July 11, 2009

ግብር አልባ ለሆነው የሥልጣን ወንበር ጥበቃ የተደረገ ሞት ሽረት

Dear readers,
Congradulations on the current development regarding our Church. Here below we have posted an article send to use by one Deje-Selamawit sister. Thank you sister. We did not include your name and e-mail, in case you may not need that.
Cher Were Yaseman,
DS
++++++++++++++++++

ባሳለፍናቸው በእነኝህ ጥቂት ቀናት ያለ አንዳች ዕረፍት ሥልጣንን ለመጠበቅ እና ሥልጣንን ለማስጠበቅ ከእንቅልፍ ማጣት ጋር የደከማችሁትን ድካም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዕድገት ደክማችሁላት ቢሆን የሰሞኑ ግርግር እና ሁካታ ቀድሞውኑ አይሞከርም ነበር።

ወንበርን ለማስከበር እና ሥልጣንን ለማቆየት አማራጭ የሌለው መፍትሔ በተቀመጡበት የሥልጣን ወንበር በቅንነት መሥራት ብቻ ነው። በፈረስ እና በሠራዊት መታመን ለፈርዖንም አልበጀው። ጥቂት ሰዎች ለአንድ ሰው - አንድ ሰውም ለጥቂት ሰዎች ጥቅም ብቻ ቆመውና ቆሞ ሲገኝ ሕሊና ምን ያህል ይሞግት ይሆን? በዛሬው ቀን ላይ ቆሞ ትናንትን ማየት እና ነገን መቃኘት የሚችል ሰው እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አባባል በእምነት እና በሃይማኖት ውስጥ መኖር የሚችል ወንጌልን መከታ ያደረገ ሰው ብቻ ነው። ሙሴ ትናንትን ለማየት እና እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ማታም ሆነ ጠዋትም ሆነ አንድ ቀን ለማለት ያስቻለው የሃይማኖቱ ብቃት ነው። ዳዊትን እና ሌሎች ነብያትንም ወደፊት የሚመጣውን ያዩ ዘንድ ያስቻላቸው ይኽንን ዓለም ለመመርመር ልበ ቅን ሆነው ስለተገኙ ነው።

እግዚአብሔርን ለማየት እና የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት በምንችልበት ወንበር ላይ ተቀምጠን ሰውን የምናይበት እና ለሰው የምንሠራበት ሁኔታ መኖር አይገባውም። እንዲህ ላለመውደቅ ስትፍጨረጨሩ እንደ እናንተው ለመነሣት የሚጣጣሩትን እጃቸውን መያዝ ብትችሉ ምንኛ እግዚአብሔር በተደሰተ ነበር። ብልጣሶር ከንግሥናው ወንበር የሚወድቅበት ሰዓት ሲቃረብ የታመነው አቅም በሌላቸው እና ሥጋ በለበሱ አስማተኞች ነበር። ዛሬም ወንበሩ ሲነቃነቅ፣ ቀበቶው ሲላላ፣ መደገፊያው ሲንሸራተት እና ማጣፊያው ሲያጥር ሰዎች መታመኛቸው ሥጋ በለበሱ እና መሣርያ በታጠቁ ሰዎች ላይ ብቻ ሆነና አረፈ። መንግሥት አስታጥቆኛል፣ መሣርያ ጨብጫለሁ፣ ባለሥልጣኖችን ዐውቃለሁ፣ ገንዘብ በእጄ ነው፣ ብናገር እደመጣለሁ፣ ብጮህ እሰማለሁ፣ ባስተባብር አሳካለሁ፤ ክፉ ቀን ቢመጣ ማምለጫ አዘጋጅቻለሁ በሚል ትምክህት ደሃን አለመመልከት እና በግፍ በመጣ ገንዘብ መታመን የዕድሜ ልክ ጸጸት ነው።

ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ለመምራት መነሣት አሁን ካለው ክብር የበለጠ ያስከብራል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያፈራችውን ሀብት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ መቦጥቦጥ የጀመራችሁና ስትቦጠቡጡ የኖራችሁ ሁሉ በወንበር ላይ ላሉት የሥልጣን ሰዎች አዝናቸሁ ሳይሆን እንዲህ ጎንበስ ቀና ሰበር ሰካ የምትሉት ለእራሳችሁ የግል ጥቅም ስትሉ መሆኑ አይጠረጠርም።

ቤተ ክርስቲያንን በአስተዳደር ጉድለት የበደላችሁት አንሶ ገንዘቧን ከካዝናዋ ስታጎድሉ እና በገንዘብዋ ሰው ገዝታችሁ ሕይወታችሁ እንዲጠበቅ ስታስደርጉ ምን ይሰማችሁ ይሆን? ማንም የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ ተብሏልና ገንዘብ ላይ ቆማችሁ፣ ገንዘብ ተደግፋችሁ፣ በገንዘብ ሰው ገዝታችሁ፣ በገንዘብ አስፈራርታችሁ እና በገንዘብ ታምናቸሁ መኖርን እስከ መቼ ትቀጥሉበታላችሁ? ቤቱን ደሃ አድርጎ እና ልጆቹን አስርቦ ከሰው ዘንድ በወርቅ ተሽቆጥቁጦ ቢታይ የልጆቹን ረሀብና የቤቱን ድህነት የሚያውቁ ሁሉ ምን ያህል ይታዘቡት! ስማችን በተለያዩ ሚድያዎች ጎድፎ እየተሰማ እኛም ደግሞ ያንን ስም ማደስና ማስተካከል ሲገባን የበለጠ በጥፋት ላይ ጥፋት እየጨመርን መሄድ አይገባንም። ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን የምንሠራበት ዘመን ይምጣ።
እንደ ሰሞኑ እንቅልፍ ማጣት እና መሯሯጥ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ለማሳደግ በርቱ። ሊጥሉኝ እና ሊጥሉብን ነው ብላችሁ የደከማችሁ ሁሉ ሃይማኖታችን ልትወድቅብን ነው በሉና ስም ያለው ሩጫ ጀምሩ።

ለቅድስት አገር ኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እድገት የቆማችሁ ሁሉ ተስፋ መቁረጥን ገንዘባችሁ አታድርጉ። ሲደፈርስ ይጠራል፤ ሊነጋም ሲል ይጨልማል። ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ጋር የታገለውን ትግል ሁላችንም በጸሎት እንታገለው።ይህም የጳውሎስ ነን የአጵሎስ ነን ለማለት ሳይሆን በቅንነት የሚመራ እግዚአብሔርንም የሚፈራ ሰው በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እንዲኖር ነው። የማይሆን ነገር የለም፤ ተሞክሮም የማይሳካ ነገር አይኖርም፤ ብቻ ሰልፉም ውጊያውም ድሉም የጌታ ይሁን። አሁንም እኛ ታጥቀን እንነሣ እንጂ መፍትሔ የሌለው እንቆቅልሽም ሆነ መልስ የማይገኝለት ጥያቄ አይኖርም። ንጉሥ ናቡከደነፆር ያለመውን ሕልም አስታውሶም የነገረው ሕልሙንም የፈታለት ነብዩ ዳንኤል ነው። እግዚአብሔር እንቆቅልሻችንን ሊፈታ ጥያቄያችንን ሊመልስ ኃይል አለው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!


2 comments:

Anonymous said...

Kale hiywot yasemalin.

Anonymous said...

ከላይ የቀረበው አስተያየት የነፍስ በላው የማህበረ ቅሉሳን ርዕሰ አንቀጽ መሆኑን ሰለማውቅ አልደንነቀኝም ምክኒያቱም እነርሱ ሊሰሩት የምይችሉትንና ያልሰሩትን ሥራ ተሰርቶ ሲያዪ እና በተፈጠርው አለመግባባት ምናልባት ተጠቃሚ እንሁናለን የሚል የቁም ቅዥት ሰላላችህ ትችታችሁ አይደንቀኝም።
እስቲ ተጠየቁ
እናንት በሐይማኖት ሺፋን የደሀውን ገንዘብ በመዝረፍ በተክርስቲያኒቱን እርቃን ከማስቀረት በስተቀር ምን የረባ ሥራ ሰራችሁ?
በዶላር ተመንዝሮ በውጭ አገር የተቀመጠው ገንዘብ ከደሀ እናት በተክርስቲያን የተዘረፈ አይደለምን?
የበተክርስቲየን አምላክ ሁሉን ይመረምራልና በቅድሚያ ከአይናአችሁ የለውን ጉድፍ አጥሩ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)