July 21, 2009

የሎንዶን ደ/ሰ/ቅ/ማርያም ሰበካ ጉባዔ በአባቶች ላይ የተፈጸመውን ወንጀል አወገዘ፣ “ገለልተኛው” መናገር ጀመረ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 20/2009)
በእንግሊዝ ሎንዶን ከተማ የምትገኘው የደብረ ሰላም ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ በቤተ ክርስቲያን በመፈጸም ላይ የሚገኘውን ጉዳይ በተመለከተ መግለጫ አወጣ፤ ፓትርያኩንም ተቃወመ። ለደጀ ሰላም በላኩት በበዚሁ ሁለት ገጽ መግለጫ ሰበካ ጉባዔው ከንዑሳን ክፍሎችም ጋር በመነጋገር ወደፊት ሰፊ መግለጫ እንደሚያወጣ ገልጿል። (ደጀ ሰላም በፒ.ዲ.ኤፍ የሚመጡ ነገሮችን የማስተናገጃ ዘዴ ስለሌላት ሙሉ መግለጫውን እዚህ እንዲመለከቱት እንጋብዛለን)።

የደብረ ሰላም ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን መግለጫ ራሱን “ገለልተኛ” እያለ የሚጠራው፣ ከአባ ጳውሎስ አስተዳደርም፣ ከ”ስደተኛውም” አይደለሁም ከሚለው ወገን ቅድሚያውን ሊይዝ ችሏል።

6 comments:

Anonymous said...

Good job. I wish all 'Adibarat' at home country would do the same thing.

Thank you DS for sharing with us.

Gemechu

qedamawi said...

የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ገለልተኞችና ሌሎችስ ለምን ዝምታን መረጡ?
በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ማለትም ዲሲ፤ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ውስጥ በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ስም የሚጠሩ በብዛታቸው 18(አስራ ስምንት) በአስተዳደር አይነታቸው ደግሞ 7(ሰባት) የተለያዩ አብያተክርስቲያናት ይገኛሉ። የአብያተክርስቲያናቱ አይነት እኔ የማውቃቸውን ልንገራችሁ ያልተጠቀሰም ካለ እናንተው ጨምሩበት፦
1. ራሱ ስደተኛ ሲኖዶስ ብሎ የሚጠራው ቡድን ውስጥ የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት
2. ራሳቸው ገለልተኛ ነን በማለት የሚጠሩ በገለልተኝነት የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት
3. በግለሰብ ስም የአባ ኤገሌ ወይም የአቶ ኤገሌ ተብለው የሚጠሩና በግለሰቦቹ የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት
4. ፓትርያርኩን እንቀበላለን ነገር ግን ሀገረ ስብከት አንቀበልም የሚሉ አብያተክርስቲያናት
5. የኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ እንቀበላለን ነገር ግን ፓትሪያርክ አባ ጳውሎስ አንቀበልም የሚሉ አብያተክርስቲያናት
6. ከአሜሪካ ውጪ በሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳትና ቆሞሳት በበላይ ጠባቂነት ወይም ባለቤትነት የሚመሩና የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት
7. የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር በመጠበቅ በሀገረ ስብከት የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት
ታድያ ይህ ቅጥ ያጣ መለያየት መንስኤው ምን ይሆን? እውነት የፓትርያክ ጳውሎስ የአስተዳደር በደል? ወይስ ሌላ ጥቅም ፍለጋ? ምክንያታቸው የፓትርያርክ አባ ጳውሎስ የአስተዳደር ብልሹነት ከሆነስ ሰሞኑን በነበረው ግርግር በዚሁ ምክንያት እየጮሁ ለነበሩት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን አይዞዋችሁ እኛም የተለየነ ለዚሁ ነው፤ ነገሩ ይህ የተበላሸው አስተዳደር የምታስተካክሉት ከሆነ እኛም ከጎናችሁ ነን ለምን አላሉም?
አቤል ዘቀዳማዊ

Dan said...

የቅዳሜ 7/17 /09 የኣሜሪካን.ድምጽ.አዲሱ.አበበ.ቃለ ምልልስ.ያልሰማችሁ.መስማት አለባችሁ::.
ያኣሜሪካን ድምጽ አገልግሎት በነጻነት (freedom of press).ባለበት ላለን ሳይቀር
አስተዋጾው ብዙ ነው::

ንጉሴ አክሊሉ የተናገሩትን ሰምቼ በቤተክርስቲያን አካባቢ እነኚህን የመሳሰሉ ካሉ የተስፋ ብርሃን ይዘው ይታያሉ; ማለት እንችላለን; መጽሀፋቸውን ገዝቼ እስካነብ ተቁነጥንጫለሁ;;

ብጱዕ ሊቀ ጳጳስ አባ ማትያስ ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ክርስቲያን ሁሉ ና ቅዱስ ሲኖዶሱ የደረሱባቸውን ችግር በሚገባ ዘርዝረው ስላቀረቡ ሊመሰገኑ ይገባል:: የምስጋና የድጋፍ ደብዳቤ እንጻፍላቸው;;

አገር ቤትም ላሉ ለሥርዓትና ቀኖና ቤተክርስቲያን ለቆሙና ለሚታገሉ ለብጹዓን ሊቀ ጳጳስት አባ ቄርሎስ;ጢሞቲዎስ ኢጺፋንዮስ ከነሱም ጋር ለቆሙ ሁሉ መጸለይና ማበረታታት ይገባናል;;

ኒውዮርክ ያሉት በገንዘብ ማባከንና ስርቆት ከተከሱበት ለማሸሽ በአባ ጳውሎስ የተላኩትን አባ ዘካርያስ መልስ ስትሰሙ ታዝናላችሁ ከዛም ሳትወዱ ትስቃላችሁ::

ቅ. ዳዊት በም 2: ቁ 4 ላይ እንዳለው እንዳይሆንም ትፈራላችሁ::

"በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ይስቃል
ጌታም ይሣለቅባቸዋል
ከዚያም በቁጣው ይናገራቸዋል
በመዓቱም ያስደነግጣቸዋል"

የቅዳሜ 7/17 /09 የኣሜሪካን.ድምጽ.አዲሱ.አበበ.ቃለ ምልልስ.
ንጉሴ አክሊሉ ያሰሙትን ቅኔ ደጋግሞ መስማት ትፈልጋላችሁ;;

ከቅኔአቸው ጥቂቱ

ሲከፋፍላቸው ሳጥናኤል እነአባን
ጌታችን ማዘኑ መቆጣቱ ገባን

ማለቱ ከበደኝ ብጹዕ ቅዱስ ጳጳስ
ሲፈታ እያየሁት መቃብሩ ሲማስ;;

ንጉሤ አክሊሉ እንዳሉት የዚህ ቅኔ የባለ ቅኔው ስም አይታወቅም:

መላእክትሂ ጳጳሳት ባስልዮ ቴዎፍሎስ ክልዔቱ;
ለሙሴ ቤተ ክህነት ቀበርዎ በሕይወቱ

ከሃምሳ አመት በፊት የተደረሰ ነው በጊዜው የነበረውን በደል ለመግልጽ::

(እኔ ጨምሬበት ቅኔ ላልተማርን ቶሎ እንዲገባን)

(መላእክትሂ) ጳጳሳትነ ጳውሎስ ዘካርያስ ገብርኤል ወእስጢፋኖስ (ሌሎችንም ጨምር) ሃምስቱ/ተሰዓቱ
ለሙሴ ቤተ ክህነት ቀበርዎ በሕይወቱ:

ትርጉም

ሙሴ ቢሞት መላእክት (አክብረው) ቀበሩት
ጳውሎስ ዘካርያስ ገብርኤል ወእስጢፋኖስ (ሌሎችንም ጨምር)
ቤተ ክርስቲያናችንን በበደል በሙስና በሕይወት ቀበሯት::ንጉሤ አክሊሉ እንዳሉት

ማለቱ ከበደኝ ብጹዕ ቅዱስ ጳጳስ
ሲፈታ እያየሁት መቃብሩ ሲማስ

እኔ ጨምሬበት

ማለቱ ከበደን ብጹዕ ቅዱስ ጳጳስ
በሙስና ወድቀው እኛም ስንታመስ
ከመቅደሱ አጠገብ የሰው ደምም ሲፈስ
በዱርየዬ ሁካታ ቤተ ክርስቲያን ሲዳስ

hayelemekael said...

1ራሱ ስደተኛ ሲኖዶስ ብሎ የሚጠራው ቡድን ውስጥ የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት they already told you 17 years ago we are hegawe senodos the one in Ethiopia is wayane senodos(Aba Gebemedhen and ንጉሴ Cabenet )no body lesson and what do you want from hegawesenodos just they want is please leave them allow

tad said...

To Abel zekedamawi;
Don't you think this should be done by Abba Abraham?. His fellow bishops are suffering in the hand of Weyane, but he resides here in the free land. Why he doesn't show leadership?

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)