July 9, 2009

በሃይማኖት ጣልቃ አለመግባት እስከ ምን?

ሰላም ደጀ ሰላማውያን
መቸም ይህ ሰሞን የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ሁላችንንም እንቅልፍ ነሥቶናል ማለት ይቻላል። ቅዱስ ሲኖዶሱ በአንድ በኩል ቅዱስነታቸው በሌላ በኩል ቆመዋል። ነገር ግን በብዙ መገናኛ ብዙሃን አገላለጽ ጉዳዩ የፓትርያርኩና የአዲስ አበባው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ተብሎ እየተዘገበ ነው። ምክንያቱ ሁለት ነው፦ ሆን ብለው ጉዳዩን ግለሰባዊ ግጭት ማድረግ የሚፈልጉ የቅዱስነታቸው ደጋፊዎች በአንድ በኩል፣ ነገሩ ያልገባቸው ሰዎች ወሬ በሌላ በኩል። የሌሎቹን ሚዲያዎች ለጊዜው ብንረሳው እንኳን ከዚህ በታች የተለጠፈው የሪፖርተር ጽሑፍ ግን ተሳስቶ የሚያሳስት መሆኑን እስቲ ተመልከቱት።Wednesday, 08 July 2009
በጌታቸው ንጋቱ

(ሪፖርተር)የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ዓለማዊ (secular) እንደሆነና የመንግሥትም ሃይማኖት እንደሌለ የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ይደነግጋል፡፡ መንግሥት በሃይማኖቶች ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባና ሃይማኖቶችም በመንግሥት ሥራ ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደማይችሉም በሕገ መንግሥቱ ላይ ሰፍሯል፡፡

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 11 ላይ እንደተቀመጠው "መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው፡፡ መንግሥታዊ ሃይማኖት አይኖርም፤ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ ሃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ይላል" በዚሁ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 27 ላይም "ማንኛውም ሰው የማሰብ፣ የህሊና እና የሃይማኖት ነፃነት አለው" ይላል፡፡

ይኸው አንቀጽ አያይዞም "ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል፤ ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመከተል፣ የመተግበር፣ የማስተማር ወይም የመግለጽ መብትን ያካትታል" ይላል፡፡ በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5 ላይ ደግሞ "ሃይማኖትንና እምነትን የመግለጽ መብት ሊገደብ የሚችለው የሕዝብን ደህንነት፣ ሰላምን ጤናን፣ ትምህርትን፣ የሕዝብን የሞራል ሁኔታ፣ የሌሎች ዜጎችን መሠረታዊ መብቶች፣ ነፃነቶች እና መንግሥት ከሃይማኖት ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚወጡ ሕጎች ይሆናል ይላል፡፡

በቀደምት የኢትዮጵያ መንግሥታት ታሪክ ሃይማኖት በመንግሥት አስተዳደር ላይ ተጽዕኖ ከማሳደርም በላይ መንግሥታቱ የየራሳቸው ሃይማኖት ያላቸው ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በሕጉ መሰረት የክርስትናም፣ የእስልምናም ሆነ የየትኛውም እምነት ተከታይ አይደለም፡፡ የመንግሥት ባለስልጣናትና ኃላፊዎች የራሳቸውን ሃይማኖትና እምነት የማራመድ ሰብዓዊ መብት ቢኖራቸውም እምነታቸውን ግን ከመንግሥት ተግባራት መቀየጥ እንደሌለባቸው ይታመናል፡፡

ማንኛውም ሰው የፈለገውን እምነትና ሃይማኖት የመከተልና የማራመድ፤ በቡድንም በሃይማኖት ተሰባስቦ የማምለክ መብቱ የተጠበቀ ቢሆንም ግለሰቡ የሚከተለው እምነትና ሃይማኖት የአገርን ሰላምና የሕዝብን ደህንነት በፍፁም ማወክ እንደሌለበትም ሕገ መንግሥቱ ይደነግጋል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ እምነት አራማጆችና የሃይማኖት ተከታዮች መካከል የተከሰቱ ግጭቶች ለመንግሥትና ለሕዝቡ የፀጥታ ሥጋት የፈጠሩበት ሁኔታ አለ፡፡ በሃይማኖት መቻቻል የምትጠቀሰው አገርም የተለያዩ ግጭቶችን በቅርቡ አስተናግዳለች፡፡ ጅማ፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ አርሲ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ የተፈጠሩ ግጭቶች የሰው ሕይወት እስከመቅጠፍም ደርሰዋል፡፡

መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ገብቼ አስተያየት አልሰጥም፣ የራሳቸውን ሥራ እራሳቸው ይስሩ ቢልም በየጊዜው በሃይማኖት ተከታዮች መካከል የተፈጠረውን ችግር ለማብረድ የግድ የሰላምና ፀጥታ ሥራውን ለመስራት እንደሚገደድ ይገልፃል፡፡ መንግሥት ሕግና ስርዓትን ለማስከበር ብቸኛ ባለመብት በመሆኑም ግጭቱን ማንም ያንሳው በምንም ምክንያት ሰላምን ለማስፈን ይንቀሳቀሳል፡፡

መንግሥት ከሃይማኖት የተለየ ነው (separation of government and religion) የሚለው የሕጉ ክፍልም የአገር ሰላምና ደህንነት ሃይማኖቶች ማወክ እንደሌባቸው ይገልፃል፡፡

በቅርብ ዓመታት ይታይ የነበረው በተለያዩ እምነት ተከታዮች መካከል የሚደረገው ግጭት አልፎ አልፎም በአንድ ሃይማኖት ተቋም ውስጥ የሚታይበት አጋጣሚ አለ፡፡ ለማሳያም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የበላይ አመራሮች መካከል የተጀመረው የቃላት ልውውጥና የተለያዩ እርምጃዎች ለአገሪቱ ሰላም አስጊ አየር ያዘለ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይገልፃሉ፡፡ የሃይማኖቱ የውስጥ ጉዳይን መንግሥት መርምሮ ውሳኔ መስጠት ባይችልም በዚህ ዙሪያ ያሉትን ሁኔታዎች በጥሞና ካልተከታተለ አደጋ መሆኑንም ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ በፊት በልደታ ቤተ ክርስቲያን በነበረው ችግር መንግሥት የፖሊስ ሰራዊት በማሰማራት ችግሩን ለመመከት ሞክሯል፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳዩ ከቤተ ክርስቲያኗ አፀድ ወጥቶ ጎዳና ላይ በመድረሱ የተወሰደው እርምጃ መንግሥትን ሲያስተች ነበር፡፡

አሁንም ፓትርያርኩ ያስተላለፉትን እግድ የተቃወሙት የአዲስ አበባው ረዳት ሊቀ ጳጳስ የራሳቸውን ሃይል በማደራጀት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከአንድ ወገን የስልጣን ጥያቄ በሌላ ወገን የሙስና ጉዳዮች እየተነሱ ቤተክርስቲያኗ የቤተሰባዊ ትስስር መድረክ መሆኗን ከወዲያ ወዲህ የሚወነጨፉ የቃላት ጦርነቶች እየተሰሙ ነው፡፡ ይህ በመንግሥት አስተሳሰብ የቤተክርስቲያኗ እና የእምነቱ ተከታዮች ራስ ምታት ሊሆን ይችላል፡፡ ጉዳዩ በዚህ መልክ ከቀጠለና መካረሮች ከበዙ ወዴት ይወስዳል የሚለው ላይ መንግሥት ምን ያህል ተዘጋጅቶበታል የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡

በተለያዩ ወገኖች የተከፈሉት የሃይማኖቱ አባቶች የራሳቸው ተከታይና ሰሚ አላቸው፤ እያፈሩም ነው፡፡ ሁሉም ወደ የአድባራቱ ሄደው ተከታዮቻቸውን ወደ ጎራው በመቀላቀል አብሯቸው እንዲሰለፍ ቢያደርጉ ግጭቱ እየሰፋ ሊሄድ እንደሚችል አባ ሳሙኤል ከታገዱ በኋላ በጠሩት ጉባኤ ላይ የተገኙ አንድ ግለሰብ ይገልፃሉ፡፡ ጭብጨባው፤ ያለው ስሜት ሁሉ ጤናማ እንደማይመስል፣ ከሃይማኖታዊ ይዘቱ ይልቅ የተደበቀ ሌላ ጉዳይ እንዳለ የሚያሳይ እንደሆነባቸውና ያ ሁሉ መቻቻል የት ገባ?" እንዳስባላቸውም ይገልፃሉ፡፡

መንግሥት "ሕዝቤን አታውኩ፤ ሰላሜን አትንኩ እንጂ ጉዳያቸውን እራሳቸው ይጨርሱ እያለ ነው" አሁን ያለውን ሁኔታ ለመቆጣጠርና ግጭቶቹ ወደ አደባባይ ወጥተው ሰላማዊ እንቅስቃሴን እስካልነኩ እርምጃ አልወስድም ያለ ይመስላል መንግሥት፡፡

በቅርብ ዓመታት ለመንግሥት ሥራ ፈተና ካደረጉ ጉዳዮች መካከል የሃይማኖት ጉዳዮች አንዱ እንደሆነ በመንግሥት የፀጥታ ዘርፍ ሥራ ላይ የተሰማሩ ኃላፊ ያስረዳሉ፡፡ ሃይማኖትን ማራመድ ብቻ ሳይሆን ሌሎች እንዳያራምዱ መከልከል፣ ምንጫቸው የማይታወቅና ሊጨበጥ የማይችል የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውሮች፣ ከሃይማኖቱ ግጭቶች የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ሃይሎችንና ሌሎችንም መንግሥት ለይቶ ያስቀምጣል፡፡

በሃይማኖት ተከታዮች መካከል ገብቶ ውሳኔ ማሳለፍ ይህን አድርጉ፣ ይህን አታድርጉ የሚል መብት መንግሥት ባይኖረውም ስለሚደረጉ እንቅስቃሴዎችና ሊያስከትሉ ስለሚችሉት ቀውሶች ከበቂ በላይ ግንዛቤ እንዳለው ይገለፃል፡፡

ኢሕአዴግ በቅርቡ ባወጣው ልሳኑ ላይ እንዳመለከተው ከግጭቶቹ ጀርባ የከሰሩ ፖለቲከኞች አሉ፡፡ "የከሰሩ ፖለቲከኞች" ብሎ ኢሕአዴግ ከሚገልፃቸው ተቃዋሚዎች በተጨማሪም የመንግሥት ባለስልጣናት ራሳቸው የሃይማኖት ግጭት ውስጥ የራሳቸው አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳበረከቱ ያምናል፡፡ በየከተማ አስተዳደሩ የእስልምና እምነት ተከታይ ሲሾም መሬት ለሙስሊሙ፤ ክርስቲያን ከንቲባ ሲሾም ለክርስቲያኑ መስጠቱ መንግሥት ነፃ ነኝ ቢልም በሃይማኖት ገመድ ተጠልፎ እንዲወድቅ ጥረት መደረጉን ያምናል፡፡

"መንግሥት ከሃይማኖት ነፃ ነኝ" ቢልም ኃላፊዎቹና ባለስልጣናቱ ግን የአንድ ወይም የሌላ እምነት ተከታይ መሆናቸው አይቀርም፡፡ የሃይማኖት ተከታይነታቸውንና የመንግሥት ኃላፊዎቻቸውን ሳያደባልቁ መስራት ያቃታቸውም መንግሥት በማይፈልገው ገበያ ውስጥ እንዲገባ ያደረጉት ባለስልጣናትም እንዳሉ ኢሕአዴግ ይገልፃል፡፡

እንደ ገዢው ፓርቲ እምነት ከተቃዋሚዎች የፖለቲካ ፍላጎት፣ ከመንግሥት ባለስልጣናት ከመስመር የወጣ አካሄድ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የሽብርና የአክራሪነት አካሄዶች በአገሪቱ ያለውን መቻቻልና አብሮ መኖር ላይ ጥቁር ጠባሳ ለመጣል እንደሚዳዳ ያስረዳል፡፡

የሃይማኖት አለመግባባቶች መንስኤ የእምነቱ ተከታዮች ብቻ ሳይሆኑ የመንግሥት የመዋቅር ክፍሎች፣ በተለይም በታችኛው እርከን ላይ ያሉ አመራሮች እንደሆኑም በማስረጃ የሚቀርቡ ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡ በደሴ የሆነውም ይኸው ነው፡፡ ለሁለት ሃይማኖቶች አንድን መሬት መስጠት ያስከተለው ቀውስ አለ፡፡ በጎንደርም የአንድ እምነት ቦታ ለሌላው ተሰጠ በሚል ግጭቶች ተከስተዋል፡፡ የእምነቱ ተከታዮች ችግርም ሳይሆን በተለይ ኢህአዴግ እንደሚገልፀው የሚቀመጡት ከንቲባዎች ወደሚያምኑት እምነት መሳባቸውና የመንግሥትን ሥራ ከሃይማኖት ጋር በመቀየጣቸው ነው፡፡

እነዚህን የመሳሰሉ ጉዳዮች በየጊዜው ሲታዩና ሲያጎነቁሉ "መንግሥት ሃይማኖቱ ምንድን ነው"፤ "ነፃ ነኝ፤ ሃይማኖቴ የሕዝቤንና የአገሬ ሰላምና ደህንነት ነው" ቢልም እነዚህ ሁሉ መጠላለፎችስ የሚሉ ጥያቄዎች ይቀርባሉ፡፡

6 comments:

Yiferdal said...

Do you know Amare Aregawi?he is the one and the other corner of woyane.I don't expect good news from his news paper/Reporter/.
we have 18 years experians from Woyane. please woyane is woyane don't give attention to them instted of working to protect the Ethiopian orthodox Tewahido church /EOTC/.
If you protect the Church you protect the country/ETHIOPIA/.God be solve the problem.

Anonymous said...

Reporter "paper" has never been the voice of the Ethiopian people.So, what do you expect from Reporter? We all know Reporter is Reporter-the ever voice of Weyanne.Those who write what they write on this "paper"have no their own fair minds. They know it this fact more than anybody tells them. I feel bad for them for being weyanne tools. Please I advise you to be a fair minded journalists.

Anonymous said...

IYYAA IYYA DHAGEESISA YOO IYYAN MALEE OLLAAN NAMAAF HINDIRMATTU,YOO IYYAN MALEE KAABAAN IYYAARIIKOO HIN JIGUU.RAAJIIN MUL'ATA DANI'EL 7;25RAAWACHUUF MAANE-TEEQEEL-FAAREES

CHANG IS COMING SOON FOR ETOC AND FOR ALL ETHIOPIA

MN

Anonymous said...

MUL'ATA DANI'EL BOQONNA 7 KANJEDHU BOQONNAA 5;25 TI HASIRAAWU.

"Adaamiin ollaa hagamssaa jirtuu himimaanshe hin qooruu" jedhama kanaafuu kuufaatii amantii ortodoxii kan haawan bayeen jiru waanta'eef durbidubummaan deesse haadhi waaqayyoo qulqulleettin maarami akka nuuwajin taatuuf hakadhaannu.mn

Anonymous said...

so basically the massacre in Desse is a way to threaten those that dont follow the Patriaarch. I grew up in US since I was 12 and this is the first time that I have been following up on the recent meeting that was called and held without the Patriarch. At the same time, the government kills in the desse church to show Abatoch in sinodose that gov. will take steps if they dont follow Patriarch. Tinbete daniel 'Talakun semehen yemetera hezbohchehen ateresaw'

Anonymous said...

I am hoping and praying kidus sinodose continue on what their doing without the Patriarch because people have died in disse, for the Abatocch good cause.Egizabeher yenezihine dem yayayele. Yebekelalem!!

'Geta hoy Semehen lementera hezboche baryawoche atersan"

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)