July 6, 2009

አያሌው ግራኝ ወይስ በረከት ግራኝ? (ክፍል 2)

አያሌው (ጎበዜ) ግራኝ ወይስ በረከት (ስምዖን) ግራኝ?

(ደጀ ሰላም፤ ጁን 6/2009)
በቅርቡ የቅ/አርሴማን ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት የደሴ ሕዝብ ሲጠይቅ ምእመኑ በጥይትና በቆመጥ ከተበተነ ወዲህ ክርስቲያኑ የአማራውን ክልል ፕሬዚዳንት አያሌው ገበዜ ሳይሆን አያሌው ግራኝ እንዳላቸው መዘገባችን፤ አቶ አያሌው ራሳቸው ከዚያው ከወሎ አካባቢ የመጡ ሰው እንደሆኑ መጻፋችን ይታወሳል። ጽሑፉን ያነበቡ አንዳንድ ሰዎች ግን አቶ አያሌው ከአማራው ክልል ባለሥልጣናት መካከል በስነምግባራቸው የተመሰገኑ፣ በሃይማኖታቸውም የማይነቀፉ ጥሩ ሰው መሆናቸውን በመግለጽ “ግራኝ” የሚለው ስም እንዳማይገባቸው ተናግረዋል።
ምናልባትም ቤተ ክርስቲያንን አምርረው የሚጠሉት የአቶ በረከት እጅ ሊኖርበት ስለሚችል “ግራኝነቱን” ከዚህ በሁዋላ ለአቶ በረከት መተላለፍ እንዳለበት ጠቁመዋል። የመንግስት የመገናኛው መስሪያቤት ሚኒስትር በረከት ስምዖን ስለ ቤተ ክርስቲያን ሊጠይቅ የወጣውን ሕዝብ “ድብቅ የፖለቲካ ዓላማ ያለው” ሲሉ “በእንግሊዝኛ” መናገራቸው በሰፊው መዘገቡ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የደሴ ሙስሊም ወገኖች መንግሥት በሚያቀርበው ዜና ሙስሊሙ ሕዝብ የቅ/አርሴማ ቤተ ክርስቲአን እንዳትሠራ ተቃውሞ እንዳለው አድርጎ ማቅረቡን በመቃወም በሰላማዊ ሰልፍ ሐሳባቸው ለመግለጽ ፍላጎት እንዳላቸው የደሴ ዜና አቀባዮቻችን ተናግረዋል። “እና ምንም ተቃውሞም፣ ቅሬታም የለንም” ያሉት ሙስሊሞቹ ለምን በእነርሱ ስም እንደሚነገድ እንዳልገባቸው ተናግረዋል። ነገሩ እውነትም እንዲህ ከሆነ ጉዳዩና ተጠያቂነቱ በአቶ በረከት ላይ የሚወድቅ፣ እርሳቸው በክርስቲያኑና በሙስሊሙ መካከል የሚፈጥሩት ችግር አካል እንደሚሆን እነዚሁ ወገኖች ተናግረዋል።

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)