July 15, 2009

ሪፖርተር ጋዜጣ የተሳሳተ መረጃ እያሰራጨ ነው

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 15/2009)
• አውራምባ ታይምስ፣ ኢትዮፕያፈርስትና ሌሎች ጋዜጦችም ተሳስተዋል
ትናንት ተሰብስበው ቃለ ጉባዔውን ያጸደቁት በቁጥር ከ21 የማያንሱ አባቶች ሆነው ሳለ 13 እንደሆኑ አድርጎ በዛሬ የረቡዕ እትሙ የዘገበው የሪፖርተር ጋዜጣ ዜና የተሣሣተ መሆኑ ታወቀ። ባለፈው እሑድ እትሙም የአንዱን ወገን ብቻ በማነጋገር ነገሩን ለማራገብ የሞከረው ሪፖርተር ጋዜጣ ፓትርያርኩ ሁሉንም ጉዳይ በቁጥጥር ስራቸው እንዳደረጉ፤ ይልቁንም የተወሰኑ አባቶች እንደተነሱባቸው ለማስመሰል ሲሞክር ተስተውሏል።


ከዚህ በፊትም ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ይቅርታ ጠይቀዋል ማለቱ ይታወሳል። ሪፖርተር ይህንን አቋም የያዘበት ምክንያት ለጊዜው ግልጽ ባይሆንም ከቁልቢ ገብርኤል በፓትርያርኩ ቀጥተባ ትዕዛዝ ወጪ ተደርጓል የተባለው ከሁለት ሚሊዮን በላይ ብር “በረከት ተቋዳሽ” ሳይሆን እንዳልቀረ ምንጮቻችን አስረድተዋል። በዚሁ መልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ብር ከተረጨላቸው ሚዲያዎች መካከል አንደኛው የሆነው የዋሺንግተን ዲሲው ሀገር ፍቅር ሬዲዮ $10 000 (አሥር ሺህ ዶላር) ማግኘቱ ይታወቃል። በሌላ በኩል ደግሞ www.ethiopiafirst.com የተባለውና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለሼህ አላሙዲን በሚያሳየው ጥብቅና “አላሙዲን ፈርስት” የሚል ቅጽል የተሰጠው ድረ ገጽ ይገኝበታል። ድረ ገጹ የቅዱስ ሲኖዶስን አባቶች ሳይስማሙ መበተን “ካርታው ተናደ” ሲል እስከ መዘገብ ደርሷል፤ ፓትርያርኩንም ከ45 ደቂቃ ያላነሰ ቃለ ምልልስ ሽፋን በመስጠት የተቀሩትን አባቶች ሲያሳጣ ሰንብቷል።

4 comments:

Anonymous said...

Egizer Yikir yibelachew "hager fikir ena ethiopiafirst"

Anonymous said...

ኢትዮጵያ ፊርስት (አላሙዲን ፈርስት)፣ ሪፖርተር እና ሃገር ፍቅር የተባሉ አፍቃሪ ወያኔዎች በፓትርያርኩ ሲሆኑ፣ ደጀ ሰላም፣ ማህበረ ቅዱሳን እና አዲሱ አበበ በአባ ሳሙኤል ወገን ናቸው። በስደት ላይ ያለው ሲኖዶስ፤ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎች እንዲሁም አይጋ ፎረም የተባለው የመለስ ዜናዊ ድኅረ ገጽ ጸጥታውን መርጠዋል። ፋ

Unknown said...

ውድ አንባቢ፣
የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ አውርደህ የእገሌ ወገን የእገሌ ወገን ማለትህን ብታስተካክል ጥሩ ነው፤ ለሃይማኖትህ ብለህ።

Anonymous said...

ሁሉም ተሳስቷል እኝኛ ልክ ነው ማለታችሁ የፈሪሳውያን ጸባይ ነው። መቼም ምንም ሪፖርተር ወደ መንግስት ጠጋ ያለ ቢሆንም እውነቱን ፈልፍሎ የሚጽፍ መሆን የታመነ ነው በበኩሌ ከእናንተ ቅጥፈት ሪፖርተር ይሻለኛል።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)