July 3, 2009

የወርቅ ኢዩቤልዩ እንዲህ አይከበርም ያለ ማነው? የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፕትርክና 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል አከባበር በቤተ ክህነቱ ግቢ


(Photo: Patriarch Basilios Inauguration in Cairo)
(ምጥው ለቤ azekiri21@googlemail.com )
«የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጵጵስና እና ፕትርክና ከግብጻውያኑ እጅ ተፈልቅቆ ወጥቶ በኢትዮጵያውያኑ ከተያዘ ወዲህ ለአገሪቱ ፈር ቀዳጅ የነበረው መልካም የአስተዳደር ፈሊጧ ጠፍቷል፤ አገርን አንድ አድርጎ ያኖረው አንድነቷ ተናግቷል፤ ከአስተዳደር መንበሯ የሚፈነጥቀው ቅድስናዋ ደብዝዟል» እያሉ በጠና የሚሞግቱ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ እንደ እነዚህ አበው አስተያዬት ቤተ ክርስቲያ ከመንበረ ማርቆስ ሙቀትና ክብካቤ ከቶዉኑም መለየት አልነበረባትም፡፡ ይልቅዬስ እንደ ጥንቱ መንበረ ፕትርክናዋ እስክንድርያ ኾኖ አስተዳደሯ ከዚያው ተመርጠው በሚመጡ ብፁዐን አበው እየተመራ መቀጠል ነበረበት ባዮች ናቸው፡፡ በአንጻሩ የሚያመዝነው የቤተ ክርስቲያሩ ሊቃውንት አስተያየት ደግሞ ያኛውን በጽኑ ያወግዛል፡፡ እነዚህኞቹ «ቤተ ክርስቲያኒቱ በጥምቀት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ወልዳ ዕውቀት መንፈሳዊን እየመገበች ያሳደገቻቸው የበቁ የተጉ አባቶች እያሉ ምነው የአገሩን ቋንቋና ባሕል በማያውቁ . ሕዝቡንም በቋንቋው እየባረኩ ማስተማር በማይችሉ «ባዕዳን» እየተመራች ትቀጥል)» ብለው ይከራከራሉ፡፡

በሁለቱም ገጽ ያሉት ሊቃውንት እንዳለመታደል ኾኖ በይፋ በተዘጋጀ ጉባኤ አቅርበው ባይከራከሩበትም በየምዕላዳቸው የሚሰጡት ምክንያት አለ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ቡድኖች ለክርክራቸው ግብ መምታት መጽሐፋዊና ታሪካዊ ምክንያት ይሰጣሉ፡፡ መጽሐፋዊው ምክንያታቸው ልዩ ልዩ ሥጋውያትና መንፈሳውያት የአስተዳደር ድንጋጌዎችን ከያዘው መጽሐፍ /ፍትሐ ነገሥት/ የሚጠቅሱት ነው፡፡ ያንን ጥቅስ እዚህ ልንጠቅስላቸው ግድ ይላል፡- «ወሰብአ ኢትዮጵያ ኢይሲሙ ላዕሌሆሙ ሊቀ ጳጳሳት እማእምራኒሆሙ፤ ወኢበሥምረተ ርእሶሙ፡፡ እስመ ጳጳሶሙ ይከውን እምታሕተ እዴሁ ለበዓለ እስክንድርያ ወውእቱ ዘይደልዎ ይoe!ም ላዕሌሆሙ ሊቀ እምኀቤሁ፤ ዘውእቱ መትሕተ ሊቀ ጳጳሳት፡፡ የኢትዮጵያ ሰዎች ከዐዋቂዎቻቸው ወገን፤ በራሳቸውም ፈቃድ ሊቀ ጳጳሳትን ለራሳቸው አይሹሙ፡፡ ጳጳሳቸው ከእስክንድርያው በዓለ መንበር ሥልጣን በታች ነውና፡፡ ከሊቀ ጳጳሳት በታች የሆነውን ሊቀ ጳጳስ ከእርሱ ወገን ሊሾምላቸው የሚገባውም እርሱ ነው፡፡» (ፍትሐ ነገሥት፣ አንቀጽ 4፣ ቁጥር 50)
እነዚህ ቡድኖች ክርክራቸውን ጥግ ድረስ ለመውሰድ የሚጠቅሷቸው ሌሎችም መጽሐፋዊ ታሪኮች አሏቸው፡፡ ከላይኛው ተጨማሪ እንዲኾን የልዩ ልዩ ቅዱሳን ዜና ሕይወትና ተጋድሎ ከሚያትተው መጽሐፍ /ስንክሳር/ አንዱን ብቻ እንጥቀስ፡፡

«በቅዱስ ሐርቤ ዘመነ መንግሥት አባ ሚካኤልም ለኢትዮጵያ ጳጳስ ሁኖ በነበረበት ግዜ፡፡ የኢትዮጵያ ንጉሥ ሐርቤ ለኢትዮጵያ አገሮች ኤጲስ ቆጶሳትን ይሾም ዘንድ አባ ሚካኤልን አዘዘው፡፡ አባ ሚካኤልም ያለ ሊቀ ጳጳሳቱ ትእዛዝ ሌሎች ኤጲስ ቆጶሳትን መሾም አልችልም ብሎ ለንጉሡ መለሰለት፡፡ ስለዚህም የኢትዮጵያ ንጉሥ ወደ አባ ገብርኤልና ወደ ግብፅ ንጉሥ እየለመነና እየማለደ ንጉሡ አባ ገብርኤልን እንዲአዝለት፤ አባ ገብርኤልም ለአባ ሚካኤል እንዲ ፈቅድለትና በተጨማሪ ሌሎች ኤጲስ ቆጶሳትን አስቀድሞ በሾሟቸው ላይ እንዲሾም እንዲህ መልእክትን ላከ፡፡ የግብፅ ንጉሥም የኢትዮጵያን ንጉሥ ፈቃዱን ሁሉ ይፈጽምለት ዘንድ አባ ሚካኤል እንዲፈቅድለት አባ ገብርኤልን አዘዘው፡፡ ከዚህ በኋላ መካንንቱ ወደ ግብፅ ንጉሥ ዘንድ ገብተው እንዲህ አሉት፡፡ በኢትዮጵያ ኤጲስ ቆጶሳት ቢበዙ ደፍረው ጳጳሳትን ይሾማሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ከቶ ወደ እኛ አይመጡም፡፡ ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ ይህን አባት አባ ገብርኤልን እንዲህ አዘዘው፡፡ ከእንግዲህ በኢትዮጵያ አገር ኤጲስ ቆጶሳትን እንዳይሾም ለኢትዮጵያ ንጉሥ የውግዘት ደብዳቤ ላከ፡፡ ሊቀ ጳጳሳቱም የግብፅ ንጉሥ እንዳዘዘው ላከ፡፡ የውግዘት ደብደቤም ወደ ኢትዮጵያ ንጉሥ ደርሳ በተነበበች ጊዜ የንጉሡ አዳራሽ ተቃጠለ፡፡ በኢትየጵያ አገርም ረኃብና ቸነፈር ሆነ፡፡ ዝናብም ተከለከለ፡፡ ችግርም ሆነ፡፡ የኢትየጵያ ንጉሥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ተላልፎአልና፡፡ ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሥ ተመልሶ ተጸጸተ፡፡ ወደ ግብፅም ይህን አባት አባ ገብርኤልን እንዲአዝለትና ከግዝቱ ይፈታው ዘንድ እየለመነ መልእክትን ላከ፡፡ የግብፅ ንጉሥም አዘዘለት፡፡ አባ ገብርኤልም የመፈቻና የቡራኬ ደብዳቤ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ እየባረከ ወደ ኢትዮጵያ ንጉሥ ላከ፡፡ ይህች የበረከት ደብዳቤ ወደ ኢትዮጵያ አገር ደርሳ በተነበበች ጊዜ እግዚአብሔር መዓቱን ከላያቸው አርቆ ይቅርታውን ሰጣቸው፡፡ ዝናብም ወረደላቸው፡፡ ቸነፈርም ተወግዶ ታላቅ ደስታ ሆነ፡፡ ይህም በዘመኑ ሆነ፡፡» /ስንክሳር፣ ሚያዝያ 10/

ከታሪክ አንጻር የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ 13ኛውን መቶ ክፍለ ዘመን ከ20ኛው ጋር የሚያገናኝ ነው፡፡ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንድ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አባት «ጵጵስና የግድ ለመንበረ ማርቆስ» ለሚሉቱ እንደ መከራከሪያ ነጥብ የሚቀርብ ተግባር ፈጽመዋል፡፡ ነገሩም እንዲህ ነው፡- በዓለም ታሪክ ተመዝግቦ እንደ ሚገኘው እ.ኤ.አ. ከ1095 - 1291 ክርስትና አብባ ፍሬ መስጠት የጀመረችበት የላቲኑ ዓለም በወቅቱ በነበረው አዝማችነት ቅድስት አገር ኢየሩሳሌምን ከመሐመዳውያን ቁጥጥር ነጻ ለማድረግና አካባቢውንም በኃይል ክርስትናን እንዲቀበል በማድረግ ጦርነት አውጆ ነበር፡፡ በጦርነቱ የተነሳ እንደተለመደው ኢትዮጵያን የሚመራት አባት ከእስክንድርያ መምጣት አልቻለም ነበር፡፡ በወቅቱ በቅድስናቸውና በአስተዳደራቸው አንቱ የተባሉትና የደብረ ሊባኖስ እጨጌ የነበሩት ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት መንበረ ጵጵስናውን እንዲይዙ ተደርጎ ነበር፡፡ ኢትዮጵያዊው ጻድቅም ተወልደው ባደጉበት ሕዝብ መካከል ተግተው በታሪክ ሲዘከሩ የሚኖሩ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሰጥተዋል፡፡ ቃለ እግዚአብሔር ያልሰማው ሕዝብ እንዲሰማ ሐዋርያት በዓለም ዙሪያ ወንጌልን ለመስበክ እንዳደረጉት ከደቀ መዛሙርታቸው የበቁትን መልምለው ኢትዮጵያን አከፋፍለው ለስብከት አሰማርተዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያሩ አስተዳደርም እንዲጠናከር፣ ገዳማቱና አብነት ት/ቤቶቹ እንዲስፋፉ አድርገዋል፡፡ ካህናትን ሹመዋል፡፡

መካከለኛው ምስራቅን ለረጅም ጊዜ ሲያውክ የነበረው የመስቀል ጦርነት ተጠናቆ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን እንደ ተለመደው ከልጆ‟ መርጣ አንዱን ወደ ርስት አገሯ ኢትዮጵያ ስትልክ በመንፈሳዊ ሕይወት ብስለታቸው በአስተዳደር ብቃታቸው የተመሰከረላቸው ጻድቅ አባት አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ይሁኑ በወቅቱ ያንን ያዩ ሊቃውንት «አንፈልግም፤ ራሳችንን በራሳችን እናስተዳድራለን፤ እንግዲህስ ይበቃናል» ሳይሉ የመጡትን አባት በክብር ተቀብለው መንበሩን አስረክበዋል፡፡ ስለዚህ የመጀመሪያዎቹ ተከራካሪዎች ይኸንን የ13ኛው መ.ክ.ዘ. ታሪክ በ20ኛው መ.ክ.ዘ. ኢትዮጵያውያን አበው ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ የተፈጠሩ አሉታዊ አስተዳደራዊና መንፈሳዊ ችግሮች ጋር እያገናኙ ይሞግታሉ፡፡ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ እግዜሩ ቢፈቅድለት የቤተ ክርስቲያሩ ጵጵስናም ኾነ ፕትርክና በኢትዮጵያውያኑ አባቶች ከተያዘ ወዲህ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡

ከላይኞቹ አንጻር ቆመው የሚከራከሩት የሚያቀርቡት ምክንያት ከቤተ ክርስቲያሩ የታሪክ ውቅያኖስ የሚቀዳ ነው፡፡ ላይኞቹ የሚጠቅሷቸውን መጽሐፋዊ ምክንያቶች «ግብጾቹ የአስተዳደር ቀንበራቸውን ሊያጠብቁብን በአዋልድ መጻሕፍቱ የጨመሯቸው «ስርዋጽ» » ብለው ውድቅ ያደርጓቸውና፤ የቤተ ክርስቲያሩን አስተዳደር ከግብጾች እጅ ፈልቅቆ ለመውሰድ ኢትዮጵያውያን ነገሥታትና ሊቃውንት በየዘመኑ ያደረጓቸውን እልኽ አስጨራሽ ትግሎችና የተገኘውን ድል በኩራት ይጠቅሳሉ፡፡

እስካሁን ባሉ መረጃዎች በ4ኛው መ.ክ.ዘ በአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ተጀምሮ ለረጅም ጊዜ የቆየውን «የግብጽ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ቅኝ ግዛት» ለመጀመሪያ ጊዜ በመቃወም ኢትዮጵያውያን አበው ኤጲስ ቆጶሳት ኾነው ይሾሙ ዘንድ ድምጹን ያሰማው በቤተ ክርስቲያሩ ቅዱሳን ተብለው ከተመዘገቡ አበው አንዱ የኾነው ንጉሥ ሐርቤይ /1060  1077 ዓ.ም/ ወስመ ጥምቀቱ ገብረ ማርያም ነበር፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በየዘመኑ የነገሡ ነገሥታትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያንኑ ጥያቄ እያነሱ ከመንበረ ማርቆስ ተሹመው የሚመጡ ጳጳሳትን ሲሞግቱ ቆይተዋል፡፡ ለእነዚህኞቹ መንበረ ጵጵስና ወፕትርክናው በግብጾቹ ተይዞ በመቆየቱ ቤተ ክርስቲያሩ ካገኘችው ያጣችው ይበዛል፡፡ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት አገሪቱንና አካባቢዋን ከአረማውያንና እስማኤላውያን ጥቃት አልታደጉም፤ ለእነሱ እጅ መንሻና መማለጃ የቤተ ክርስቲያኒቱ በእሷም በኩል የአገሪቱ ሀብትና ንብረት ባክሩል፤ አስተዳደር ባለመቻላቸው በየዘመኑ ቤተ ክርስቲያሩ በልዩ ልዩ ውስጣዊ የነገረ ሃይማኖትና አስተዳደራዊ ክፍፍሎች እንዲሁም ግጭቶች እንድትታመስ አድርገዋል፤ እነሱ ከፊት ቆመው መንገድ በመዝጋት ኢትዮጵያውያኑ ሊቃውንትና ቅዱሳን በዘመናቸው ለአገራቸውና ለቤተ ክርስቲያናቸው ጠቃሚ ሥራ ሳይሠሩ እንዲያልፉ አድርገዋቸዋል፤ አገሪቱ በጠላት እጅ ሥር ስትወድቅ ሕዝቡንና ቤተ ክርስቲያሩን ለጠላት ትተው ወደ አገራቸው ሔደዋል ወ.ዘ.ተ. የሚሉ ወቀሳዎችን ደርድረው እራሳችንን በራሳችን ማስተዳደር በመቻላችን ቤተ ክርስቲያናችን አድጋለች ይላሉ፡፡

በእውነቱ የክርክር ገመዱ በዬትም ያዝምም በዬት ዛሬ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከዬትኛውም የውጭ አስተዳደር ነጻ ኾና፤ መናብርተ ጵጵስናዋም ይሁኑ ፕትርክናው በራሷ ልጆች ተይዘው «ራሷን በራሷ» እየመራች ትገኛለች፡፡ እንደውም አክርሞን ሊሰናበተን ውኃውን ማፍሰስ ብቻ የቀረው 2001 ዓ.ም ይህ አስተዳደራዊ ነጻነት በከፊልና ሙሉ በሙሉ የተረጋገጡበት ወርቃማ የታሪክ አንጓዎች ምክንያታዊ በኾነ መልኩ የሚዘከሩበት ዓመት ነው፡፡ እሱም ብቻ አይደለም፤ (ከላይ ከነክርክራቸው ቢጋር ካቀርብካችው ቡድኖች የትኞቹን ያስደንግጥ ዬትኞቹን ጥርስ ያስነክስ ባላውቅም) ከመሰንበቻው ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ግቢ ቱር ብሎ እየጓነ በመፈንዳት የቤተ ክርስቲያሩን ልጆች እያሸበረን ያለው ዜና መፈንዳት የጀመረበት ያለፈው የግንቦትና ፍንዳታ ተጋግሎ የቀጠለበት እየተገባደደ ያለው የሰኔ ወራት፤ አበው ለ1600 ዓመታት የተጋደሉለት የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ነጻነት ትግል በከፊልና ሙሉ በሙሉ ድል ያስመዘገበባቸው 80ኛና 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ መታሰቢያ ወራት ናቸው፡፡

በቤተ ክርስቲያሩ የታሪክ መዝገብ ጵጵስናን በሚመለከተው ምእራፍ እንደ ሰፈረው ግብጾቹ መልካም ፈቃዳቸው ኾኖ ለመጀመሪያ ጊዜ አራቱ ኢትዮጵያውያን አበው [መምህር ደስታ (አቡነ አብርሃም)፤ መምህር ኃይለ ማርያም (አቡነ ጴጥሮስ)፤ መምህር ወልደ ኪዳን (አቡነ ይስሐቅ)፤ መምህር ኃይለ ሚካኤል (አቡነ ሚካኤል)] «ይደልዎ» ተብለው ኤጲስ ቆጶስነት የተሾሙት ግንቦት 25 ቀን 1921 ዓ.ም ነበር፡፡ ዘንድሮ 80ኛ ዓመቱ፡፡ ኢትዮጵያ በፋሺስት እሳት ስትጋመድ ባዕታቸውን ወደ ግብጽ አዙረው እሳቱ የፈጀውን ፈጅቶ ሲጠፋ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት የመጨረሻው ግብጻዊ የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ በሞተ ሥጋ አስገዳጅነት መንበሩን ሲለቁ /መንበረ ሊቀ ጵጵስናውን/ በ1943 ዓ.ም ተረክባ ስታበቃ፤ ቤተ ክርስቲያሩ ሰኔ 21 ቀን 1951 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነቷ ግቢ መንበረ ፕትርክናዋን ሠርታ የራሷን ልጅ በመሾም ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ግዞት ሙሉ በሙሉ ነጻ ኾነች፡፡ ልክ 50ኛ ዓመቱ፡፡

ታዲያ ከእግዚአብሔር በታች ቤተ ክርስቲያሩን እንዲመራ ሥልጣን የተረከበው ቅዱስ ሲኖዶስ ለዛሬ ሕልውናው መሠረት የኾኑትን እነዚህን በዓላት ሳያስበው በኾነው መልኩ እያከበራቸው እንደኾነ ይስተዋላል፡፡ በኾነው መልኩ ሲባል አንድም ሲኖዶሱ እየተገባደደ ያለው ዓመት ከላይ የተጠቀሱት ዐበይት ድሎች የሚወሱበት መኾኑን የዘነጋው፤ ምናልባት አስታውሶትም ከኾነ ሊያከብረው ግድ የሌለው ስለ ሚመስል (የአንድን ግለሰብ ልደት ወይም የሹመት በዓል ለማክበር ቀሚሱን እየጎተተ ገንዘብ ሲመዠርጥ ወገቡ እስኪንቀጠቀጥ ቆሞ ሲያወድስ የምናየው ሲኖዶስ ይኸንን ታላቅ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ነጻነት የተረጋገጠበትን በዓል ለማክበር በግልጽም በስውርም ለማክበር ሲንቀሳቀስ አላየንም አልሰማንምና )፤ አንድም ብዙ ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ዐበይት የመታሰቢያ በዓላት /ያውም መንፈሳውያት/ በሚከበሩበት መልኩ ሳይኾን በራሱ አስተዳደር እንቅስቃሴ ካለመርካት በመጣ ክርክርና ጉትቻ እያከበረው ስለሚመስል ነው፡፡ የኾነ ጉዳይ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል ብዙ ታስቦ ተደግሶለት ሰፋ ያለ እድምተኛ ተጋብዞ በደስታ ሲከበር እያየ ለኖረ ሕዝብ «ጥላቻና ጉትቻ ምን በዓል ማክበር ነው)» ቢል የሚገርም አይኾንም፡፡ ነገር ግን ለዚህ ጽሑፍ አቅራቢ እነዚያ በዓላት እየተከበሩ ነው፡፡ ይህንን የሚለው እየተስተዋለ ያለው የእርግጫና ቱጫ በዓል አከባበር ለቤተ ክርስቲያሩ የነገ እርምጃ መንገድ ይጠርጋል፤ በዚህም በያለንበት ኾነን የቤተ ክርስቲያናችንን አስተዳደራዊ ብልዬት እያየን አንገታችንን ያስደፋንን ሁሉ ቀና ያደርገናል ከሚል ነው፡፡
እንደተሰማው ባለፈው ግንቦት (የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን አበው ሥልጣነ ኤጲስ ቆጶስነትን በተረከቡበት ወር ልክ 80ኛ ዓመት ላይ) ተደርጎ በነበረው መደበኛ ጉባኤ ላይ በትርያርኩና የቤተ ክርስቲያሩ አስተዳደራዊ ጉዞ መንገዱን ስቷል ይስተካከል ባሉ ሊቃነ ጳጳሳት መካከል ሞቅ ያለ እሰጥ አገባ ተነሥቶ ነበር፡፡ እሰጥ አገባው እንደገና የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ትርያርክ ከፍ ባለ መንፈሳዊ ደስታ የተመረጡበት የሰኔ ወር 50ኛ ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት ምናልባት በየወሩ ሲሰበሰብ የመጀመሪያ በኾነ መልኩ ሰኔ 29 ቀን 2001 ዓ.ም አስቸካይ ምልአተ ጉባኤ እንዲጠራ ኾሩል፡፡ ኃላፊነት ያለባቸው ሊቃነ ጳጳሳትም ለዚሁ ታላቅ ጉባኤ ከየሀገረ ስብከታቸው ወደ መንበረ ትርያርኩ እየተሰበሰቡ ነው፡፡ በፍንዳታው እየተረበሽን ያለን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ ወሳኝ ጉባኤ አንገታችንን ላስደፉን በርካታ አስተዳደራዊ ችግሮች መፍትሔ ይሰጣል ብለን ውጤቱን በጉጉት እየጠበቅን ነው፡፡
የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ የጉባኤው ሒደትና ውጤት የሚከተሉት እንዲኾኑ ይመኛል፡፡ ወዲያውም መልእክቱን ያስተላልፋል፡፡
1. የዚህ ቅዱስ ጉባኤ አባላት /ብፁዐን አበው/ ከእንካ ሰላትያ ርቀው የቤተ ክርስቲያሩን ልጆች በሀፍረት አንገታችንን ያስደፉ ልቡናችንን ሲበዘብዙ የሚኖሩ መሠረታዊ ችግሮች ላይ ተወያይተው በመንፈሳዊ ሐሴት እግዚአብሔርን እንድናመሰግን እነሱንም እንድናከብራቸው የሚያደርጉ ውሳኔዎችን በጉጉት እንደምንጠብቅ እንዲረዱ፤ እንደ ተለመደው በኮሚቴ ይጠና ብላችሁ እንዳትቀብሩትና እንዳትቀብሩን፤

2. ሊቃነ ጳጳሳቱ ቤተ ክርስቲያናቸው ሥልጣኑን የሰጠቻቸው ከውስጣዊ ምዝበራና ከውጫዊ ውርወራ እንዲጠብቋት መኾኑን ተገንዝበው ያለምንም ፍርሐትና አድር ባይነት ቀረቡ በተባሉትም ኾነ እነሱ በየማስታወሻቸው በያዟቸው ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግሮች ዙሪያ እንዲከራከሩ

3. ጉባኤው በቤተ ክርስቲያሩ መሠረታዊ የአስተዳደር ችግሮች ላይ ተወያይቶ መፍትሔ ሲሰጥና ቤተ ክርስቲያሩ ተጠያቂነትንና ግልጽነትን ያረጋገጠ አስተዳደራዊ ስልት ስትዘረጋ የጥቅም ጉሮሮአችን ተዘጋ ብለው የሚጮኹ ውሾች በቤተ ክህነቱ ውድማ እንደሚኖሩ አውቀው እዚያ ወርቃማ ውሳኔ ላይ እንዳይደርሱ በግልጽና በስውር የሚያቀብሏቸውን የሐሳብ ተዋሕስያን ይዘው ወደ ተቀደሰው ጉባኤ እንዳይገቡ፤ የሽጉጥ ማስፈራሪያቸውንም ከቁብ እንዳይቆጥሩ፤

4. ውይይታቸውና ውሳኔያቸው ሁሉ የነገውን የቤተ ክርስቲያን ጉዞ የሚያስተካክል እንጂ የትላንትን ስሕተት የሚደግም ወይም ምክንያት የሚሰጥ እንዳይኾን፤

5. የአገሩ መንግሥት ከቤተ ክህነቱ ቅጽር ግቢ ተስፈንጥሮ ወደ ላይ ጉኖ ሲያበቃ የሚነጉደውን ዜና አልሰማም ማለት ጅልነት ስለሚኾን በግልጽም ይሁን በስውር በጉባኤው ላይ እጁን እንዳያሳርፍ፤ ለአባቶቻችን ነጻነት እንዲሰጥ፤

6. ምእመናን አሁን ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት ያገለግሉን ዘንድ እግዚአብሔር የሾመልን አገልጋዮቻችን እንጂ የቤተ ክርስቲያሩ ባለቤቶች እኛ መኾናችንን ተረድተን ጉዳዩን በጥንቃቄ እንድንከታተለውና ነገ እናገኘው ዘንድ ለምንፈልገው የእናት ቤተ ክርስቲያናችን ሙቀት እውንነት አባቶቻችን በጥንካሬ ተወያይተውና ተከራክረው ጠቃሚ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ በያለንበት ግፊት እንድናደርግ፤

7. የቤተ ክርስቲያሩን የነገ ጉዞ የተቃና እንዲኾን ከልብ የሚመኙና ለዚያም በትጋት የሚሠሩ ግለሰቦች፣ ድርጅቶችና ማኅበራት ቤተ ክርስቲያን ከተጣባት የአስተዳደር ደዌ የምትፈወስበት ጊዜው አሁን መኾኑን ተረድተው እውነት እንድታሸንፍ የቻሉትን ያህል እንዲያደርጉ፤

ያ የኾነ ጊዜ ጵጵስና ወደ ኢትዮጵያ የገባበት 80ኛ ዓመት ቤተ ክርስቲያሩ መንበረ ፕትርክናዋን አደላድለ ከልጆ‟ መርጣ ሎመጀመሪያ ጊዜ ያስቀመጠችበት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል ተከበረ እንላለን፡፡ ይህችን አጭር መጣጥፍ ሳዘጋጅ በተለይ የጵጵስናን የሽግግር ታሪክ በሚመለከት ዲ.ን መርሻ አለኸኝ የተባሉ ሰው «ዜና ጳጳሳት» በሚል አሳትመው ያቀረቡልን መጽሐፍ በዋና ምንጭነት አገልግሎኛልና ምስጋናዬ ይድረሳቸው፡፡ ቸር ወሬ ያሰማን፡፡

3 comments:

Anonymous said...

we hope so sir!

Anonymous said...

ISNA… Evangelical Call for Faith Coalition

By Fahad Faruqui


"I love my next door Muslim neighbour and I love you," Warren told a cheering, receptive ISNA audience.

WASHINGTON — America’s famed evangelist Pastor Rick Warren has proposed a Muslim-Christian coalition to combat bias and prejudices across the world.
"Frequent stereotyping of all of us needs to be challenged," Warren, founder and pastor of the Southern California Saddleback Church, told the annual convention of the Islamic Society of North American (ISNA), currently in session in Washington DC.

"It needs to be challenged not by one group, in other words Muslims challenging Muslim stereotypes and Christians challenging Christian stereotypes.

"We need a coalition of people…who’d say that we’re not going to allow stereotyping of anybody."

Warren, one of the most influential Christian leaders in the world, told his Muslim audience that "the two largest faiths on the planet" must start action to combat bias and solve global problems.

"Talk is very cheap. I am not interested in interfaith dialogue; I am interested in interfaith projects."

Outlining practical steps, Warren called on Muslims and Christians to work together to promote peace, restore civility and create respect among people.

"This is the time for action; this is the time for civility; this is the time for respecting each other; it’s the time for the common good."

He also urged them to be partners in working to end "the five global giants" of war, poverty, corruption, disease and illiteracy.

"Some problems are so big you have to team to tackle them."

ISNA's annual convention, which dates back to 1963, is the largest gathering of Muslims in North America attended by tens of thousands every year.

This year’s convention, which ends on July 6, features some 300 speakers touching on several key issues such as spirituality, economic development, family, Islamic banking and outreach.

Muslim Bias

Warren, a popular evangelist whose churches minister to some 20,000 people every week, expected criticism for accepting the invitation to address the Muslim gathering.

"It's easier to be an extremist of any kind because then you only have one group of people mad at you," he said in his 20-minute speech.

"But if you actually try to build relationships — like invite an evangelical pastor to your gathering — you'll get criticized for it. So will I."

Anti-Muslim sentiments have been on the rise in the US, home to nearly seven to eight million Muslims, since the 9/11 attacks.

Many American Muslims face discrimination and stereotyping because of their Islamic attires or identities, while others blame the problem on misconceptions about their faith.

"The fastest way to raise money is to demonize the enemy and make people hate them," Warren underlined.

"The fastest way to raise ratings on television is to create conflict."

The Pew Research Center for the People and the Press and the Pew Forum on Religion and Public Life found that the negative view of Islam in society is largely affected by the media.

The head of the Union for Reform Judaism (URJ), America's largest Jewish movement, has accused US media and politicians of demonizing Islam and portraying Muslims as "satanic figures."

"I love my next door Muslim neighbour and I love you," Warren told a cheering, receptive ISNA audience.

LOM said...

Dear Anonymous

I believe that by quoting Fahad Faruqui's article you have placed your view.
I would like to comment on
One
The posted article is about the history of EOTC.I could not see the direct relation.
Two
For the record,you have quoted that muslims are discriminated and stereotyped becuase of their identity.What is that identity ?That identity is the accumulated effect of years and years of constant violence and cruelity caused by the followers starting from the finder (P.Muhammed).Putting that aside or if all that was not true or if we just focus on what is happening in the world right now .There were 40Jihad Attacks Reported - 154 Dead Bodies - 290 Critically Injured
from june 27 to july 03 all in the name of 'Allah'.If Islam is not what you say it isn't why didn't its religous leaders condemn this act or even apologze for the victims family or even hold a prayer.
Think about it and answer it for yourself

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)