛሬ ግን ሁላችን እንደምናውቀውና የአደባባይ ምስጢር እንደሆነ ሁሉ የጠላቶችዋ መሳለቂያ የልጆችዋ አንገት መድፊያ ለመሆን በቅታለች ይህ ሁሉ የሆነው እግዚአብሄር አእምሮውን ለቦውን ስሎ ለንስሐ ያብቃቸውና! በብጸዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና ነው ቅዱስነታቸው አምስተኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው በተሰየሙ ግዜ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ፀሓይ ወጣላት ተብሎ ነበር ኋላ ላይ በተግባር የታየው ግን ወጥታላት የነበረችው ፀሃይ ጠልቃባት በጽልመት መንጦላእት ተጋርዳ በድንግዝግዝ እንደምታይ ነው የሆነችው መቼም እግዚአብሄር በደሙ የዋጃት ናትና ስለማይተዋት በዚህ በከፋውና በከረፋው ግዜም የቤተ ክርስቲያን ጠበቆችን ማስነሳቱ አልቀረም

የቤተ ክርስቲያኒቱ ምእመናን በሀገር ውስጥም በውጭም ያለው በአባቶች ላይ ያለው እምነት እየተሙዋጠጠ ባለበት በዚህ ፈታኝ ወቅት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ከዚህ በኋላስ ስለ ቤተ ክርስቲያን ዝም አንልም አይናችን እያየ ቤተ ክርስቲያኒቱ የወንበዴዎች ዋሻ ሆና ስትጠፋ ዝም ብለን ዓናይም በማለት እንደ ቀደሙት አባቶች እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሆናችሁ ምእመኑን ያስደመመ ታላቅ ውሳኔ በማድረጋችሁ ያልተደነቅ እውነተኛነቱንም ያልተጠራጠረ አልነበረም ቢባል ማጋነን አይሆንብኝም በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሙሉ ድምጽ የጸደቀው ውሳኔ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ደምዋን እየመጠጡ ላሉት የቅዱስ ፓትርያርኩ ዘመዶችና የእርሳቸው አፋሽ አጎንባሾች የመርዶ ያህል አስደንጋጭ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው በመሆኑም ባለ በሌለ ሓይላቸው ይህን በአባቶች ላይ የተፈጠረውን የመነቃቃት መንፈስ ለማዳፈን ያደረጉትን የውንብድና ተግባር በመገናኛ ብዙሃን ደርሶናል

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በራስዋ ልጆች መመራት ከጀመረችበት ባለፉት ሃምሳ አመታት እንኩዋን ሊፈጸም ሊታሰብ የማይገባው አስነዋሪ የውንብድና ተግባር በቅዱስ ፓትርያርኩ አፈ ቀላጠዎች በብጸዓን አባቶች ላይ ተፈጽሙዋል ለነዚህ ወሮ በሎች ኃይልና ብርታት የሆናቸው የአንዳንድ ጳጳሳት በፍርሃት ከአላማ ማፈግፈግ መሆኑ አሌ የማይባል እሙን ነገር ነው ፖለቲካዊ ስልትን የስልጣናቸው ማራዘሚያ አድርገው የሚጠቀሙት ቅዱስ ፓትርያርኩ በዘመዶቻቸውና በጥቅመኞቻቸው እንዲሁም በቤተ ክርስቲያኒቱ ገንዘብ ባፈሩዋቸው ቅጥረኞች አማካይነት በአባቶች መካከል መከፋፈል መፍጠራቸው ለማፍያ ቡድኑ መጠናከር አስተዋጽኦ አድርጉዋል፡፡

ይህ የወሮበልነት ተግባር ከቅዱስ ፓትርያርኩ እውቅና ውጪ የተፈጸመ ነው ለማለት በጣም ይከብዳል ከቤተ መንግስት ባልተናነሰ መልኩ ከፍተኛ ጥበቃና ፍተሸ በሚደረግበት የቤተ ክህነት ግቢ ያለከልካይ የአባቶች መኖሪያን ቤት በር ከድብደባ አልፎ ሰብረው እስኪገቡ ድረስ እነዚያ ዓይናቸው እሳት የሚተፋ የሚመስለው እንኩዋን ግቢው ተገብቶ በውጭ እንኩዋን የሚያልፈውን ቀልብ የሚነሱ የቤተ ክህነት ጠባቂዎች አስቀድመው ሀበተ እንቅልፍ ታድሉዋቸው ነበር ካልተባለ በስተቀር የዚያን ቀን ስለሆነው ሳይሰሙ ሳያዩ የቀሩት ደግሞስ ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ በቪኦኤ እንደተናገሩት አሳፋሪው ትእይንት እንዳበቃ ቅዱስ ፓትርያርኩ ወዲያው ወደ መድረኩ መውጣታቸውና ድርጊቱ የተፈጠመባቸውን አባቶች ማነጋገር አንድ መልእክት የለውም ትላላችሁ? ከዚህ የባሰ እንዳይደርስብህ እወቅበት ለማለት አይመስላችሁም?

በማፈያው ቡድን ማስፈራሪያም ሆነ በመንግስት ግፊት ለግዜው እንደ ሎጥ ሚስት ወደ ኋላ በመመመለሳችሁ የእናንተ ማፈግፈግ በብጸዓን አባቶች ላይ ይህ ጥቃት እንዲቃጣባቸው ምክንያት ሆንዋል ይህ ነግ በእኔ መሆኑን አትዘንጉ ከዚህ በኋላ ወደ ኋላ ብትመለሱ የከበራችሁባትና ለዘላለምም በምትከብሩባት ቤተ ክርስቲያናችሁ እድል ፈንታ ጽዋ ተርታ አይኖራችሁም ለግዜው በቅዱስ ፓትርያርኩ መንግስት የከበሬታ ወንበር ልታገኙ ትችሉ ይሆናል ይህም ቢሆን ለግዜው ነው ዘላቂ ጥቅም እንጂ ዘላቂ ወዳጅ የሌላቸው ቅዱስነታቸው የተነሳባቸውን የተቃውሞ ማዕበሉን በእናንተ ጀልባነት ቀዝፈው ከወጡ በኋላ እንደ አሮጌ ቁና አሽቀንጥረው ባይጥሉዋችሁ ከምላሴ ጸጉር ይነቀል! በእናንተ ፍርሓት የማፈያው ቡድን ተጠናክሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የሚነግስ ከሆነ ከእንግዲህ አባቶቻችን ብለን እናንተን ለመጥራት እንቸገራለን ለያዛችሁት ታላቅ ማዕረገ መዋረድ ካልተቆረቆራችሁ ጵጵስናውን በገዛ እጃችሁ አሽቀንጥራችሁ እንደወረወራችሁት ቁጠሩ ስለዚህ ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ክብር ከቆሙትና ስለእርስዋም መከራ እየተቀበሉ ያሉት አባቶችን በግብር ምሰሉዋቸው እናንተ ዛሬ መከራ ይገጥመናል ብላችሁ ቤተ ክርስቲያንን ዙሪያዋን ከቦ እያፈረሳት ላለው ወንበዴ ቡድን ሃይል ድምጽ ሆናችሁ ብትገኙ ታሪክ ይፋረዳችሁዋል እኛም የቤተ ክርስቲያን ጠበቆች ሳትሆኑ የቅዱስ ፓትርያርኩ አሻንጉሊቶች መሆናችሁን ተገንዝበን አባትነታችሁን እንፍቃለን ይህ እንዳይሆንና ታሪክ እንዳይበላሽ ለሐዋርያት ጥባት የሰጠ አምላክ ለእናንተም ድፍረቱን ይስጣችሁ እላለሁ

Anonymous said...

የተከበራችሁ የደጀ ሰላም ደንበኞች በውነት ንጹሐን ኦርቶዶክሳውያን ከሁናችሁ ምን ዐለ ስለ ቤተ ከርስቲያናችሁ ብትጸልዩ ማውግዙ ትታችሁ በከፋት ሰይጣንን በልጥችሁት እና ንስሐ ግቡ ምክንያቱ ብዙ ሕዝበ ክርስቲያን ኣሳዝናችሁ ወደ ሌላ እምንት እየነዳችሁት ነው የናንተው መላ ምት ዋጋ የለውምና ማን እንደሆናችሁም ትታወቃላችሁና ኣሁንም ኣምላክ ይወዳችኋል ተምለሱለት ፤ ቅዱሳን ኣባቶቻችሁ ስለ ሰደባችሁ የጸደቃችሁ ኣይምሰላችሁ የልቁንም እናንተና ዘራችሁ ሁሉ እያስረገማችሁ ነው።
ለኣዲሱ ትውልድም ክፋት ኣታስተምሩት ከሁሉ በበለጠ ክዚህ ኣገር የተወለዱተ ኣንበርዛቸው ይልቁንስ ቅድሱ ኦርቶዶክሳዊ እምነታችን እና ክቡር የሆነውን ባህላችን እናውርሳቸው እንጂ፡

Anonymous said...

የተከበራችሁ የደጀ ሰላም ደንበኞች በውነት ንጹሐን ኦርቶዶክሳውያን ከሁናችሁ ምን ዐለ ስለ ቤተ ከርስቲያናችሁ ብትጸልዩ ማውግዙ ትታችሁ በከፋት ሰይጣንን በልጥችሁት እና ንስሐ ግቡ ምክንያቱ ብዙ ሕዝበ ክርስቲያን ኣሳዝናችሁ ወደ ሌላ እምንት እየነዳችሁት ነው የናንተው መላ ምት ዋጋ የለውምና ማን እንደሆናችሁም ትታወቃላችሁና ኣሁንም ኣምላክ ይወዳችኋል ተምለሱለት ፤ ቅዱሳን ኣባቶቻችሁ ስለ ሰደባችሁ የጸደቃችሁ ኣይምሰላችሁ የልቁንም እናንተና ዘራችሁ ሁሉ እያስረገማችሁ ነው።
ለኣዲሱ ትውልድም ክፋት ኣታስተምሩት ከሁሉ በበለጠ ክዚህ ኣገር የተወለዱተ ኣንበርዛቸው ይልቁንስ ቅድሱ ኦርቶዶክሳዊ እምነታችን እና ክቡር የሆነውን ባህላችን እናውርሳቸው እንጂ፡

Anonymous said...

የተከበራችሁ የደጀ ሰላም ደንበኞች በውነት ንጹሐን ኦርቶዶክሳውያን ከሁናችሁ ምን ዐለ ስለ ቤተ ከርስቲያናችሁ ብትጸልዩ ማውግዙ ትታችሁ በከፋት ሰይጣንን በልጥችሁት እና ንስሐ ግቡ ምክንያቱ ብዙ ሕዝበ ክርስቲያን ኣሳዝናችሁ ወደ ሌላ እምንት እየነዳችሁት ነው የናንተው መላ ምት ዋጋ የለውምና ማን እንደሆናችሁም ትታወቃላችሁና ኣሁንም ኣምላክ ይወዳችኋል ተምለሱለት ፤ ቅዱሳን ኣባቶቻችሁ ስለ ሰደባችሁ የጸደቃችሁ ኣይምሰላችሁ የልቁንም እናንተና ዘራችሁ ሁሉ እያስረገማችሁ ነው።
ለኣዲሱ ትውልድም ክፋት ኣታስተምሩት ከሁሉ በበለጠ ክዚህ ኣገር የተወለዱተ ኣንበርዛቸው ይልቁንስ ቅድሱ ኦርቶዶክሳዊ እምነታችን እና ክቡር የሆነውን ባህላችን እናውርሳቸው እንጂ፡

Anonymous said...

abyetu aednen men zemen lay deresen? leka endih nachew? egziabhere ehyann chlo new zm yalew? ygermal patriyarku papasatn kasdebdebu bhula beziaw seat ebytachew hiydew teyekuachew lemn? memot aelememotachewn lemaregaget new? ygermal abune pawlos neger mndnew teblew byteyeku sltanna genzeb blew endemilu alteraterm yememenu guday kemegemeriam gemro gudayachw aydelem ahunm egziabher egun zrgtual enamesegnewalen lk endesachw yalu besiatl malet baamyrican and menekusy ale ybalal kefafleh gza ataralehu trmsu lesost aemet yahl new ybalal zemenu aelkual ena eyandandu lerasu yalks ysely le byte krstian yalks

Tefera MD said...

ለስብሰባው የመጡት ሊቃነ ጳጳሳት ሁሉ ወደ ሃገረ ስብከታቸው እንደተመለሱ ሁሉ አቡነ ቄርሎስም ወደሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል። ከጥቂት ሰዓታት በፊት አነጋግሬያቸው ነበር ዜናው ፍጹም ውሽተ ሲሆን በራቸው የተሰበረ ማግስት ብቻ ነው ቤተሰብ ጋር ያደሩት እንጂኢ ሁኔታው ደጀ ሰላም እንደሚዋሸው አይደለም።

Anonymous said...

Dear Deje Selamoch, would you, PLEASE, consider the comment posted by someone above and I pasted here. የተከበራችሁ የደጀ ሰላም ደንበኞች በውነት ንጹሐን ኦርቶዶክሳውያን ከሁናችሁ ምን ዐለ ስለ ቤተ ከርስቲያናችሁ ብትጸልዩ ማውግዙ ትታችሁ በከፋት ሰይጣንን በልጥችሁት እና ንስሐ ግቡ ምክንያቱ ብዙ ሕዝበ ክርስቲያን ኣሳዝናችሁ ወደ ሌላ እምንት እየነዳችሁት ነው የናንተው መላ ምት ዋጋ የለውምና ማን እንደሆናችሁም ትታወቃላችሁና ኣሁንም ኣምላክ ይወዳችኋል ተምለሱለት ፤ ቅዱሳን ኣባቶቻችሁ ስለ ሰደባችሁ የጸደቃችሁ ኣይምሰላችሁ የልቁንም እናንተና ዘራችሁ ሁሉ እያስረገማችሁ ነው።
ለኣዲሱ ትውልድም ክፋት ኣታስተምሩት ከሁሉ በበለጠ ክዚህ ኣገር የተወለዱተ ኣንበርዛቸው ይልቁንስ ቅድሱ ኦርቶዶክሳዊ እምነታችን እና ክቡር የሆነውን ባህላችን እናውርሳቸው እንጂ፡

I do not think you are doing the right thing to tackle the current problem. Please,re-consider what you are doing. Is that the only way to contribute to your mother Church. I still believe you are children of the church but making a graving mistake in the process. Why you are not using this opportunity to open discussion that focus on our real problems and brain-storm what we the memenan can do for the church and leave the personal issues and internal problems resolved by another means? Please, PLEASE, PLEASE, PLEASE, PLEASE, PLEASE, ...Yekir yeblen

Anonymous said...

Tefera MD said...

“ለስብሰባው የመጡት ሊቃነ ጳጳሳት ሁሉ ወደ ሃገረ ስብከታቸው እንደተመለሱ ሁሉ አቡነ ቄርሎስም ወደሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል። ከጥቂት ሰዓታት በፊት አነጋግሬአቸው ነበር ዜናው ፍጹም ውሸት ሲሆን በራቸው የተሰበረ ማግስት ብቻ ነው ቤተሰብ ጋር ያደሩት እንጂኢ ሁኔታው ደጀ ሰላም እንደሚዋሸው አይደለም።”
“የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያወልቅ”

ውድ ደጀ ሰላማውያን ሰላም ይብዛላችሁ። መቸም በዚህ ወቅት በቤተ ክርስቲያን ላይ በተፈጠረው የታሪክ ጠባሳ ቆሽቱ ያላረረ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተካታይ የለም። አንድ ደጀ ሰላማዊ ቀደም ብሎ የቤተ ክርስቲያናችንን ውድቀት ከሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የ16ኛው መቶ ክ/ዘ ዝቅጠት ጋር አነጻጽሮ እንዳስነበበን አስታውሳለሁ።አዎ ልክ ነው የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ልክ አሁን በእኛ ቤተ ክርስቲያን እየተፈጸመ ያለውን ድርጊት አከናውነውታል። በስልጣን ሽኩቻ ጳጳስ ጳስስን አስደብድቧል፤መርዞ ገድሏል፤ አስገድሏል፤መማለጃ በመስጠት ስልጣን አደላድሏል፤በጎጥ ጵጵስናን ተቀብሏል እንዲያውም እኮ መንበረ ፖፑንም ወደ ፈረንሳይ የወሰዱበት ጊዜ ነበረ።ብቻ ምንም ያላደረጉት አልነበረም።ወዳጆቼ ቀጥታ ቅጁ እኛ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየሆነ ነው።ይህ ደግሞ የመጨረሻው ሞት ነው።በጣም የሚገርመኝ ነገር ይህን እያየን አንዳንዶቻችን በተለይ ከላይ ያነበብነውን አስተያየት የሚሰጡ እንደ እነ ‘Tefera MD’ ያሉ የሌባ አይነ ደረቆች መኖራቸው ነው። Tefera MD ለመሆኑ አንተን የቆጨህ ምኑ ነው? የአቡነ ቄርሎስ ቤተ ክህነት ግቢውን ለቅቀው ከዘመዶቻቸው ተጠግተው መኖራቸው? ወይስ በራቸው ተደብድቦ መሰበሩ? በወሮበሎች ዛቻ እንግርግሪያ መንገላታታቸው? ለህይወታቸው እንዲሰጉ መደረጋቸው? አንተዬ ከመቼ ወዲህ ነው የተንገላቱ ጳጳሳትን አነጋግረህ ለደጀ ሰላማውያን ዜና አብሳሪ የሆንኸው? አቡነ ቄርሎስን ምነው አሁን ብቻ አነጋገርሃቸው? ምነው በራቸው በተሰበረ ማግስት አነጋግረህ ስለ ጤንነታቸው አላካፈልኸን? አሁን በአንተ አስተያየት አቡነ ቄርሎስ ጉዳት አልደረሰባቸውም እየሆነ ያለውን ተቀብለውታል እያልኸን ይሆን? አንተ እንደምትለው ከሆነ ወይ አብረሃቸው ሀገረ ስብከታቸው ነው ያለኸው አለዚያም በስልክ የምትጠይቃቸው የቅርባቸው ነህ። እስኪ እንግዲያው አቡነ ቄርሎስ ስለ ተፈጠረው አጠቃላይ የሚሉትን አነጋግረህ አውሳን፤ በተለይ በመጨረሻው ቀን ስለ ተላለፈው ውሳኔ ያላቸውን ሐሳብ ግለጽልን በጥቅምት ስለሚካሄደው ስብሰባም ምን ውጤት ሊመጣ እንደሚችል ያላቸውን ሐሳብ ጨምረን። Tefera MD የምትለው ዘገባ እውነት ከሆነ ያቀረብኳቸውን ጥያቄዎች እንደምትመልስልኝ ተስፋ አደርጋለሁ እየዋሸህ ከሆነ ግን ወደ አእምሮህ ይመልስህ እላለሁ።

ቸር ይግጠመን፤ለእውነት የሚቆም ልብ ይስጠን

tad said...

I don't buy Teffera's argument because we have to show solidarity with Abune Kerlos and any other bishops who are suffering in the hand of the wicked Abune Paulos. So, is there any awy we can help Abune Kerlos, at least financially.
Thanks

kussarro said...

4th anonymous ! don't afraid to say wrong is wrong .

we have to pray ! also we have to say wrong is wrong.In church history there were such kind of pops.pap Lyon( on the councel of celcedon) is one of them . real fathers reject his 'Yeslttan temat'and his christology. my brother/sister how can we witness for truth with out saying wrong is wrong.
I believe , we couldn't judge someone as rightous or sinfull. It is GOD's authority.However, we can say someone's doing is right or wrong.this is not judgement. it is showing/indicating/ someone's mistake.
let me ask you ; let,you knew Hanania and his wife. They were your family in LORD . You got Hananiya and his wife befor they stand infront of Saint Peter. you were with buyer and you knew how much they sold their land and they told you wrong figure.you knew as they knew the purpus of selling their land . what would you say for them about the wrong amount?
christianity is life . not drama.
we need to seek answer for our day to day life.
MAY GOD BLESS OUR CHURCH !!!!!!!!

Tefera MD said...

በእኔ አስተያየት ላይ አስተያየት ለሰጠኸው ሰው። ጥያቄህ ጥሩ ነው ልመልስልህም ፈቃደኛ ነኝ። በአባቶች ቤት መሰበር ካዘኑትና አጥጥብቀው ከሚቃወሙት ሰዎች አንዱ ነኝ። አቡነ ቄርልልስ ቤታቸው በተሰበረ ማግስት በአሜሪካን ድምጽ ሬድዮ ቀርበው ስለ ጥጠንነአታቸው ራኣሳቸው ተናግረዋል። እሳቸው በእኔ ላይ ምንም ጉዳት አልደረሱአም እያሉ ደጀ ሰላም ግን በግድ ተጎድተዋል እያለች ነው ማንን ማመን እንዳለብን ግልጽ ይመስለኛል። ይልቁንስ መንግስት ይህን አደጋ ያደረሱ ሰዎችን እንዴአት ማወቅ ውቃተው የሚለው ላይብናተኩር ይሻላል። ቤተ ክርስቲያናችን ከመቸውም በላይ ተዋርዳለች ስለዚህ ውሸቱን ትተን እውነት እእንዲወጥጣ ብንጸልይና ብንታገል ይሻላል። እኔ አቡነ ቄርሎስን አደጋው መድረሱ በዜና ከመውጣቱም በፊት ሆነ ከዛም በኋላ አነጋግሬያቸዋለሁ። ይይህን አስተያየት ለመጽጻፍ ያስገደደኝ ከእውነት የራቀ ዜና በመተላለፉ ነው። የብፁዕነታቸውን ስልክ ቁጥር ደጀ ሰላም እንዳደረገችው ዌብ ሳይትት ላይ ለጥፌ የአባቶቼን ክብር ዝቅ አላደርግም። ወገኞቼ የአንድ ሊቀ ጳጳስ ስልክ ዌብ ሳይት ላይ ስትለጥፉ ያንን ስልክ ለእስላሙም ለጴንጥጠውም ለቤተክርስቲያን ጠላቶችም አሳልፋችሁ መስጠታችሁን የተረዳችሁ አይመስለኝም። እባካኣችሁ ጊዜያዊ ስሜታችንን በማስታገስ በማስተዋል እንንቀሳቀስ።

Salem said...

Shame on you Aba Gebriel, Gerima, and other bishops who collaborate with the mafia leader and groups. We have no place in our hearts for you as the spiritual fathers anymore. You know it the whole world is watching you what you do daily. Until justice prevails on our church we promise to expose everything about you. No kidding. If you are not belong to our church we are not belong to you. For the last 17 years we assumed you were doing what you were supposed to do. Now we know who you are, what you stand for and who you worship to. If you don’t stand for our church we stand against you. Trust me we are everywhere. In betekihenet, neges beal, marfia bet,…

Arise, O LORD; let not man prevail: let the heathen be judged in thy sight.
Psalms 9:19
O LORD our Lord, how excellent is thy name in all the earth!
Psalms 8:9

tad said...

To Teffera;
I can respond to you in Amharic because I don't have the Amharic letters access in my computer. Well, I hope you agree with me that we don't have to wail until he is hurt to help some body who fought the fight for all EOC members, if what you claim is trustworthy. Let focus on what we agree instead of nagging on the minor issues. Did the murderer went to Abune Kerlo's house to hurt him? No doubt. Did God protect him? Of course. So, God did his job,the murderes did their job, and let us do our job, to help the Archbishop.
Thanks

Tefera MD said...

I Agree with you Ted we need to figth to the truth. This is not political fight we dont need FUKERA like Selam. When we fight for the truth we have to follow Jesus. 'ጠላቶቻችሁን ውደዱ ፣ ለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ... እንዳል ጠላቶቻችንን ማሸነፍ ያለብን ወንጌልን መሳሪያ በማድረግ ነው ትግላችን ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከዲያቢሎስ አሰራር ጋር መሆን አለበት። ለዚህ ደግሞ ፓትርያርኩንም ቢሆን ስራቸውን እየተቃወምን የቤተክርስቲያኒቱ ህግ እንዲከበር መታገል እንጂ ጭፍን የጥላቻ ዘመቻ ብናደርግ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር አይሆንም። ነገ በቤተክርስቲያኒቱ የወደፊት እድል ላይ የሚወስኑ ብፁዓን አባቶች ተቀራርበውና ተስማምተው ህገ ቤተክርስቲያንን እንዲያስከብሩ የሚያቀራርብ ስራ መስራት እንጂ የሚያለያዩ ድርጊቶች ይቁሙ እላለሁ።

Anonymous said...

ሰላም አቁዋምሽና ስምሽሽ አብሮ ስለማይሄዱ ወይ ስምሽን አለበለዚያም አቁዋምሽን መለወጥ ይኖርብሻል። እግዚአብሔር በሽሾማቸው ላይ አፍሽን ማላቀቅሽ ከበረከት ይልቅ መቅሰፍትን ነው የሚያመጥጣው። ይህን አይነቱ ከደርግ የተወረሰ የመፈክር አይነት አነጋገር ከክርስቲያን ሥነ-ምግባር ውጪ ነው። ማን ያውቃል የመናፍቃንም መልዕክተኛ ልትሆኚ ትችያለሽ!!!!

tad said...

Teffera, in principle I agree with you that love you enemy is the golden teaching of our lord and I also know Noah's story from the bible that the son who laughed at him was cursed, but the issue is that how long you tolerate your father get drunk all the time and goes naked on the street . Are you not going to be ashamed and even put your father under house arrest,or take him to Tsebel,.... Well I am not going to laugh at him but no doubt I will get him help.
These bishiops need help,at least tell them that we are going to hold them accountable.
God bless
Let not

Anonymous said...

To
Teffera MD,

“ቆቅ ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ”
የተጠየቅኸው እና መልሱ አይገናኝም እኮ። የገረመኝ ነገር በአቡነ ቄርሎስ ከቤተ ክህነት ለቀቁ ተብሎ ለደጀ ሰላማውያን ስለተነገረ በጣም የቆጨህ ይመስላል።ከአስተያየት ሰጭዎች መካከል በዚህ ርእስ ላይ እንዳንተ ደጋግሞ ያቀረበ አላየሁም ምነው እንቅልፍ ነሳህ? የማፍያው ቡድን አባል ነህ? አስተያየት ሰጭ በመምሰል ሐሳብ ልትሰርቅ ተመድበህ ነው አይደል? አሁን እኮ ብዙ ጊዜ ተደብቆ መሄድ አይቻልም በቃ አውቀንሃል ጊዜ ታጠፋ እንደሆን እንጅ የምትለው ጠብ አይልም አናምንህም ይልቁንስ ከቁልቢው ካዝና ስንት እንደ ደረሰህ አጫውተን እንደሱ ይቀልልሃል እሺ? ልብ ይስጥህ

Anonymous said...

ለተፈራ፡ኤም፡ዲ፡እና'ለ"አሳቡ"፡ተጋሪዎች፥
በቃለ፡እግዚአብሔር፡እያስታከኩ፡ለቤተ፡ክርስ
ቲያናችን፡አጥፊዎች፡መሟገት፤ኃጥያትም፡ወ
ንጀልም፡ነው።"ጸሎት"፥"ጸሎት"እያሉ፡ማው
ራቱ፡በማጅራት፡መቺዎች፡ሃይል፡አባቶችን፡ላስ
ደበደቡት፡የጥፋት፡ርኩሰት፡ምልክቶችም፡አልበ
ጃቸው!

የተዋህዶ፡ሕዝበ፡ክርስቲያንን፡ቅሬታና፡በሐዘን፡
የተመላ፡ተቃውሞ፡ለማሽመድመድ፡ጊዜህን፡ከ
ማባከን፡የምትለው፡ካለህ፡ለአውሬውና፡ተራዳኢ
ዎቹ፥በቃችሁ፡የቅዱስ፡ያሬድን፥የፃድቅን፡ቅዱ
ስ፡አባታችንን፡አባ፡የተክለ፡ሃይማኖትን፥የአባቶ
ች፡አባ፡አብርሃምና፡አባ፡ጴጥሮስ፡ቤተ፡ክርስቲያ
ን፡አትበጥብጡ፥አታፍርሱ፡ብለህ፡መለእክትህ
ን፡አስተላልፍላቸው!ለኛ፡የፍቅርም፡ሆነ፥የጾም
ና፡ጸሎት፡ሥርዓታችን፡የተዋህዶ፡እምነታችን፡
አካል፡ስለሆነ፥አትቸገርበት!አድህነነ፡ከመአቱ
...በማለት፡ሱባኤ፡የገቡና፡ምልጃ፡የቆሙ፡የሃ
ይማኖተ፡አብው፡ልጆች፡እንዳልስ፡በምን፡ታው
ቀዋለህ?ዳግማይ፡ሱስንዮሳውያንንና፡ግብረ፡አበ
ሮቻቸውን፡ከቤተ፡ክርስቲያናችን፡ጨርሶ፡ለማስ
ወገድ፥የጥንቶቹ፡አባቶች፡ከየደብራቸው፡ወጥተ
ው፡በመታገልና፡በማታገል፡ተዋህዶ፡እምነታች
ንንና፡ኢትዮጵያዊነታችንን፡እንዳስከበሩት፡ሁ
ሉ፥የዛሬውም፡ትውልደ፡ቤተ፡ክርስቲያን፡የጀመ
ረው፡ቆራጥ፡አለሁ፡ባይነት፡የተዋህዶ፡ልጅ፡ከሆ
ንክ፡አያስደንግጥህ።እንዲህ፡ሳይሆን፡ቀርቶ፡ለአ
ውሬው፡መዳን፡የምታላዝን፡ከሆንክ፥አመጽህ፡በ
እግዚአብሔር፡ወገኖች፡ላይ፡በመሆኑ፡በለዓም፡ላ
ይ፡የተመዘዘው፡ሠይፈ፡እግዚአብሔር፡ከሚደመ
ስሳቸው፡ወገን፡እራስህን፡ስለደመርክ፡የምርጫህ
ን፡ታገኛለህ!!!

http://keyboards.geez.org/#Keyman6

በቋንቋችን፡ለመጻፍና፡ለማንበብ፡ከላይ፡ያለውን፡
መጠቆምያ፡በመምታት፡ገብቶ፡በነፃ፡መውሰድ፡
ስለሚቻል፡እየበረታን፡በመማር፡ቋንቋችንንና፡ፊ
ደላችንን፡እናስከብር!

የቅዱስ፡ገብርኤል፡ድጋፍ፡አይለየን!

እግዚእትነ፡ማርያም፡የተዋህዶን፡ልጆችሽን፡ከ
ተቃጣብን፡የጥፋት፡ሃይል፡እንዲያድነን፡ልጅ
ሽና፡ወዳጅሽ፡እግዚእነ፡እየሱስ፡ክርስቶስን፡አ
ማልጂን!አሜን።

ዘደብረ፡ሊባኖስ፡ነኝ።

Anonymous said...

ይህ ብሎግ እውነት የኦርቶዶክሳውያን ነው ወይስ የጸረ ኦርቶዶስክሶች። በአብዛኛው ጸረ ክርስቶስ የፖለቲከኞች እና የጦረኞች ቃላት ነው እማነብበር

Anonymous said...

”…ንስሐ ግቡ ምክንያቱ ብዙ ሕዝበ ክርስቲ
ያን ኣሳዝናችሁ ወደ ሌላ እምንት እየነዳች
ሁት ነው የናንተው መላ ምት ዋጋ የለው
ምና…”

ሑሉም፡ለየራሱ፡ስለ፡መተላለፉ፡ንስሐ፡መግባት፡
እንደሚገባው፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ታስተምራለች።
እዚህ፡ላይ፡ንስሐ፡ሊገቡ፡ይቅርና፥አሻፈረኝ፡ብለ
ው፡ቤተክርስቲያናችንን፡ለሚበጠብጡት፡መደገ
ፊያ፡“ንስሐን”እንደማስፈራርያ”መጠቀም፡አሳ
ፋሪ፡ግድፈት፡መሆኑ፡ነው።የዚህ፡አሳብ፡አቅራቢ፡
ቢያስተውል፡ኖሮ፥ባለፉት፡17ዓመታት፡ቤተ፡ክ
ህነታችን፡ጠባቂ፡በማጣቷ፡በነጣቂዎች፡የተወሰዱ
ት፡የተዋህዶ፡ምእመናን፡ቁጥር፡የሚያመለክተው፡
ብጥፋት፡ርኩሰት፡ሰዎች፡እየተፈፀመብን፡ያለውን፡
በደል፡ነው።ሁኔታው፡እንዲህ፡ሆኖ፡ሳለ፡ያብዬን፡
ወደምዬ፡ለመላከክ፡መሞከር፡ከእውነት፡የራቀ፡ከ
መሆኑም፡በላይ፡ለሥህተትና፡ጥፋት፡የሚዳርግ፡
ነው።እናስተውል!


ሌላውደግሞ፡ምንም፡ማሥረጃ፡ያልሰጠበትን፡ው
ንጀላ፡እንዲህ፡ሲል፡ያቀርባል፡-
“I still believe you are children of the church but making a graving mistake in the process.”

አንደኛው፡ደግሞ፡የራሱን፡አስተሳሰብ፡በማቅረብ፡
ምሣሌ፡መሆን፡ሲችል፥የከለከለው፡ያለ፡ይመስል፡ ”Why you are not using this opportunity to open discussion that focus on our real problems and brain-storm what we the memenan can do for the church …”ይልና፥እዚያው፡በዚያው፡በፊት፡
ያለውን፡በመደርመስ፡ “and leave the personal issues and internal problems resolved by another means?”ይላል።አግባብ፡ያለው፡አቀራረብ
አይደለም!


ተዉ፡እባካችሁ፡እያስተዋልን፡እንነጋገር!እንዴ
ት፡ተደርጎ፡ነው፡“ወደ፡ፊት፡እንሂድ፥ግን፡ባለ
ንበት፡እንቁም”እየተባለ፡በጎ፡ሥራን፡ለመሥራ
ት፡መመካከር፡የሚቻለው?!

የተዋህዶ፡አምላክ፡ከወደቅንበት፡አዘቅት፡
ያውጣን!አሜን፡፡

ለዛሬው፡እዚህ፡ላይ፡ላብቃ፥
ዘደብረ፡ሊባኖስ፡ነኝ፡፡

Melkamu said...

Let us pay close attention to ourselves so that we are not deceived into thinking that we are following the strait and narrow way, when in actual fact we are keeping to the wide and broad way. The following will show you what the narrow way means: fasting, standing, moderation, the purifying draught of dishonor, sneers, derision, insults, the cutting out of ones own will, patience in annoyances, unmurmuring endurance of scorn, disregard of insults, and the habit, when wronged of bearing it sturdily; when slandered, of not being indignant; when humiliated, not to be angry; when condemned, to be humble. Blessed are they who follow the way we have just described, for there is the Kingdom of Heaven.

http://www.ninesaintsethiopianorthodoxmonastery.org/

Anonymous said...

Ds Patriyariku kulubi Gebriel tgntewu hzbe kristian zm alachew alu,Srachewun tqbloale malt nwu?
Kristianoch hasabachewun ltikimtu sbseba kwdihu bteleyaye hunita mgletse alebachewu elalehu? Enantes mntlalachhu?

ewnetu said...

please read

http://www.thetruthfighter.net/

ewnetu said...

የጠላታቸን ቢሆንም ጊዜዉ
ሃይሉ ቢጸናም ቢያስፈራም ግርማዉ
ዛሬም እኛው ነን እምናሸንፈዉ
ነገም እኛው ነን እማናሸንፈዉ


ዋናው ጣለታችን ዲያቢሎስ ነዉ እሱም እራሱን ማሀበረ ቅዱሳን እያለ በሚጠራው የግብጻውያን አሽከር ማህበር ውስጥ ሰርጎ ስለገባ ወገኔ ተባበርና ጸብል እናስጠምቃቸው
ከታሰሩ ወዲያ መፈራገጥ
ለመላላጥ ይባላል
ስለዚህ ዳንኤል ክስረትና አንተን መሳይ የተዋህዶ ግባቶ መሬት ቆፋሪዎች በቆፈራችሁላት ጉርጋድ ተገቡበታላችሁ

የምናመልከው አምላክ ከሁሉም ይበልጣል እና
ለማየት ያብቃችሁ


ዋናው የተዋህዶ ጠላት ሃሰተኛው "ማህበረ ቅዱሳን" ነው

አሁንም በሃገር ውስጥም በውጭም ያሉ እወነተኞቹ የተዋህዶ አባቶች እድሜአቸውን ያርዝምልን እንወዳቸዋለን አነድ ቀን ወደ ሰላም ይመታሉ ሁሉም አባቶቻችን ናቸው ጣለታቸን ግን ማ.ቅ ብቻ ነው

ይቆየን

Anonymous said...

ደጀ ሰላም ከምታቀርብልን የመወያያ አርስት እየወጡ በተለያዩ አርስቶች ግርጌ እነ እውነቱ እና መሰሎቹ የማኅበረ ቅዱሳንን ሥም እያነሱት ነው። ለመሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን የሚጠሉ ሰዎች እነ ማን ናቸው? በአጠቃላይ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚጠሉ ሰዎች በሦሥት ከፍለን እንያቸው፦
፩. በዓላማ እንዲጠፋ የሚፈልጉ ናቸው
• አክራሪው የእስልምና ቡድን
• የቤተክርስቲያን የውስጥ መናፍቃን(ተሃድሶ)
• መናፍቃን(“ጴንጤ”)
እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ቡድኖች የማኅበሩን አገግሎት በደንብ ጠንቅቀው ያውቁታል፤ እንዲሁም ዓላማውም በሚገባ ተረድተውታል። አክራሪው እስላም በቤተክርስቲያን ላይ በተለያዩ ጊዜያት የሚያደርሱት ጥፋት እየተከታተለ መረጃ እየሰበሰበ እኩይ ተግባራቸውን እያጋለጣቸው ስለሆነ የማኅበሩን መኖር የእግር እሳታቸው ነው። ወደፊትም ላቀዱት ጥፋት ይከታተለናል ብለው ስለደመደሙ ማኅበሩ እንዲጠፋ ደፋ ቀና እያሉ ነው።ይህ ማኅበር ኢትዮጵያን የማስለም ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅፋት ሆኖብናል ብለው በግልፅ በተለያዩ የእስልምና ፓል ቶክ ውይይት እየሰማናቸው ነው።
ሌሎቹ ሁለቱም መናፍቃን የውስጡም የውጩም ግብራቸውና ዓላማቸው ማኅበሩ በሚገባ አውቆት አጥብቆ ስለሚቃወማቸው እነሱም ይሄንን ስለተረዱት የተለያዩ አጋጣሚዎች በመጠቀም ስሙን ሲያነሱት እናያቸዋለን፤ እዚህ ላይ እውነቱን(ውሸቱን) ልብ በሉልኝ። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱም መናፍቃን የተዋህዶ እምነትን የማጥፋት ዘመቻቸው ማህበሩ እስካለ ድረስ ማስፈጸም አንችልም ብለው ስለወሰኑ በማንኛውም መንገድ እንዲሁም ከአክራሪው እስላሙ ጋር ተባብረውም ቢሆን ሊያጠፉት ይፈልጋሉ።
፪. የቢተክህነቱ ወሮበሮች(ማፍያ/ጨለማን የወደዱ) አካላት
እነዚህኞቹ ደግሞ በጊዜአዊ ጥቅምና ሥልጣን የሰከሩ ናችው። አቶ ንጉሴም ከነዚህኞቹ ቡድን ጋር መድቤዋለሁ። ማኅበሩን የሚጠሉበት ዓላማቸው ማኅበሩ በያዘው የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ይከበር የሚለው ጥብቅ አቋሙ ነው። ይኸው እነዚህ ሆዳቸው አምላክ የሆነባቸው ወገኖች ማኅበሩን ቢችሉ ለማፍረስ ነበረ፤ ነገር ግን ስላልቻሉ የማኅበሩን ስም የማጥፋት ዘመቻ ተቀጣሪው ጀሌያቸው አቶ ንጉሴ ጀምሮታል።
፪. የማኅበሩን አገልግሎትና ዓላማ ያልተረዱ ወገኖች
እነዚህ ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳንን በሥም ብቻ ያውቁታል። የማኅበሩ ሥም እንኳ የሰሙት ከተሃድሶ መናፍቅ፤ ከአቶ ንጉሴ ወይ ደግሞ ከአክራሪው እስላም ነው። እናም አንድ ጊዜ የሰሙት ወሬ ብቻ ይዘው ማኅበሩን ይጠሉታል። እንደው ማኅበረ ቅዱዳን ማን ነው፤ ዓላማው ምንድ ነው፤በቤተክርስቲያኒቱስ የትኛው መዋቅር ሥር ነው ያለው፤ ብሎ ለመጠየቅ ጆሮዋቸው የዘጉ ባይጠፉም፤ ለመጠየቅ ተዘጋጅተው አጋጣሚው ያላገኙ ወገኖች እንዳሉም እገምታለሁ።
እግዚአብሔር ተዋህዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን።

Anonymous said...

Dear All,

We shall focus on ourselves as the Fathers will be fine and they can adjust themselves after few weeks/days very soon which is usual.

I assume they will have some sort of good digis/kitfo/kurt/... to enjoy then their extreme agendas will disappear soon.

We shall pray for the for future betterment of our Church and country as a whole.

Long Live for Abune Paulos and PM Meles

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)