July 20, 2009

የማፊያው ቡድን ድምጽ በአሜሪካ “ማጥቃት” ጀመረ፤ የቁልቢ ብር ሥራውን እየሠራ ነው


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 19/2009)
• ንጉሴ ቅ/ሲኖዶሱን “የፓትርያርኩ ካቢኔ” አለው፣

የማፊያው ቡድን የውጪ ሀገር አንደበት የሆነው የዲሲው ሀገር ፍቅር ሬዲዮ ደጀ ሰላምን ሲሰድብ ዋለ። ከነገሩ ጋር በቀጥተኛ ግንኙነት ስሙ ያልተነሣው ነገር ግን እጅጋየሁ በየነን (ኤልዛቤልን) እና ግብረ አበሮቿን ቃለ ምልልስ በማድረግ አባቶችን ሲያዋርድ የሰነበተው ንጉሴ ወ/ማርያም ጥቃቱን በማጠናከር ቅ/ሲኖዶስን “የፓትርያርኩ ካቢኔ”፣ ፓትርያርኩ ሊያፈርሱትም ሆነ ሊገነቡት የሚችሉት ኮሚቴ እንደሆነ አድርጎ ሲያስረዳ ተሰምቷል።
For your information, follow this link about Negussie W/Mariam.


የማፊያው ድምጽ ተናጋሪ ንጉሴ ከዚህ በፊት $10 000 ዶላር የመቀበሉ ነገር በቅ/ሲኖዶስ ፊት መቅረቡና ፓትርያርኩም በዚህ ነገር መበሳጨታቸው፤ በዚህም ምክንያት የነገሩ አካሄድ ያላስደሰተው ንጉሴ በተለይም በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ መጀመሩ ይታወሳል። በቅርቡ ደጀ ሰላም ባቀረበችው ዜና ቅዱስ ፓትርያርኩ ራሳቸው በቀጥታ ከሚያዙበት የቁልቢ ገብርኤል ካዝና ከሁለት ሚሊዮን ያላነሰ ብር ማውጣታቸው መዘገቡ ይታወሳል። ምናልባት የቁልቢ ብር ዋሺንግተን ዲሲ ሳይደርስ እንዳልቀረ ተገምቷል።

የቅ/ሲኖዶስ አባላት ከፓትርያርኩ ጋር ከተለያዩባቸው ጉዳዮች አንዱ ፓትርያርኩ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አልቀበልም ማለታቸው፣ ቅ/ሲኖዶስም ተጠሪነቱ ለእርሳቸው እንደሆነ አድርገው ማቅረባቸው መሆኑ ይታወሳል። ፓትርያርኩ ቅዱስ ሲኖዶስን የበላይነት “ተቀብዬአለሁ” ቢሉም ንጉሴ ግን የጥንቱን ዜማ እስካሁን በማዜም ላይ ይገኛል። ንጉሴና እጅጋየሁ ቅ/ሲኖዶስ ሙሉ በሙሉ ባለመፍረሱ በመናደዳቸው “ይህንን አድርገውብናል” ያሏቸው ላይ ጥቃት ጀምረዋል። ሀገር ውስጥ የብፁዓን አባቶችን ቤቶች በመሰባበር፣ ጋዜጠኞችን በመደብደብና በማስፈራራት ሲንቀሳቀሱ በውጪ ደግሞ በንጉሴ ሬዲዮ አማካይነት ስም ማጥፋት ጀምረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቤተ ክህነቱ ጉዳይ ጦዞ አደባባይ ከወጣበት ከግንቦት 2001 ዓ.ም ጀምሮ ዜናውን ለምእመናን በማድረስ ላይ የምትገኘውን ብሎግ፤ ደጀ ሰላምን፤ አንድ ጊዜ የማህበረ ቅዱሳን ነው ሌላ ጊዜ ደግሞ የሌሎች ነው በማለት የማፊያው ቡድን በማስወራት ላይ ሲሆን ምእመናን እንዳያነቡና እንዳያዉቁ ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።

ብሎግ ማድረጋችንን (መጦመራችንን እንቀጥላለን)! ጭንቀታችን ስለቤተ ክርስቲያናችን እንጂ ስለነንጉሴና ማፊያው ቡድን አይደለም።

ቸር ወሬ ያሰማን!!
አሜን
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ለሀገር ፍቅር ሬድዮ
(ከአቤል ዘቀዳማዊ)
ይድረስ ለሀገር ፍቅር ሬድዮ አዘጋጆች፤የዛሬው የእለት ሰንበት ዝግጅታችሁ ተከታትዬዋለሁ። በእውነት ግን አቶ ንጉሴ እና ዶ/ር በላይ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ህግ እና ቀኖና ተቆርቃሪዎች ናችሁ ወይስ የቅዱስ ፓትሪያርኩ ህገ ቤተክርስቲያን ጥሰትን ተባባሪዎች? የህገ ቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ብትሆኑ ኖሮ ግን የቤተክርስቲያኒቷን ህግ እና ቀኖና የሚያፋልሱ ዝግጅቶች ባላቀረባችሁ ነበር። ለመሆኑ የጠቅላይ ሚኒስተር የካቢኔ አባላት እንዴት ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋራ በምሳሌነት ሊወዳደር ይችላል?እኔ አላውቀውም በእናንተ ዝግጅት እንደገለጻችሁት የጠቅላይ ሚኒስተር የካቢኔ አባላት የጠቅላይ ሚኒስተሩ ታዛዥ እና መመሪያ አስፈጻሚ ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል፤ ነገር ግን የኢ/ኦ/ተ/ቤተከርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያኒቱ የመጨረሻ ከፍተኛ ሥልጣን ባለቤት ነው። ህገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 5 እና 7
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፓትርያርኩም ጭምር ሊቃነ ጳጳሳት እና ኢጲስ ቆጶሳትን ያካትታል። ቅዱስ ሲኖዶስ የፓትሪያርኩን መመሪያ እና ትእዛዝ በመጠባበቅ ወይም በመከታተል የሚሰራ ሳይሆን ፓትሪያርኩ ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እና መመሪያ ተቀብሎ የማስፈጸም ግዴታ አለበት ይህም በህገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 8 እና 15 ተገልጾዋል። ስለዚህ እንደው በማያገባችሁ ነገር እየገባችሁ ህዝበ ክርስቲያኑን ግራ አታጋቡት፤ ተቆርቋሪነታችሁ ለህገ ቤተክርስቲያን ከሆነ ግን ህጉ ምን ይላል ብላችሁ አንብቡት። አንድ ተራ ምእመን ቤተክርስቲያኒቱ ስልጣን የሰጠቻቸውን ሊቃነ ጳጳሳትን መዝለፍ እንዲሁም በቤተክርቲያኒቱ አስተዳደራዊ መዋቅር ሥር እያገለገሉ የሚገኙትን ማኅበራትን የስም ማጥፋት ዘመቻ ቤተክርስቲያናችንም ስለሚያስነቅፍ እንደዚህ አይነት ከእውነት የራቀ ለማንም ምንም ጠቀሚታ የሌለው ዝግጅት ተገቢ አይደለም።
እግዚአብሔር እውነቱን ይግለጽላችሁ!!! አሜን

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)