July 25, 2009

አቡነ ቄርሎስ የቤተ ክህነት ግቢን ለቀቁ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 25/2009)
በማፊያ ቡድን አባሎችና ወረበሎች መኖሪያቸው የተሰባበረባቸውና በሕይወታቸው ላይ አደጋ የተቃጣባቸው አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ለደህንነታቸው በመስጋት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢን ለቅቀው እንደወጡ የቅርብ ምንጮች ገለፁ።

የቅዱስ ሲኖዶስ የበላይነት አልቀበልም ብለው በማስፈራራትና በሀይል ጭምር አጀንዳውን ጠምዝዘው ጊዜያዊ እፎይታ ካገኙት ፓትርያርክ ጋር በገቡት አለመግባባት የግል ቂም ተይዞባቸው አደጋ የተጣለባቸው ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ሰሞኑን የጠቅላይ ቤተ ክህነትን ግቢ ለቅቀው የወጡ ሲሆን አንዳንዶች ወደ ሀገረ ስብከታቸው ወደ ወሎ መሄዳቸውን ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ እዚያው አዲስ አበባ ከሰዎች ዘንድ ማረፋቸውን ተናግረዋል።

“ለሕይወቴ ደህንነት አይሰማኝም” እንዳሉ የተጠቆመው ብፁዕነታቸው ዕቃቸውን ጠቅልለው ሲወጡ መታየታቸው ሲዘገብ ሌሎች አባቶችም ቢሆኑ በተመሳሳይ የደህንነት ስጋት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። የደጀ ሰላም ምንጮች ጨምረው እንደተናገሩት የፓትርያርኩ ወዳጆች የተባሉት ሳይቀሩ በፍርሃት መያዛቸው ሲነገር ፓትርያርኩ ይቃወመኛል የሚሉት ላይ አደጋ ከማስጣል አይመለሱም የሚለው ጉዳይ እያደገ መምጣቱ ታውቋል።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)