July 22, 2009

የቤተ ክህነቱ ማፊያ ቡድን አሁንም አልተያዘም፤ ውንብድናው ከተፈፀመ ሳምንት ሆነው

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 22/2009)

ሳምንት ረቡዕ ጁላይ 15 ምሽት፣ ለሐሙስ ዋዜማ ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው ያለውን የመብራት መጥፋት ተገን ባደረጉ ሰዎች በብፁዓን አባቶች ላይ አደጋ ለመጣል በተደረገውና በንብረት ውድመትና አባቶችን በማጎሳቆል እንዲሁም አፍኖ በመውሰድና በማስፈራራት በተፈጸመው ወንጀል ቤተ ክህነቱን የተቆጣጠረው የፓትርያርኩ “ቤተ ዘመዶች ቡድን” እንዲሁም በጉቦ የተገዙ “የመንግስት ደህንነት ሠራተኞች” እንደሚገኙበት ውስጥ አዋቂዎች እየተናገሩ ቢሆንም እስካሁን በወንጀሉ ተጠርጥሮ የተያዘም ሆነ የተመረመረ ሰውና ቡድን እንደሌለ ታውቋል።


“ሊቀ ኅሩያን” የሚል የማዕረግ ስም ተሰጥቶት ታላቁን የቤተ ክርስቲያኒቱን የሰበካ ጉባዔ ማደራጃ መምሪያ ሃላፊነት የተቆጣጠረው የፓትርያርኩ እህት ልጅ በሆነው በአቶ ያሬድ ከበደው መሪነት የሚንቀሳቀሰው የማፊያ ቡድን የተጠናከረና መሳሪያ የታጠቀ ሲሆን አደጋ በመጣልና በማስፈራራት ከዚህ በፊትም ልምድ አለው። ከዓመታት በፊት በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ሕጉ በቆመበት የአንድ ባህታዊ ነፍስ በጠፋባት ዕለት “ጥይቲቱን ያስወነጨፈው እርሱ ነው” እየተባለ ሲታማ የኖረው ያሬድ የቤተ ክህነቱ ቁጥጥር ክፍል ሀላፊ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱ የጀርባ አጥንት የሆነው የሰበካ ጉባዔ መምሪያ የበላይ ነው። ይህ መምሪያ በተወዳጁ መንፈሳዊ አባት በሊቀ ጉባዔ አባ አበራ በቀለ መሪነት ለአስርት ዓመታት ሲተዳደር የነበረ ሲሆን አባ አበራ ከፓትርያርኩ በደረሰባቸው መገፋት የሕክምና ርዳታ ሳያገኙ፣ በአንዲት ቆርቆሮ በቆርቆሮ ቤት ውስጥ ኖረው በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ሊለዩ በቅተዋል።

ስለ ረቡዑ አደጋ አስተያየት የጠየቅናቸው የቤተ ክህነት ሠራተኞች እንደሚናገሩት “እነ ያሬድ የጠሉትን ሰው በማንኛም መልኩ ከማጥቃት ወደ ሁዋላ” እንደማይሉ ገልጸው በዚህ ወንጀላቸው ደግሞ በመንግስት ደህንነት ውስጥ የሚሰሩ ወይም ይሰሩ የነበሩ ሰዎች እንደሚተባበሯቸው ተናግረዋል። ደህንነቶቹ ለምን በዚህ ወንጀል እንደሚሳተፉ ምክንያታቸውን የሚዘረዝሩት ውስጥ አዋቂዎቹ “ሰዎቹ በገንዘብ ይደለላሉ፣ የቤተ ክህነት ቤቶች ይሰጧቸዋል፣ ወይም ፓትርያርኩ የሥጋ ዘመዶች ይሆናሉ” ሲሉ አብራርተዋል።

በግንቦት 2001 ዓ.ም ለቅዱስ ሲኖዶስ በቀረበና የፓትርያርኩን አስተዳደራዊ በደሎችና ወንጀሎች በዘረዘረ አንድ መረጃ ላይ ፓትርያርኩ “በሙስናና በተለያዩ ከፍተኛ ችግሮች በደል ተገኝቶባቸው ከመንግሥት በግምገማ የሚባረሩ አካላትን ከጥፋታቸው ሳይታረሙ ከነችግራቸው በማቅረብ ቤተ ክርስቲያኒቱን የዘራፊዎች ዋሻ አድርገዋልታል፡፡” የሚል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበረ ታውቋል።

በርግጥም መንግስት የደህንነት ሃይሎቹ በፈለጉት መልክ ወንጀል ሲሰሩ ሊቆጣጠር የሚችልበት ዘዴ ከሌለው አገራችን የድህረ-አፓርታይድ ደቡብ አፍሪካ ዕጣ እየገጠማት ነው የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ ፈጥሯል። ፓትርያርኩ ከዚህ በፊትም የሚቃወሟቸውን ሰዎች በመንግስት ስም እንደሚያስፈራሩ ይታወቃል።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

>

18 comments:

Anonymous said...

Thank you DS for the info.

Tunsisa

Anonymous said...

Thank you for your up to date information. Please every one united and pray to the Almighty God to give us His guidance and solution to the problems now our church facing. We have to leave everything to Him. May God be give us His blessing to our church.

Anonymous said...

enante mafeya yemetebalu menednachihu ? yebuna gebena mafia nachihu weyis yeshae mafia jebena nachu? enante mognoch egeziabher yemayay mesloachu tidekmalachu enantem alekachihum (paulos)weyewilachu kenu meshebachu nseham satgebu mekretachu new.

ተዋሕዶ-ዘቦትስዋና said...

Dear beloved Tewahedo followers,

"Peace be unto you" John 20:19

I wondered why we are not seeing a genuine way out to the problems in our church.
I know we all believe that if God wishes so, He can bring solution which is beyond comprehension.

But could we be delaying His healing Hand by pushing Him out of our plans and the approaches we are taking?

I am certain that there is no Tewahedo follower that was not "wounded inside" and still in pain because of what happened to our fathers who are members of the Holy Synod.

“So when you see the abomination of desolation spoken of by the prophet Daniel, standing in the holy place let the reader understand it... ” Matt 24:15

I believe it is my fair "observation" that there are mistakes on the side of Abba Pawulose and also on the side of his opponents in terms of their approach and the stand they took. Again, there are mistakes on the side of Mahbere Kidusan because of their approach in boldly denouncing believers confessing the same doctrine but differing on issues of administration. Mahbere Kidusan, in my opinion, has been the backbone of our church in terms of revealing the subtle mission of the so called TEHADISO but they (the Mahbere) also makes mistakes by generalizing everybody that differed in terms of “rules” and label TEHADISO; sometimes over issues of personal difference.

If that is the case it will only be fair for them to label Abba Pawulsoe also “TEHADISO” because he has failed to abide by the rules in one or another way. But they didn’t come out clear when it came to facing the truth in that regard.

Let's stop living according to the famous childhood stories like the case of "THE SOUR GRAPE AND THE SWEET LEMON”. I presume it is self explanatory.

All the fights, accusations and defamation we are witnessing here and there are mainly of administrative nature which does not lead anyone to inherit the kingdom of God.

It fills the faithful with distrust to witness excommunication of our other church members. Are they heretics just because they disapproved the things that are going wrong in the church?

Apostolic Anathemas issued are to the likes of Arius, Nestorius and Macedonius; not to believers confessing the same doctrine and differing on issues of administration. We have few Christian countries confessing the same doctrine with EOTC yet having no administrative unity with us at all.
Are we not encouraged by our church leaders to partake in the Holy Communion with them? So why are we excommunicating our own fellow Tewahedo believers just because they differed on issues of administration?
Let's stop for a while "our Vehicle" which is driving us to consumption, and give it a second thought to see if it is not leading us to the wrong destination or not, and then turn back to the right direction to the Kingdom of God.

I would like to quote from the words of the late Abune Gorgorios when he once said, "It is easy to become a deacon, a priest, a bishop, and even a patriarch; but it is very difficult to become a "CHRISTIAN"

Let's remind ourselves that we cannot become true Christians just because we know the bible or the rules or just because we have been ordained as one of the above.

I believe it is necessary to have rules and abide by it as it is the custom everywhere, including secular institutions. But it saddens the flocks so much to witness the "Shepherds" splitting themselves over administrative issues and even worse, excommunicating each other.

I want to believe that the devil is behind the scene of all these tribulations and enjoying itself seeing the church going through such trying times.

Let's really pray for the unity and integrity of our Church!

Let's beseech God to grant us the wisdom and strength to overcome the challenges so that we shall glorify His name for delivering us through these difficult times.

Let's focus on things which could promote peace without compromising our faith in God.

"Nevertheless when the Son of man cometh, shall He find faith on the earth?” Luke 18:8

Nisir said...

Response to Adera yemilachihu
በመሰረቱ በአንዳንድ ነጥቦችህ ላይ ባልስማማም ስለሰጠኸው የሰከነ አስተያየት ይበል ይበል ብያለሁ። ማህበረ ቅዱሳን ክብዙዎች የሚለየው እና ጥርስ ውስጥ የሚያስገባው ጉዳይ ለቤተ ክርስቲያን ችግሮች አፈታት የሚከተለው አካሔድ ይመስለኛል። ችግር በተፈጠረ ቁጥር መግለጫ እያወጡ እና እያወገዙ ከአስተዳደሩ ተለይተናል ስም አንጠራም እያሉ ተለይቶ መሔድን በፍጹም አያምንበትም። ይህ የሚሆነው ማህበረ ቅዱሳን የችግሩን መኖር ወይም አሳሳቢነት ሳይረዳው ቀርቶ ሳይሆን አፈታቱ መፍትሔን አያመጣም እንዲያውም ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል እንዲሉ በተበላሸው በቤተክህነት አስተዳደር ወስጥ ችግር በተፈጠረ ቁጥር ጠላታችን ዲያቢሎስ በአንዳንድ ድብቅ ዓላማ ባላቸው ሰዎች እያደረ ምዕመናንን ከመንጋው ማራቅ እና መለየት ይጀምራል የሚል እምነት ስላለው ነው። ስለዚህ ማህበሩ የቤተ ክርስቲያንን ችግር መፍታት የሚቻለው ራሷ ቤተ ክርስቲያኗ ባላት የመንፈሳዊ አስተዳደር ስርዓት እና መዋቅር መሰረት ሲሆን እና ሁሉም ክርስቲያን ይህን መዋቅር ክወረቀት አልፎ ስራ ላይ እንዲውል በየደረጃው እያጠናከረ ድርሻውን ሲወጣ ነው ብሎ ያምናል። አንተ በቤትህ ውስጥ ችግር ቢፈጠር እዚያው ሆነህ ችግርህን ትፈታለህ ወይም ለእርዳታ ትጮኻለህ እንጂ ገለልተኛ ነኝ ወይም አይመለከተኝም ብለህ እንደማትሔደው ማለት ነው።
እንግዲህ ሁላችንንም ከአጥቢያችን ጀምሮ የቤተ ክርስቲያኗን መንፈሳዊ አሰራር አስተዳደር በስራ ላይ ለማዋል እና ለማጠናከር ድርሻችንን ተወጥተናል ወይ? ይህን ሳንወጣ ዛሬ ብቻቸውን ቀርተው ህገ ቤተ ክርስቲያን ይከበር ባሉ እና እንግልት ዛቻ ማስፈራሪያ በደረሰባቸው አባቶች ላይ እንዲህ ቢያረጉት ኖሮ እያሉ መፍረድ ያስቸግራል። የሁላችንም በየደረጃው ድርሻችንን ሳንወጣ አክርፈን መቀመጣችን ግን የፓትሪያርኩ ዘመዶች እና ሌሎች የቤተ ክርስቲያን ነገር ጉዳያቸውም ያልሆነ ሰዎች አስተዳደሩን እንዲሞሉት እና ይህ አሳዛኝ መከራ እንዲደርስ ሆነ።
ይልቁኑም እኔ እንድታስተውለው የምፈልገው ከአስተዳደሩ ተለይተናል የሚሉት ሰዎች ምንም እንኳን ውጪ ውጪውን የሚያቀርቡት ምክንያት የአባ ጳውሎስን አስተዳደር ቢሆንም በውስጣቸው ድብቀው ያያዙት መንጋውን ነጥሎ በቤተ ክርስቲያን ስም ገንዘብ እየሰበሰቡ ለራስ መበልጸግ፤ ተሰሚነት ያላቸውን አገልጋዮች በማስመጣት የሚሰሩትን ቢዝነስ ማጠናከር፤ ሰዎችን ውስጥ ለውስጥ በገንዘብ ወደ ውጪ ሀገር የማስመጣት ቢዝነስ መስራት ወዘተ ወዘት እና/ወይም የቤተ ክርስቲያኗን ዶግማና ቀኖና ማንም አያየንም በሚል በየጊዜው በሚመቻቸው መልኩ እየቀናነሱ በሂደት ከነጭራሹ ማጥፋት ነው። ያን ጊዜ ችግሩ ላይመለስ የሐይማኖት ችግር ይሆናል። የሚያሳዝነው እኩይ ብእሲ ያቀድም ሰናየ ክፉ ሰው መልካሙን ያስቀድማል እንዲሉ እኛ ከፊት ለፊት የተቀመጠችልንን የአስተዳደር በድል ብቻ እየተመለከትን ሌላውን አለማስተዋላችን ነው።
ወንድሜ የእኔ ምክር በቤተ ክርስቲያን ጉዞ መከተል ያለብን እዚያው ሆኖ ለሐይማኖቷ መስራትን ብቻ እንጂ ሌሎች እስኪስተካከሉ ወይም እስኪያስተካክሉት ተነጥሎ በመቆም አይደለም። ከጓደኞቻ ተለይታ ያደገች ማሽላ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ እንዳይሆንብን
ቸር ይግጠመን

Anonymous said...

Nisir ቃለ ሕይወት ያሰማልን

እንዲህም ዓይነት እዉነትን የሚናገር አለ ማለት ነዉ እግዚአብሔር ይጠብቅህ/ሽ
እባክህ/ሽ ደግመህ ጻፍ

አንባቢ ነኝ

Anonymous said...

DS thank U for u'r information.
?. Do u think that Woyane did not involved in our church problems?

K Abrha w atsebha

ተዋሕዶ-ዘቦትስዋና said...

Dear Nisir,

I am impressed by your reaction to my comment.( I would have loved to write in Amharic like you but I can't; it is just because I am unable to use the software on my PC- my sincere apology for that!!)

I assume you have realized my point(and probably many other people's) and I appreciate that you have not tried to defend in a way which could deny the fact( in case you are one of the members).

Absolutely I agree with you that it is only the approach that brings criticism to the Mehaber; otherwise it is only "The Devil" that can oppose Mahbere Kidusan regarding the way Mahbere kidusan maintained an amazing standard in which it spurred and inspired millions towards spritual life.

I would love to know the points on which you don't agree with me so that we could learn from each other.

May the Good God bless us all!

YeAwarew said...

ጳጳሱን በዱላ?

(ቦጋለ ዳኜ ‐ ከካሊፎርንያ)
ጳጳስ እህል ይጥም እንጀራ ይበላ፣
በማይመስልበት ምድር በጦብያ በሞላ፣
የስድቡ ሲደንቀን ተቃጣበት ዱላ፣
በምጡ ዋዜማ እንጃ ካሁን ሁዋላ።
መስፍን ዘውድ ሊጭን ቄስ ዲያቆን ሊካን፣
እንዲህ በቀላሉ መች ተገኝቶ አቡን፣
አቡኑን ፍለጋ ሲጎርፍ ከያቅጣጫው፣
ስንቱን ደራሽ ወሃ አዞ እንዳልጨረሰው፣
በትረ ቃየል ሰጡት በትረ ሙሴን ትተው።

Selam all:

Thank you Deje Selam for keeping us updated. But don’t be expecting any kind of probe or investigation on the perps(the attack “Ninja”(as Azekiri21 blogger calls them) group) that are behind all the intimidation, persecution and …… only God know what.

And I don’t think the “woyanne” govt will do anything even if somebody comes up with a video evidence of the attack. “Tebaqiwan yamenech beg latuwan wuchi tasadiralech” indil.
It is no use, will never happen.

The only alternative is to make sure that this kind of attack and intimidation will not happen again to the true fathers by hiring private “Security” (people they trust) or something similar. God ! It makes me sad and tearful and furious that our Church fathers have to fear for their life in this time and day, in their own country, b/n their own people. What a sad story !

At least they had peace and respect they deserve. But… may be it is the “end of times” as they say.
May God protect His Church and the true Fathers, it’s only God now.

And – comment writers “Nisir” and “Adera yemilachihu” – keep it up ! You are good, few of the best I have seen.
“Deje Selamawian”: let us take their example,
- good comment
- they identify themselves with a nick name (no Anonymous comment).

“Adera yemilachihu” wrote” … “ I would love to know the points on which you don't agree with me so that we could learn from each other.”
That is a sign of a great personality ( not to be taken as “kentu wudasie”), willing to learn from others.
That is one of the signs of being a true Christian.

God bless,
Cher neger yaseman,
YeAwarew

Nisir said...

አንደኛው ነጥብ ገለልተኞችን ያወገዘ ወይም በአንተ አገላለጽ ኤክስ ኮሚኒኬት ያደረገ የለም። እኔ የማህበሩ አባል ባልሆንም ዓለማውን እና አካሔዱን ለብዙ ዓመታት በነበሩኝ አጋጣሚዎች ተረድቼዋለሁ። አሁን ግን የምናገረው በተረዳሁት ነገር የራሴን አስተያየት ነው።
በገለልተኞችም ሆነ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ስር ነን እያሉ የፓትርያርኩን ስም ከመጥራት የዘለለ ሥራ ባልሰሩት ዓብያተ ክርስቲያናት ውስጥ አያሌ ኦርቶዶክሳውያን አሉ። የማህበረ ቅዱሳን አባላትም በዓላማ የሚያገለግሉት በእነዚሁ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ነው ። ትክክል አይደለም የተባለው አካሔዱ ነው። ለቤተ ክርስቲያን ችግር እስከ መጨረሻው መጋደል እንጂ ገለል ማለት የሚል አቋም በታሪክም በትውፊትም አያዋጣም፤ በቤተ ክርስቲያን ሥር ነን ለሚሉትም ቢሆኑ የፓትርያርኩን እና የጳጳሳትን ስም መጥራት ብቻ በአስተዳደሩ ውስጥ ለመሆን ማስረጃ ሊሆን አይገባም የሚል ነው። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ በቦርድ አባላት አካባቢ ያሉ ሰዎች ሃሳቡን ስለማይደግፉት በአብዛኛው ምዕመናን/ት ደግሞ ስለ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ከልምድ የዘለለ ጠለቅ ያለ እውቀት ስለሌለን፤ ስለ ቤተ ክርስቲያን ችግር ለማወቅ እና ለመወያየት ትዕግስቱም ስለሌለን መጥተን ቅዳሴ አስቀድሰን ገንዘባችንን መጽውተን በሌላው አያገባኝም ወይም ጊዜ የለኝም ብለን ስለምንጠፋ በተለይ ደግሞ ሰባኪያኖቹ ከዘወትር ስብከት እና የበዓላት ትምህርቶች ውጪ መርሀ ግብር ነድፈው ምዕመኑን ስለቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ምንነትና ጥቅም ፤ስላለው ድርሻ ስለማያሰለጥኑት፤ ወይም ማሰልጠን ስለማይፈልጉ፤ወይም በዚህ ዙሪያ እንዳያስተምሩ ቦርዱ ወይም የጋበዛቸው አካል ስለሚከለክላቸው፤ ምናልባት አንድ ቀን ቢያስተምሩ ሁለተኛ ዕድሉን ስለማያገኙት....ሌላም ሌላም ተደማምሮ በልምድ በምናገባኝ የምንንቀሳቀስ ለጥቂቶቹ የምንመች ምዕመናን/ት በዝተናል። ይህ ሁሉ በልምድ የሚሔደው ምዕመን በማወቅ በማስተዋል ቢሔድ ምን ያሀል ወደፊት በተጓዝን ለሌሎችም በተረፍን ነበር።
አሁን ያለፈው አልፏል፤ ከእያንዳንዳችን የሚጠበቀው የግድ የማህበረ ቅዱሳን አባል መሆን አይደለም። ባይሆን ስለማህበሩ ያሉንን ጥያቄዎች በአውሮፓም በአሜሪካም በሀገር ቤት ከሚገኙት ቋሚ አድራሻቸው ሄዶ በመጠየቅ የራስንም ሀሳብ በማካፈል ወይም እስካሁን የሰሩትንና ስለ እነርሱ በየአቅጣጫው የሚወራውን በመንፈሳዊ ብስለት በመመርመር እና በመመዘን ጥርጣሬን ማስወገድ ለአገልግሎታችን ይጠቅመናል ። በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያንን ብለው የዛሬውን ብቻ ሳይሆን የሩቁን የልጅ ልጆቻቸውን ዘመን ጭምር አስበው በማስተዋል ከሚያገለግሉ በሁሉም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ከሚገኙ አባቶች እናቶች ወንድሞች እና እህቶች፤ ማህበራትም ጋር አብሮ መስራት ነው። ዋናው ነገር ግን ተበታትኖ ከሚሰጥ አገልግሎት በመቀናጀት በመነጋገር ስትራቴጂዎችን ነድፎ በጋራ መስራት ፍሬውን የቅርብ ያደርገዋል እግዚአብሔርንም ደስ ያሰኛል።ያም አይደል በህብረት መኖር?
ለሁሉም ግን የቤተ ክርስቲያን ችግርን እዚህ ተነጋግረን ስለማንጨርሰው በአደባባይ እየተመካከርን ለመስራት ያብቃን
ቃለ ህይወት ያሰማልን!

tad said...

To Nisir:
In principle I am for united EOC under diocese. But the problem comes when we talk how to reach there, as two of the beginners of independent churches in USA are abba paulos ans abba mathias, yrs ago.
My other problem is most of the bishops who come to lead churches in diaspora start from power point of view instead of dialogue.
Dont' forget also we can't talk about church unity alone by forgetting justice,equality, freedom and unity of our beloved Ethiopia.
Thanks

Anonymous said...

To Nisir and "Adera Yemilachihu"

I am very impressed by the way you talked to each other. What a wise way?!!!. I am sure it is a good lesson to the rest of us.

Keep it up and reason out your idea with a fear of God and for the betterment of our holy Church.

Chala

Anonymous said...

What do you expect from wenbede leadership? Justice or injustice? You talk a lot about bringing the mafia to justice. Are you aware that we have no accountable leadership at all in the country? In a country where there is no justice seeking justice is joking. We have a mafia government that fosters mafias in other institutions including in the Churches and Mosques. Otherwise how far is betkihenet from Arat Kilo or Fedral Police office? How much percent are you sure the government was not terrorizing this? If the govermnet was not in it, it was easy to capture the mafias. However, mafia government never brings mafias to justice.Tagaye Paulos has never been a representative of the head of the Church ever since he came to the office on day one. He has a well documented evidence of crimes including the murder of the monk at Estifanos church. Trust me. This guy is doing his assignment. dividing the church, exercising his dictatorship, fighting the truth speakers, killing the church right defenders, collaborating TPLF in prisioning hundreds of peaceful university students, and so forth.

As long as there is no freedom in that country, religious institutions will never be free and don't expect justice where there is tyranny. How many of you are ready to fight tyranny first? Raise your hands, I don't see any in this group. Let us help those who fight tyranny,tyranny,tyranny, because tyranny is the real prblem of Ethiopia.

Anonymous said...

Nisir and "Adera Yemilachihu"

Egziabyer estachihu. Very nice dialogue. We are hearing you.

Egzabher Betekristiayanachinin yitebklin

Anonymous said...

ወዴት እንሄዳለን?

እስካሁን ድረስ ቤተ ክርስቲያንን እየመሩ ያሉ ጳጳሳትን በተመለከተ በአመኙ በኩል ከመንፈስ ቅዱስ በታች የቤተ ክርስቲያን መሪና ጠባቂ የጳጳሳት ጉባዔ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደሆነ ይታመን ነበር፡፡ ሰሞኑን በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል ሲካሄድ የቆየውና በፓትርያርኩ ላይ ግልጽ ተቃውሞ ባሰሙ ጳጳሳት ላይ የጉዳት ማድረስ ሙከራ ከተደረገ በኋላ ሐምሌ 10 በስምምነት ተጠናቀቀ የተባለው ስብሰባ ሂደት ግን የሚያመለክተው ከዚህ የተለየ ነው፡፡

በአንዳንድ የቅዱስ ሲኖዶሰ አባላት በሆኑ ጳጳሳት ዘንድ እየታየ ያለው መከፋፈል፣ ለእውነት አለመቆም፣ ከቤተ ክርስቲያኑ ሕግና ሥርዓት ይልቅ ለፓትርያርኩ ሃሳብ ተገዢ መሆን፡ የአባቶችን መንፈሳዊ ዝቅጠት የሚያመለክት ሲሆን ቤተ ክርስቲያኒቱ በቅዱስ ሲኖዶት እንደምትመራ ለሚያምን እና ለሚመሰክር ምዕመን ሁሉ አንገት የሚያስደፋ ጥቁር የታሪክ ክስተት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም ሌላ የጨለማ ዘመን ውስጥ እንደምትገኝ በገሀድ ያየንበት ወቅት ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የምትመራው በቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ፓትርያርኩ ራሳቸውን እንደጣዖት ከሕግ በላይ ካደረጉ፣ አንዳንድ ጳጳሳትም ይህን የሳቸውን ፍላጎት እና የራሳቸውን ጥቅም ለማሟላት ቅዱስ ሲኖዶስን ሕልውናውን ለማሳጣት የሚያውኩ ከሆነ ቤተ ክርስቲናችን ቅዱስ ሲኖዶስ አላት ብሎ መናገሩ በዲያስፖራ ‹‹ሕጋዊ ሲኖዶስ›› ነኝ እያለ ምዕመናንን ግራ ከሚያጋባው አካል አይለይም፡፡ እስካሁን ድረስ አባቶች አሉን፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኗን ይጠብቃል በማለት ነበር በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የቆየንው፡፡ እንግዲህ ቤተ ክርስቲያኒቱ በውስጥም በውጪም የወንበዴዎች ዋሻ ከሆነች፣ ወዴት እንሄዳለን?

ከሰሎሞን ቀጥሎ እስራኤልን ይመራ ዘንድ በዙፋኑ የተቀመጠው ሮብአም በላያቸው የተጫነውን ቀንበር እንዲያነሳላቸው እና በመልካም አስተዳደር ሕዝቡን እንዲያገለግል ሲመክሩት አልሰማም ብሎ የአብሮ አደጎቹን ክፉ ምክር በመስማት በላያቸው ባለው ቀንበር ላይ የባሰ ሸክም እንደሚያጸናባቸው ስለተናገረ ህዝቡ ‹‹ሕዝቡ በዳዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም፡፡ እስራኤል ሆይ ወደ ድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፤ ዳዊት ሆይ አሁን የራስህን ቤት ተመልከት፡፡›› በማለት ወደየድንኳኖቻቸው ተመልሰዋል፡፡ ብዙዎችም ዛሬ ይህን በመሰለ የፓትርያርኩ ሕገ ወጥነት እና በአንዳንድ ጳጳሳት ደካማነት ‹‹እግዚአብሔር ሆይ የራስህን ቤት ተመልከት›› በማለት ወደ ሌላ ድንኳን ለመመልከት እየተገደዱ ነው፡፡

ኧረ ለመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን ከመንበረ ማርቆስ፡ ከእስክንድርያ መንበር ተላቃ ራሷን እንድትመራ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ነገሥታትና ሊቃውንት በ50 ዓመት ታሪክ ውስጥ እንዲህ ዓይነት አሳዛኝታሪክ ሲታይ ምን ይሉ ይሆን? ፓትርያርኩ እንደሮብአም የሚሰሙት ምክር የመሰሎቻቸውን ከሆነ፣ ለእውነት በቆሙ አባቶች ላይ በሕይወታቸው እስከ ማስፈራራት ድረስ ቀንበር የሚጫንባቸው ከሆነ ፓትርያርኩ እና መሰሎቻቸው ቤተ ክርስቲያንን ለመምራት እንኳን መንፈሳዊው ብቃት ዓለማዊ ጥበብም ይጎድላቸዋል፡፡

ቤተ ክርስቲናችን ለ1600 ዓመታት ማርቆስ አባታችን፣ እስክንድርያ እናታችን ብላ ነው በብዙ ውጣ ውረድ ያለፈችው እና እዚህ የደረሰችው፡፡ አሁን ግን የእረኝነት ኃላፊነታቸውን በዘነጉ ፓትርያርክና ጳጳሳት ያለ አባት እና ያለ እናት ሊያስቀሩን በቀን የበቀል ኃይልን፣ በሌሊት ጨለማት ተገን አድርገው ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡ ታዲያ እስራኤላውያን ወደየድንኳኖቻቸው እንደተመለሱ እኛስ አባትና እናት እንደሌለው ሆነናልና ‹‹ማርቆስ አባታችን እስክንድርያ እናታችን›› ብለን ወደ ቀደማው ድንኳን እንሂድ?

ተዋሕዶ-ዘቦትስዋና said...

Dear Nisir and others, who commented our dialogue as a favorable one,

God bless you for the good response which reflected your positive mindset.

I agree with Nisir that we cannot exhaust all the issues we have in our church by just discussing them online. But if at least we all refrain from "Blasphemy" we would be pleasing the Almighty and invite Him to deliver us through.

Could others also follow the example of Nisir and mine too,please? At least in terms of having discretion in our comments-that doesn’t mean that we have surrendered to "the wolves in the sheep....." when we are faced with such.

Again let's be tolerable to those who make mistakes while trying to do good things.
"Mikir 'ina Buti (a punch) le sechiwu kelal newu" yilalu andandoch siteritu.
“ Kebero siyayut yamir siyizut yadenagir" endemibalewu malet newu.

Most of the times it is easy to make brilliant comments and criticize others when we are just bystanders; implementation is always a challenge and sometimes with its unforeseen crisis.
Let's overcome the feelings of vindictiveness through prayer (real prayer).

We don't necessarily need to be members of Mahbere Kidusan to become true Christians, and a true Christian also can never tarnish the good image of Mahbere Kidusan.

May the prayer and humility of Our Devout and Holy fathers be with us!

May the meekness and love of St. Mary, The Ocean of Love, fill in our hearts!

Glory, Majesty and Dominion to The Father, and The Son, and The Holy Spirit, One God from ages unto ages! Amen

Yours,
From Southern Africa

YeAwarew said...

Selam all:

“Adera yemilachihu” wrote… “…I agree with Nisir that we cannot exhaust all the issues we have in our church by just discussing them online….”

Well, discussing them is always the 1st step. If we can really discuss them and come up with good solutions those we (ourselves) rise to implement – put them to work. But if it to “discuss only” (talk)… we can talk till we drop with exhaustion … and that will not take us anywhere. “If you want to talk the talk, are you ready to walk the walk ?” indilu.

Most successful N.P.O.’s (mahiberat like MK) were started by few people who dared to “walk the walk” not just talk. Hope you understand what I am trying to convey.
The problem with these kinds of online …open discussions is – you never know who is in for the true cause or who’s “fake”. Because some people are just anti… like “diablos. And specially with most comment writers (here in DS) who like to stay “anonymous”, a real discussion is not really “plausible”. Too many “passer by’s”, no one really sticks around.

Well, what say you ?

Yiqoyen,
May God protect His Church and the true Fathers,

YeAwarew

ተዋሕዶ-ዘቦትስዋና said...

Dear YeAwarew,

Thank you very much.

Let's mean (do) what we say. But when we decide to walk the walk let's do it the right way.I don't mean we have to fold our arms and sit back until we are able to do it in perfection;no body can become perfect but let's refrain from deliberate destructive words and actions, and admit the mistakes we may have made on the way.

Otherwise no one will bring a better solution.Of course, a better solution can only come from ABOVE. What does that mean? No matter how hard we struggle, unless we do it as faithfuls according to the will of God; any change which might come forth will not be for the betterment we are dreaming for.I hope you will agree with that.
(No doubt, a change will come sooner or later).

Let's pray( real prayer).I know every one is praying; but are we doing it in a manner that takes our prayer beyond the cloud? The question is to all of us. We can't lie to God.

"But he that shall endure unto the end, the same shall be saved" Matt 24:13

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)