July 21, 2009

የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዝግጅት በቅንጭቡ፤ ኪነ ጥበባዊ ቅንብር በዳን


(ደጀ ሰላም፣ July 21/ 2009)

ማለቱ ከበደን ብጹዕ ቅዱስ ጳጳስ፣
በሙስና ወድቀው እኛም ስንታመስ፣
ከመቅደሱ አጠገብ የሰው ደምም ሲፈስ፣
በዱርዬ ሁካታ ቤተ ክርስቲያን ሲዳስ።


የቅዳሜ 7/17 /09 የኣሜሪካን ድምጽ አዲሱ አበበ ቃለ ምልልስ ያልሰማችሁ መስማት አለባችሁ:: ያኣሜሪካን ድምጽ አገልግሎት በነጻነት (freedom of press) ባለበት ላለን ሳይቀር አስተዋጾው ብዙ ነው::

ንጉሴ አክሊሉ የተናገሩትን ሰምቼ በቤተክርስቲያን አካባቢ እነኚህን የመሳሰሉ ካሉ የተስፋ ብርሃን ይዘው ይታያሉ; ማለት እንችላለን; መጽሀፋቸውን ገዝቼ እስካነብ ተቁነጥንጫለሁ።

ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አባ ማትያስ ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ክርስቲያን ሁሉ እና ቅዱስ ሲኖዶሱ የደረሱባቸውን ችግር በሚገባ ዘርዝረው ስላቀረቡ ሊመሰገኑ ይገባል:: የምስጋና የድጋፍ ደብዳቤ እንጻፍላቸው።
አገር ቤትም ላሉ ለሥርዓትና ቀኖና ቤተክርስቲያን ለቆሙና ለሚታገሉ ለብጹዓን ሊቀ ጳጳስት አባ ቄርሎስ;ጢሞቲዎስ ኢጺፋንዮስ ከነሱም ጋር ለቆሙ ሁሉ መጸለይና ማበረታታት ይገባናል።

ኒውዮርክ ያሉት በገንዘብ ማባከንና ስርቆት ከተከሱበት ለማሸሽ በአባ ጳውሎስ የተላኩትን አባ ዘካርያስ መልስ ስትሰሙ ታዝናላችሁ ከዛም ሳትወዱ ትስቃላችሁ::
ቅ.ዳዊት በም2 ቁ.4 ላይ እንዳለው እንዳይሆንም ትፈራላችሁ::

"በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ይስቃል
ጌታም ይሣለቅባቸዋል፣
ከዚያም በቁጣው ይናገራቸዋል፣
በመዓቱም ያስደነግጣቸዋል"

የቅዳሜ 7/17 /09 የኣሜሪካን ድምጽ አዲሱ አበበ ቃለ ምልልስ ንጉሴ አክሊሉ ያሰሙትን ቅኔ ደጋግሞ መስማት ትፈልጋላችሁ። ከቅኔአቸው ጥቂቱ

ሲከፋፍላቸው ሳጥናኤል እነአባን፣
ጌታችን ማዘኑ መቆጣቱ ገባን፣
ማለቱ ከበደኝ ብጹዕ ቅዱስ ጳጳስ፣
ሲፈታ እያየሁት መቃብሩ ሲማስ።

ንጉሤ አክሊሉ እንዳሉት የዚህ ቅኔ የባለ ቅኔው ስም አይታወቅም:

መላእክትሂ ጳጳሳት ባስልዮ ቴዎፍሎስ ክልዔቱ፣
ለሙሴ ቤተ ክህነት ቀበርዎ በሕይወቱ።

ከሃምሳ አመት በፊት የተደረሰ ነው በጊዜው የነበረውን በደል ለመግለጽ::

(እኔ ጨምሬበት ቅኔ ላልተማርን ቶሎ እንዲገባን)

(መላእክትሂ) ጳጳሳትነ ጳውሎስ ዘካርያስ ገብርኤል ወእስጢፋኖስ (ሌሎችንም ጨምር) ሃምስቱ/ተሰዓቱ፣
ለሙሴ ቤተ ክህነት ቀበርዎ በሕይወቱ።

ትርጉም

ሙሴ ቢሞት መላእክት (አክብረው) ቀበሩት
ጳውሎስ ዘካርያስ ገብርኤል ወእስጢፋኖስ (ሌሎችንም ጨምር)
ቤተ ክርስቲያናችንን በበደል በሙስና በሕይወት ቀበሯት::

ንጉሤ አክሊሉ እንዳሉት

ማለቱ ከበደኝ ብጹዕ ቅዱስ ጳጳስ
ሲፈታ እያየሁት መቃብሩ ሲማስ

እኔ ጨምሬበት

ማለቱ ከበደን ብጹዕ ቅዱስ ጳጳስ፣
በሙስና ወድቀው እኛም ስንታመስ፣
ከመቅደሱ አጠገብ የሰው ደምም ሲፈስ፣
በዱርየዬ ሁካታ ቤተ ክርስቲያን ሲዳስ።

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)