July 31, 2009

ጠቅላይ ቤተ ክህነት “አዲስ ነገር ጋዜጣን” ከሰሰ

• መጋቤ ካህናት ኃ/ሥላሴ “ደጀ ሰላም”ን ነቀፉ፣

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 30/2009)
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት “አዲስ ነገር ጋዜጣን” መክሰሱ ተሰማ። ከግንቦት 2001 ዓ.ም እስከ ሐምሌ አጋማሽ ድረስ በቅዱስ ፓትርያርኩና በቅ/ሲኖዶሱ መካከል የተፈጠረውን ውጥረትና አለመግባባት ስትዘግብ የነበረችው ሳምንታዊ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ታምራት ነገራ እና ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው ሪፖርተር አብርሃም በጊዜው በፖሊስ ተጠርተው የቀረቡት አዲስ አበባ ፖሊስ (አራዳ ክ/ከተማ) ሲሆን ቃላቸውን ሰጥተው በዋስ መለቀቃቸው ታውቋል።


የቅዱስ ፓትርያርኩን ስምና ክብር በማጉደፍ፣ በሐሰት ስማቸውን በማጥፋት እንዲሁም ሐሰተኛ ዜና በማቅረብ የተከሰሱት ጋዘጤኞቹ የምርመራ መዝገባቸው ወደ አቃቤ ሕግ ከተላከ በሁዋላ የሚያስከስሳቸው ሆኖ ከተገኘ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚችሉ ተጠቁሟል። ጋዜጠኛ አብርሃም ይህንኑ ዘግቦ ሲመለስ ባልታወቁ ሰዎች መደብደቡን መዘገባችን ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ “ደጀ ሰላም”፣ ቪኦኤና አንዳንድ የሀገር ውስጥ ጋዜጦች ከጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ጋር የሚቃረን ሥራ ሠርተዋል፣ የቤተ ክርስቲያንን ክብር አዋርደዋል ሲሉ አንድ የቤተ ክህነት ባለስልጣን ተናገሩ። ባለስልጣኑ መጋቤ ካህናት ኃ/ሥላሴ ዘማርያም “መሰናዘሪያ” ከተሰኘ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሚዲያዎቹን ከወቀሱ በሁዋላ በዚህ ጉዳይ አሉበት የተባሉትን ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን “ተሳስተዋል” ማለታቸው ታውቋል።

መጋቤ ካህናት ኃ/ሥላሴ ወደ ካህናት አስተዳደር ከመምጣታቸው በፊት በድሬዳዋ ሀ/ስብከትና በቤቶች አስተዳደር የሰሩ ሲሆን በተለይም በቤቶች አስተዳደር ውስጥ በሚሰሩበት ወቅት የቤተ ክርስቲያኒቱን ቤቶች ቁልፍ በመሸጥ ሀብት ያካበቱ “የማፊያው ቡድን” አባልና “ሙሰኛ (ኮራፕት)” መሆናቸው ይነገራል። በዚህ ምግባራቸው ይታወቁ እንጂ ማንም ደፍሮ የማይናገራቸው በትግሉ ዘመን መሳሪያ አንስተው ከተዋጉትና ስልጣን በኢሕአዴግ እጅ ከገባ በሁዋላም ቀደም ብሎ በትግራይ የሰሩ ነባር ታጋይ በመሆናቸው ሳይሆን አይቀርም ተብሏል።

July 30, 2009

+++++++ - - - - - - ???? ?? About Mahibere Kidusan


Dear Deje Selamaweyan,
Greetings to you all.
Although our mother Church is in great problem, most of us tend to argue about some points only, one of which is Mahibere Kidusan.

For the Church's sake, please limit all your comments about Mahibere Kidusan here. Positive, negatives or questions about MK should and must be posted here. Please be civil!!!
The burning issue for Deje Selamaweyan should be what we should do untill Tikimt. We will re bring that topic to the forfront.

Chere Were Yaseman,
amen
+++++++++++++++++++++++++
(አቤል ዘቀዳማዊ)
ደጀ ሰላም ከምታቀርብልን የመወያያ አርስት እየወጡ በተለያዩ አርስቶች ግርጌ እነ እውነቱ እና መሰሎቹ የማኅበረ ቅዱሳንን ሥም እያነሱት ነው። ለመሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን የሚጠሉ ሰዎች እነ ማን ናቸው? በአጠቃላይ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚጠሉ ሰዎች በሦሥት ከፍለን እንያቸው፦
፩. በዓላማ እንዲጠፋ የሚፈልጉ ናቸው
• አክራሪው የእስልምና ቡድን
• የቤተክርስቲያን የውስጥ መናፍቃን(ተሃድሶ)
• መናፍቃን(“ጴንጤ”)
እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ቡድኖች የማኅበሩን አገግሎት በደንብ ጠንቅቀው ያውቁታል፤ እንዲሁም ዓላማውም በሚገባ ተረድተውታል። አክራሪው እስላም በቤተክርስቲያን ላይ በተለያዩ ጊዜያት የሚያደርሱት ጥፋት እየተከታተለ መረጃ እየሰበሰበ እኩይ ተግባራቸውን እያጋለጣቸው ስለሆነ የማኅበሩን መኖር የእግር እሳታቸው ነው። ወደፊትም ላቀዱት ጥፋት ይከታተለናል ብለው ስለደመደሙ ማኅበሩ እንዲጠፋ ደፋ ቀና እያሉ ነው።ይህ ማኅበር ኢትዮጵያን የማስለም ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅፋት ሆኖብናል ብለው በግልፅ በተለያዩ የእስልምና ፓል ቶክ ውይይት እየሰማናቸው ነው።
ሌሎቹ ሁለቱም መናፍቃን የውስጡም የውጩም ግብራቸውና ዓላማቸው ማኅበሩ በሚገባ አውቆት አጥብቆ ስለሚቃወማቸው እነሱም ይሄንን ስለተረዱት የተለያዩ አጋጣሚዎች በመጠቀም ስሙን ሲያነሱት እናያቸዋለን፤ እዚህ ላይ እውነቱን(ውሸቱን) ልብ በሉልኝ። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱም መናፍቃን የተዋህዶ እምነትን የማጥፋት ዘመቻቸው ማህበሩ እስካለ ድረስ ማስፈጸም አንችልም ብለው ስለወሰኑ በማንኛውም መንገድ እንዲሁም ከአክራሪው እስላሙ ጋር ተባብረውም ቢሆን ሊያጠፉት ይፈልጋሉ።
፪. የቢተክህነቱ ወሮበሮች(ማፍያ/ጨለማን የወ ደዱ) አካላት
እነዚህኞቹ ደግሞ በጊዜአዊ ጥቅምና ሥልጣን የሰከሩ ናችው። አቶ ንጉሴም ከነዚህኞቹ ቡድን ጋር መድቤዋለሁ። ማኅበሩን የሚጠሉበት ዓላማቸው ማኅበሩ በያዘው የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ይከበር የሚለው ጥብቅ አቋሙ ነው። ይኸው እነዚህ ሆዳቸው አምላክ የሆነባቸው ወገኖች ማኅበሩን ቢችሉ ለማፍረስ ነበረ፤ ነገር ግን ስላልቻሉ የማኅበሩን ስም የማጥፋት ዘመቻ ተቀጣሪው ጀሌያቸው አቶ ንጉሴ ጀምሮታል።
፪. የማኅበሩን አገልግሎትና ዓላማ ያልተረዱ ወገኖች
እነዚህ ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳንን በሥም ብቻ ያውቁታል። የማኅበሩ ሥም እንኳ የሰሙት ከተሃድሶ መናፍቅ፤ ከአቶ ንጉሴ ወይ ደግሞ ከአክራሪው እስላም ነው። እናም አንድ ጊዜ የሰሙት ወሬ ብቻ ይዘው ማኅበሩን ይጠሉታል። እንደው ማኅበረ ቅዱዳን ማን ነው፤ ዓላማው ምንድ ነው፤በቤተክርስቲያኒቱስ የትኛው መዋቅር ሥር ነው ያለው፤ ብሎ ለመጠየቅ ጆሮዋቸው የዘጉ ባይጠፉም፤ ለመጠየቅ ተዘጋጅተው አጋጣሚው ያላገኙ ወገኖች እንዳሉም እገምታለሁ።
እግዚአብሔር ተዋህዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን።
አቤል ዘቀዳማዊ

+++++++
የሀገር ፍቅር ራዲዮ - አለመታደል!

ዘክርስቶስ

አገር ቤት ከርሜ መጣሁ። መቼም የኛ ነገር ”መለያየት ሞት ነው” ሳይሆን ”መለያየት ሕይወት ነው” የተባለ ይመስል ”መለያየት መለያየት አሁንም መለያየት” ሆኗል ሥራችን። ለምሳሌ ስሙን ”አንድነት” ብሎ የሰየመው ፓርቲ ወደ መለያየት እያመራ መሆኑ ለሰማ ሰው ባይገርም ደስ አይልም። እጅግ በጣም እጅግ አሳዛኙ ነገር ግን በቅዱስ ሲኖዶስ ዙሪያ የሆነው እና እየሆነ ያለው ነገር ነው። ደጉ ንጉሥ ክርስቶስ መፍትሔውን ይስጠን!
አገር ቤት ሆኖ ብሎጎችንና እና አጽራረ መንግሥት የሆኑ ገጸ ድሮችን ማየት አይቻልምና ለ፮ ሳምንታት እዛ ያሉትን ሚድያዎች ነበር የምከተታለው። በፕሮክሲ ስሞክርም ያው አንዴ መብራት አንዴ ስልክ እየጠፋ አገር ቤት እየሆነ በነበረው ነገር ዙሪያ በዝርወት ያሉት ድረ ገጾች እና ራዲዮኖች ምን እያሉ እንደሆነ በኢንተርኔት ዳሰሳ ለማወቅ አልቻልኩም ነበር። እናም ትላንት ወደ ሁለተኛው አገሬ መጥቼ ማንበብና ማዳመጥ ያዝኩ። ቀልቤን የሳበው በማኅበረ ቅዱሳን ዙሪያ የዘነበው የሀገር ፍቅር ራዲዮ የስድብ ሞገድ ነው።
የ፲፩ ዓመት የራዲዮው አድማጭ እንደመሆኔ መጠንና ማኅበረ ቅዱሳንን በቅርብ የማውቄን ያህል ራዲዮው ስለማኅበሩ ባቀረባቸው ዝግጅቶች ዙሪያ አንድ ሁለት ነገር ለማለት እነሆ ተነሳሁ።
በሚመስለኝ ነገር ወይም በምመኘውና በምገምተው ነገር ሳይሆን በማውቀው ነገር ላይ ነው የማተኩረው። አቶ ንጉሤና ዶ/ር በላይ በማኅበረ ቅዱሳን ዙሪያ እያቀረቡት ያለው ነገር ፍጹም ሐሰት ከመሆኑም በላይ ታላላቅ ጉዳዮችን እንደ ጥቃቅን፤ በጎ ነገሮችን እንደ በደል፤ ያልተደረጉ ነገሮችን እንደተደረጉ፤ የተደረጉ ነገሮችን እንዳልተደረጉ አድርጎ የሚያቀርብ እጅግ የወረደ ዝግጅት ነው ብለው ደረጃውን አይገልጸውም። ታላላቅ ነገሮችን ከራሱ ስሜት፡ ጥቅምና አቅም ብቻ የሚመለከት ሰው መቼም ያልታደለ ነው ብዬ አምናለሁ።
እስቲ ከሚሉት ነገር አንዳንዱን ላንሳ።
ስለ አመሠራረቱ
ማኅበሩ ባልነበረበት ዘመንና ቦታ ነበረ ማለት የማይገናኙ ነገሮችን በማገናኘት ኢህአፓን ሉሲ ነች ያቋቋመችው ወይም ኢህአፓ በነሉሲ ዘመን ነበር ከሚለው ተረት ጋር ሲነጻጸር ልዩነቱ የዘመን ርዝማኔ ብቻ ነው ።
ስለ አደረጃጀቱና ስለ አባላቱ
ከጥሩ ጭንቅላት የሚወጣን ጥሩ ንግግር የሚያደርገውን ልጅ ”ተንኮለኛ” እያለ በሚጠራ ማኅበረሰብ ያደግን ነና የኛ ነገር መውቀስ የምንፈልገው አካል ካለ የሚያስወቅስ ነገር ይኑረውም አይኖረውም ሳይገደን በጎ ነገሩን ሁሉ እየጠቀስን እንደ መጥፎ ነገር ነው የምናወራው። ሀገር ፍቅሮችም የማኅበረ ቅዱሳንን ጠንካራ አደረጃጀትና የአባላት የማንነት ስብጥርን በተመለከተ ሲናገሩት ጥሩ ሆኖ እያለ ሲያቀርቡት ግን መጥፎ ለማስመስል ታትረዋል - ባይሳካላቸውም።
የተጠያቂነት ነገር
ስለ ኦዲትና ስለ ሂሳብም ከተነሳ በራሱ አሠራርና በፈቃጅ አካሉ እውቅና ያለው አሠራር አለው - ማኅበሩ። ይልቁንም የአድባራትና ገዳማት ሂሳብና ኦዲት ዘመናዊ አሠራር እንዲከተል ለማድረግ የሚያግዝ አቅም አለው - ስንታደል የምንጠቀምበት።
የገቢ ምንጭን በተመለከተ
ለቤተ ክርስቲያኒቱ መሠራት ካለበት ነገር አንጻር ማኅበሩ እጅግ ብዙ ገንዘብና ሌላ ቁሳዊ ግብአት የሚያስፈልገው ሥራ መሥራት ይቀረዋል። ከተመሠረተበት ጊዜ አንጻር ግን እግዚአብሔር ይመስገንና እጅግ ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠርቷል። እየሠራም ነው። ወደፊትም እንደ እግዚአብሔር ቸርነትም ከአባቶችና እና ኃላፊነታቸን ከሚወጡ ምእመናንን ጋር ሆኖ ይሠራል። እንኳን ታላላቅ ሥራዎችን ለመሥራት ቀርቶ እነ አቶ ንጉሤም እንኳን ራዲዮናቸውን ለማስቀጠል ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል። እናም አነጋጋሪ ጉዳይ መሆን ያለበት የማኅበሩ ገቢ ማስገኛ ነገሮችን መክፈት ሳይሆን የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጉዳያችን ለሆንን ሰዎች ሁሉ የሚያስቆጭ ነገር የማኅበሩ የገቢ ምንጭ ከሥራው አንጻር በበቂ ሁኔታና በብዛት አለመስፋፋቱ ነው። ለዚህም የሁላችን አስተዋጽኦ ያስፈልጋል።
ማኅበረ ቅዱሳን የሰዎች ስብስብ ነውና አባላቱ ድካም ይኖርባቸዋል። በቅዱሳን ስም እና የቅዱሳንን በረከት ምርኩዝ የእግዚአብሔርን ቸርነት መከታ አድርጎ የተቋቋመውም ድካም ያለባቸው ሰዎች ስብስብ በመሆኑ ነው። አባላቱ ከማንኛውም ሰው ጋር የሚጋሩትን ድካም ጠቅሶ ጥላሸት መቀባት ግን አየር ላይ በሚታዩ የፖለን ዱቄቶች ምክንያት የፀሐይ ብርሃንን ውበት አጣጥሎ ብርሃን አይደለም ጨለማ ነው ማለት እንዳይሆን ሁለቴ እናስብ።
በነፃ አገር በነፃ አየር የሀገር ፍቅር ራዲዮን የምትሰሙም ሆናችሁ ምንጭ ያደረገውን የስድብ መፅሐፍ የምታነቡ ወደ በአካል ወደ ማኅበሩ በመጠጋት ስለማኅበሩ ተረዱ። በአካለ ሥጋ ለማትችሉ የሚከተሉት ገጸ ድሮች ይጠቅማሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
http://www.eotc-mkidusan.org/ http://www.mahiberekidusan.org/
http://www.tewahedomedia.org/
ስለሚታወቀው ነገርና መረጋገጥ ስለሚችል ነገር መናገር የማይችል ሰው ስለማይታወቀው ነገርና መረጋገጥ የማይችለውን ነገር በመጥቀስ ማስፈራራቱ የተለመደ ነው። አድማጮችና አንባቢዎች ግን ከዚህ ወጥመድ ውጡ። እንደሚታወቀው ስሜት፡ ወሬ እና ጤዛ በዛው መጠን እና ይዘት የሚቆየው ያው የጽድቅ ፀሐይ እስኪወጣ ብቻ ነው። ይህ የጽድቅ ፀሐይም ሁሌ እንደወጣ ነው።
እስከዛ ግን በዶክተር በላይ ማፈሬ ነው።

July 29, 2009

"ኘትርክናው ከሆነላችሁ መልካም" ግብጻውያን

ዳሳሽ (ዘፍኖተ አበው)
ግብጻውያን መንበረ ኘትርክናውን ሲሰጡን ከሆነላችሁ መልካም ብለው እንደነበር ይነገራል። ታዲያ ትንቢታቸው ሰርቶ ይሁን ወይም የእኛው ስንፍና መንበሩን ከተረከብን ⁄ራሳችንን ከቻልን⁄ አንስቶ ውጣ ውረድ አላጣንም። የመጀመሪያው ፖትርያርክ ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ በብዙ ሕመም ተንገላተው አረፉ። ሁለተኛው ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ በደርግ ባለሥልጣናት ተይዘው በእስር ቤት ተገደሉ።

ሦስተኛው ፖትርያርክ ብፁዕ አቡነ ተክለሃይማኖት ከደርግ ጋር በነበረው አለመግባባት ሰውነታቸውን በፆም በጸሎት ቀጥተው ሃያ አራት ኪሎ እስኪደርሱ ከስተው ተጐድተው አረፉ። አራተኛው ፖትርያርክ ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ የኢሠፖ አባል ሆነው በመገኘታቸው ከደርግ ውድቀት በኋላ ሕዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ የገዛ ባልንጀሮቻቸው ይበቃዎታል ብለዋቸው ከሥልጣን ወረዱ ⁄ጡረታ ወጡ⁄ ብዙም ሳይቆዩ በኬንያ ጠፍተው አሜሪካ ገቡና ኘትርክናው የኔ ነው ማን ነክቶኝ አሉ። ቤተክርስቲያኒቱን ለሁለት ከፍለው አዋረዱ። አምስተኛው ፖትርያርክ ⁄ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ⁄ ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ አንድ ጊዜ ከባህታውያን ሌላ ጊዜ ከሊቃውንት ሌላ ጊዜ ከሲኖዶስ አባላት እየተጣሉ ቤተክርስቲያኒቱን የሁከት አደባባይ አደረጓት። ይኸው አስራ ሰባት ዓመት ሙሉ በጉቦ፣ በዘረኝነት ሲያምሱን ከርመው በቃዎ ሲባሉም አብረን እንጠፋታለን እንጂ ማን ነክቶኝ አሉ።
ታዲያ ይህች ቤተክርስቲያን በራሷ ሲኖዶስ መመራቷ ተሳክቶላታል ትላላችሁ? ለነገሩ ጎጆ ከወጡ በኋላ የእናት ጓደ የለም። ግብጻውያንን በመከራ ተላቀን መልሰን ጓዳቸውን አንናፍቅም። ይኸ ካልሆነ ግን ምን ይሻለናል፤ ያዘኑብን ካለ ፈልገን ይቅርታ እንጠይቅ ይሆን? ወይም ግብጻውያኑ የፈጠሩብን የሕሊና ተጽዕኖ ካለ ያንን ለማስወገድ አንድ ጊዜ እንምከር? መልሱን ለእናንተው ትቼዋለሁ።

ለቅዱስነትዎ ይድረስ

ዳሳሽ (ዘፍኖተ አበው)
መቼም ከተሾሙ አንስቶ ደስ ያሰኙበት ዘመን እንዳልገጠምዎ ጠንቅቀው የሚያውቁት የሚረዱት ይመስለኛል። ዛሬ ደግሞ የማይወጡት ፈተና ገጥምዎታል። ⁄ፈተና ያልኩት በእርስዎና በዘመዶችዎ አባባል ለመግለጽ ያህል ነው⁄። ለመሆኑ ቅዱስነትዎ ይኸ ሁሉ ውጣ ውረድ የገጠምዎ ለምን ይመስልዎታል። የቅርብዎ ሰዎች እንደሚናገሩት ዋነኛ ምክንያቶች እነዚህ ይመስሉኛል፤

1. እልክ
እልክ ፀጋዎ ነው። የተቀየሙትን በንስሐ ካልተመለሰ አውለው አያሳድሩትም። ሰው ምን ይለኛል ዘዴ ብጠቀም ይሻላልም የለም። በቃ ከተጣሉ ተነስ ታጠቅ ነው። አንዳንዴ እንደውም የእልክዎ ብዛት ከጤናዎ መታወክ ጋርም ተጨምሮ የቤትዎን መስታወት ሊያሰብርዎ እንደሚደርስ ይነገራል። ይኸ ለጊዜው ጠቃሚ ቢመስልዎትም የኋላ ኋላ ግን የጠላትዎን ቁጥር ጨምርዎቦታል። አጠገብዎ ያለውም ፈርትዎ እንጂ ወድዎት ስላልሆነ ቀን እንዲጠብቅልዎ አድርጐታል።
2. ዘመድ
በቤተክህነቱ ጊቢ የሚንጎራደዱ ማን ያለኛ የሚሉ ዘመዶችዎ ለመጠላትዎ ዋነኛ ምክንያት ናቸው። ‘‘የቤተ ዘመዱ‘‘ እየተባለ በዙሪያዎ እስክስታው ሲወርድ አብሮ ያለ መስሎ አገብዎ ያለው እንኳን እያዘኑብዎ መሆኑን አይርሱ። ከቆብ በኋላ ዘመድ ከሞት በኋላ ሥጋ ቆጠራው ብዙዎችን አሳዝኗል። በተለይ በተለይ አንዳንዶቹ ዘመዶችዎ ደግሞ ጳጳሳቱን አንተ እያሉ ሲጣሩ መነኮሳቱን ሲያንጓጡ መታየታቸው ቤተ ክህነቱን መጫወቻ አደረጉት አስብሏል። ሊቃውንቱ ተጨንቀው በብዙ ምክር የወሰኑትን ውሳኔ ከእርስዎ ዘመዶች አንዱ አትክልተኛም ቢሆን በማግስቱ ያስለውጠዋል። ይሄ አካሄድ አባቶችን ተስፋ አስቆርጧል። የዝንጀሮ መንጋ ባማረ ማሳ ላይ የተሰማራ ያህል ዘመዶችዎ ቤተክህነቱን ስፍራው መከራ አብዝተውበታል። እነዚህ ዘመዶችዎ ትናንት ያስናቅዎ ያዋረድዎ ሳያንስ አሁን ደግሞ መኝታ ክፍልዎን ወረው ግድ የለም እገሌን ስለኛ ይተውት እያልዎ ነው። ከቤተክርስቲያን ይልቅ ዘመዶችዎን ከሰሙ ቀባሪ ያጣሉ የመጨረሻውን ውድቀትም ይወድቃሉ።
++++++++++++++++
ፀአዳ የለበሰ ስታዩ ፈዛችሁ፣
የፀደቀ ብፁዕ አባት ነው ብላችሁ፣
እንደዋኋ እርግብ አፍ ከከፈታችሁ፣
ሥጋ ደሙ ሳይሆን ጥይት ነው ካፋችሁ፡፡

አባን ማመን ቀረ ሞኝ አትሁን ተሜ፣
ብዙ ታዝቤአለሁ ከስጢፋኖስ ቆሜ
ጥይት ነው መፍቻቸው አይደለም መስቀሉ፣
የቀዳማይ ጳውሎስ እምነትና ውሉ፡፡

ካቡን አትመኑ ካባ ነው ብላችሁ፣
መሠረት የለውም እንዳይፈርስባችሁ
የዘንድሮ ካባ በር ሠባሪ ሆኗል፣
ከካባነት ዘሎ በር ይፈነክታል፡፡

እጅግ አየሁ ባይኔ ዘንድሮ አባ ግቢ፣
ጳጳስ እሚያበሉ የሚያለብሱ ጋቢ፣
አቃቢት ከሆኑ ስልጣን ሹመታቸው
ቀዳማይ እመቤት ይጨመርላቸው
ከጨጌ ቤት ሆኗል ማደርያ ቤታቸው፡፡

እንግዳ/ ክኖርዌ፡ሀምሌ 13.ቀን 2001


‘‘ለሀገር ፍቅር ሬዲዮ" አዘጋጅ ለአቶ ንጉሤ የተሰጠ መጠነኛ አስተያየት

ዳሳሽ ⁄ዘፍኖተ አበው⁄
አቶ ንጉሤ
መቼም አንተ አምላክህ የላይኛው ሳይሆን ዓለምን ይገዛል ተብሎ የተነገረው የሰው ልጆች ጠላት ገንዘብ ነው። ለገንዘብና ለእግዚአብሔር በአንድ ላይ መገዛት ስለማይቻል አንዱን መምረጥ ግድ ነው።
አንተ ደግሞ ምርጫህን አስተካክለሃል ፈጣሪህን ክደህ ገንዘብን አምላኬ ፈጣሪዬ ጌታዬ ብለሃል። ያዝልቅልህ ካዘለቀህ። ለመሆኑ ንጉሤ ቤተክርስቲያኒቱን ለማወክ ከማፍያዎቹ ጋር የተስማማኸው በስንት ዶላር ነው? ማለት የተሻለ የሚከፍልህ ካገኘህ ፊትህን ስለምታዞር ለማንኛውም እወቀው ብለን ነው? የፖትሪያርኩ ወገኖች ይህን ያህል ከፍለውኛል የተሻለ ከተገኘ በጨረታው አልገደድም የሚል ማስታወቂያ ብትሰራ ያተርፍሃል ብለን እናስሳለን።

አቶ ንጉሜ ኘሮግራምህ ፖትሪያርኩን የሚጎንጥ አንደሆነ እመለከታለሁ። ለመሆኑ ይህን የምታደርገው ሆን ብለህ ነው ወይስ ሳታውቀው። አንድ ነገር ላስታውስህ በ7⁄19⁄09 የተሰራውን የዕለተ ሰንበት ዝግጅትህን አድምጬዋለሁ። በአንተም በዚያ ጨዋ እንግዳህ ⁄ጨዋ ስንለው ደስ ሊለው ይችላል። ጨዋ ማለት ያልተማረ ደንቆሮ… ነው⁄ ዝግጅት እጅግ ተደንቀናል። ለማንኛውም ከአንተ ልጀምር።
ሲኖዶሳችንን በሁለት ለመክፈል ሞክረሃል1. የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እውቀታቸው የተመሰከረላቸው የጎጃም የጎንደር የቅኔ የዜማና የመጻሕፍተ ብሉያት ወሐዲሳት ትርጓሜ ምስጢር የገባቸው እነዋሸራ… መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲዎች ብቃታቸውን የመሰከሩላቸው የዕለት ዕራታቸውን ከውሻ ጋር ታግለው ያገኙ የነበሩ፣በብትውናቸው የሚታወቁ፣ ንጽሕናቸው የተመሰከረላቸው
2. በዘመድ በጓደኛ፣ በብርና በወርቅ ምልጃ በብልጣብልጥነት ሰርገው የገቡ ከገዳም ኑሮ የፈረንጅ አገሩ በልጦባቸው ሕዝባቸውንም እርግፍ አድርገው ትተው። የየቀኑን የዌስተርን ቴሌቪዥን ሳፖኘራ ሲመለከቱ ቆይተው ዶላር ጭነው አጋጣሚ ሲያገኙ ወደ ናቋት አገር ገብተው የተሾሙ ብለሃል።
ከዚያም ከውጭ የገቡትን ኮንነህ ሲኖዶሱ መንፈሳዊ እንዳይሆን አደረጉት ብለሃል። ለነገሩ ይሄ ሁሉ ሐተታ አንድ ሰው ለመሳደብ መሆኑን ኋላ ላይ ከምትናገረው መረዳት ይቻላል። ነገር ግን ሳታውቀው ሐተታህ ከአቡነ ጳውሎስ ጋር ያፋጥጥሃል። ለመሆኑ ከአንደኛውና ከሁለተኛው ቅዱስ ፖትሪያሪኩ የትኛውን ቦታ ሰጠሃቸው። ባህታዊ ሊቅ ⁄የዋሸራ የትርጓሜ የቅኔ ሊቅ⁄ ንጽሕናቸው የተመሰከረላቸው …አልካቸው? ወይስ ፈረንጅ አገር ከርመው ሶፓኘራ ሲመለከቱ ቆይተው ዶላር ጭነው ድንገት ዘው ካሉት መደብካቸው… መልሱን ለአንተና ለአንባቢዎቻችን ትቸዋለሁ። ለማንኛውም ፖትሪያርኩ ይሄ የችግር ቀን ሲያልፍ ጎንጠኸኛል ብለው ስለሚነሱብህ ከአሁኑ ቁርጥህን እወቀው። አንተ እንደው አታፍር የተነሱብህ ቀን ደግሞ ‘‘አባ ዲያብሎስ‘‘ ስትል እንሰማህ ይሆናል።
በሌላ በኩል ጳጳሳቱን ለመሳደብ ብለህ ዶላር ጭነው ሄደው ተሾሙ ብለሃል። ይኸም ፖትሪያርኩ ዶላር ጭኖ የሄደን ይቀበላሉ በጉቦ ይሾማሉ ያሰኝብሃል። ለምን አንድ ጊዜ ብቻ አስበህ ትጽፋለህ ..ሁለት ጊዜ አስበህ ብትዘጋጅ ይሻልሃል። ድንቄም ጋዜጠኛ አንተ ጋዜጠኛ ሳይሆን የመንደር መርፌ ወጊ ብትሆን ይሻልህ ነበር። እንጥል ቆራጩ ሁሉ በሰለጠነበት ዘመን ያገኘኸውን ትናገራለህ። የሚሰማህ ታዝቦህ ታዝቦህ እንደኩፍኝ ወጥቶለታል። ያንተን ነገር ⁄መጨረሻ⁄ ፈጣሪ ያሳየን ብሎ ትቶታል።
ሌላው ንጉሴ ዶ⁄ር ተብዬ ባልደረባህ ስለማኅበረ ቅዳሳን ያቀረበውን ሐተታ ⁄ጥናት⁄ ሰምቼ ሆዴ እስኪቆስል ስቄያለሁ። ለመሆኑ ዶክተሩ Drive through ነው ወይስ…። መጀመሪያ የቤተክርስቲያን ቃላት እንዲያጠና መዝገበ ቃላት ብትሰጠው። አቡነ ቀውስጦስ እላለሁ ብሎ አቡነ ቀውጢዎስ ሲል ስሰማው አሳፋሪ ነው። ጥናቱን አጥንቼ ቀርቤያለሁ ብሎ ቀርቦ አስር ጊዜ ሲታረም ለሰማ የማንነው ደፋር ያሰኛል። በዚያ ላይ ስለማኅበረ ቅዳሳን ያቀረበው ጥናት ላይ አንዳንድ ነገሮች ልጠቁምልህ፤
• በመጀመሪያ ደረጃ ጥናቱን ለማጥናት መረጃ አድርገህ ያቀረብከው Google የሚለውን ሳይት ነው። Google በየት ሀገር ነው ለጥናት መረጃ የሚሆነው። ያገኘ ሁሉ በሚጽፍበት ማንም ተነስቶ የወረወረውን ሁሉ አነሱም እንዲህ ብሏል ተብሎ የሚቀርብበት የአስተያየት ጥርቅም ውስጥ ገብተህ መዋኘትህ ያሳዝናል። Google Christ ክርስቶስ ብትለው። ክርስቲያኖች ያሉትንም Anti C hristየሰነዘሩትንም ሁሉ ደባልቆ ያቀርብልሃል። መለየት የአንባቢው ፈንታ ነው። አልያ ጥሩ መረጃ ታማኝ ምንጭ መፈለግ ይገባል። ክርስቶስ ሲባል የሁሉንም ሐሳብ ይዞ ቀርቦ እንደሚናገር አላዋቂ አጥኚ ሆነሃል። Google Ethiopia ብትለው የኢትዮጵያን በጎ ጎን የተጻፈለትንም እነ Oxford famine ረሃብ ብለው ሲተረጉሙ ምሳሌ ያደረጉበትንም ያቀርብልሃል። እንዳንተ ያላ አላዋቂ አጥኚ ያገኘው ዕለት ኢትዮጵያ ማለት ረሃብ እንደሆነ ከGoogle አግኝቻለሁ ሊለን ነው ማለት ነው።

ስለ ማኅበረ ቅዳሳን Google ከምትል የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ራሷን ተቋሟን ጠይቃት። አንተ እንዳልከው ቤተ ክርስቲያኒቱ የማታውቀው ማኅበር አይደለም። የሲኖዶስ አባላት የፈረሙበት ደንብ ያለው ሕጋዊ እውቅና ያለው ማኅበር ነው። ይህንን ቤተ ክርስቲያኒቱ ራሷ ትነግርሃለች።
• በሌላ በኩል ማኅበረ ቅዱሳን ራሱን ካደራጀ በኋላ ‘‘ከቤተ ክርስቲያናችን ሱበካ ጉባኤ ጋር ራሱን እንደለጠፈ ይናገራል።‘‘ ብለሃል። ማኅበረ ቅዳሳን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ደረጃ በሰንበት ት⁄ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር የሚንቀሳቀስ ማኅበር ነው እንጂ በሰበካ ጉባኤ መምሪያ ሥር አይደለም። አባባልህ በራሱ በጣም ግልጽ ያልሆነና የተምታታ መሆኑን የቤተ ክርስቲያን ልጆች የሆኑ ሁሉ ይረዱታል።
• ከቤተ ክርስቲያናችን ሰበካ ጉባኤ ጋር ራሱን እንደለጠፈ ስትል ከየትኛው ሰበካ ጉባኤ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ወይስ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ደረጃ ካለው የሰበካ ጉባኤ መምሪያ? ይኸን እንኳን መለየት የማትችል ደካማ ቢጤ ነህ። አባላት በአባልነት የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤ አባላት ናቸው። ይኸንን ማንም አይከለክላቸውም። ማኅበሩ በማኅበርነት ግን የሰንበት ት⁄ቤቶች ማ⁄መምሪያ አካል ነው። እስኪ ይሄንን እንኳን ለማጥናት ሞክር አጥንቻለሁ ከማለትህ በፊት።
• አቡነ ቴዎፍሎስን ለማስገደል የሞከሩ ናቸው የሚል ቅብጥርጥር ካወራህ በኋላ በተለይም የስብከት ጉባኤው ለመበረዝ የተነሱ ናቸው ብለሃል። የትኛውን የስብከት ጉባኤ? የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴውን ማለትህ ነው? የሰበካ ጉባኤያትን ማለትህ ነው? አማርኛህ ዲቃላ መነሻና መድረሻ የሌለው አፍንጫና ዓይን የሌለው ስለሆነ ግራ ተጋብተህ ግራ ታጋባለህ። ይቅር ይበልህ ፈጣሪ። ማኅበረ ቅዱሳን ስብከተ ወንጌል አስፋፋ እንጂ አልበረዘም ይኸንን የቀመሱት ይመሰክሩል። በየኮሌጅና ዩኒቨርሲቲው ያሉ የማኅበሩ ፍሬዎች በመላው ዓለም ያሉ አባላቱ በአገልግሎቱ የተጠቀሙ ምእመናን ሁሉ ይንገሩህ። ሲገባህ አይደል ለነገሩ።
ለማንኛውም ጥናትህ በሙሉ ውሸት ነው
1. ቤተ ክርስቲያን አታውቃቸውም ሕጋዊ አይደሉም ብለሃል ፤ ውሸት
2. ከሰበካ ጉባኤ እንደተለጠፉ ይናገራሉ ብለሃል፤ በሰ⁄ት⁄ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ነው ማኅበሩ ስለዚህ ውሸት
3. ስብከት ጉባኤውን ለመበረዝ ያልከውም አማርኛውን ላቃናልህና ስብከቱ ወንጌሉን ለመበረዝ ቢባል እንኳን ውሸት
4. አቡነ “ቀውጢዎስን” ⁄ይታረምና አቡነ ቀውስጦስን⁄ ተሳደቡ ብለሃል። ሊቀጳጳሱ ያወጡትን መጽሐፍ ያከፋፍል የነበረ ማኅበረ ቅዱሳን ነው። በዋሽንግተን ዲሲ የተዘጋጀውን ኤግዚቤሽን ⁄የማኅበረ ቅዱሳን⁄ ባርከው የከፈቱለት እርሳቸው ናቸው። ማኅበረ ቅዱሳንና አቡነ ቀውስጦስ ተጣልተውም አያውቁም መቼም አይጣሉም፤ ያጣላሃቸው አንተ ነህ፤ ይህም ፈጠራህ ውሸት ነው።
ለማንኛውም ዶ⁄ር በላይ ፊደል ተማር፣ ታሪክ አጥና። በቤተ ክርስቲያን አጠገብ እንዳላለፍክ ያስታውቃል ከቤተ ክርስቲያን ትንሽ ለማወቅ ሞክር ክርስቲያን ትሆን…ባላየ አንደበትህ ትችት አይቅናህ እላለሁ። እናንተም ቀጥሉበት።
እኔም እቀጥላለሁ ያገናኘን

በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ በአስተዳደር ቦርዱና በአባቶች ካህናት የወጣ የአቋም መግለጫ


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ሐምሌ ፲፱/፳፻፩ ዓ.ም. (July 26, 2009)
በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ በአስተዳደር ቦርዱና በአባቶች ካህናት የወጣ የአቋም መግለጫ፦
(Read in pdf here)

በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁሐዋ.፳፥፳፷
ይድረስ፦ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ በሙሉ።
ጉዳዩ፦ የቅዱስ ሲኖዶስ ሉዐላዊነት መከበር ስለሚገባው እና ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት በተመለከተ።
መግቢያ፦

ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመባል የምትታወቀው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ ከተመሠረተችበት ጊዜ አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ እጅግ ሊስተዋል የሚገባው ሥራ አከናውናለች፤ ወደፊትም ለማከናወን ተዘጋጅታለች። ቃላት ሊገልጸው፣ አንደበት ሊተርከው፣ ሕሊና ሊያሰላስለው፣ አእምሮ ሊያወጣውና ሊያወርደው ከሚችለው በላይ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽማ የተሰጠች እምነትን፣ በአምላካችን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተዋጀችውን፣ በነቢያትና በሐዋርያት መሠረትነት የታነጸችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖትና ሥርዓት፣ ትውፊትና ቀኖናን በመቀበል፤ ለሃይማኖቷ ተቆርቋሪ፣ ለሥርዓቷ ተገዥ የሆኑ ካህናትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን፣ ዲያቆናትና መዘምራንን እንዲሁም ጠቅላላው ምእመንን በውስጧ በመያዝ ለተሠሩትም ሆነ ወደፊትም ለሚሠሩት አበይት ክንውኖች መሠረት መጣልዋ ከምንም በላይ ሊጠቀስና ሊዘከር የሚገባው አብይ ጉዳይ ነው።

በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የተመሠረተቸውን እና ዋጋ የተከፈለባትን እምነት ከመናፍቃን እና ከከሀዲያን ጠብቀውና ተከላክለው በማቆየት ለእኛ ያስረከቡንን የሃይማኖት አባቶቻችንንና እናቶቻችንን አደራ ለመጠበቅና ለማስጠበቅ መዘጋጀት፤ የተቀበልነውንም ታላቅ አደራ ለተተኪው ትውልድ ለማስረከብ በሚኖረው ሒደት ብዙ ውጣ ውረድ፣ ብዙ ፈተና እና ድካም መኖሩ ሳይነገር የታወቀ ሳይታለም የተፈታ ነው። ሆኖም ግን የሃይማኖት መገለጫና ዋነኛው መንገድ በጠባቡ በር ማለፍ ስለሆነ ፈተናውን ተቀብሎ፣ መከራውን ችሎና ታግሦ የሰይጣንን ደባ እያፈራረሱ በድል መጓዝ አባቶቻችን ያለፉበት በመሆኑ እኛም በዚያው መንገድ ልናልፍ ግድ ነው። በመሆኑም ከቤተ ክርስቲያናችን ምሥረታ ጀምሮ በየትኛውም መልኩ የልዩነት ኅብረት ሳናደርግ የብፁዓን አባቶቻችንን ቡራኬ በመቀበል ዛሬ የደረስንበትን ሥፍራ ለማየት ችለናል።

መልእክት፦

እንደሚታወቀው የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥር ፲፫ እና ጥር ፳ ፲፱፻፺፱ ዓ.ም በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና በካናዳ ቶሮንቶ የጳጳሳት ሹመት ሲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ በአገራችን በኢትዮጵያ የለም ፤ መንበሩም የመንበሩም ጠባቂዎች በምድረ አሜሪካ ይገኛሉ፤ በማለት ሃይማኖታችንና ሥርዓታችን ከሚፈቅደው ውጪ ሕጋዊ ሲኖዶስ በስደት ያለው ነው በማለት በቅድስት አገር ኢትዮጵያ ሲኖዶስ እየተባለ የሚጠራ አካል እንደሌለ አድርገው በተነሡት ሰዎች ላይ ይህ ሁኔታ በተፈጸመ ማግስት ያለማንም አነሳሽነት ትክክለኛው መንገድ የትኛው እንደሆነ በመረዳት ጥር ፳፭/፲፱፻፺፱ ዓ.ም. ባወጣው አቋም ላይ ሲኖዶስ አንድ እንደሆነ፤ መንበሩም በቅድስት አገር ኢትዮጵያ እንደሆነ ለሕዝባችን አበክረን መግለጻችን የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። በመልእክታችንም ሰዎች ይሰደዳሉ እንጂ አገር አይሰደድም፤ አገር እንደማይሰደድ ሁሉ መንበርና ሲኖዶስም አይሰደዱም፤ ስለዚህም እንዲህ ያለውን አካሄድ እንደ እምነታችን በፍጹም የማንቀበለው ነውበማለት መጥቀሳችን የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ከማስጠበቅ አንፃር የበኩላችንን አደራ መወጣታችን እንደነበር ግልጽ ነው።
ቤተ ክርስቲያናችንም በቅድስት አገር ኢትዮጵያ የአስተዳደር ብልሹነት እንዳለ በመግለጽ በዚያው ቀንና ዓመተ ምሕረት ለቅዱስ ሲኖዶሱ መልእክቷን አስተላልፋለች። በመልእክቷም ቤተ ክርስቲያኒቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ በተቀመጠበት ወንበር ማድረግ የሚገባውን ሳያደርግ ቀርቶ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተለያዩ ፈተናዎች ሲቃጡ ዝም ብሎ ሁኔታዎችን በቸልተኝነት መመልከት አግባብ አይደለም። ታፍራና ተከብራ የኖረችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አቅጣጫ አለመቃኘት ቸልተኛነት ነውና ሊታሰብበት ይገባል። በመሆኑም ፍትህ ያልሰፈነበት፣ የአስተዳደር ድክመት የሚታይበት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ የበላይነት ያልተረጋገጠበት እና የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ቸል የተባለበት ሁኔታ በቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ እየተንሰራፋ እና እየተንጸባረቀ የመጣ በመሆኑ እርምት ሊወሰድበት ይገባዋል በማለት መልእክታችንን ማስተላለፋችን የሚታወስ ነው። በመጨረሻም የአስተዳደር ችግር ተወግዶ አስተማማኝ ሁኔታ ሲፈጠር በብቸኛና በአንድ ሲኖዶስ ሥር ታቅፈን እምነታችንን እንደምናራምድ ቃል ስንገባ ለቤተ ክርስቲያናችን መፍትሔ ከሚፈልጉ ጋር አብረን ተሰላፊ በመሆን ይህን መላ-ቅጡ የጠፋ አካሄድ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ እንሰለፋለን፤ የጅምራችን ስኬታማነት እና የሕልማችን ገሃድነት ቅርብም ባይሆን ሩቅ አይደለም በማለት ነበር።

ልዑል እግዚአብሔር ሁሉን በጊዜው ውብ አድርጎ ይሠራልና ትናንትና የቤተ ክርስቲያን ሉዐላዊነት ተደፍሯል፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ተንቋል፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ፈርሷል፣ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ጠፍቷል፣ የሲኖዶስ የበላይነት ተዘንግቷል፤ በማለት እናሰማው የነበረውን ድምጽና እየጮህን ያለውን ጩኸት ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል ያሉ ብዙኻን ብፁዓን ጳጳሳት፤ በየአብያተ ክርስቲያኑ ያሉ ካህናትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ ዲያቆናትና ዘማርያን፣ እንዲሁም መላው ምእመናን የሚያስተጋቡት ሆኗል። ይህም ሁኔታ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ያሉትን የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች መነጋገሪያ አጀንዳቸውን አንድ ብቻ አድርጎታል፤ ይኸውም የአስተዳደር በደል የሌለበት የሲኖዶስ የበላይነት ይከበር የሚል ነው።

ባለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ እጅግ ታሪካዊ የሆነው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሞትም ሽረትም፣ ትግልም ሽንፈትም፣ ውደቀትም መነሣትም ከአገር ሸሽቶ ሳይሆን እዚሁ ባለንበት ሥፍራ ነው በማለት ቆርጠው በመነሣት የአስተዳደር በደል አለ፤ ያለ አግባብ የሚባክን የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ አለ፤ ሁኔታዎች በቅዱስ ሲኖዶስ ሳይሆን የሚመሩት በፓትርያርኩ ብቻ ነው፤ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ቀና የሆነ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ሐሳብ ሲያቀርቡ ከቦታቸው እንዲነሡ ይደረጋሉ፤ ለእውነት የቆሙ ሰዎች ብዙ መከራ እየደረሰባቸው ይታያል፤ በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል። የዚህ የእውነት ድምጽ ግን የተነሡበትን ዓላማ እና እየተጓዙበት ያለውን መንገድ አልጋ በአልጋ አላደረገውም፤ ይልቁንም ይህንን በማለታቸው ማስፈራራትና ዛቻ እንዲሁም ድብደባ ደርሶባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የስም ማጥፋት ዘመቻ እየተደረገባቸው መሆኑ ለሁላችን ገሐድ ሆኖ ተደምጧል። ቅዱስ ሲኖዶሱ የአንድ ነገድ መሰባሰቢያ፣ የዝምድና ሥራ የሚሠራበት ሥፍራ፣ ገንዘብ ያለአግባብ የሚባክንበት ቦታ፣ ለእድገት የሚቀርቡ ሐሳቦች ተዳፍነው የሚቀሩበት መስክ እየሆነ መጥቷልና ፍጹም ክርስቶሳዊ የሆነ ሥራ ይሠራበት የሚሉ ብፁዓን አባቶች ተነሥተዋል። ይህም በቆራጥነት የተነሡበት ዓላማቸው መክኖ እንዳይቀር፤ በውስጣቸው የተዳፈነው የእውነት መንፈስ በተለያዩ ፍርሀቶች እንዳይገታ፤ ለአባቶቻችን ልንጸልይ እና በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ልንረዳቸው የሚያስፈልግበት ጊዜ አሁን መሆኑን ከመቼውም የበለጠ ልናስብበት ይገባል። እንደሚታወቀው ኢትዮጵያን ያህል አገር አና ኦርቶዶክስን ያህል ፍጹም እምነት የያዘች ቤተ ክርስቲያናችን ለአያሌ ዘመናት ለግብፅ እንደ አገረ ስብከት እየተሰጠች ቡራኬ ስትቀበል ኖራለች። የሃይማኖት መሪዎቿ ብቻ ሳይሆኑ የአገር መሪዎቿ ጭምር ኢትዮጵያ እራሷን ችላ የእራሷን ፓትርያርክ ልትሾም የሚያበቃትን ሲኖዶስ እንደ እምነት ቀዳማዊነቷ እንድታገኝ ሲሞክሩላትና ሲታገሉላት ኖረዋል። ይህ ጥያቄም መልስ ያገኘው የዛሬ ሃምሳ ዓመት በ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. ነው። ኢትዮጵያ ለዘመናት ትመኘው የነበረውን የሲኖዶስ መንበር የያዘችውና ያገኘቸው በጾም በጸሎት እና ቆራጥ በሆኑ የሃይማኖት አባቶቿ እና እናቶቿ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም። በእግራቸው ሲጓዙ በግብጽ በረሐ ወድቀው የቀሩት አባቶቻችን የደከሙበት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ የበላይነቱን ጠብቆ እንዲኖር እንጂ ቅዱስ ሲኖዶሱን የበታች አድርጎ በመቁጠር የሰዎችን ሉዐላዊነት ለማንጸባረቅ አለመሆኑ ግልጽ ነው።

ሲኖዶሱ ዘላለማዊ በመሆኑ እስከ መጨረሻው ይኖራል፤ ተሿሚዎቹ ግን አላፊዎች በመሆናቸው ከመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ጀምሮ እስከ ዛሬ አምስት ፓትርያርኮች ተሾመዋል። ቋሚና ዘላለማዊ የሆነውን መንበር የበላይነቱን ማስከበርና ማስጠበቅ የሁላችን ኃላፊነት በመሆኑ ዛሬም እንደ ትናንት የልዩነት ኅብረት ሳናደርግ ለአንድ ሲኖዶስ ህልው መሆን እስከ መጨረሻው እንታገላለን። ተቃውሟችን ከሰዎች ጋር ሳይሆን ሲኖዶሱን የበታች አድርጎ ከሚመለከተው አስተሳሰባቸው ጋር ነው። ምን ጊዜም ቢሆን የሲኖዶሱ የበላይነት በጥያቄ ውስጥ መግባት አይኖርበትም። አባቶቻችንና እናቶቻችን የደከሙበትና የሕይወት መሥዋዕት የከፈሉበት ቅዱስ ሲኖዶስ የበላይነቱ ተጠብቆ እንዲኖር እንጂ የአገር መሪ ሲቀየር አብሮ የሚቀየር ፓትርያርክ እንዲፈራበት አልነበረም። እዚህ ላይ በደንብ ትኩረት ሊሰጥበት የሚገባው አብይ ጉዳይ ቢኖር ሲኖዶስ ያለፓትርያርክ መኖር ይችላል፤ ፓትርያርክ ግን ያለሲኖዶስ መኖር አይችልም። ይህ ዓረፍተ ነገር ለሁላችን ግልጽ ከሆነ የቅዱስ ሲኖዶስ የበላይነትም አሻሚ የሌለው፤ በምንም ሁኔታ ለድርድር የሚቀርብም አይደለም።

ይህ እውነታ የገባቸው በዘመናት መካከል የተገኙ ቆራጥ አባቶች መከራ ቢመጣ እንወጣዋለን፤ ሞት ቢመጣ እንጋፈጠዋለን፤ የሲኖዶስ የበላይነት ይከበር፤ ሙስና ለአንዴም ለዘላለምም ይጥፋ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትደግና ትስፋፋ፤ በማለት ተነሥተዋልና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንን እግዚአብሔር እንዲታደግልን በጸሎት፤ ሕሊናም ተሰጥቷናልና በማስተዋል እንድንመላለስ በቆራጥነት እንነሣ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የፓትርያርክነትን ሥልጣን በተረከቡበት ጊዜ እንዲህ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፦ በዘመናት መካከል ወደ እምነታቸው ምንጭ ለመድረስ ወደ እስክንድርያ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በምድረበዳ ወድቀው የቀሩ ኢትዮጵያውያን አሁን በዓፀደ ነፍስ ሆነው የዚህ ክብር ተቀባዮችና ተካፋዮች ናቸው። ይህ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ንግግር እንኳንስ በሕይወት ያለነውንና በዓፀደ ነፍስ ያሉትን ኢትዮጵያውያንን የክብር ተካፋይ እንደሚያደርጋቸው ሲያስረዳ አሁን ይህን ክብር ያለአግባብ ለመጠቀም እና የበላይነቱን ከማጉላት ይልቅ ገዢውን ተገዢ፣ መሪውን ተመሪ፣ ቋሚውን ጊዜያዊ አድርጎ ማቅረብ ከሥርዓት ውጪ መሆን ነው። በመጨረሻም ለረጅም ዓመታት እየታየ ያለውን ይህን የመለያየት መንፈስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ልዑል እግዚአብሔር ከእኛ ሊያስወግደው መንገድ እያሳየን በመሆኑ ለእውነት በእውነት ቆመው የቅዱስ ሲኖዶስ የበላይነትን ለማስከበር ከሚታገሉት ጋር አብረን እንሰለፍ። ይህ የሲኖዶስ የበላይነት ሲረጋገጥ እኛም ያለፉት ጥቂት ዓመታት ጥያቄአችን ይመለሳልና ለዚህ ትግል በጸሎትም በገንዘብም በእውቀትም የሚገባንን ያህል ድርሻችንን እንወጣ።

ማጠቃለያ፦

በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ በአስተዳደር ቦርዱ እና በካህናተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በጠቅላላው ምእመን የወጣው ይህ የጋራ መግለጫ ከዚህ በታች በሰፈሩት ነጥቦች ላይ የተመሠረተ ነው።

፩- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ እድገት ለማይሹትና በእኛም መለያየት የሚፈጠረውን አጋጣሚ ጠብቀው ለሚነሡ መናፍቃን ምንም ዓይነት መግቢያ ቀዳዳ ላለማበጀት በጽናት እና በቆራጥነት መቆማችንን ለማሳየትና ብሎም ቤተ ክርስቲያን በኛ ዘመን ፈተና ላይ ስትወድቅ አላፊ ለሆነ ጊዜያዊ ሥልጣን ብቻ የሚረባረቡትን የሥልጣን ሰዎች ድርጊታቸው ተገቢ አለመሆኑን አበክሮ ለመግለጽ ነው።

፪- የቤተ ክርስቲያን አደራችንንና የእምነት ድርሻችንን በተገቢው መንገድ ከመወጣት አኳያ ለተተኪው ትውልድ የተስተካከለ እና ወጥ የሆነ የአሠራር መንገድ ትቶ ለማለፍ፤ ተተኪው ትውልድም የአባቶቹን አርአያ በመከተል የታሪኩን ምንነት እና የሲኖዶስን ሁኔታ ጠንቅቆ እንዲያውቅ ለማትጋት ነው። በተለይም እንዲህ ያለው ሁኔታ ሲፈጠር ዝምታን ገንዘብ ከማድረግ ይልቅ እውነታው የቱ እንደሆነ በገሐድ በመናገር የሕሊና እረፍት ለማግኘትም ጭምር ነው።

፫- ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ ሊያመጣ የሚቻልበትን መንገድ ማመቻቸት ከሁሉም የበለጠ በመሆኑ እንቆቅልሻችን እንዲፈታ የሲኖዶስ የበላይነት እንዲከበር ማስደረግን ቦታ በመስጠት ነው። ሁሉ ነገር እያለን የጎደለን ነገር ቢኖር ተከባብሮ መኖርና ፍቅር ማጣት በመሆኑ ሥርዓትን አስከብሮ እና ሃይማኖትን ጠብቆ ለመኖር ከወዲሁ ለመዘጋጀት በማሰብ ነው።

በመጨረሻም ይኼን የእውነትና የሰላም የደወል ጥሪ ያደመጣችሁ ካህናትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ዲያቆናትና መዘምራን፣ እንዲሁም ጠቅላላ ሕዝበ ክርስቲያን ጸሎትን እና ልመናን ወደሚሰማ ወደ ልዑል እግዚአብሔር ልመናችሁን አቅርቡ። የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ፣ የቅዱሳን ጸሎት እና የመላእክት ተራዳኢነት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፤ አብሳሪው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የሰላም የፍቅርና በአንድነት ለአንድነት መሥራትን ገንዘብ እንድናደርግ የተለመደ ብሥራቱን ያሰማን አሜን!!


ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር!!

ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ

ሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ
ደጀ-ሰላም መዝሙር ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ (U.S.A.) www.debreselam.net
Debre Selam Medhanealem Ethiopian Orthodox Tewahedo Church 4401 Minnehaha Avenue South Minneapolis, Minnesota 55406
Tel. (612) 721‐1222 (U.S.A) www.debreselam.net Page 1
ሐምሌ ፲፱/፳፻፩ ዓ.ም. (July 26, 2009)

July 28, 2009

ርዕሰ አንቀጽ፦ “ደጀ ሰላም” የማን ናት?

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 28/2009)

ሁልጊዜም ቢሆን ማንነትን መጠየቅ፣ ማወቅና መለየት ይገባልና አንዱ ሌላውን “አንተ ማነህ?” ይለዋል። “ደጀ ሰላምም” ተራው ደርሷት “ማነሽ? የማነሽ? ከማን ወገን ነሽ? ከእኛ ወይስ ...?” ተብላለች። ጥያቄው የመጣው በተለያዩ መንገዶች ቢሆንም ዋነኞቹ ግን የሚከተሉት ናቸው።
1. አስተያየት ሰጪዎች በመሰላቸው መንገድ፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች “የነእንትናና የነእንቶኔ” ብለዋታል፣
2. የዲሲው ባለ 10ሺህ ዶላሩ “የማፊያው ጋዜጠኛ” የማህበረ ቅዱሳን ናት ብሏታል፣
3. ማህበረ ቅዱሳን ራሱ ደግሞ “የእኔ አይደለችም፣ አላውቃትም” ብሏታል፣
4. የማፊያው ቡድን ምንጯን ለማወቅ ደፋ ቀና እንደሚል ተረድተናል፣
5. ቅዱስነታቸውና አቡነ ገብርኤል “ስማችንን አጥፍታለች” ብለው “የት ባገኘናት” ብለዋታል።
“ደጀ ሰላም” ስለ ራሷ እንዲህ ትላለች።

የተጀመረችው በ2006 ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 3 ዓመታት ደስ ባላት፣ አትኩሮቷን በሳቡ ጉዳዮች ዙሪያ ስትጦምር (ብሎግ ስታደርግ) ቆይታለች። ብሎግ ናትና ከየት ሀገር ነሽ፣ ማነው የጣፈሽ፣ ማን አገባሽ? ማን ፈታሽ? የሚላት የለም። ስለ ጡመራ (መ ይጠብቃል) ወይም ብሎጊንግ የማያውቁ ሰዎች ደግሞ መከራዋን ሲያበሏት ይህንን ለመጻፍ ተነሳች።

አንድ ታሪክ ስለ ታዋቂ ጦማሪ (ብሎገር) በማንሳት እንጀምር።
ሰውየው ኢራቃዊው ሳላም ፓክስ (Baghdad Blogger Salam Pax) ይባላል። እውነተኛ ስሙ አይደለም። መጦመሪያ ስም ነው። ምንም ውስጥ አወቅ ዜና በማይሰማበት የኢራቅ ጦርነት ወቅት ከባግዳድ ተቀምጦ ስለ ከተማዋ ሁናቴ ለወዳጁ ይጽፈው የነበረውን ሐተታ “ብሎግ”ከፍቶ ይልክለት ነበር። በሁዋላ ያንን ብሎግ ("Where is Raed?" የሚል ብሎግ) ዜና ማሰራጫዎች አገኙትና የሰውየው ማንነት ሳይታወቅ ነገር ግን በሚያቀርባቸው ሐተታዎችና ተአማኒ ዜናዎች ከበሬታን አገኘ።
It began as an internet joke with a friend. But then the media - including the Guardian - picked it up, and suddenly he was the Baghdad blogger, the most famous web diarist in the world. Salam Pax describes what it was like to play cat-and-mouse with Saddam's censors.

ጦርነቱ አልቆ፣ አማሪካኖች ባግዳድን ተቆጣጥረው ነገር ከበረደ በሁዋላ ያንን ጦማሪ ቢፈልጉ ማግኘት አልቻሉም። በሁዋላ ላይ በብዙ ማግባባት ማንነቱን ዘ ጋርዲያን ደረሰበት፣ እርሱም ራሱን ገለጠ። ዘግየት ብሎ ለእነርሱው ተቀጥሮ እስከ መስራት ደረሰ። ለህይወቱ የሚያሰጋው ነገር ሲመጣ አገር ጥሎ ለተወሰኑ ዓመታት አሜሪካ እስከመኖር ደረሰ። ታሪኩንና ይጦምረው የነበረው ነገር ሁዋላ ላይ መጽሐፍ አድርጎ The Baghdad Blog (ISBN 1-84354-262-5) አሳትሞታል።ወዘተ ወዘተ። ዝርዝሩን ራሳችሁ አንብቡት!!!

ይህንን ለማለት የተፈለገበት ምክንያቱ አንድን ጦማሪ “የት ነህ? ከማን ወገን ነህ?” ብሎ ማፋጠጥ ያሳፍራል፣ ነውርም ነው ለማለት ነው። ንጉሴ ሆነ አቡነ ገብርኤል፣ ፓትርያርክ ጳውሎስ ሆኑ ገለልተኛ-ስደተኛ፣ ማህበረ ቅዱሳን ሆነ ማህበረ ሰንበቴ “ድንበር አትለፉ” እንላቸዋለን።

መልሳችን “የምንጽፈውን እንጽፋለን”፤ “ለቤተ ክርስቲያናችን የሚበጀውን እገሌ ይቆጣናል፣ እገሌ ያፈርሰናል፣ እገሌ ያግደናል፣ እገሌ ይቀየመናል ሳንል እንጽፋለን”። ከልባችን መሆኑን ሁሉም እንዲረዳው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስም ሆኑ ከቧቸው ያለው የማፊያ ቡድንን ለምን እንደምንቃወማቸው እንዲያውቁ በሰፊው መዘገባችንን በእግዚአብሔር ቸርነት እንቀጥላለን። “አባቶቼን አዋረዱብኝ” የሚል ካለ ጠበቃነቱ ለቤተ ክርስቲያኑ ወይም ለማፊያው መሆኑን እየጠየቅን እንሞግተዋለን።
“እኛ የቤተ ክርስቲያን ነን”!!! የማንም አይደለንም!!!
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን

እስከ ጥቅምት ቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ምን እንሥራ?

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 28/2009)

ያለፈው የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ እንዳይሆን ሆኖ ከተበተነና ለጥቅምት ካደረ ወዲህ አጀንዳው መቀዝቀዝ የጀመረ ይመስላል። አንዳንዶች ተስፋ በመቁረጥ፣ አባቶች ላይም ጥርጣሬያቸውን በማስፋት እንዲያውም የሃይማኖቱን ነገር ችላ እስከማለት ደርሰዋል ይባላል። የማፊያው ቡድን ብቻ የያዘውን ይዞ “ጥቅምት እንዳትመጣ ባይጸልዪም” ያኔም ቢሆን ጥቅሙን ሳያስነካ፣ ወንበሩን ሳያስደፍር፣ ዝርፊያውን ለመቀጠል ቀንተሌት እየሠራ ነው። ሕብረትም አለው። ሕብረት የሌለውና አሰባሳቢ ያጣው ለቤተ ክርስቲያን የሚያስበው ወገን ነው። ከዚያውም ቢሆን አንዳንዱ “የአባቶችን ገመና አትግለጡ” እያለ ስለ ማፊያው ቡድን እንዳይወራ በጥቅሳጥቅስ ያስፈራራል። ሌላው ደግሞ እኔን ካልነኩኝ እግዜር በፈቀደው ቀን ይፍታው ብሎ መሽጓል። አንዳንዱ ደግሙ ሲያመቸው ከመዘመርና “ሆ” ከማለት ውጪ ነገሩንም ከመጀመሪያው አልሰማውም። እና ሁላችንም እንዲህ ቁጭ ብለን ጥቅምት ትድረስ?

ደጀ ሰላም አንዳንድ የመፍትሔ ሐሳቦች እንዲሰጡ ስትጋብዝ ከዚህ በፊት በወጡ በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሞቀ ውይይትና ምልልስ የያዛችሁትን ደጀ ሰላማውያንም “ያንን ገታ አድርጋችሁ፣ ሌላ ጊዜ እንመለስበታለንንና፣ ወደዚህኛው ኑ” በማለት ነው።
የውይይት ነጥቦች:-
1. እስከ ጥቅምት አባቶቻችንን እያጽናናን፣ አይዟችሁ እያልን እናበርታቸው፣ ተስፋ አትቁረጡ እንበላቸው፣
2. ለጥቅምቱ ስብሰባ ምእመናን እንዲያስቡበት፣ እንዲጸልዩበት መረጃውን እናድርስ፤ በተለይም ለሰ/ት/ቤት ወጣቶች ስለ ነገሩ እናስረዳቸው፣
3. በመንግስት በኩል ላሉ ሰዎች ጉዳዩ የእምነት ጉዳይ እንጂ የነርሱን “ወንበርና ሥልጣን” ፍለጋ እሽቅድምድም ላይ እንዳልሆንን እንግለጽላቸው። እንደከዚህ በፊቱ “ከወያኔ ጋር አልሰራም” በማለት ምንም የሚለወጥ ነገር አይመጣም፤
4. እስቲ እናንተ ደግሞ ጨምሩበት
ማጠቃለያ
እዚህ የሚቀርቡትን ሐሳቦች አጠናቅረን ለብፁዓን አባቶች፣ ለአበቶችና ለሚመለከታቸው ሰዎች ለማድረስ መቻል ይኖርብናል።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

July 25, 2009

አቡነ ቄርሎስ የቤተ ክህነት ግቢን ለቀቁ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 25/2009)
በማፊያ ቡድን አባሎችና ወረበሎች መኖሪያቸው የተሰባበረባቸውና በሕይወታቸው ላይ አደጋ የተቃጣባቸው አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ለደህንነታቸው በመስጋት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢን ለቅቀው እንደወጡ የቅርብ ምንጮች ገለፁ።

የቅዱስ ሲኖዶስ የበላይነት አልቀበልም ብለው በማስፈራራትና በሀይል ጭምር አጀንዳውን ጠምዝዘው ጊዜያዊ እፎይታ ካገኙት ፓትርያርክ ጋር በገቡት አለመግባባት የግል ቂም ተይዞባቸው አደጋ የተጣለባቸው ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ሰሞኑን የጠቅላይ ቤተ ክህነትን ግቢ ለቅቀው የወጡ ሲሆን አንዳንዶች ወደ ሀገረ ስብከታቸው ወደ ወሎ መሄዳቸውን ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ እዚያው አዲስ አበባ ከሰዎች ዘንድ ማረፋቸውን ተናግረዋል።

“ለሕይወቴ ደህንነት አይሰማኝም” እንዳሉ የተጠቆመው ብፁዕነታቸው ዕቃቸውን ጠቅልለው ሲወጡ መታየታቸው ሲዘገብ ሌሎች አባቶችም ቢሆኑ በተመሳሳይ የደህንነት ስጋት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። የደጀ ሰላም ምንጮች ጨምረው እንደተናገሩት የፓትርያርኩ ወዳጆች የተባሉት ሳይቀሩ በፍርሃት መያዛቸው ሲነገር ፓትርያርኩ ይቃወመኛል የሚሉት ላይ አደጋ ከማስጣል አይመለሱም የሚለው ጉዳይ እያደገ መምጣቱ ታውቋል።

July 24, 2009

ፓትርያርኩ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ኃላፊዎችን ሰበሰቡ፤ መመሪያ ሰጡ

• መንግሥት ገለልተኛ ባለመሆኑ እየተወቀሰ ነው፣
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 24/2009)
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ከሥልጣናቸው በማንሳት አስተዳደሩን ጠቅልለው የያዙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ትናንት ሐሙስ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችን፣ ፀሐፊዎችንና ሌሎች ሃላፊዎችን በመሰብሰብ መመሪያ ሲሰጡ መዋላቸው ተሰማ።


በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ለግማሽ ቀን በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሠራተኞችም እንዲገኙ የተደረገ ሲሆን በዚህ መልክ ፓትርያርኩ የሀገረ ስብከቱን ሃላፊዎች የመሰብሰብ ልምድ እንዳልነበራቸው ታውቋል። ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ከስልጣናቸው ከወረዱ በሁዋላ አውሮፓ ውስጥ ትምህርት ላይ የሚገኙትን ቀሲስ ፋንታሁን ሙጬን በሥራ አስኪያጅነት የመደቡት ቅዱስ ፓትርያርኩ እርሳቸውን ለማስተዋወቅ በሚል በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ መገኘት የመረጡት “ለማስፈራራት እና የአቡነ ሳሙኤል ደጋፊዎችን ደግሞ ለማናደድ” መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። መጪው የመስቀል በዓል እንደከዚህ ቀደሙ በድመቀት እንዲከበር ቅዱስነታቸው በዚሁ ስብሰባ ላይ መመሪያ መስጠታቸውም ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዱስ ሲኖዶስ ከቅዱስ ፓትርያርኩ በገጠመው ሁነኛ ፈተና ምክንያት ችግር ላይ በወደቀባቸው ባለፉት ሁለት ወራትና በችግሩ አፈታት ወቅት መንግሥት ገለልተኛ ከመሆን ይልቅ ከአቡነ ጳውሎስ ጋር በመወገን መቆሙን የሚቃወሙ ሰዎች ሐሳባቸውን በማቅረብ ላይ መሆናቸው ታወቀ። እነዚሁ ለመንግሥት ቅርበት ያላቸው አንዳንዶቹም በመንግስት ሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች እንደሚናገሩት መንግሥት በዚህ ግርግር ወቅት ገለልተኛ ሆኖ መቆም ሲገባው ድንበሩን በማለፍ የአቡነ ጳውሎስ ፍላጎት ማስፈጸሚያ መሆኑን አጥብቀው ተከራክረዋል። በተለይም የደህንነት ክፍሉ በፍፁም የተሳሳተ መረጃና አቅጣጫ የአቡነ ጳውሎስ ደጋፊ ሆኖ መዝለቁን የሚናገሩት እነዚሁ ወገኖች መንግስት ይህንን ጉዳይ እንዲያጣራ በመጠየቅ ላይ ናቸው ተብሏል:፡

ጉዞ ወደ እስክንድርያ በድጋሚ? እንዴት ተደርጎ!!!

(ደጀ ሰላም፣ ጁላይ 23/2009)
የተወደዳችሁ ደጀ ሰለማውያንና ደጀ ሰላማውያት፣
አንድ ጦማሪ ወዳጃችን ‹‹ማርቆስ አባታችን እስክንድርያ እናታችን›› ብለን ወደ ቀደመው ድንኳን እንሂድ? ብለው መጣጥፍ ማቅረባቸው ይታወሳል። በዚሁ መነሻነት ሁልጊዜ “ጦማሪያችን” ብርሃናዊት በበኩሏ የሚከተለውን ጽሑፍ ልካልናለች። ሁለቱም ጸሐፍት የሚያነሷቸው ሐሳቦች የግላቸው እንጂ “ደጀ ሰላም ተቀብላ ያጸደቀችው” እንዳልሆነ በማስታወስ ወደ ምንባቡ እንጋብዛችሁዋለን።
ቸረ ወሬ ያሰማን
+++++++++++++++++
ጉዞ ወደ እስክንድርያ በድጋሚ? እንዴት ተደርጎ!!!
(ከብርሃናዊት )

እስክንድርያ፡ ከአትናቴዎስ ማረፍ በሁዋላ፡ እናታችን ሆና አታውቅም፡፡ እውነተኛ እናትነትዋ፡ በደጋጎቹ በነቄርሎስ፥ በነዲዮስቆሮስ ጊዜ አብቅቶዋል፡፡ ከአትናቴዎስ ስደት በሁዋላ መተካት የጀመሩት የእስክንድርያ ጳጳሳት ሁሉ ኢትዮጵያንና ቤተክርስቲያኑዋን በሁለት ቢላዋ ሲበሉዋት ነው የኖሩት፡፡ ቀድሞ፡-

• የኢትዮጵያውያንን ቅድመ-ታሪክ የያዙ መሕፍት ሁሉ ከምድረ ኢትዮጵያ ጠፍተው፡ በምትኩ ዐረብኛና የግብውያንን ገድል የሚተርክ መሓፍት ብቻ እንዲበዙ በማድረግ፡

• ግዕዝኛን አጥፍቶ፡ በምትኩ፡ ዐረብኛ ብቻ እንዲተካ ለማድረግ፡ ብዙ የቤተክርስቲያን የግዕዝ መሕፍትን፡ (የተወሰኑ የሃይማኖት መሕፍት ብቻ ሲቀሩ) የታሪክ፥ የፍልስፍና፥ የዕደ ጥበብ፥ የትውፊት መጻሕፍትን በደካማ ነገሥታት እያደሩ በማስጠፋት፡

• እንደ አፄ ዐምደ ጽዮን የመሳሰሉ፡ የዚህን ነገር አደገኛነት የተረዱ ነገሥታት፡ ወደቀደመ ሥርኣት ለመመለስ ያደረጉትን እርምጃ አምርሮ በመቃወም፡ ታሪካቸውን ገልብጦ በመጻፍና ያለስማቸው ስም በመስጠት፡ “ያባታቸውን ሚስት ያገቡ” በማለት፡ ኢትዮጵያውያን የነርሱን ፈለግ እንዳይከተሉ በመከላከል፡ ሌሎች ነገሥታትም የርሱን ፈለግ ሲከተሉ፡ ወይም ቀድሞ የተከተሉ ከነበሩ፡ “በዘመኑ ንጉሥ እከሌ የግብን ጳጳስ በመቃወሙ እግዚአብሔር ተቆጥቶ ረሃብ ሆነ” የሚሉ እንቶ ፈንቶ ተረቶችን በመፍጠር፡ የኢትዮጵያውያን ምዕመናንን ሥነ-ልቦና በፍርሃት በመያዝ፡

• ከዚህም አልፎ ተርፎ፡ “ሥጋ በመለኮት ፀጋ ሲበቃ ሊሰወር አይችልም፡ ስውር ባሕታዊ የሚባል ነገር የለም፡ ክርስቶስም ረቂቅ መለኮት ቢኖረውም፡ ሥጋውን ሊያረቅቀውና ስውር ሊያደርገው አይችልም” እያሉ ኢትዮጵያውያንን ለዘመናት ከኖሩበት ክርስቶሳዊ እምነታቸውና ሥውር ባሕታውያንን የማናገር ፀጋቸው ለማላቅቅና፡ በምትኩ፡ የነርሱን ሁለት ባሕሪ የመሰለ አስተምህሮ እንዲቀበል በማስገደድ፡ በ5ኛው ክፍለ ዘመን በዋልድባ ላሉ መነኮሳትና ሊቃውንት መበታተንና መጨፍጨፍ ምክንያት በመሆናቸው (ዛሬ የግብጽ ኦርቶዶክስ “ተዋሕዶ” ቤተክርስቲያን እያልን ስንጠራቸው ይገርመኛል፡፡ የሃይማኖት ቃላቸው በተግባር ሲገለጥ ምን እንደሆነ ስለማያውቁ፡ በኢትዮጵያ ምድር ከባሕታውያን ጋር ሲጣሉ ኖሩ፡፡ ለመሆኑ፡ ግብውያን “ሥላሴ በስም ሦስት ናቸው እንጂ በአካል ሦስት አደሉም” እንደሚሉ ስንቶቻችን እናውቃለን? የኛ ቤተክርስቲያን ግን፡ በተረዳ ነገር “አብ የራሱ የሆነ ፍጹም አካል አለው፡ ወልድ የራሱ የሆነ ፍጹም አካል አለው ፡መንፈስ ቅዱስ የራሱ የሆነ ፍጹም አካል አለው፡ ወልድ ሰው የሆነው በተለየ አካሉ ነው” ብለን ስናምን፡ ግብጻውያኑ ግን አካል ያለው ወልድ ብቻ ነው ይላሉ፡፡ የአባ ሕርያቆስን ቅዳሴ የት እንዳገቡት እንጃ፡፡ ምናልባት አባ ሕርያቆስ ግብጦች በሁዋላ በሓሰት እንዳጻፉት ሳይሆን፡ በዋልድባ የነበረ ኢትዮጰያዊ ነው የሚለው የአባ ተስፋ ሥላሴ argument ትክክል ሆኖ ይሆን? ይመስላል!)

• ኢትዮጵያውያን፡ ከማንም በፊት፡ በመልከ-ጼዴቅ በኩል የክህነት ፀጋ ተቀብለው ሳለ፡ ሁዋላም፡ በታቦተ ጽዮን መምጣት ጊዜ፡ በሌዋውያን ካህናት በኩል “እስራኤል ዘነፍስ” ተብለው፡ ክህነታቸውን አጽንተው፡ የክህነት ግምጃ ቤት ሆነው ሳለ፡ ግብጻውያኑ ለነርሱ ዐረባዊ ተንኮል እንዲያመቻቸው፡ መልከ ዴቅንና ከንግስተ ሳባ በፊት ያሉ የኢትዮጵያ ካህናትን አስደናቂ መንፈሳዊ ኑሮና እግዚአብሔራዊ ትምህርት የሚዘክሩ መሕፍት እንዳይነበቡ በማውገዝና፡ “የማንም ደብተራ የጻፋቸው ድግምቶች” የሚል ስም በማሰጠት፡ ከኢትዮጵያ ምድር ወጥተው በሜሮዌና ኑብያ እንዲሰደዱ በማድረግ፡ ኢትዮጵያውያን ከሳባ በፊት ያለውን ታሪካቸውን እንዳያውቁ በተቻላቸው መጠን በመታገል፡

• እግዚአብሔር “ኢትዮጵያውያኑ የሰጠሁዋቸውን ሃብተ-ክህነት ንቀው፡ ባላልኩዋቸው መንገድ ሄደውብኛልና፡ ትቀጣቸው ዘንድ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፡ ነገር ግን ጠላቶቻቸውን (ዐረባውያን ግብጦችንና ሌሎች ስደተኛ ክስርቲያን ነን ባዮችን) እንጂ እነርሱን አትንካ” በማለት ለዮዲት ጉዲት አይሁዳዊ ቅድመ አያት የቅጣትን ፈቃድ በመስጠቱ፡ ትልቅ ችግር በኢትዮጵያ ተከስቶ፡ ኢትዮጵያን እርስ በርስ ብቻ ሳይሆን ከአምላክ ጋር ጭምር እንዲጣሉ ምክንያት በመሆን፡

• በኢትዮጵያ የነበሩና፡ በሰላም ወደ ክርስትና መቀላቀል የጀመሩ ቤተ እስራኤላውያንን፡ “ሰቃልያነ እግዚእ” እያሉ ነገሥታቱ ሁሉ እነርሱን ለማጥፋት እንዲተባበሩ በመቀስቀስና፡ ነገሥታቱ እምቢ ካሉም “የክርስቶስ ወዳጅ አይደለህም” እያሉ ከሌሎች ስደተኛ የሮምና የሌሎች የውጭ ሃገር ተወላጅ ክርስቲያኖች ጋር በመተባበር፡ ቅስቀሳ በማካሄድ፡ በኢትዮጵያ ምድር ቤተ እስራኤላውያንን እንደማርያም ጠላት እንዲታዩ በማድረግ፡

• በዚህ ድርጊታቸው ተከፍቶ፡ ከበዙ ሙከራ በሁዋላ፡ ጥምቀቱን ሁሉ ትቶና ማተቡን በጥሶ ወደሁዋላ እየተመለሰ ጭምር፡ ራሱን ለማደራጀት የበቃው የቤተ እሥራኤልና የሌሎችም የተገፉ ኢትዮጵያውያን ጦር፡ በዮዲት ጉዲት አማካኝነት ተነስቶ፡ ዐረብ-ነክ የሆኑ ቅሪቶችን ለማጥፋት በመነሳቱ፡ በሰበቡ ለብዙ የቤተክርስቲያን ሃብት መውደምና ብዙ ካህናት መታረድ ምክንያት በመሆን፡

• ኢትዮጵያ በሕገ-ልቦና እና በሕገ-ኦሪት ጸንታ የነበረች በመሆንዋ፡ ሊቃውንቶችዋ ሁሉንም ከሕገ-ወንጌል ጋር አስተባብረው በሚያስተምሩበት ወቅት፡ “የምታስተምሩት ኑፋቄ ነው” በማለት በመቃወምና፡ ልክ እንደዘመኑ ተሃድሶ መናፍቃን “ገና ከኦሪት ያልተላቀቃችሁ” በማለት ትልቅ ረብሻ በማስነሳት፡ ከ700 በላይ መተኪያ የሌላቸው ሊቃውንት፡ በአክሱም ዘመነ መንግሥት፡ በኢትዮጵያ ምድር በማስጨፍጨፍና በማሳደድ፡

• ኢትዮጵያዊው የሥዕል አሳሳል ዘይቤ ጠፍቶ፡ በምትኩ በነርሱ መልክ ዐረባዊ መልክ ያለው ሰው እንዲሳል በመጎትጎት፡ እምቢ ካሉም፡ ኢትዮጵያውያን ሰዓሊዎችን ምላስና እጃቸውን ከነገሥታት ጋር በመተባበር በማስቆረጥ፡

• “የብሕትውና ሁሉ ጀማሪ አባ እንጦንስ ነው” በማለት ያለማዕረጉ ከሚገባው በላይ ማዕረግ ሰጥተው፡ በኢትዮጵያ ላይ ድንቅ ተአምራትን ያደርጉ የነበሩና ብዙ ገዳማትን በኢትዮጵያ ዙርያ ክልሎች ያቀኑ ናዝራውያን ባሕታውያንንና ካሕናትን በማሳደድ፡ ክርስቶስን ሲወለድ እጅ መንሻ የሰጡትንና ከነርሱ ተምሮ የመነነውን ሁሉ እንደሌለ በመቁጠር፡ እስከዋልድባ በማሳደድና የአክሱምን ቤተ ክህነት ከእጃቸው ፈልቅቆ በመውሰድ የኢትዮጵያን ቤተክህነት ለዘላለሙ በመለወጥ (የኢትዮጵያ አብነት ትምህርት ቤት ግን ኢትዮጵያዊውን ሥርዓት በመጠበቅ፡ የቤተክህነቱን ያህል ሳይበገርላቸው እስከዛሬ በእግዚአብሔር ቸርነት ዘልቆዋል፡፡)

• ንጉሥ፡ ሁሉ “አል…” በሚል ቅጥያ እንጂ “አፄ” በሚል ቅጥያ እንዳይጠራ ለማድረግ የተቻላቸውን ሁሉ በመሥራት: ለዛሬዎቹ አረማውያንና ዐረባውያን ወገኖቻቸው “አልነጃሺ የተባለ ሙስሊም ንጉሥ ነበር”… ቅብርጥሶ የሚል የፈጠራ ታሪክ መንገድ በመክፈት፡

• ለዚህ ጥፋትን አዘል አገልግሎታቸው፡ ሓዋርያዊነቱ ቀርቶ ንግድ እስኪመስል ድረስ፡ ነብዩ በትንቢቱ እንዳለው፡ ኢትዮጵያውያንን ለግብጽ ጉስቁልና በመንዳት፡ ብዙ ወርቅና ብር እጅ መንሻ ከኢትዮጵያውያኑ ሲጎርፍና ሲቸገሩ፡ “ይህ መንፈሳዊ አገልገሎት እንጂ ሥጋዊ አደለም” ብሎ እንኩዋን ሃይ ያለ አንድም ግብጣዊ ክርስቲያን ባለመኖሩ፡ እንዲያውም፡ እጅ መንሻው በድብቅ “እከሌን ትተህ እከሌን አንግሥልኝ” ለሚል መማጠኛ ጭምር እንዲውል በመፍቀድ፡ የለየለት የዛሬውን ቤተ ክህነትና መንግሥት ትስስር የሚመስል የማፊያ አሠራር በመንደፍ፡ ነገሥታቱን በሥልጣን ሽኩቻ በማባላት፡ እነርሱ ግን በመሃል ቤት ወርቃቸውን በማጋበስ፡

• ከዚህም የባሰው ደግሞ፡ ምንኩስናቸውን ያፈረሱ እና አንዱ ደግሞ ሃይማኖቱ እስላም የሆነ ከአንድም ሁለት ሦስት ጋጠወጥ ግብጣውያን ጳጳሳት፡ ወደኢትዮጵያ መጥተው የቻሉትን ያህል ሃይማኖታዊ ቅርስና ወርቅ ዘርፈው ሲሄዱ፡ ግብጥ ላይ የሚያወግዛቸው እንኩዋ አለመኖሩ፡ ይልቁንም “ደግ አረግህ ልጄ” የሚል በሚመስል አኩዋሁዋን ምንም ሳይባሉ ኑሮዋቸውን እንዲቀጥሉ በማድረግ


አሁን በዘመናችን ደግሞ፡-


• በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያን ይዞታ በመቀናቀንና መነኮሳቱን በማስቸገር

• አንድ ተአምር መሰል ነገር የተሰራላቸው እንደሆን፡ በየኢንተርኔቱ በየመጽሐፉ በየምናምኑ በማስነገር፡ ውስጠ-ኑፋቄ የሆነ አደገኛ ትምህርታቸውን በተሃድሶዎች በኩል በማስፋፋት- አዎን! ያንን እስኪበቃኝ ታዝቤያለሁ፡፡ ተመሳስለው ቤተክርስቲያን የገቡ ተሃድሶዎች በሙሉ ወይ አፍቃሬ-ግብጽ፡ ወይ አፍቃሬ-ግሪክ ናቸው፡፡ ስብከታቸውን፡ አንድምታቸውን፡ መጽሓፋቸውን ማዳነቅና የኢትዮጵያውን ግዕዛዊ ስብከትና አንድምታ ደግሞ እንከኑን በማብዛት፡ የምእመናንን ልብ መሸርሸር የዕለት ተዕለት ሥራቸው ነው፡፡ ያም፡ እውነት ግብጽን ወይም ግሪክን ወደው ሳይሆን፡ ኢትዮጵያዊውን ትምህርትና ትውፊት ለመደምሰስ፡ በቅድሚያ እርሱን የማይተካ፡ በስም ግን ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሥርዓት ወደቤተክርስቲያን ማስገባት እንዳለባቸው፡ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው፡፡ (በሚያሳዝን ሁኔታ፡ የዘመኑ መንፈሳዊ መጽሓፍ ጸሓፊ ሁሉ፡ ያለ ሽኖዳ አባት ያለ ግብጽ ገዳማት የማያውቅ ይመስል፡ “አስቄጥስ”…. “አስቄጥስ”….. “ሽኖዳ”…. “ሽኖዳ” የሚል መጽሓፍና ኅትመት ብቻ በማባዛት፡ በኢትዮጵያ የሕይወት ቃልን እየተናገሩ፡ ግን ሰሚ አጥተው እያለፉ ያሉ ባሕታውያንንና ያብነት ትምህርት ቤት መምህራንን ትምህርትና ቃለ ምዕዳን እየተከታተሉ በጽሑፍ በማስፈር ፈንታ፡ የቲዮሎጂ ምሩቅና ጋዜጠኛ ሁሉ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተከርስቲያን ተከታይ እስኪመስል ድረስ፡ ቅኔያዊውና ወዝ ያለው የኢትዮጵያውያን ቃለ እግዚአብሔር ከትውልዱ ጆሮ እንዳይደርስ ደንቃራ እየሆነ ይገኛል፡፡ በግብጽ አስቄጥስን አስቄጥስ ያደረጉዋት፡ ቁስቁዋምን ቁስቁዋም ያደረጉዋት እኮ ቀደም ሲል የነበሩ ኢትዪጵያውያን መናንያን ነበሩ እንጂ ሌላ አደለም!)

• በግብጽ ስደት ወቅት፡ እመቤታችን በኮቲባና ትዕማን የደረሰባትን እንግልት፡ በልዋጩ ለኢትዮጵያውያን ለመስጠት በመዳዳት፡ “ግብጾች እንዲህ አደረጉ የሚለው የኢትዮጵያውያን ፈጠራ ነው” በማለት ራሳቸውን በትዕቢት በመኮፈስ፡ ምግባር ጉድለታቸውን ሁሉ በኢትዮጵያውያን ላይ በማላከክ

• የእግዚአብሔር ካህን ዮቶርን (የሙሴ አማትን) ለሙሴ በሕገ- እግዚአብሔር ፈንታ ጥንቆላን ያስተማረ እርሱ ነው በማለት፡ የአረማውያን ፈርኦኖቻቸውን ስምና ዝና ሳይቀር በካህኑ ዮቶር ፈንታ በመከላከል፡ በውዳሴ ማርያም ትርጉዋሜ እንዲገባ በማድረግ፡

• የቀስተ ደመና እና የባንዲራችንን ትስስር ለማስቀረት፡ በዚሁ መጽሓፍ ላይ፡ በቀስተ ደመናው ጎልቶ የሚታየው አረንጉዋዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ቀርቶ፡ ጎልቶ የማይታየውን በመውሰድ፡ የቀስቱ ቀለም ጥቁር፡ ነጭ፡ ቀይና ብጫ ነው በማለት፡ ከራሳቸው ባንዲራ ቀለማት ጋር ተጠጋግቶ ተተክቶ እንዲነበብ በማድረግ፡ ከዚህም አልፎ ተርፎ፡ አረንጉዋዴ ቢጫ ቀይ የሆነውን የተለመደውን የኢትዮጵያውያንን ማተብ፡ በራሳቸው ባንዲራ ቀለማት በመተካት፡ ጥቁር ነጭ ቀይ በማድረግ፡ “ነጩ ሕይወት፡ ቀዩ የክርስቶስ ደም፡ ጥቁሩ የገሃነም ምሳሌ ነው” በማለት እንዳፈቀዳቸው ትርጉም በመስጠት ሲያቄሉን በመኖር፡ (ከማንኛውም ቀለም፡ ተለዋጭ ትርጉም መስጠት የሚቻል መሆኑን አንዘንጋ)

….ይህንና ይህን በመሳሰለው፡ ፈጽሞ የማንግባባባቸው የእስክንድርያዎች ዲስኩርና ውስጠ-ጠላትነት ምክንያት፡ ዳግም በግብጽ ቅኝ ግዛት እንድንገዛ ለተመኘህበት ደጀሰላም ንስሓ ግባ፡፡ የደጀ ሰላምን ጽሑፍ አንብቦ በልቡ የተመኘም ሁሉ ንስሓ ይግባ፡፡

እስክንድርያ አደለችም፡ ኢትዮጵያ ናት እናታችን፡፡ ትናንት አቦ አቦ ስንላቸውና ስንክባቸው የነበሩትን አባቶች፡ በሥራቸው ምክንያት ዛሬ መሬት ስናወርዳቸው፡ አለቃ አያሌው ታምሩ በመንፈስ እያዩ ምን ይሉ ይሆን? እውነተኛው ጠንቅ መቼ እንደጀመረና ምን እንደሆነ ግልጽ አድርገው ተናግረውት ነበር እኮ? እነ ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ምን ይላሉ? እስክንድርያ ምን ያስኬደናል ቅኝ ግዛት ፍለጋ? ከላይ የተዘረዘረው የግብጻውያን ወንጀል ሁሉ ከሌሎች የኛ ስንፍናዎችና አላዋቂነት ጋር ተደማምሮ የት ድረስ እንዳዘቀጠን በደንብ የተረዱ፡ የአሁኑ ቤተ-ክህነት ችግርም እንዴት እንደሚፈታ በደንብ የሚያውቁ፡ እነርሱን የመሰሉ ሊቃውንት፡ ታሪክ አዋቂዎችና የክህነት ባለቤቶች እያሉ፡ እስክንድርያ የምንሄደው አል ነጃሺን ፍለጋ ነው ወይ? ወይስ አሁን ደሞ እጅ መንሻ አባይን አንደኛችንን አስረክበን ሌላ 1600 ዓመት ከግብጽ ውሃ ስንለምን ልንኖር ነው? ወይስ ዴር ሱልጣንን እጅ መንሻ እንስጥ? እግዚአብሔር ሌላ ግራኝ፡ ሌላ ዮዲት ያስነሳ ወይ? እሱ ነው ያማረን? ምን ችግር አለ? እኛ ብቻ ያማረንን እንግለጥ እንጂ እነርሱ እንደሆን ዝግጁ ናቸው- እንደጥንቱ ሊግጡንና ከቻሉ ሊያጠፉን የኛዎቹ ፍልስጤማውያን ራሳቸው አሰፍስፈዋል፡፡

መድሓኒቱን አፍንጫችን ሥር አስቀምጠን፡ ወንዝ ተሻግሮ የሰው ቤት መቀላወጥ፡ ያውም የማይመስሉንን ሰዎች ቤት መቀላወጥ፡ ራስን የመጥላትና የራስን ሊቃውንትን የመናቅ አባዜ እንጂ ሌላ ስም የለውም፡፡

ሌላውም የተዋሕዶ ልጅ ነኝ የሚል ሁሉ፡ ኢትዮጵያን ሳይሆን ግብጽን በኢትዮጵያ ላይ ከመስበክ መቆጠብ ይገባዋል፡፡ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ናት- ሥርኣቱዋና ከአምላክ የተቀበለችው አደራም 7 ቃልኪዳናት እንጂ አንድ ብቻ የሥጋ ወደሙ ቃል ኪዳን አደለም፡፡ ታቦትን፡ ግርዛትን፡ ጠበልን፡ ብሕትውናን፡ የተቀደሱ እንስሳትን መብላትን፡ ሥርዓተ መንግሥትን፡ የቀስተ ደመና ሰንደቅ ዓላማችንን፡ የቤተልሔምን ምሳሌያዊ ህንጸትና የንጹህ ስንዴ ሕብስት የመፈተት ምሳሌያዊ ሥርዓትን… ይህን ሁሉ ገና ለግብጾች ስናስረዳ መኖር የለብንም፡፡ የምንሰዋው ቁርባን እንኩዋ ተምሳሌቱ የኛ ምሉዕ እና ሦስቱንም ሕግጋት (ሕገ-ልቦና፡ ሕገ-ኦሪትና ሕገ-ወንጌል) አጠቃልሎ የያዘ ነው- ሁለቱን በተምሳሌትነት፡ አንዱን በአማናዊነት፡፡ እንደመናፍቅ “ዋናው ክርስቶስ ነው” እያልን መቅለጥ ካልፈለግን በቀር እስክንድርያ የሚያዞረን ጉዳይ የለም፡፡

July 23, 2009

‹‹ማርቆስ አባታችን እስክንድርያ እናታችን›› ብለን ወደ ቀደመው ድንኳን እንሂድ?

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 22/2009)

እስካሁን ድረስ ቤተ ክርስቲያንን እየመሩ ያሉ ጳጳሳትን በተመለከተ በአማኙ በኩል ከመንፈስ ቅዱስ በታች የቤተ ክርስቲያን መሪና ጠባቂ የጳጳሳት ጉባዔ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደሆነ ይታመን ነበር፡፡ ሰሞኑን በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል ሲካሄድ የቆየውና በፓትርያርኩ ላይ ግልጽ ተቃውሞ ባሰሙ ጳጳሳት ላይ የጉዳት ማድረስ ሙከራ ከተደረገ በኋላ ሐምሌ 10 በስምምነት ተጠናቀቀ የተባለው ስብሰባ ሂደት ግን የሚያመለክተው ከዚህ የተለየ ነው፡፡በአንዳንድ የቅዱስ ሲኖዶሰ አባላት በሆኑ ጳጳሳት ዘንድ እየታየ ያለው መከፋፈል፣ ለእውነት አለመቆም፣ ከቤተ ክርስቲያኗ ሕግና ሥርዓት ይልቅ ለፓትርያርኩ ሃሳብ ተገዢ መሆን፣ የአባቶችን መንፈሳዊ ዝቅጠት የሚያመለክት ሲሆን ቤተ ክርስቲያኒቱ በቅዱስ ሲኖዶስ እንደምትመራ ለሚያምን እና ለሚመሰክር ምዕመን ሁሉ አንገት የሚያስደፋ ጥቁር የታሪክ ክስተት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም ሌላ የጨለማ ዘመን ውስጥ እንደምትገኝ በገሀድ ያየንበት ወቅት ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የምትመራው በቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ፓትርያርኩ ራሳቸውን እንደ ጣዖት ከሕግ በላይ ካደረጉ፣ አንዳንድ ጳጳሳትም ይህን የሳቸውን ፍላጎት እና የራሳቸውን ጥቅም ለማሟላት ቅዱስ ሲኖዶስን ሕልውናውን ለማሳጣት የሚያውኩ ከሆነ ቤተ ክርስቲናችን ቅዱስ ሲኖዶስ አላት ብሎ መናገሩ በዲያስጶራ ‹‹ሕጋዊ ሲኖዶስ›› ነኝ እያለ ምዕመናንን ግራ ከሚያጋባው አካል አይለይም፡፡ እስካሁን ድረስ አባቶች አሉን፣ “ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቃል” በማለት ነበር በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የቆየንው፡፡ እንግዲህ ቤተ ክርስቲያኒቱ በውስጥም በውጪም የወንበዴዎች ዋሻ ከሆነች፣ ወዴት እንሄዳለን?

ከሰሎሞን ቀጥሎ እስራኤልን ይመራ ዘንድ በዙፋኑ የተቀመጠው ሮብአም በላያቸው የተጫነውን ቀንበር እንዲያነሳላቸው እና በመልካም አስተዳደር ሕዝቡን እንዲያገለግል ሲመክሩት አልሰማም ብሎ የአብሮ አደጎቹን ክፉ ምክር በመስማት በላያቸው ባለው ቀንበር ላይ የባሰ ሸክም እንደሚያጸናባቸው ስለተናገረ ህዝቡ ‹‹ሕዝቡ በዳዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም፡፡ እስራኤል ሆይ ወደ ድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፤ ዳዊት ሆይ አሁን የራስህን ቤት ተመልከት፡፡›› በማለት ወደየድንኳኖቻቸው ተመልሰዋል፡፡ ብዙዎችም ዛሬ ይህን በመሰለ የፓትርያርኩ ሕገ ወጥነት እና በአንዳንድ ጳጳሳት ደካማነት ‹‹እግዚአብሔር ሆይ የራስህን ቤት ተመልከት›› በማለት ወደ ሌላ ድንኳን ለመመልከት እየተገደዱ ነው፡፡

ኧረ ለመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን ከመንበረ ማርቆስ፡ ከእስክንድርያ መንበር ተላቃ ራሷን እንድትመራ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ነገሥታትና ሊቃውንት በ50 ዓመት ታሪክ ውስጥ እንዲህ ዓይነት አሳዛኝታሪክ ሲታይ ምን ይሉ ይሆን? ፓትርያርኩ እንደሮብአም የሚሰሙት ምክር የመሰሎቻቸውን ከሆነ፣ ለእውነት በቆሙ አባቶች ላይ በሕይወታቸው እስከ ማስፈራራት ድረስ ቀንበር የሚጫንባቸው ከሆነ ፓትርያርኩ እና መሰሎቻቸው ቤተ ክርስቲያንን ለመምራት እንኳን መንፈሳዊው ብቃት ዓለማዊ ጥበብም ይጎድላቸዋል፡፡

ቤተ ክርስቲናችን ለ1600 ዓመታት ማርቆስ አባታችን፣ እስክንድርያ እናታችን ብላ ነው በብዙ ውጣ ውረድ ያለፈችው እና እዚህ የደረሰችው፡፡ አሁን ግን የእረኝነት ኃላፊነታቸውን በዘነጉ ፓትርያርክና ጳጳሳት ያለ አባት እና ያለ እናት ሊያስቀሩን በቀን የበቀል ኃይልን፣ በሌሊት ጨለማት ተገን አድርገው ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡ ታዲያ እስራኤላውያን ወደየድንኳኖቻቸው እንደተመለሱ እኛስ አባትና እናት እንደሌለው ሆነናልና ‹‹ማርቆስ አባታችን እስክንድርያ እናታችን›› ብለን ወደ ቀደመው ድንኳን እንሂድ?
(አንድ ደጀ ሰላማዊ እንደጻፉት)

ድንቄም ተቆርቋሪ


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 22/2009)
ምላስህ ለሰላው ለሀገር ጠላቱ፣
ይደረስህ ጦማሬ ለንጉሴ ከንቱ።
ዛሬ ደግሞ መጣህ አብረህ ከጳውሊ፣
አበው ሲተርቱ አህያ ካመዱ፣
ሞስሰው ተገኙ ጳውሊ ከንጉሱ።


ድሮውንስ ቢሆን ገና ከጅምሩ፣
ያፈረሰ ዲያቆን ኮቶሊክ ባትርያርክ፣
ስምምነት ደርሰው ውሸትን ለመስበክ፣
ጳውሊም አሰናድቶ መቶ ሺ ብር ወረት፣
አትርፎ ለመምጣት ንጉሴ ሲዋትት፣
ሊያፈርሰው ጀመረ የቅዱሳንን በዓት፣
ገበያውም ደርቷል ዲሲ-ቤተ ክ’ነት።

ይሉኝታ የላቸው ፈጣሪን አይፈሩ፣
አንደበታቸው መርዝ ቀና አይናገሩ፣
ወይ ዘይት የላቸው መብራት አያበሩ፣
ጨለማ ሆነዋል በብርሃን እየኖሩ።

ምዕመናን እንንቃ ጊዜው የሥራ ነው፣
ቤታችን ፈት ናት ጠባቂው ጳውሊ ነው።
ያሬድ ቄሰ ገበዝ ሰባኪው ንጉሴ፣
ተስፋ እንዳንጠብቅ ከነዚህ ሕዳሴ።

ጊዜው ሳይመሽብን ለሥራ እንነሳ፣
ጸሎትን እንጨምር በጾምም እንበርታ፣
ከሰማይ መልስ አለ በቃሉ ለፀና፣
ተዋሕዶ ንጽሕት ታብባለች ገና።
(ስንታየሁ ከሰሜን አሜሪካ)

July 22, 2009

የወቅቱን የቤተ ክርስቲያን ችግር አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ጥሪ አስተላለፉ


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 22/ 2009

በወቅቱ በቤተ ክርስቲያናችን የተፈጠረውን ችግር አስመልክቶ የዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም መልእክት አስተላለፉ፣ ጥሪ አቀረቡ፣ አቋማቸውንም ገለፁ። መንግሥትም "በአሳለፍነው ወቅት ተናገረ እንደተባለውና አበው ሊቃነ ጳጳሳትም እንደመሰከሩለት የቅዱስ ሲኖዶስን ሕግና ደንብ በማክበርና በማስከበር እስከ መጨረሻው አቋሙን ሳይለውጥ የጥቅመኞችንና የራስ ወዳዶችን ወሬ ቦታ ሳይሰጥ ሊቀጥልበት ይገባል" ሲሉ ጠየቁ።

“የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሀሳብ ነው” በሚለው ሐዋርያዊ ቃል መግለጫቸውን “ ለቅድስት ተዋሕዶ እምነታችን ራሳችሁን ለሰጣችሁና ለመስጠት ዝግጁዎች ለሆናችሁ ወገኖቼ፤ የአብያተ ክርስቲያናት ሀሳብ ሀሳባችሁ፣ የአብያተ ክርስቲያናት ችግር፣ ችግራችሁ መሆኑን ለተረዳችሁና ለመረዳት ዝግጁዎች” ለሆኑ ሰዎች ያስተላለፉት ብፁዕነታቸው የችግሩን አጠቃላይ ሒደት ከቅዱስ መፅሐፍ ጋር እያመሳከሩ አቅርዋል። በቅዱስ ጳውሎስ ቃል ስንመዘን “ብዙዎቻችን ከመስመሩ ወጣ ብለን የራሳችንን ሀሳብና ፍላጎት ስነከተል ጥቂቶቻችን ደግሞ ስለ እውነት ስለ አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአቅማችንን ስንጥር እንታያለን። ሌሎቻችን ደግሞ በግላችን ካቋቋምነው ቤተ ክርስቲያንና ማህበር ውጪ እንደማይመለከተን ሆን አንዳንድ ጊዜ እንደ አስታራቂ ሽማግሌ፣ አንዳንድ ጊዜ እንደ ወቅቱ፣ እንደ ነፋሱ ስንወዛወዝ እንገኛለን” ብለዋል።

በጠቅላላው በአሁኑ ወቅት ለግል ዝናና ለስልጣን ተብሎ ወንጀል እየተሰራ መሆኑን፣ አበው ሊቃነ ጳጳሳት መንገላታታቸውን፣ የቤተ ክርስቲያን ችግር ሳይፈታ “በቀጠሮ ሰበብ” በይደር መተላለፉን፣ “እኔ ከሞትኩ” በሚለው እንስሳዊ ፈሊጥ “ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በልጆቿም ሆነ በተቃዋሚዎቿ ፊት የሀፍረት ካባን እንድትለብስ” መገደዷን” በሰፊው አብራርተው “ለወጋቸውና ለሥልጣናቸው፣ ለጥቅማቸውና ለክብራቸው ሲሉ የእግዚአብሔርን ትዛዝ እጅግ የናቁትን ለይተን እንወቅ” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። በተለይም በሰሜን አሜሪካ ያለውን “የግል ቤተ ክርስቲያን የሚያስተዳድሩ” ሰዎች በተላለፈ በሚመስል አስተያየታቸው ደግሞ “በቤተ ክርስቲያን ስም የግል ጎጆ መቀለሱን ትተን ፣ ከውስጥ ሆነን በእውነትና በዓላማ እንሟገታቸው (ወንጀለኞቹን)፤ ስህተቶቻቸውንም በግልጽ እናሳያቸው” ብለዋል።

እውነትን ያ ፍርሃት በድፍረት እንመስክር ያሉት ብፁዕነታቸው “መንግስት በአሳለፍነው ወቅት ተናገረ እንደተባለውና አበው ሊቃነ ጳጳሳትም እንደመሰከሩለት የቅዱስ ሲኖዶስን ሕግና ደንብ በማክበርና በማስከበር እስከ መጨረሻው አቋሙን ሳይለውጥ፣ የጥቅመኞችንና የራስ ወዳዶችን ወሬ ቦታ ሳይሰጥ ሊቀጥልበት ይገባል” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። አባቶችን በማስፈራራት፣ በአፈናና በዛቻ፣ በስም ማጥፋትና በአድማ የተከናወነውን የመጨረሻውን ስብሰባ የተቃወሙት ብፁዕነታቸው “እሳቱ ተዳፈነ እንጂ አልጠፋም” ብለዋል። “ጥቅምት (ጉባዔው የሚደረግበት ወቅት) ነገ ነውና የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዳይናጋ፣ ሥርዓቷ እንዳይበረዝ፣ ቀኖናዋ በሆያ ሆዬ እንዳይለወጥ፣ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች የሆናችሁ ሁሉ ከዚህ ዕለት ጀምሮ በየአለንበት በጋራም ሆነ በግል እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት እንለምነው። … የተራራቅን ተቀራርበን፣ የተለያየን ተገናኝተን ለመጸለይና ለመዘመር እግዚአብሔርንም ለማመስገን እንድንችል የሚከብድብኝ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሀሳብ ነው እንበል” ሲሉ አባታዊ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ላለፉት ሦስት ዓመታት በኒውዮርክና በዲሲ አህጉረ ስብከት በሊቀ ጵጵስና በማገልገል የሚገኙ አባት ሲሆኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሙሉ በሙሉ የዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት በማስተዳደር ላይ ይገኛሉ። ብፁዕነታቸው ይህንን መልእክት በቀጥታ በማስተላለፋቸው ብዙ ምእመናንን አነገታቸውን ከደፉበት ቀና ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

(የመልእክቱን ሙሉ ቃል ለማንበብ የሀገረ ስብከቱን ድረ ገጽ እዚህ ይመልከቱ)

የቤተ ክህነቱ ማፊያ ቡድን አሁንም አልተያዘም፤ ውንብድናው ከተፈፀመ ሳምንት ሆነው

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 22/2009)

ሳምንት ረቡዕ ጁላይ 15 ምሽት፣ ለሐሙስ ዋዜማ ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው ያለውን የመብራት መጥፋት ተገን ባደረጉ ሰዎች በብፁዓን አባቶች ላይ አደጋ ለመጣል በተደረገውና በንብረት ውድመትና አባቶችን በማጎሳቆል እንዲሁም አፍኖ በመውሰድና በማስፈራራት በተፈጸመው ወንጀል ቤተ ክህነቱን የተቆጣጠረው የፓትርያርኩ “ቤተ ዘመዶች ቡድን” እንዲሁም በጉቦ የተገዙ “የመንግስት ደህንነት ሠራተኞች” እንደሚገኙበት ውስጥ አዋቂዎች እየተናገሩ ቢሆንም እስካሁን በወንጀሉ ተጠርጥሮ የተያዘም ሆነ የተመረመረ ሰውና ቡድን እንደሌለ ታውቋል።


“ሊቀ ኅሩያን” የሚል የማዕረግ ስም ተሰጥቶት ታላቁን የቤተ ክርስቲያኒቱን የሰበካ ጉባዔ ማደራጃ መምሪያ ሃላፊነት የተቆጣጠረው የፓትርያርኩ እህት ልጅ በሆነው በአቶ ያሬድ ከበደው መሪነት የሚንቀሳቀሰው የማፊያ ቡድን የተጠናከረና መሳሪያ የታጠቀ ሲሆን አደጋ በመጣልና በማስፈራራት ከዚህ በፊትም ልምድ አለው። ከዓመታት በፊት በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ሕጉ በቆመበት የአንድ ባህታዊ ነፍስ በጠፋባት ዕለት “ጥይቲቱን ያስወነጨፈው እርሱ ነው” እየተባለ ሲታማ የኖረው ያሬድ የቤተ ክህነቱ ቁጥጥር ክፍል ሀላፊ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱ የጀርባ አጥንት የሆነው የሰበካ ጉባዔ መምሪያ የበላይ ነው። ይህ መምሪያ በተወዳጁ መንፈሳዊ አባት በሊቀ ጉባዔ አባ አበራ በቀለ መሪነት ለአስርት ዓመታት ሲተዳደር የነበረ ሲሆን አባ አበራ ከፓትርያርኩ በደረሰባቸው መገፋት የሕክምና ርዳታ ሳያገኙ፣ በአንዲት ቆርቆሮ በቆርቆሮ ቤት ውስጥ ኖረው በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ሊለዩ በቅተዋል።

ስለ ረቡዑ አደጋ አስተያየት የጠየቅናቸው የቤተ ክህነት ሠራተኞች እንደሚናገሩት “እነ ያሬድ የጠሉትን ሰው በማንኛም መልኩ ከማጥቃት ወደ ሁዋላ” እንደማይሉ ገልጸው በዚህ ወንጀላቸው ደግሞ በመንግስት ደህንነት ውስጥ የሚሰሩ ወይም ይሰሩ የነበሩ ሰዎች እንደሚተባበሯቸው ተናግረዋል። ደህንነቶቹ ለምን በዚህ ወንጀል እንደሚሳተፉ ምክንያታቸውን የሚዘረዝሩት ውስጥ አዋቂዎቹ “ሰዎቹ በገንዘብ ይደለላሉ፣ የቤተ ክህነት ቤቶች ይሰጧቸዋል፣ ወይም ፓትርያርኩ የሥጋ ዘመዶች ይሆናሉ” ሲሉ አብራርተዋል።

በግንቦት 2001 ዓ.ም ለቅዱስ ሲኖዶስ በቀረበና የፓትርያርኩን አስተዳደራዊ በደሎችና ወንጀሎች በዘረዘረ አንድ መረጃ ላይ ፓትርያርኩ “በሙስናና በተለያዩ ከፍተኛ ችግሮች በደል ተገኝቶባቸው ከመንግሥት በግምገማ የሚባረሩ አካላትን ከጥፋታቸው ሳይታረሙ ከነችግራቸው በማቅረብ ቤተ ክርስቲያኒቱን የዘራፊዎች ዋሻ አድርገዋልታል፡፡” የሚል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበረ ታውቋል።

በርግጥም መንግስት የደህንነት ሃይሎቹ በፈለጉት መልክ ወንጀል ሲሰሩ ሊቆጣጠር የሚችልበት ዘዴ ከሌለው አገራችን የድህረ-አፓርታይድ ደቡብ አፍሪካ ዕጣ እየገጠማት ነው የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ ፈጥሯል። ፓትርያርኩ ከዚህ በፊትም የሚቃወሟቸውን ሰዎች በመንግስት ስም እንደሚያስፈራሩ ይታወቃል።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

>

“ብሩን መልስና ተመለስ ወደ እውነት” (ለንጉሴ ወ/ማርያም)


(ከደጀ-ሰላማዊው)
ዜና አስውቦ ማቅረብ ገንዘብህ ነበረ፣
አሁን ሐሰት ገዛህ ተከተተ ቀረ።
ቅንነት የሌለህ ለጥቅም የተጋህ፣
ለካስ ትንሽ ሰው ነህ ገንዘብ የሚገዛህ።
ወሬ ለአገር ላይጠቅም ሥልጣን ላያረጋ፣
ሰጪ እና ተቀባይ ሥራውን ዘነጋ።


ምን ነበረ ቢቀር ጉዳችሁ ባይወጣ፣
በአንድ መቶ ሺህ ብር የሚሊዮን ጣጣ።
አተርፋለሁ ብለህ ንጉሤ ተሞኘህ፣
ላትገፋው ጀምረህ ግብርህ አጋለጠህ።
ለእናት ኢትዮጵያ ተቆርቋሪ መስለህ፣
ዜና ስታሰማ ጉቦ በሉ ብለህ፣
ብዙ ጊዜ ሰማን የአንተ አድማጮች ሆነን፣
ዛሬ ተረኛ ነህ አንተ ደግሞ አድምጠን።
ይኼ ነው ንጉሤ አሰማኸን ብሥራት፣
አንተው ጉቦ በላህ የዜናው ባላባት።
ምን ዓይነት ሎተሪ ምን ዕጣ ገጠመህ?
“አባ ይፍቱኝ” ልትል ልትሳለም ሄደህ፣
መፍታቱን ተዉና እነሆ ጉድ ሠሩህ፣
በአንድ መቶ ሺህ ብር የፊጥኝ አሰሩህ።
ያለ ግብሬ ልግባ እንዲህ ከሆናችሁ፣
ሰጪና ተቀባይ እግዚአብሔር ይፍታችሁ።
የሰየምከው ጣቢያ “ሀገር ፍቅር” ብለህ፣
“ፀረ ሀገር” ተብሏል በቃ አድማጭም የለህ።
ሁለት ሞት አትሙት በጉቦ እና በሐሰት፣
ብሩን መልስና ተመለስ ወደ እውነት።
((ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 21/2009: ይህ ግጥም የተጻፈው ለሀገር ፍቅር ሬዲዮ አዘጋጅ፣ $10000 ዶላር ተቀብሎ አባቶችን በማንጓጠጡ በተቀየሙ አንድ ምእመን ነው።)

July 21, 2009

የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዝግጅት በቅንጭቡ፤ ኪነ ጥበባዊ ቅንብር በዳን


(ደጀ ሰላም፣ July 21/ 2009)

ማለቱ ከበደን ብጹዕ ቅዱስ ጳጳስ፣
በሙስና ወድቀው እኛም ስንታመስ፣
ከመቅደሱ አጠገብ የሰው ደምም ሲፈስ፣
በዱርዬ ሁካታ ቤተ ክርስቲያን ሲዳስ።


የቅዳሜ 7/17 /09 የኣሜሪካን ድምጽ አዲሱ አበበ ቃለ ምልልስ ያልሰማችሁ መስማት አለባችሁ:: ያኣሜሪካን ድምጽ አገልግሎት በነጻነት (freedom of press) ባለበት ላለን ሳይቀር አስተዋጾው ብዙ ነው::

ንጉሴ አክሊሉ የተናገሩትን ሰምቼ በቤተክርስቲያን አካባቢ እነኚህን የመሳሰሉ ካሉ የተስፋ ብርሃን ይዘው ይታያሉ; ማለት እንችላለን; መጽሀፋቸውን ገዝቼ እስካነብ ተቁነጥንጫለሁ።

ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አባ ማትያስ ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ክርስቲያን ሁሉ እና ቅዱስ ሲኖዶሱ የደረሱባቸውን ችግር በሚገባ ዘርዝረው ስላቀረቡ ሊመሰገኑ ይገባል:: የምስጋና የድጋፍ ደብዳቤ እንጻፍላቸው።
አገር ቤትም ላሉ ለሥርዓትና ቀኖና ቤተክርስቲያን ለቆሙና ለሚታገሉ ለብጹዓን ሊቀ ጳጳስት አባ ቄርሎስ;ጢሞቲዎስ ኢጺፋንዮስ ከነሱም ጋር ለቆሙ ሁሉ መጸለይና ማበረታታት ይገባናል።

ኒውዮርክ ያሉት በገንዘብ ማባከንና ስርቆት ከተከሱበት ለማሸሽ በአባ ጳውሎስ የተላኩትን አባ ዘካርያስ መልስ ስትሰሙ ታዝናላችሁ ከዛም ሳትወዱ ትስቃላችሁ::
ቅ.ዳዊት በም2 ቁ.4 ላይ እንዳለው እንዳይሆንም ትፈራላችሁ::

"በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ይስቃል
ጌታም ይሣለቅባቸዋል፣
ከዚያም በቁጣው ይናገራቸዋል፣
በመዓቱም ያስደነግጣቸዋል"

የቅዳሜ 7/17 /09 የኣሜሪካን ድምጽ አዲሱ አበበ ቃለ ምልልስ ንጉሴ አክሊሉ ያሰሙትን ቅኔ ደጋግሞ መስማት ትፈልጋላችሁ። ከቅኔአቸው ጥቂቱ

ሲከፋፍላቸው ሳጥናኤል እነአባን፣
ጌታችን ማዘኑ መቆጣቱ ገባን፣
ማለቱ ከበደኝ ብጹዕ ቅዱስ ጳጳስ፣
ሲፈታ እያየሁት መቃብሩ ሲማስ።

ንጉሤ አክሊሉ እንዳሉት የዚህ ቅኔ የባለ ቅኔው ስም አይታወቅም:

መላእክትሂ ጳጳሳት ባስልዮ ቴዎፍሎስ ክልዔቱ፣
ለሙሴ ቤተ ክህነት ቀበርዎ በሕይወቱ።

ከሃምሳ አመት በፊት የተደረሰ ነው በጊዜው የነበረውን በደል ለመግለጽ::

(እኔ ጨምሬበት ቅኔ ላልተማርን ቶሎ እንዲገባን)

(መላእክትሂ) ጳጳሳትነ ጳውሎስ ዘካርያስ ገብርኤል ወእስጢፋኖስ (ሌሎችንም ጨምር) ሃምስቱ/ተሰዓቱ፣
ለሙሴ ቤተ ክህነት ቀበርዎ በሕይወቱ።

ትርጉም

ሙሴ ቢሞት መላእክት (አክብረው) ቀበሩት
ጳውሎስ ዘካርያስ ገብርኤል ወእስጢፋኖስ (ሌሎችንም ጨምር)
ቤተ ክርስቲያናችንን በበደል በሙስና በሕይወት ቀበሯት::

ንጉሤ አክሊሉ እንዳሉት

ማለቱ ከበደኝ ብጹዕ ቅዱስ ጳጳስ
ሲፈታ እያየሁት መቃብሩ ሲማስ

እኔ ጨምሬበት

ማለቱ ከበደን ብጹዕ ቅዱስ ጳጳስ፣
በሙስና ወድቀው እኛም ስንታመስ፣
ከመቅደሱ አጠገብ የሰው ደምም ሲፈስ፣
በዱርየዬ ሁካታ ቤተ ክርስቲያን ሲዳስ።

ጳጳስ

(ቦጋለ ዳኜ ‐ ከካሊፎርንያ)

ጳጳስ እህል ይጥም እንጀራ ይበላ
በማይመስልበት ምድር በጦብያ በሞላ
የስድቡ ሲደንቀን ተቃጣበት ዱላ
በምጡ ዋዜማ እንጃ ካሁን ሁዋላ።

መስፍን ዘውድ ሊጭን ቄስ ዲያቆን ሊካን
እንዲህ በቀላሉ መች ተገኝቶ አቡን
አቡኑን ፍለጋ ሲጎርፍ ከያቅጣጫው
ስንቱን ደራሽ ወሃ አዞ እንዳልጨረሰው
በትረ ቃየል ሰጡት በትረ ሙሴን ትተው።

በ1940ዎቹ መጀመርያ በርካታ ጳጳሳት በመሾማቸው በጊዜው የነበረውን ደስታ ለመግለጽ፤
ስሬ መድሓኔዓለም ላይ በዓለ ሲመተ ጵጵስና ሲከበር፤ የታወቁት የቅኔ መምህር Aለቃ ጥበቡ ገሜ
የተቀኙትን መወድስ እስቲ እንመልከት። ቅኔውም ይመዝገብላቸው።*
--- ቦጋለ ዳኜ ‐ ከካሊፎርንያ

*መወድስ
“ይቤ ባስልዮስ በከመ ፈቀደ
ሃይለ ሥላሴ ይገብር ወዘከም ሀለየ ይፌጽም፤
አምጣነ አልቦ ዘይብሎ እምነገሥተ ኩሉ ዓለም
ዘንተ አህሰምከ።
ምክሩስ ለሀይለ ሥላሴ ነገዱ ለሴም
ይሄሉ ለዓለም።
ወይትቃወሞ በግብር መንበረ ዓመፃ ከዓዌ ደም።
ወቆሙ ጳጳሳት አእማደ ሰላም፤
ኢትዮጵያ ማእከሌኪ በየማን ወበጸጋም።
ወአመ ይዌውኡ ጸር ውሉደ መርገም፤
ኢታርምምኬ አልጋ ወራሽ ወልUል መኮንን ኢትጸመም።

(ጥበቡ ገሜ ዘስሬ መድሐኔ ዓለም፤ ሰላሌ)

የማፊያው ቡድን ድምጽ ንጉሴ ወ/ማርያም ፓትርያርኩ “ገንዘብ በመቀበል ጵጵስና ይሾማሉ” አለ


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 20/2009)

የዲሲው ንጉሴ ወ/ማርያም “ነገር አሳመርኩ፣ የተቀበልኩትን የቁልቢ ብር ተግባር ላይ አዋልኩ” ብሎ ፓትርያርኩን ከሥልጣናቸው ሊያወርዳቸው የሚችል ክስ አቀረበባቸው።

በዚሁ “አቡነ ፋኑኤልንና ሌሎች አባቶችን ለማዋረድ” ባቀረበው ፕሮግራም “በገንዘብ የተሾሙ” ያላቸውን ለመጠቃቀስ የሞከረ ሲሆን “ገንዘብ ተቀብሎ የሾማቸው ወይም ያስሾማቸው” ማን እንደሆነ ሳይናገር ቀርቷል። ስለዚህም ንጉሴ ይህንን “ታላቅ ምስጢር” ስለነገረን “ታንኪው’ እንለዋለን። ዝርዝር የፕሮግራሙን ጉዳይ የምንመለስበት ስለሚሆን በዚሁ እያቆየነው አንዲት ደጀ-ሰላማዊት (orthodoxawit) ካቀረቡት አስተያየት እንድትቋደሱ እንጋብዛችሁዋለን።

በነገራችን ላይ “የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪው ንጉሴ” መሳሪያ ታጥቆ እንደሚዞር፣ በዚህ ምክንያት ታስሮ እንደነበር ያውቃሉ?

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
ደጀ ሰላም

++++++++++++++++++++++++++++++++
The “Green minded” individuals: “ይህን የሚያደርግ ሰው ይህንንም የሚይዝ የሰው ልጅ፥ እንዳያረክሰው ሰንበትንም የእጁንም ክፋት ከማድረግ የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።” (ኢሳ 56-2)
(By Orthodoxawit )
For Christians the Sabbath day is a special day. Because of the greatness of what was done for us, Christians, dedicate this day to the worship our Lord who has saved us by grace. Blessing on this day comes from reserving oneself from wickedness. But we, laity of EOTC, in the Diasporas are not very lucky on this. There is always some thing that will ruin this blessed day and forces us to use our brains to think, our mouth to utter and our fingers to write.
The issue that made me write today is what I have heard on the Ethiopian media Hager Fiker Radio this weekend .This is for Ato Negusse ,questions on the your broadcast on June 19/09 and untainted advice for your service. This is presented to you with a direct quotation and paraphrasing of what you have said on June 19/09 program About Holy Synod. I would like weigh your analysis with your own expression፡ “የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ገበና አደባባይ እያወጡ”፣ “መንፈስ ቅዱሰ የተለየው ሲኖዶስ”።

As we all know the Holy Synod had weeks of dispute that had been settled unfairly and unwisely but I don’t believe it is appropriate to address the Holy Synod unholy as you have said. As an orthodox Christian by now you should know The Holy Synod is called Holy Synod with impartiality. It is the inheritor of the sit of the Holy Apostles there fore it is Holy. It is convention and an agreement to address it in this manner. The appointed head Bishop is called the Holy Patriarch and the rest Bishops. eg Coptic Holy Synod, Greek Holy Synod (United States of America cabinet is called The Cabinet that is naming convention to imply its uniqueness) So it is unwise to call Bishops “ለመንፈስቅዱስ የማይገዙትን አጋልጦና እርቃናቸውን አቁሞ” Surely we can use this on conditions of dogmatic heresy like that of Arius who was humiliated and condemned on the Council of Nicea.

“አንብሮተ እዱን አናታቸው ላይ አስቀምጦ በመንፈስ ቅዱስ የሚሾማቸው እና የሚያስተዳድራቸው ..ታላቁ ራስ ፓትሪያርካቸው ነው እነርሱ ራሳቸው የመረጡት ማለት ነው”። On this part you elaborated how the Holy Patriarch ordains Bishops by placing His hand on their heads. My first advice - even though I am no way an expert of Geez but I believe “አንብሮተ እድ” means placing hand or to place a hand so using it in conjunction with “ን አናታቸው ላይ አስቀምጦ” will make you a criminal in the Geeze world as our Fathers would say so I urge you to work more on your Geez before torturing the beautiful Holy language.

My Second advice and question comes after this statement you made seconds after the phrase I quoted above “እግዚአብሔር ሳይፈቅድ በመንፈስ ቅዱስ ሳይመረጥ የስልጣን ጥመኛ ሆኖ የሚገኝ አባል …” the rest I will not rephrase since it is unethical and unmanned even to quote. So according to you initially you said Bishops are appointed and ordained by the Holy Patriarch with the help of Holy Spirit so are you telling us the same Holy Spirit you mentioned makes mistakes(God Forbid) in appointing its ambassadors or are you telling us the Holy Patriarch makes mistake or even get backhander and bribes to appoint Bishop “ በዘመድ በጓደኛ በብልጣብልጥነት በራስ ፍላጎት ሰርገው የገቡ”.. So are you telling us the Holy Patriarch is corrupted enough that he sits ion the Holy chair and appoints Bishops based upon relationship and personal favor and self initiation.

Ato Nigusse your program has been full of contradiction please listen to it again and give your opinion on this I will present and reveal to you the rest and the final conclusion as God permits, tomorrow but I want you to be very care full on how you address the Holy Patriarch because some of your view are serious accusations that could led you great crimination in the face of both the Church and Social law.

ይቆየን

የሎንዶን ደ/ሰ/ቅ/ማርያም ሰበካ ጉባዔ በአባቶች ላይ የተፈጸመውን ወንጀል አወገዘ፣ “ገለልተኛው” መናገር ጀመረ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 20/2009)
በእንግሊዝ ሎንዶን ከተማ የምትገኘው የደብረ ሰላም ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ በቤተ ክርስቲያን በመፈጸም ላይ የሚገኘውን ጉዳይ በተመለከተ መግለጫ አወጣ፤ ፓትርያኩንም ተቃወመ። ለደጀ ሰላም በላኩት በበዚሁ ሁለት ገጽ መግለጫ ሰበካ ጉባዔው ከንዑሳን ክፍሎችም ጋር በመነጋገር ወደፊት ሰፊ መግለጫ እንደሚያወጣ ገልጿል። (ደጀ ሰላም በፒ.ዲ.ኤፍ የሚመጡ ነገሮችን የማስተናገጃ ዘዴ ስለሌላት ሙሉ መግለጫውን እዚህ እንዲመለከቱት እንጋብዛለን)።

የደብረ ሰላም ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን መግለጫ ራሱን “ገለልተኛ” እያለ የሚጠራው፣ ከአባ ጳውሎስ አስተዳደርም፣ ከ”ስደተኛውም” አይደለሁም ከሚለው ወገን ቅድሚያውን ሊይዝ ችሏል።

July 20, 2009

ሰበር ዜና (Breaking News) መንግሥት “ፓትርያርኩን ተቃወሙ” ያላቸውን ማነጋገር ጀምሯል


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 20/2009)

በቅርቡ በቅዱስ ሲኖዶስና በፓትርያርኩ መካከል በተፈጠረው ችግር “ፓትርያርኩን ተቃውመዋል”፣ በተለይም ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን ሰዎች መንግሥት በማነጋገር ላይ እንደሚገኝ ለመንግሥት ቅርበት ያላቸው ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ያለ ምንም መጥሪያ ወይም ስብሰባ ሰዎቹን ከተለያዩ ቦታዎች በመያዝ በሚደረገው በዚህ ምርመራ አከል ጥያቄና መልስ አሁን የተወሰነውን ውሳኔ ሕዝቡ እንዳይቃወም፣ እነርሱም በተቃውሞ እንዳይሰለፉ ሲናገሩ ተሰምተዋል።

በዚሁ የጅምላ ጥያቄና ምርመራ ከተጠየቁት መካከል የአስኮ ገብርኤል ፀሐፊ ቀሲስ ሰሎሞን ቶልቻ፣ የዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤተ ክርስቲያን ፀሐፊ መምህር ሰሎሞን በቀለ፣ መምህር ሱራፌል ወንድሙ፣ ባሕታዊ ሶፎንያስ፣ የልደታ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ቀሲስ ኃ/ገብርኤል፣ የጴጥሮስ ወጳውሎስ አስተዳዳሪ አባ ገብረ ሕይወት፣ የአራዳ ጊዮርጊስ አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ በቀለ እንዲሁም የቀጨኔ ቤተ ክርስቲያን ቁጥጥር ክፍል ኃላፊ መምህር ሽታ እና ሌሎችም እንደሚገኙበት ምንጮቻችን አብራርተዋል። ተመርማሪዎቹ “ለብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጋር ስላላቸው ግንኙነት ከመጠየቃቸውም በላይ ሕዝቡ ወደ ተቃውሞ እንዳይገባ እንዲያረጋጉ፣ ይህ ባይሆን ግን ለሚፈጠር ማንኛውም የሕዝብ ተቃውሞ ተጠያቂዎች እንደሚሆኑ ተገልጾላቸዋል ተብሏል።


እነዚሁ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ የተሰማሩና ለቤተ ክርስቲያን ባላቸው ቅንዓት የፓትርያርኩን ቤተ ዘመዳዊ አሠራር የተቃወሙ ሰዎች ለምን ማስፈራሪያ እንደሚደርስባቸው እንዳልገባቸው ተናግረዋል። ጉዳዩን የገለጽንላቸው የደጀ ሰላም ተባባሪ አባት እንደተነተኑት መንግሥት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ለመደገፍ ከመፈለግ ሳይሆን ጉዳዩ ከእጁ እንዳይወጣ ከመፍራት እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ መሆኑን ተናግረዋል። በርግጥም መንግሥት በዚህ አካሄዱ ከገፋበት “መንግሥት ከነቀዘው አስተዳደር ጋር ቆሟል ያሰኘዋልም” ብለዋል።

የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ተጠናቀቀ በተባለበት ወቅት ቅዱስነታቸው ባስነበቡት መግለጫ መጨረሻ ላይ “ሰላምና መረጋጋት” የምትለውን ቃል የተጠቀሙት የመንግስትን የልብ ትርታ ለማነሳሳትና ከራሳቸው ጎን ለማቆም በመፈለግ እንደሆነ ተንታኞች ይናገራሉ። የኢሕአዴግ መንግሥት መንበረ ሥልጣኑን ከተቆጣጠረበት ከ1983 ዓ.ም (1991) ጀምሮ በየዘማነቱ ከሚጠቀምባቸው ቃላት “ፋሽኑ ያላለፈባት” ብቸኛ ቃል ብትኖር “ሰላምና መረጋጋት” የምትለው መሆኗን ያስታወሱት ተንታኞች “በሰላምና መረጋጋት ስም የቤተ ክርስቲያናችን አጀንዳ ተዳፍኖ ሊቀር ይችላል” ብለዋል።

በዚህ በኩል ያሉ ሒደቶችን እየተከታተል እናቀርባለን፣ ተከታተሉን።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

“ፓትርያርኩ አሸነፉ” መባሉን አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ተቃወሙ፤ ሌሎች ደገፉ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 17/2009)

በቅርቡ የተጠናቀቀው የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ በተፈለገው መልኩ ባይሄድም “ፓትርያርኩ አሸነፉ” መባሉን ግን እንደማይቀበሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ገለፁ። ሌሎች ደግሞ ደገፉ:: እነዚሁ በክህነት አገልግሎትና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የተሰማሩ አስተያየት ሰጪዎች እንደተናገሩት ጉዳዩ ለጥቅምት የተቀጠረ በመሆኑ ፓትርያርኩን “አሸንፈዋል” ማለት እንደማይገባ አስረድተዋል።

ከተወሰኑት ውሳኔዎች መካከል የፓትርያርኩ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን መቀበል፣ የበላኢ ቅ/ሲኖዶስ እንጂ ፓትርያርኩ አለመሆናቸውን መቀበላቸው እንዲሁም ሥራ አስፈጻሚው ሥራውን እንዲቀጥል መፍቀዳቸው መልካም ዜናዎች መሆናቸውን የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ የአቡነ ሳሙኤልን አለመመለስ ብቻ ተመልክተን ፓትርያርኩን አሸናፊ ማድረግ አይገባም ብለዋል።


ይህንን የሚተቹ ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው አሁን በቤተ ክርስቲያን የተፈጠረውን ሁኔታ ለማሻሻል እድል ቢኖርም ውሳኔዎቹ ግን ከላኢ እንደተገለጸው ለቤተ ክርስቲያናችን መልካም ሆነው የሚገኙ አይደሉም ብለዋል። ሥራውን እንዲቀጥል የተፈቀደለት ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪነቱ ለፓትርያርኩና ለሥራ አስኪአጁ መደረጉ ትልቅ ውድቀት መሆኑን በአብነት ያነሳሉ።

እስቲ እናንተስ ምን ትላላችሁ?

የማፊያው ቡድን ድምጽ በአሜሪካ “ማጥቃት” ጀመረ፤ የቁልቢ ብር ሥራውን እየሠራ ነው


(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 19/2009)
• ንጉሴ ቅ/ሲኖዶሱን “የፓትርያርኩ ካቢኔ” አለው፣

የማፊያው ቡድን የውጪ ሀገር አንደበት የሆነው የዲሲው ሀገር ፍቅር ሬዲዮ ደጀ ሰላምን ሲሰድብ ዋለ። ከነገሩ ጋር በቀጥተኛ ግንኙነት ስሙ ያልተነሣው ነገር ግን እጅጋየሁ በየነን (ኤልዛቤልን) እና ግብረ አበሮቿን ቃለ ምልልስ በማድረግ አባቶችን ሲያዋርድ የሰነበተው ንጉሴ ወ/ማርያም ጥቃቱን በማጠናከር ቅ/ሲኖዶስን “የፓትርያርኩ ካቢኔ”፣ ፓትርያርኩ ሊያፈርሱትም ሆነ ሊገነቡት የሚችሉት ኮሚቴ እንደሆነ አድርጎ ሲያስረዳ ተሰምቷል።
For your information, follow this link about Negussie W/Mariam.


የማፊያው ድምጽ ተናጋሪ ንጉሴ ከዚህ በፊት $10 000 ዶላር የመቀበሉ ነገር በቅ/ሲኖዶስ ፊት መቅረቡና ፓትርያርኩም በዚህ ነገር መበሳጨታቸው፤ በዚህም ምክንያት የነገሩ አካሄድ ያላስደሰተው ንጉሴ በተለይም በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ መጀመሩ ይታወሳል። በቅርቡ ደጀ ሰላም ባቀረበችው ዜና ቅዱስ ፓትርያርኩ ራሳቸው በቀጥታ ከሚያዙበት የቁልቢ ገብርኤል ካዝና ከሁለት ሚሊዮን ያላነሰ ብር ማውጣታቸው መዘገቡ ይታወሳል። ምናልባት የቁልቢ ብር ዋሺንግተን ዲሲ ሳይደርስ እንዳልቀረ ተገምቷል።

የቅ/ሲኖዶስ አባላት ከፓትርያርኩ ጋር ከተለያዩባቸው ጉዳዮች አንዱ ፓትርያርኩ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አልቀበልም ማለታቸው፣ ቅ/ሲኖዶስም ተጠሪነቱ ለእርሳቸው እንደሆነ አድርገው ማቅረባቸው መሆኑ ይታወሳል። ፓትርያርኩ ቅዱስ ሲኖዶስን የበላይነት “ተቀብዬአለሁ” ቢሉም ንጉሴ ግን የጥንቱን ዜማ እስካሁን በማዜም ላይ ይገኛል። ንጉሴና እጅጋየሁ ቅ/ሲኖዶስ ሙሉ በሙሉ ባለመፍረሱ በመናደዳቸው “ይህንን አድርገውብናል” ያሏቸው ላይ ጥቃት ጀምረዋል። ሀገር ውስጥ የብፁዓን አባቶችን ቤቶች በመሰባበር፣ ጋዜጠኞችን በመደብደብና በማስፈራራት ሲንቀሳቀሱ በውጪ ደግሞ በንጉሴ ሬዲዮ አማካይነት ስም ማጥፋት ጀምረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቤተ ክህነቱ ጉዳይ ጦዞ አደባባይ ከወጣበት ከግንቦት 2001 ዓ.ም ጀምሮ ዜናውን ለምእመናን በማድረስ ላይ የምትገኘውን ብሎግ፤ ደጀ ሰላምን፤ አንድ ጊዜ የማህበረ ቅዱሳን ነው ሌላ ጊዜ ደግሞ የሌሎች ነው በማለት የማፊያው ቡድን በማስወራት ላይ ሲሆን ምእመናን እንዳያነቡና እንዳያዉቁ ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።

ብሎግ ማድረጋችንን (መጦመራችንን እንቀጥላለን)! ጭንቀታችን ስለቤተ ክርስቲያናችን እንጂ ስለነንጉሴና ማፊያው ቡድን አይደለም።

ቸር ወሬ ያሰማን!!
አሜን
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ለሀገር ፍቅር ሬድዮ
(ከአቤል ዘቀዳማዊ)
ይድረስ ለሀገር ፍቅር ሬድዮ አዘጋጆች፤የዛሬው የእለት ሰንበት ዝግጅታችሁ ተከታትዬዋለሁ። በእውነት ግን አቶ ንጉሴ እና ዶ/ር በላይ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ህግ እና ቀኖና ተቆርቃሪዎች ናችሁ ወይስ የቅዱስ ፓትሪያርኩ ህገ ቤተክርስቲያን ጥሰትን ተባባሪዎች? የህገ ቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ብትሆኑ ኖሮ ግን የቤተክርስቲያኒቷን ህግ እና ቀኖና የሚያፋልሱ ዝግጅቶች ባላቀረባችሁ ነበር። ለመሆኑ የጠቅላይ ሚኒስተር የካቢኔ አባላት እንዴት ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋራ በምሳሌነት ሊወዳደር ይችላል?እኔ አላውቀውም በእናንተ ዝግጅት እንደገለጻችሁት የጠቅላይ ሚኒስተር የካቢኔ አባላት የጠቅላይ ሚኒስተሩ ታዛዥ እና መመሪያ አስፈጻሚ ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል፤ ነገር ግን የኢ/ኦ/ተ/ቤተከርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያኒቱ የመጨረሻ ከፍተኛ ሥልጣን ባለቤት ነው። ህገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 5 እና 7
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፓትርያርኩም ጭምር ሊቃነ ጳጳሳት እና ኢጲስ ቆጶሳትን ያካትታል። ቅዱስ ሲኖዶስ የፓትሪያርኩን መመሪያ እና ትእዛዝ በመጠባበቅ ወይም በመከታተል የሚሰራ ሳይሆን ፓትሪያርኩ ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እና መመሪያ ተቀብሎ የማስፈጸም ግዴታ አለበት ይህም በህገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 8 እና 15 ተገልጾዋል። ስለዚህ እንደው በማያገባችሁ ነገር እየገባችሁ ህዝበ ክርስቲያኑን ግራ አታጋቡት፤ ተቆርቋሪነታችሁ ለህገ ቤተክርስቲያን ከሆነ ግን ህጉ ምን ይላል ብላችሁ አንብቡት። አንድ ተራ ምእመን ቤተክርስቲያኒቱ ስልጣን የሰጠቻቸውን ሊቃነ ጳጳሳትን መዝለፍ እንዲሁም በቤተክርቲያኒቱ አስተዳደራዊ መዋቅር ሥር እያገለገሉ የሚገኙትን ማኅበራትን የስም ማጥፋት ዘመቻ ቤተክርስቲያናችንም ስለሚያስነቅፍ እንደዚህ አይነት ከእውነት የራቀ ለማንም ምንም ጠቀሚታ የሌለው ዝግጅት ተገቢ አይደለም።
እግዚአብሔር እውነቱን ይግለጽላችሁ!!! አሜን

July 18, 2009

አንዳንድ ነጥቦች ስለ ሕገ ቤተ ክርስቲያን

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 18/2009)
(አቤል ዘቀዳማዊ እንደጻፈው)
እንግዲህ የዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የእናተው ዘገባ ካየሁ በኋላ፤ ከራሴ ጋር ብዙ ጥያቄዎች በማንሳት ተከራከርኩና ህገ ቤተ ክርስቲያንም ማገላበጥ ጀመርኩ ።
ከጥያቄዎችም መካከል፦
• የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግ ያውቁታል ወይስ አያውቁትም ?
• የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ያለባቸው ኃላፊነትስ በትክክል ተረድተውታል ወይ?
• ከዚህ በኋላስ ሊቃነ ጳጳሳቱ በምን ሞራል ነው ልጆቻቸው መባረክ የሚችሉት?
• ለቤተ ክርስቲያኒቱ ህግና ሥርዓት ተቆርቃሪዎች እውነተኞቹ ነገር ግን በቁጥር ትንሽ የሆኑት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እንዴት ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር ሊገናኙ ይችላሉ?

እስቲ ቅዱስ ፓትርያርኩም ሆነ ብዙዎቹ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የማይቀበሉት ህገ ቤተክርስቲያን ስለ ፓትርያርክ ስልጣንና ተግባር ምን ይላል? ለዚሁ ጥያቄ መልስ ለማግኘት በራሳቸው በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተቀባይነት ያላገኘውን ህገ ቤተክርስቴያን ካነበብኩት ላካፍላችሁ
1. ፓትርያርክ ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው (ሕገ ቤተክርስቲያን 1991)
2. ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስና የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባዎችን ይመራል
3. በቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ለብፁዓን ጳጳሳት የሊቀ ጵጵስና መዓረግ ይሰጣል
4. ለታላላቅ ገዳማት አበ ምኔቶችና በሀገረ ስብከቱ ለተመረጡ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች የመዓረግ ስም ይሰጣል
5. ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጡና የተላለፉ ሕጎች፤ ደንቦች፤መመሪያዎችና ልዩ ልዩ ውሳኔዎች በተግባር መዋላቸውን ይከታተላል
የፓትርያርክ ከስልጣን መውረድስ ህገ ቤተክርስቲያን ምን ይላል?


ፓትርያርኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ከተሾመ በኋላ የተቀበለውን ኃላፊነት በመዘንጋት፦
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት የሚያፋልስ፤ቀኖና ቤተክርስቲያንን የሚያስነቅፍ ተግባር ፈጽሞ ከተገኘ
• በፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ አምስት ከቁጥር 172 እስከ 208 በተደነገገው መሰረት በደለኛ ሆኖ ከተገኘ
• በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በ1991 በወጣው ሕገ ቤተክርቲያን አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ ሰባት መሰረት በተሾመበት ቀን የገባው ቃለ መሐላ ያልጠበቀ እንደሆነ
በአጠቃላይ ታማኝነቱ፤መንፈሳዊነቱና አባትነቱ በካህናትና በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት ያጣ ሆኖ ቤተክርስቲያንን የሚያስነቅፍ መሆኑ በትክክል ከተረጋገጠ ከስልጣኑ ይወርዳል። በሱ ምትክም ሌላ ተመርጦ ይሾማል። ፓትርያርክ እስኪሾም ግን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ይመረጣል። የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣው ሕገ ቤተክርስቲያን 1996 አንቀጽ 16
ሕገ ቢተክርስቲያን ይህ ሆኖ ሳለ የአሁኑ ፓትርያርክ ከላይ የተጠቀሱት ህጎች ሁሉ እያፈረሱ፤ እኛም እያየነቸው የቅዱስ ሲኖዶሱም አባላት እያዩዋቸው እስካሁን ድረስ በዝምታ ታልፈዋል። ከዚ በኋላስ መፍትሔው ምንድ ነው? ተስፋ ቆርጦ መተው ወይስ ከጥቂቶቹ ለሕገ ቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ አይዞዋችሁ እኛም ከጎናችሁ ነን በማለት መስራት? መልሱን ለውድ ደጀ ሰላማውያን/ት በመተው አንድ ነገር ግን ላሰምርበት እወዳለሁ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን በፓትርያርክ ላይ ፓትርያርክ የሚል ህግም ደንብም የላትም።
እግዚአብሔር ተዋህዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን

ስለ ቅ/ሲኖዶስ ስብሰባዎችና ውሳኔዎች ሒደት የአዲስ ነገር ጋዜጣ ልዩ ሪፖርታዥ

ቅዱስ ሲኖዶስ ፓትርያርኩ በሥራ አስፈጻሚው ላይ የጣሉትን እግድ እንዲያነሱ ውሳኔ አሳለፈ፤ ወሳኙን አጀንዳ ለጥቅምት ቀጠረ
(ቅዳሜ ሐምሌ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. July 18, 2009)
• አንድ ጳጳስ በለሊት ደህንነት ቢሮ ተወሰዱ፣
• የጳጳሳት መኖሪያ ቤት በምሽት ተደብድቧል፣
• ፓትርያርኩ ሕገ ቤተክርስትያን አላውቅም አሉ፣


መነሻ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ የሚያስተዳድሩት ቤተክርስቲያን ሙስና ተንሰራፍቶበታል፣ ቤተክርስቲያኒቱ የምትመራው ጉዳዩ በማይመለከታቸው ሹማምንትና፣ ቀደም ሲል የአርቲስት መሐሙድ አህመድ ባለቤት የነበሩት፣ ከደረግ ዘመን ጀምሮ ስማቸው አንድም ግዜ በበጎ የማይነሳውና በአሁኑ ግዜ የፓተርያርኩ የቅርብ አማካሪ በሆኑት ወ/ሮ እጅጋየሁ በተባሉ ግለሰብ ነው፣ ፓትርያርኩ ያልወደዱት ወይም ያልተደሰቱበት ጳጳስ ወይ የቤተክርስቲያን አገልጋይ በእኚህ ሴት አማካኝነት ስሙ እንዲጠፋ፣ እንዲወገዝና በቅጥረኞች ማስፈራሪያ እንዲደርሰው ይደረጋል።

በተጨማሪም ቤተክርስቲያቱ በፓትርያርኩ ዘመዶች የተሞላና የእነሱ ጥቅም ማስፈጸሚያ ሆኗል በሚል የሲኖዶሱ አባላት በተደጋሚ ምሬታቸውን ሲገልጹ መቆየታቸውን መረጃዎች ያስረዳሉ።

ይህንንም በስብሰባ ላይ የተናገረ ጳጳስ በግልም ሆነ በቡድን ማስፈራት የሚደርስበት ሲሆን አብዛኛዎቹ የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት የሆኑ ጳጳሳት የቻሉትን እየሞከሩ በትዕግስት ቆይተዋል።

የአቡነ ሳሙኤል መምጣትና ለውጡ

አቡነ ሳሙኤል በዋልድባ ገዳም ውስጥ መነኩሴ የነበሩ ሲሆን አዲስ አበባ በመምጣት ቤተክርስቲያኒቱን እያገለገሉ የቀለም ትምህርታቸውን ዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት በመማር ራሳቸውን ካሻሻሉ በኋላ ያሳዩት ለውጥና ችሎታቸው ታይቶ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ጸሐፊ ሆነው ይሾማሉ። በዚህ የሹመት ግዜ ፓትርያርኩ ወደ ሥልጣን እንዲመጡ ከተባረሩርት አምስት ሰዎች መካከል አንዱ ሲሆኑ፣ ፓትርያርኩ ሥልጣን ላይ ከወጡም በኋላ አብረው በመስራት ቤተክርስቲያኒቱ እንድትለወጥ ጥረት ሲያደርጉ ነበር።

ፓትርያርኩ መንበረ ሥልጣናቸውን እየተለማመዱ ሲመጡና ዘመዶቻቸውን ወደቤተክርስቲያኒቱ በማምጣት የግልንና የቤተሰብ ጥቅም ማስጠበቅ ሲጀምሩ እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊ ሥራ እየተበላሸ ሲመጣ አቡነ ሳሙኤል ሙግት ጀመሩ። ሙግቱ ያልተስማማቸው አቡነ ጳውሎስ አባ ሳሙኤልን ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅት አንስተው የብስራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ አድርገው ሾሟቸው። ውሳኔውን ያልተቀበሉት አቡነ ሳሙኤልም በዛው ሳምንት ወደ አሜሪካ አገር በማቅናት ለአስር ዓመታት ራሳቸውን በትምህርት ሲያደራጁ ቆይተው የተለያዩ ትምህርቶችን ከተማሩ በኋላ ወደ አገራቸው በመመለስ ተመልሰው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራአስኪያጅ ሆነዋል። በሥራ አስኪያጅነታቸው ያሳዩት የሥራ ተግባር በሲኖዶሱ ተደንቆላቸው የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ሆነውም ተሹመዋል።

የአቡነ ሳሙኤልና የፓትርያርኩ የጸብ መነሻ

ቅዱስ ሲኖዶሱ ቋሚ ሲኖዶስና ሙሉ ሲኖዶስ ተብሎ በሁለት ይከፈላል። ቋሚ ሲኖዶሱ ሦስት ጳጳሳት ያሉት ሲሆን 51 የሀገረ ስብከት ሊቀጳጳሳት ያሉት ሙሉ ሲኖዶሱ በስብሰባ ያሳለፈውን ውሳኔ ተቀብሎ የሚሰራ ሲኖዶ ነው። ሙሉ ሲኖዶሱ በየሦስት ወሩ ወይም አስቸኳይ ስብሰባ ሲጠራ የሚሰበበሰብ ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የምትመራውም ይህ ሲኖዶስ ሕገ-ቤተክርስቲያኑን መሠረት በማድረግ ለሚያሳልፈው ውሳኔ ተገዢ በመሆን ነው።

ነገር ግን ፓትርያርኩ በራሳቸው መንገድ የሚያሳልፉትን ውሳኔ በተለያየ መንገድ ተፈጻሚ በማድረግ ሲኖዶሱን ሲያዋርዱና ሲዘልፉ ጳጳሳቱን ሲሻቸው በገንዘብ እየደለሉ፣ አሊያም በማስፈራራት ወይም በማገድ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል። ነገር ግን አቡነ ሳሙኤል የአዲ አበባ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ከሆኑ በኋላ ገጥሟቸው የማያውቅ የማይገዳደሩት ጠላት እንደመጣባቸው በማመን በአባ ሳሙኤል ላይ ወታደሮቻውን አሰማሩባቸው።በከፍተኛ ደረጃም የአሉባልታ ዘመቻ አወረዱባቸው።

የኢትዮጵያ ሚሊኒየም (2000)

ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያውያንን ሚሌኒየም እንዴት ታክብር በሚለው ሐሳብ ላይ ሲኖዶስ ከተስማማ በኋላ ኮሚቴ ይቋቋማል የኮሚቴው ሰብሳቢም አቡነ ሳሙኤል ሆነው ይሾማሉ ይህ ያላስደሰታቸው አቡነ ጳውሎስ እንደለመዱት ወታደሮቻውን በአቡነ ሳሙኤል ላይ ያሰማሩባቸዋል። በወቅቱም አቡነ ሳሙኤል ለ15 ቀናት ስብሰባ እስራኤል አገር ሄደው በነበሩበት ወቅት ፎቷቸው በታተመበት በራ ወረቀት ላይ “የሚሊኒየሙ አባት” የሚል ጹሑፍ በመጻፍ ልክ አቡነ ሳሙኤል በደጋፊዎቻቸው አማካኝነት የበተኑት አስመስለው ጸብ ይቀሰቅሳሉ። ሚሊኒየሙን ለማክበር የተቋቋመው ኮሚቴ ሰብሳ ምም ሳይሰሩ የራሳቸውን ፎቶ አትመው “የሚሊኒየሙ አባት” በሚል ጹሑፍ በተኑ ሲሉ አብጠለጠሏቸው ኮሚቴው መፍረስ አለበት ብለው በመወሰን ኮሚቴውን አግደው ወ/ሮ እጅጋየሁ ከነግብርአበሮቻው ያሉበት ኮሚቴ እንዲቋቋም ተደረገ።

ይህ ኮሚቴም በአባ ሳሙኤል ከሚተዳደሩት የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ደብራት እያንዳንዳቸው 10 ሺሕ ብር በማውጣት የፓትርያርኩን ፎቶ አሰርተው እንዲለጥፉ ትዕዛዝ አስተላለፈ። ሐመር መኪና ተገዝቶ ሽልማት እንዲሰጣቸውም አስገዳጅ መዋጮ ጠየቀ። አባ ሳሙኤልም በዚህ ጉዳይ ላይ እሺ አላሉም፤ በየገጢሩት ስንት የተጎሳቆሉ ቤተክርስቲያናት ባሉበትና የኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት በወደቀበት በዚህ ሁኔታ እንዲህ ያለ መዋጮም አይደረግም የፓትርያኩ ፎቶ በየደብሩ እዲሰቀልም ሕገ ቤተክርስቲያ አትፈቅድም ሲሉ ክልከላ አደረጉ። በዚህ ውሳኔያቸውም ጥርስ ውስጥ ገቡ።

የጸቡ መፋፋም

ቅዱስ ሲኖዶሱ የፓትርያኩ አምባገነንት ሲበዛበት፣ የቤተክርስቲያኒቱ መዝበራ ሲበፋፋም፣ ዕድገቷ ተቋርጦ ቤቱ ሙስና የሰፈነበትና ተቆጣጣሪ የሌለው የዘመድ ቤት ሲሆን አንድ ውሳኔ አሳላፈ። ፓትያርኩ በማንኛውም አስተዳደራዊ ሥራ ውስጥ ጣልቃ እንዳይገቡ የሚከለክልና አስተዳራዊ ሥራን የሚሰራ ከሲኖዶሱ ጳጳሳት ውስጥ ሰባት አባቶች ያሉበት አንድ ኮሚቴ ከግንቦት 6 ቀን እስከ ግንቦት 13 ቀን አድርጎት በነበረው ስብሰባ አቋቋመ።

የመንፈሣዊ ኮሌጁ ደን አቡነ ጢሞቲዎስ የኮሚቴው ሰብሳቢ፣የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ ሳሙኤል ጸሐፊ እንዲሁም፤የሐዋሳ ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ ፋኑኤል፣የጅማ ሐገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ እስጢፋኖስየአዳማ ሀረገ ስብከት ጳጳስ አቡነ ጎርጎሪዮስ፣ የደሴ ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ አትናቲዮስ እናየከንባታና ሀዲያ ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ መልጸዲቅ የሥራ አስፈጻዊ ኮሚቴው አባላት ሆነው ተሾሙ።

ኮሚቴው ሥራውን እንደጀመረ የተከፈተበትን የአሉባልታ ዘመቻ ወደጎን በመተው ሲንቀሳቀስ የቆየ ሲሆን ጸቡ አደባባይ እንዲወጣ መነሻ ምክንያት ከሆኑት ጉዳዮች አንድ ውሳኔ አሳለፈ። ውሳኔው ፓትርያርኩ ከሲኖዶሱ እውቅና ውጪ ጉዳዩ የማይለከታቸውን የቤተክርስቲያን ሹማምት ሰብስበው ወደጣሊያን ጉዞ አደረጉ። በዚህ ጉዞ ወቅትም በኋላ ላይ ማስተባበያ ቢሰጡም በኢትዮጵያ “ታቦተ ጽላት ይታያል” ብለው መግለጫ ሰጡ ይህንኑ የውጭ ሚዲያዎች አስተጋቡ።

ፓትርያርኩ ከጉዞ ሲመለሱ ስለአካሄዳቸው ማብራሪያ እንዲሰጡ ከኮሚቴው ተጠየቁ። እንዴት እጠየቃለሁ ሲሉም ዘራፍ አሉ። በመካሉ አቡነ ሳሙኤል ጽዮን ግርማ ከተባለች የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አዘጋጅ ጋራ ቅዳሜ ግንቦት 25 ቀን 2001 ዓ.ም. በወጣው ጋዜጣ ላይ ሰፋ ያለ ቃለምልልስ ሰጡ። በቃለምልልሱም ወቅትም ለአንድ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ቤተክርስቲያን ከቴክኖሎጂው ጋር እኩል በመራመድ ወጣት ምዕመናንን መሳብ አለብን ከሚለው መነሻ ሃሳብ ተነስተው በኢንተርኔት ስርአተ ቅዳሴን መከታተል ይቻላል የሚል መልዕክ አዘል ቃለ ምልልስ ሰጡ። በጉዳዩ ላይ በሳምንቱ ማብራሪያ ሰጡ።ይህ ያልተዋጠላቸውና በአጋጣሚው አቡነ ሳሙኤልን አውግዘው ከሥልጣን ማውረድ የሚፈልጉ አሉባልታውን ተያያዙት።

ወ/ሮ እጅጋየሁም በሌላት የቤተክርስቲያን እውቀት አቡነ ሳሙኤልን አብጠልጥላ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ጻፈች። በዚህ የተበሳጩ ሌሎች ግለሰቦችም በጉዳዩ ላይ ወ/ሮ እጅጋየሁ ሌላ ሰው አጽፈው በስማቸው ያወጡትን ጹሑፍ ተቃውመው ተጨማሪ አስተያየቶችን ሰጡ። ጉዳዩን በሚመለከትም ምንም አይነት አስተያየት እንደማያስተናግዱ በመግለጽ ዘጉት።

አቡነ ጳውሎስ በዚህ የተናደዱ ይመስላል ጋዜጠኞችን ሰብስበው “አባ ሳሙኤል በኢንተርኔት ማስቀደስ ይቻላል ብለው ቤተክርስቲያኒቱን አዋርደዋል” በማለት አብጠለጠሏቸው። ማምሻውንም ሲኖዶሱ ላቋቋመው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ለአባ ሳሙኤል የእግድ ደብዳቤ አስተላለፉ።

የሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ

አቡነ ሳሙኤል ደብዳቤው እንደደረሳቸው በሕገ ቤተክርስቲያን መሰረት የሾማቸው ሲኖዶሱ በመሆኑ ሊያግዳቸውም የሚችለውም ሲኖዶሱ መሆኑን በመጥቀስ እግዱን እንደማይቀበሉት ገልጸው ደብዳቤ ጻፉ። ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶሱም በአስቸኳይ ተጠራ። አቡነ ጳውሎስ ሲኖዶሱን እኔ አልጠራሁም በማለት ለማንገራገር ቢሞክሩም ጳጳሳቱ የማይሰበስቡን ከሆነ እኛ ራሳችን እንሰበሰባለን በማለታቸው ፍርሃት ስላደረባቸው ሲኖዶሱን ሰብስበውታል።

ማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን 2001 ዓ.ም.

የተጠራው ሙሉ ሲኖዶስ ለስብሰባው በቤተክነት ቅጥር ግቢ ባለው መሰብሰቢያ አዳራሽ ከጠዋት ጀምሮ ቢሰባሰብም ከመካረር ውጭ ምም መፍትሄ ሳያበጅ አቡነ ጳውሎስም እግዱን በሚመለከት የቀረቡትን መወያያ አጀንንዳዎች አልቀበልም በማለታቸው ያለምም ውጠጤት ተበትኗል።

ረቡዕ ሐምሌ 1 ቀን 20001 ዓ.ም.

በዚህ ዕለት ጳጳሳቱ እጅግ ተቆጥተው ፓትርያርኩ ኮሚቴውንም ሆነ አባ ሳሙኤልን ያገዱት ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጭ ሆነው ነው። የሳቸው ተጠሪነት ለሲኖዶሱ ነው ጳጳሳት መሾምም ሆነ ማገድ የሚችለው ሲኖዶሱ እንጂ እሳቸው አለመሆናቸውን በመጥቀስ ስህተት መስራቸውን አምነው ይቅርታ እንዲጠይቁና እግዱን እንዲያነሱ ይጠይቋቸዋል።

“ይህን በፍጹም አልቀበልም እንደውም እንዲህ ያለ ሕገወጥ ስብሰባ አልመራም” በማለታቸው፤”ስብሰባውን የማይመሩ ከሆነ አዳራሹን ለቀው ይውጡልን” በማለት ጳጳሳቱ ቢጠይቋቸውም “አልወጣም የምትሉትን እዚሁ ቁጭ ብዬ እሰማለሁ” በማለታቸው 41 የሚሆኑ ጳጳሳት ሰብሰባውን ረግጠው በመውጣት ለብቻቸው በሌላ አደራሽ ተሰባስበዋል።

ለብቻው ተሰብስው በደረሱበት ድምዳሜም ፓትርያርኩ ያሳለፉት የዕግድ ውሳኔ ሕገ ቤተክርስቲያንን የተከተለ ባለመሆኑ እግዱ እንዲነሳ እሳቸውን በተመለከተ የአስተዳደር ስራውን ጨርሶ መስራ ስላልቻሉና ቤተክረስቲያኒቱን ወዳልተፈለገና ፍጹም ወደተበላሸ አቅጣጫ እየወሰዷት በመሆኑ ከጸሎት ውጭ በማንኛውም አስተዳደር ስራ እዳይገቡ እንደራሴ ሊሾምባቸው ይገባል በሚል ውሳኔ ላይ ደርሰው ይህን ውሳኔ ለማጽናት ለአዳሪ ቀጥረው ተለያይዋል።

ሐሙስ ሐምሌ 2 ቀን 2001 ዓ.ም.

ከጠዋቱ አንድ ሰዓት አቡነ ሳሙኤልን ወደ ቢሮአቸው ከዛም ወደ ሲኖዶሱ ስብሰባ ሊወስዳቸው የመጣው ሹፌራቸው ቁልፍ ተቀምቶ አቡነ ሳሙኤል ከሚኖሩበት የመንፈሣዊ ኮሌጁ ግቢ መኖሪያቸው እንዳይወጡ በሦስት ሲቪል በለበሱ ወጣቶች ታግተው ዋሉ። ቀኑን ሙሉ ማን ወደሳቸው ግቢ አይገባም ማን እንዲወጣ አልተፈቀደለትም። ፓትርያርኩ በተመሳሳይ ሁኔታ አይታገዱ እንጂ እሳቸውም ወደሲኖዶሱ ስብሰባ እንዲገቡ አልተፈቀደላቸውም። ይህ የተደረገውም ሲኖዶሱ ነፃ ሆኖ ውሳኔውን እዲያሳልፍ ታስቦ እንደሆነ ተገልጾላቸው በማግስቱ እገታው ተነስቶ ሁለቱም ስብሰባ እንዲገቡ ተደረገ።

አርብ ሐምሌ 3 ቀን 2001 ዓ.ም.

ስብሰባው የተመራው እንደወትሮ በፓትርያርኩ ሳይሆን በከፍኛ የመንግሥት ባለሥልጣን አባይ ፀሐዬ ነበር። እንዲሁም ኮሚሽነር ወርቅነህ ገበየሁና ሌሎች ሁለት ባለሥልጣናት ስብሰባውን አጅበውት ውለዋል።

መንግሥት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው በመግለጽም ቤተክርስቲያኒቷን ወደ ሰላም ለማጣት ሕገቤተክርስቲያኒቷንና የሲኖዶሱን ውሳኔ አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ሲኖዶሱም ተሰብስቦ ይበጃል ያለውን ውሳኔ እንዲያሳልፍ መክረው ስብሰባው በተረጋጋ መንፈሥ ሰኞ ዕለት እንዲቀጥልና ይበጃል ያለውን ውሳኔ እንያሳልፍ አሳስበው ተለያይተዋል።

ሰኞ ሐምሌ 6 ቀን 2001 ዓ.ም.

ጳጳሳቱ አርብ ዕለት በተሰጣቸው ተስፋ ስብሰባው በተረጋጋ መንፈሥ ይቀጥላል የሚል ስሜት የነበራቸው ቢሆንም ፓትርያርኩ ምም የተለየ መሻሻል ሳያሳዩ በአቋማቸው በመጽናት በቀዳሚነት አጀንዳ ተይዞ የነበረውን የሥራ አስፈጻሚውን እግድ አላነሳም በማለት አሻፈረኝ አሉ።

ሲኖዶሱ የሾማቸውን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከሕገ ቤተክርስቲያን ሕገ ደንብ ውጪ ለም ታገዱ የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አቡነ ጳውሎስ፤ኮሚቴው የተሰየመው መተዳደሪያ ደንብ አቅርቦ ከሐምሌ 5 ቀን 2001 ዓ.ም. በኋላ ለሲኖዶሱ እንዲያቀርቡ እንጂ ከዛ ውጭ እየተሰበሰቡ የፈለጉትን ውሳኔ ለማሳለፍ ባለመሆኑ መተዳደሪያ ደንቡን አዘጋጅተው ሳያቀርቡ በሱ ጉዳይ ላይ በስብሰባው መነጋገር እንደማይፈልጉ ፓትርያርኩ በመናገር ምላሽ መስጠታቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል።

ሊቃነ ጳጳሳቱ መተዳደሪያ ደንቡን አዘጋጅተው መጨረሳቻን ኮሚቴው በስብሰባው ላይ ሲገልጹ፤ፓትርያርኩም ቀበል ብለው ስራችሁን ስለጨረሳችሁ መተዳሪያ ደንቡ ወደ ሕግ ክፍሉ ተመርቶ ይመርመር ይላሉ። ጳጳሳቱም ሲኖዶሱ ከላይ መተዳሪ ደን አውጥቶ ያስተዳራል እንጂ ወደታች ልኮ ሕግ አያጸድቅም መተዳደሪያ ደንቡ ተመርምሮ መታየት ካለበትም ገለልተኛ የሆነ የውጭ ኮሚቴ እንዲያየው መደረግ እንዳለበት በመግለጽ ተከራክረዋቸዋል።

ዋናው ጉዳይ መተዳደሪያ ደንቡ ሳይሆን መጀመሪያ ከሲኖዶሱ እውቅና ውጭ የተደረጉ እግዶች ይነሱ የሚለው ነው በሚል ጠንካራ መከራከሪያ በማቅረብ ቢሞግቷቸውም ፓትርያርኩ በጀ የሚሉ ሆነው አልተገኙም።

ሲኖዶሱም እንደሌሎች ስብሰባዎች ውሳኔን የሚያሳልፈው በድምጽ ብልጫ በመወሰን ሳይሆን ሁሉም በመተማመን ውሳኔ በመሆኑ ሊስማሙ ባለመቻላቸው በዕለቱ ተሰብስበው ከነበሩት 39 ጳጳሳት 26ቱ እንግዲያው ስብሰባው ስናደርግ ከመንግስ ታዛቢ ይኑርልን በማለት ለማግስቱ ቀጠሮ በመያዝ ስብሰባውን ጥለው ወጥተዋል።

በማግስቱ የወጣው ሪፖርትር ጋዜጣ “የመንግሥት ባለሥልጣናት በሰጡት ማሳሰቢያ መሠረት፣ 39 የሲኖዶስ አባላት ከትናንት በስቲያ ሐምሌ 6 ቀን 2001 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ የስብሰባ አዳራሽ ተሰብስበው የነበረ ቢሆንም፣ በማግስቱ፣ ትናንት በተነሳ ነጥብ ባለመስማማታቸው፣ 13 ሊቃነ ጳጳሳት ስብሰባውን አቋርጠው መውጣታቸውንና ጉዳዩ በጠረጴዛ ዙሪያ ሊፈታ ባለመቻሉ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ መጠየቁን ምንጮች ለሪፖርተር ጋዜጣ ገለፁ።” በማለት ጥለው የወጡትን ጳጳሳት ቁጥ ወደ 13 ዝቅ በማድረግ ፍጹም የተሳሳተ ዘገባ ይዞ ወጣ።

ዕረቡ ሐምሌ 7 ቀን 2000 ዓ.ም.

ከፌደራል ጉዳዮች ሚንስትር የምግስት ተወካይ የተላከለት ሲኖዶሱ በታዛቢ ፊት ስብሰባው የተከናወነ ሲሆን ለዕለቱም ተይዞ የነበረው አጀንዳ ፓትርያርኩ ሥራ አስፈጻሚው ላይ የሰጡት የእግድ እርምጃ ይነሳ የሚል ነበር። እንደሰሞኑ ሁሉ በዕለቱ ፓትርያርኩ ግትር ሆነው የቆዩ ሲሆን ጳጳሳቱ በአንድ ድምፅ እየለኑ፣ እያግባቡና እየተቆጡ ለማሳመን ቢሞክሩም አሻፈረኝ ብለው ቆዩ።

በኋላ ማምሻውን ከመንግሥት ተወካይና ከጳጳሳቱ ሕገቤተክርስቲያን እዲያከብ ሲጠየቁ “እደውም ሕገ ቤተክርስቲያን የሚባል ነገር አላውቅም”በማለት ለሲኖዶሱ አስደንጋጭ ንግግር ተናግረዋል።

በዚህ ወቅት አንድ ጳጳስ “እኔ እየገባኝ እንዳለው እኚህ ሰውዬ ሕገ ቤተክርስቲያኑ የማወቅ ያለማወቅ ጉዳይ አይደለም። እዚህ ብንጨቃጨቅ ዋጋ የለውም። አሟቸው ሊሆን ስለሚችል ሆስፒታል እንውሰዳቸው።” ብለዋል።

ሌሎቹም ጳጳሳት ሕገቤተክርስቲያን የማያውቁ ከሆነ ፕትርክናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው እንዲለቁ በማለት ጠንካራ ወቀሳ ሲሰነዝሩባቸውና እንዳውም ለዚህ አባባላቸው ተንበርክከው ይቅርታ ካልጠየቁ ሲኖዶሱ የሚያሳልፈው ውሳኔ ከባድ እንደሆነ በመግለጽ ገስጸዋቸዋል። በዚህ ግዜም እንደተባሉት ሳይንበረከኩ ወንበራቸው ላይ እንደተቀመጡ ሕገ ቤተክርስቲያንን አከብራለሁ እግዱን አንስቻለሁ በማለት እግዱን አንስተዋል። በማግስቱም አቡነ ሳሙኤል ላይ የሰጡትን እግድ እንዲያነሱ በሚጠይቀው አጀንዳ ላይ ለመወያያት ቀጠሮ ሰጥተው ተለያይተዋል።

ረቡዕ ሐምሌ 7 ቀን 2000 ዓ.ም. ከምሽቱ አራት ሰዓት

ለስብሰባም ሆነ ለሌላ ጉዳይ ጳጳሳቱ ከየሀገረ ስብከታቸው ሲመጡ የሚያርፉበት ቤት የሚገኘው አምስት ኪሎ ባለው የጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ባለ ሕንጻ ውስጥ ነው።

በዕለቱ አካባቢው የመብራት ተረኛ በመሆኑ መብራት አልነበረም ጀነሬተሩም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ጠፍቷል። ልክ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ በህንፃው ላይ የሚገኙት የከምባታና ሃዲያ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ፣ የአቡነ ኢጲፋኒዮስ፣ የአቡነ ሉቃስ፣ የመንፈሣዊ ኮሌጁ ዲን አቡነ ጢሞቲዎስ፣ የሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ጳጳስ የአቡነ ቄርሎስ በር እኩል መደብደብ ይጀምራል በኃይለቃል ድምጽም እንዲከፍቱ ይጠየቃሉ ሁኔታው ያላማራቸውና ጭለማው ፍርሃት የፈጠረባቸው ጳጳሳት ለፖሊስ ስልክ ይደውላሉ ግን የደረሰላቸው አልነበረም። በር ላይ ላሉት ጥበቃዎች በመደወል ድረሱልን በራችን እየተደበደበ ነው የሚል ጥሪ ያሰማሉ መጣን ከማለት ውጭ የሚመጣላቸው ያጣሉ። ቤታቸው አጠገብ ላጠገብ ቢሆንም ደፍሮ የሚወጣ አልተገኘም። እርስ በርሳቸው ባደረጉት የስልክ ልውውጥ ከሳሎኖቻው ወጥተው መኝታ ክፍላቸው ለመግባት ተመካክረው ወደየመኝታ ክፍላቸው ይገባሉ። የሌሎቹ ጳጳሳት በር አልከፈት ሲል የሰሜን ወሎው ሀገረስብከት ጳጳስ የአቡነ ቄርሎስ በር ግን ተሰበረ። አቡነቄርሎስ መኝታ ክፍላቸው ገብተው የሚመጣውን ሲጠባበቁ፤ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች የመኝታ ቤቱን በር እየደበደቡ “ትከፍታለህ ክፈት” በማለት ስድብና ዘለፋን በመሰንዘር የመኝታ ቤታቸውን በር መደብደብ ይጀምራሉ በመጨረሻም ያሰማራቸው ሰው እዲመለሱ ትዕዛዝ ያስተላለፈላቸው በሚመስል ሁኔታ ጥለዋቸው ሄደዋል።

ሁኔታውን ለማመልከት በማግስቱ ስል ወደደወሉበት ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ለምን እንዳልደረሱላቸው ሲጠይቁ ፖሊሶቹ መምጣታቸውን ነገር ግን በሩ ላይ ያሉት ጥበቃዎች ሰላም ነው ብለው እንደመለሱላቸው ገልጸዋል።

ከግቢው ውጭ ቃሊቲ በሚገኘው ቤተሰቦቻቸው ቤት አድረው የነበሩት የሐዋሳው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ ፋኑኤል ቤትም ሲደበደብ ያደረ ሲሆን በሩ የብረት በመሆኑና አልከፍም በማለታቸው ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ቀርቷል። የከምባታና ሃዲያ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ መልከጸዲቅ ላፍቶ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መጥተው በራቸው ለደበደቡት ሰዎች በመክፈታቸው ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ከቤታቸው ይዘዋቸው ጴጥሮስ እየተባለ በሚጠራ አካባ ባለ የደህንነት ቢሮ ወስደዋቸው በስሰባው ላይ አክርረው የሚሰጡትን አስተያየት እዲቀንሱ የሚያሳስብ ማስጠንቀቂያ ለሦስት ሠዓት ያህል ከተሰጣቸው በኋላ ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል።

ጳጳሳቱ በዚህ ሁኔታ ስብሰባ ተሰብስቦ ውሳኔ ማሳለፍ ለሕይወታቸው አስጊ በመሆኑ መንገስት ለደህነታችን ጥበቃ ካደረገ አንሰበሰብም በማለታቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወርቅነህ ገበየሁ ሰብስቧቸው ምንም ስጋት እዳይገባቸው ቃል በመግባት ተሰብስበው ውሳኔ እዲያሳልፉ አዟቸው ሲኖዶሱ ለአርብ ተቀጥሮ ተለያይዋል።

በትናንትናው ዕለትም ሲኖዶሱ ተሰብስቦ ለቤተክርስቲያኒቱ ሰላምና ለጳጳሳቱ ደህንነት ሲባል የአባ ሳሙኤል እገዳ ማንሳትን በሚመለከት የተያዘው አጀንዳ ለጥቅምት ወር እንዲተላለፍ ተወስኗል።

እስከዛው አሁነ ሳሙኤል በሥራ አስፈጻሚው ጸሐፊነታቸው እየሰሩ እንዲቀጥሉ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሥራስኪያጅ እንዲሆኑ ፓትርያርኩ የሾሟቸው ግለሰብ ተነስተው ሲኖዶሱ የራሱን ሥራ አስኪያጅ እንዲሾም ሥራ አስኪያጁም ተጠሪነቱ ለሲኖዶስ እንዲሆን በማት ውሳኔ አስተላፈው በጥቅምት ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘው ተለያየተዋል።

Comments To Be Moderated

Dear Deje-Selamaweyan/yat,

The DS team would like to thank each and everyone of you for your attentive follow up of Church developments for quite some time. God willing the issue seems to reach another stage, which needs our cummulative service for the betterment of our religion.

In the mean time, some readers went out of line and write non-dejeselamawi comments, that offended many of us. Thus, from now on, all comments will be moderated, unwatned ones will not be allowed, and those of positive sentiment will be given the chance.

Cher Were Yaseman,
Amen
DS


የግርግሩ ፍጻሜ ማግሥት

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 18/2009)
• የተመዘበረው የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ቤት አልተሠራም፣
• ቅ/ሲኖዶስ የሰየማቸው የሥ/አስፈጻሚ አባላት ለቀዋል፣
• በግርግሩ ፍጻሜ መንግሥት እፎይታ አግኝቷል፣

በትናንትናው ዕለት “በስውሩ እጅ” እርዳታ ፓትርያርኩ ቅ/ሲኖዶስን ካሸነፉ ጀምሮ በቤተ ክህነት አካባቢ ያለው ግርግር ፀጥ ማለቱ ታውቋል። ለሁለት ወራት ሲታወክ የሰነበተው ግቢ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በደርግ ዘመን እንኳን ሆኖ የማያውቀውን፣ አባ ጳውሎስ ካስደፈሩት በሁዋላ ጸጥታ ሰፍኖበታል ተብሏል።


በችግሩ ውስጥ መፈናፈኛ አጥቶ የነበረው መንግሥት አዲሱ የለውጥ ሒደት ምንም እርምጃ አለማምጣቱን ከተረዳና ጳጳሳቱም በእጃቸው የገባውን ዕድል መጠቀም እንዳልቻሉ ሲገነዘብ አቅጣጫውን በመቀየር ከፓትርያርኩ ጋር መቆምን እንደመረጠ ተንታኞች ገልጸዋል። መንግሥት እውነተኛ የለውጥ ፍላጎት ቢኖረው እንኳን ብፁዓን አባቶች ግን የሚጠበቅባቸውን ያህል በተጠናከረና በዲሲፕሊን ላይ በተመሠረተ አሠራር የተካኑ ባለመሆናቸው በቆረጣ የገባው የማፊያው ቡድን ሊበታትናቸው ችሏል። ፓትርያርኩን ለሕገ ቤተ ክርስቲያንና ለቅ/ሲኖዶስ የበላይነት ለማስገዛት ይቻል ዘንድ ዋዜማው ላይ ከተደረሰ በሁዋላ በአባቶች መከፋፈልና ጠንካራ አቋም ማጣት ነገሩ እንደከሸፈ ያስረዱ አንድ ውስጥ አዋቂ “አውሬው ከቆሰለ በሁዋላ አመለጠ” ሲሉ ነገሩን በምሳሌ አስረድተዋል። የቆሰለው አውሬ ቁስሉን እየላሰ እንደማይቀመጥ ያብራሩት እኒሁ ሰው ያቆሰሉትን ለማጥፋት ተመልሶ መምጣቱ አይቀርም ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ረቡዕ ሌሊት በማፊያው ቡድን ቤታቸው የተሰባበረባቸው ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ከዘመድ ተጠግተው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ። ብፁዕነታቸው የተሰበረውን በር ጠግኖ ወደ ቤታቸው የሚመልሳቸው “አናጢ” በሀገር በመጥፋቱ ዛሬም በሰው ቤት ይገኛሉ ተብሏል። የወንጀሉ ፈጻሚዎችና ግብረ አበሮቻቸው ፍንጭ እስካሁን ያልተገኘ ሲሆን ጉዳዩን የአዲስ አበባ ፖሊስ እየተከታተለው መሆኑም ተሰምቷል።

በተያያዘ ዜና ቅ/ሲኖዶስ አቋቁሞት የነበረውና በፓትርያርኩ የታገደው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሥራውን እንዲሠራ “ዕግዱ ተነስቶለታል” ቢባልም ሊቆጣጠረው ይገባ ለነበረው አካል ማለትም ለፓትርያርኩና ለሥራ አስኪያጁ ተጠሪ እንዲሆን በመደረጉ የኮሚቴው አባላት እንደማይቀጥሉ ታውቋል። ፓትርያርኩ ዕግዱን አንስቻለሁ ያሉት ኮሚቴው በስም ብቻ እንጂ በግብርና በሥራ እንደማይኖር ካረጋገጡ በሁዋላ እንደሆነ የቅርብ ሰዎች ገልጸዋል። በዚህ ግርግር ውስጥ መከራ የደረሰባቸውና ማስፈራሪያ ያገኛቸው አባቶች ግን “ቤተ ክርስቲያናችንን ጥለን የትም አንሄድም፤ ፓትርያርኩንም አናኮርፋቸውም” ሲሉ ተሰምተዋል። ሕዝቡ ግን በነገሩ ሁሉ መበሳጨቱ ታውቋል። መንግስት በበኩሉ በቀላሉ የተጀመረውና ወደሁዋላ የጦዘው ውጥረት ለጊዜው መርገቡ ቢያስደስተውም ትልቅ ቤት ሥራ መውሰዱን ማወቅ እንዳለበት ተንታኞች ጠቅሰዋል።

እስቲ ቸር ወሬ ያሰማን እንበላ!!!
አሜን ብለናል።

July 17, 2009

የሁለቱ ወር የቅ/ሲኖዶስ ውጣ ውረድ ሲጠቃለል፤ ሪፖርታዥ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 17/2009)

ከግንቦት 6/2001 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሁለት ወራት ሲተረማመስ የነበረው ጉባዔ በመጀመሪያ የተነሳበትን ጉዳይ ከግቡ ሳያደርስ፣ “በስውር እጅ” ድል አድራጊነት፣ በፓትርያርኩ የበላይነት ተጠናቋል። ለመሆኑ ችግሩ ከመጀመሪያው ምን እንደነበር ማንሳት ይገባል። ቤተ ክርስቲያን በተለይም በፓትርያርክ ጳውሎስ መንበረ ፕትርክና ከመቼውም ጊዜ በላይ ውድቀት ላይ እንደምትገኝ የቅ/ሲኖዶስ አባላት ተገንዝበዋል። መገንዘብ ብቻ ሳይሆን በዚህ ዓመት በአንድነት መናገርም ጀምረው ነበር። ችግሩ የተረዱ አባቶችም ለቅ/ሲኖዶስ ባቀረቡት ባለ 21 ገጽ ዶኩሜንት ችግሩን በዝርዝር አቅርበው ነበር። ይኸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዋና ዋና አንገብጋቢ ችግሮች እና መፍትሔዎች፦ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ” በሚል ርዕስ የቀረበው ዶኩሜንት በሚከተሉት ጉዳዮች ዙሪያ ያጠነጥናል።

1 ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚፈጽሟቸው ስሕተቶች፣
(ይህም 23 ነጥቦችን ያዘለ ነው፤ እንደ አስፈላጊነቱ ወደፊት በዝርዝር እናቀርበዋለን፤)
2 ጠቅላይ ጽ/ቤቱን በተመለከተ አሉ ችግሮች (ባለ 9 ነጥብ ሐሳብ)፣
3 የችግሮቹ ማጠቃለያ፣
4 የአጭርና መካከለኛ ጊዜ የመፍትሔ ሐሳቦች፤

የነገሩን አካሄድ የተረዱት ፓትርያርኩ ጉዳዩን ለማኮላሸት “የነገሩ ጠንሳሽ” ናቸው ያሏቸውን ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በማንሳት በምትኩ በከፋፍለህ ግዛው ዘዴ ሀ/ስብከቱን ለአራት ጳጳሳት ሊሰጧቸው ቃል ገቡላቸው። ከነዚህም መካከል አንደኛው አቡነ ገብርኤል ናቸው። ይህንን እጅ መንሻ የተቀበሉት አቡነ ገብርኤል ዛሬ ጉባዔው እስከተፈጸመበት ዕለት ድረስ የቤት ሥራቸውን በትጋት ሲሰሩ ሰንብተዋል። ከዚህም ባሻገር የተነሳውን ነውጥ አቅጣጫ ለማስቀየር ፓትርያርኩ አዳዲስ ጳጳሳትን “መሾም እፈልጋለሁ” ብለው አቀረቡ። ሊሾሙ የተዘጋጁት “አባቶች” በአብዛኛው የእርሳቸው ጋሻ ጃግሬነታቸውን ገና ከጠዋቱ ያስመሰከሩ ናቸው። ቅ/ሲኖዶሱ ይህንን ሹመት አልቀበልም በማለት ላለፉት 17 ዓመታት ያላሳየውን ድፍረት አሳየና ፓትርያርኩንና “የማፊያውን ቡድን” አስደነገጠ። ማፊያው ቡድን በፍጥነት ወዲያዉኑ በመንቀሳቀስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን “የሚያዋርድ መጽሐፍ” ኣሳትሞ ማሰራጨት ጀመረ። የመጽሐፉ “ደራሲም” አዲስ መኪና ተሸለመ። መጽሐፉም በቤተ ክህነት ግቢ እና በመስኪድ አካባቢ በስፋት መሰራጨት ይዟል። ይህ መጽሐፍ እየተሰራጨ ሌላ መጽሐፍ እንዲዘጋጅ ተደረገ። አዲሱ መጽሐፍ የ10 ጳጳሳትን ስም ለማጥፋት የተዘጋጀ ሲሆን ከነዚህም አንደኛው ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ነበሩ። የመጽሐፉ ይዘት ለነዚህ አባቶች እንዲገለጽላቸው ከተደረገ በሁዋላ አፋቸውን ዘግተው እንዲቀመጡ ወይም የፓትርያርኩ ደጋፊዎች እንዲሆኑ ተደረጉ። አቡነ እስጢፋኖስም ይህንኑ ተቀብለው ሲኖዶሱን በማፍረስ ረዱ። ይህንን በማድረጋቸው የራሳቸውን “ጉድ” ለመደበቅ ቤተ ክርስቲያንን “ጉድ አደረጓት”። ቤተ ክርስቲያን በንስሐ ያጠበችላቸውን ሃጢአት ሰዎች ስላልረሱት እነርሱን ለማስደሰት ብለው “ይቅር” ያለቻቸውን ቤተ ክርስቲያን” አሳዘኗት። ያተረፉት ነገር ለጊዜው መጽሐፉ ታትሞ እንዳይሰራጭ ማድረግ ብቻ ነው።

ከዚአ ማፊያው ቡድን በአንድ በኩል፣ ፓትርያርኩ በአንድ በኩል በብፁዓን አባቶች ላይ ዘመቱባቸው። ስማቸውን ማጥፋት፣ ማስፈራራት፣ መዛት ቀጠሉ። እንዲያውም ፓትርያርኩ መስመር አልፈው “ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አልቀበልም” ብለው የክህደት ቃል ተናገሩ። ለዚህ ቃላቸው ሳይገሰጹ፣ ሳይቀጡና ኢቅርታ ሳይጠይቁ፣ ማፊያው ቡድን አበውን ቤት በመሰባበር በርግጥም ዛቻው በቃላት ብቻ እንደማይገታ አሳየ። አባቶችም ማንም እንደማይደርስላቸው ካረጋገጡ በሁዋላ “እሺ እንደቃሎ ታዛዥ ነን” ብለው ለፓትርያርኩ እጃቸውን ሰጡ። በዚሁ ተጠናቀቀ። አዲስ ምዕራፍ ተጀመረ ማለቱ ይሻላል።

የሰውን አየነው አሁን የእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ ይጀምራል። ሁሉም በቤተ ክርስቲያን የጭንቅ ቀን ተመዘነ። የቀለለው ቀለለ፤ የተዋረደው ተዋረደ። በዚህ ውስጥ ለቤተ ክርስቲያናቸው የቆሙት በሙሉ ዋጋ ከፋይ በሆነው አምላክ መመስገናቸው አይቀርም። ለሌሎቻችን ግን ይብላኝልን!!! ስለዚህ ተስፋ እንቁረጥ? “ምን ጳጳስ አለ?” ብለን በቀቢጸ ተስፋ ወደየቤታችን እንግባ፣ ወደ ኣለሙ እንሰማራ፣ ወደ መናፍቁ አዳራሽ እንሂድ፣ ከስደተኛው እንደመር? በጭራሽ!!!!! ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገላችን ሰማዕትነትም ቢሆን እንቀበል ዘንድ መዘጋጀት ካለብን ጊዜው አሁን ነው። በተለይም በኢትዮጵያ ያሉ አበው፣ ወንድም እህቶች በሙሉ “የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ነው” እየተባሉ የፓትርያርክ ጳውሎስንና የማፊያውን ውሳኔ እንዲቀበሉ ይገደዳሉ እምቢ ካሉም “መንግሰት ሰላም ለማስከበር” ደረታቸውን በጥይት፣ እጃቸውን በብረት፣ ጉልበታቸውን በእንብርክ ማድቀቁ አይቀርም። ምዕመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን ለማዳን መነሣት ካለባቸው ጊዜው አሁን ነው። በመሸሽ፣ ከቤተ ክርስቲያን በመቅረት፣ ገለልተኛ ሆኛለሁ.ተሰድጃለሁ በማለት ሳይሆን ቤቱን እንዲያጸዳ አምላክን በመለመን የዘመናችን “ልዮናውያን” መታገል አለብን።

ዛሬ ቤተ ክህነታችን ያለበት ሁኔታ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የካቶሊኮች ሁኔታ ጋር በጣም ተመሳሳይ ነው። በአባቶች በኩል ያለው ሥርዓት አልበኝነቱ፣ ገንዘብ ወዳድነቱ፣ እግዚአብሔርን አለመፍራቱ፣ ለምንኩስና ክብር አለመስጠቱ፣ ምዕመናንን አለመጠበቁ ወዘተ የዘመነ ሉተርን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ያስታውሰናል። ካቶሊክ ቤተ ክርስቲአን እንዲያ በብልግና በመበሻቀጧ ምን መጣባት? ሉተር ተነሳባት። እኛስ እግዚአብሔር በምን ይቀጣን ይሆን? በእስላሞች ሰይፍ? በመናፍቃን ወረራ? እርሱ ባለቤቱ ያውቃል። ለሃጢአታችን ግን ዋጋ ሳንከፍል አናመልጥም። ንስሐ እስካልገባን ድረስ። ዛሬ የቤተ ክርስቲያን መናገሻ የሆነውን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ያስደፈሩት ፓትርያርክ እንደ አቡነ መርቆርዮስ እንኳን ዕድሜ ለንስሐ ሳያገኙ እንዳይቀሩ በጣም ያሰጋቸዋል። እግዚአብሔር የሰጣቸውን ዕድል አልጠቀም አሉ። 17 ዓመት ሙሉ ያዋረዷት ቤተ ክርስቲያን እንደ ደካማ ተቆጥራ በድል የወጡ መሰላቸው። የምጥ ጣር እንደሆነ ማን በነገራቸው። መቸም ይህንን ማን ይነግራቸዋል። እርሳቸውስ ምን ጆሮ አላቸውና። (“ነባዕነ ነባዕነ፤ ከመ ኢነባዕነ ኮነ፤ ጮኽነ ጮኽነ፣ እንዳልጮኽነ ሆነ” አለች አሉ ውሻ!!!)

ታሪክን የሚለውጥ አምላክ ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

ስውሩ የአቡነ ጳውሎስ እጅ ድል አደረገ፤ ስብሰባው “የፓትርያርኩን አቋም በመደገፍ” ተፈጸመ፤ ጋዜጣዊ መግለጫም ተሰጠ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 17/2009)

• የአቡነ ሳሙኤል ዕገዳ አልተነሣም፣
• እንደተለመደው www.ethiopiafirst.com እና ሀገር ፍቅር ሬዲዮ ውሳኔውን ያውጁታል፣

. We have the English translation at the end of this article,

ለብዙ ዕለታት፣ ቀንና ሌሊት ሲወጣ ሲወርድ፣ በየሰዓታቱ ሲለዋወጥ በመጨረሻም አባቶች ላይ ጥቃት ሲሞክር የከረመው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ያለምንም ውጤት የቅዱስ ፓትርያርኩን “መመሪያ” ሰምቶና ተቀብሎ፣ “እሺ በጄ” ብሎ ተበተነ። ስውሩ የአቡነ ጳውሎስ እጅም አሸነፈ።

ዛሬ በተካሄደው የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ ላይ ፓትርያርኩ በፈለጉትና በወደዱት መልክ ነገሮችን ለማስኬድ የቻሉ ሲሆን “ዱርዬዎች ያዘጋጁት” ያሉትን ሕገ ቤተ ክርስቲያን “ተቀብዬአለሁ” ከማለት በስተቀር አንድም ፋይዳ ያለው አጀንዳ አልተነሣም ተብሏል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የፓትርያርኩ ተቃዋሚ እንዲሁም የቅ/ሲኖዶስ አበው ቡድን ሁነኛ መሪ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በሀ/ስብከታቸው ላይ የተጣለባቸው እገዳ እስከ ጥቅምት ጉባዔ ድረስ እንዲጸናባቸው ተፈርዶባቸዋል። ብፁዕነታቸው በደህንነታቸው እየተሳበበ “በቤት ውስጥ እገታ” ከስብሰባ እንዲቀሩ ሲደረግ ሰንብቶ ዛሬ ውሳኔው ተላልፎባቸዋል ተብሏል።

በዛሬው ስብሰባ ላይ የአባቶች ጥበቃ ጉዳይ ከመጤፍ ሳይቆጠር ከመታለፉም በላይ በማፊያው ቡድን የተሰባበረው የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በር እስካሁን እንዳልተሠራ ታውቋል። የማፊያው ቡድንና ሌላው “ስውር እጅ” አባቶች ላይ ከፍተኛ ሥነ ልቡናዊ (ሳይኮሎጂካል) ጫና በማሳደራቸው አባቶች ደፍረው ለመናገር ሳይችሉ ቀርተዋል።

ጉዳዩ በዚህ መልክ እንዲጠናቀቅ ያላሰለሰ ጥረት ያደረጉት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ አባቶች በፍጥነት እንዲፈርሙ በማግባባት በኩል ተሳክቶላቸዋል ተብሏል። ስብሰባው እንደ ተጠናቀቀም ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን “ሰላም ወርዷል” ተብሎ ሲነገርም ተሰምቷል። አቡነ እስጢፋኖስ፣ አቡነ ሙሴ፣ አቡነ ገሪማ፣ አቡነ ገብርኤል፣ አቡነ ጎርጎርዮስና አቡነ ይስሐቅ የፓትርያርኩ ቀኝ እጅ በመሆን “ቅዱስ ሲኖዶስን አፍርሰው ቤተ ክርስቲያኒቱን ገድለዋታል” ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች መስክረዋል። ከዚህ በሁዋላ የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ እደግፋለሁ ባለው መንግስት አማካይነት ፓትርያርኩ ተቃዋሚዎቻቸውንና ለቤተ ክርስቲያን የቆሙትን፣ ቅ/ሲኖዶስ አይደፈር ያሉትን በሙሉ በበቀል እንደሚያጠፉ ይጠበቃል።

የፓትርያርኩና የማፊያው ቡድን ከ”ስውሩ እጅ” ጋር በመሆን የበቀል በትሩን በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ላይ፣ የቤተ ክህነት ሠራተኞች ላይ፣ በብፁዓን አባቶች ላይ እንዲሁም ከመጀመሪያው “እጁ አለበት” ባሉት ላይ ሁሉ ይነዝራሉ ተብሏል። ቤተ ክርስቲያን በቅርብ ጊዜ ታሪኳ እንዲህ ዓይነት ውርደትና ውድቀት ገጥሟት አያውቅም ተብሏል። “ምዕመኑ መከፋፈሉን ትቶ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያድን” አባቶች መጠየቅ ጀምረዋል።

የቤተ ክርስቲያን አምላክ ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
++++++++++++++++++++++++++++
Deje-Selam, Jul 17/2009)
. The “invisible hands” of Abune Paulos have won – The meeting end by supporting the Patriarch’s opinion – A press release was given
. The ban on Abune Samuel has not been raised ,,
. Read the News in Amharic HERE,
. As usual Ethopiafirst and Hager Fiker are announcing the verdict!
+++++

The issue , raised in the Holy Synod assembly has been going back and forth for the several weeks with controversial decisions and resulting in the assault of the Arch Bishops, has ended by hearing and fully accepting the course of action of the holy patriarch.

On the assembly held today, the Patriarch had been full in control of the strength and led the meeting in his way. He has verbally said “I accept” the Canon of the Church which he has called a ‘Vagabond deed” on yesterday’s meeting.

Abune Samuel, the Arch Bishop of Addis Ababa Archdiocese was one of the opponents of Aba Paulos, was banned from His service at the diocese and it has been decided that the banning will not be lifted a until October. His Grace has not been able to attend the meeting because he has bee house arrested by the militia who claim that this is for his safety
The attack on Wednesday was over looked in today’s meeting and the property damage on
Abune Kyrllos’s home has not been fixed. The mafia group and the invisible hands of Aba Paulos has caused a great psychological pressure on the fathers.

Abune Estiphanos, who played a great role in diverting the meeting principles, made the fathers to sign the agreement as soon as possible. A press release was given and acted as if “Peace has been accomplish”.Some have commented that “Abune Estiphanos,Abune Muse,Abune Gabriel,Abune Yisak,Abune Gorgoriyos had been the right hand of Abune Paulos and have defied the impartiality of the Holy Synod and have destroyed the Church”.By government ,that has initially declared that it will accept the decision of the Holy Synod,Abune Paulos is believed to start his revenge on all who have stood by the Church’s canon and rites.
The Patriarch and the Mafia group with the ‘invisible hands’ will start its vengeance on Addis Ababa church and monastery heads,Bete Kehnet employees, Bishops and on any one they think are involved in the act. Ye Ethiopia BeteKristian(EThioan Chruch) has never in history faced such a disgrace.”Laity should stop the division and save their Church” was the pleading heard from some fathersPeople Who Attacked Ethiopian Bishops Are not Arrested

(Deje Selam, July 17/2009)

Wednesday evening at around 10 pm, during the power interruption in the area, armed people invaded the homes of the Arch Bishops, damaged their property and even tried to cause harm on the fathers. Some of the Fathers were abducted and terrorized by these militia groups. It is suspected that the “Patriarch’s family and their mafia group” is behind this offense. The mafia group is still atlarge and nobody is in custody.


Ato Yared (Mr Yared) Kebedew that goes with the title ‘Like Hiruyan’, who is presently the head of the Sebeka Gubae Maderaja Memria and known to be the cousin of the Abune Paulos, is also the leader of the strong mafia group and also believed to be armed. Ato Yared ,who has always been suspected for firing the bullet that killed the monk at the tragic incident in Kidus Estiphanos feast day celebration years ago, was also the head(Halafi) of the “Bete Kehnet Kuteter kifle”.The Sebeka Gubae Maderaja Memria former head ,the beloved Leke Gubae Aba Abera who lived and died in a small hut made of iron sheet on all sides , was exceptionally ignored and neglected by Abune Paulos

When we asked some of the employees of the Bete Kehenet about the incident on Wednesday, they said - Ato Yared’s group will not hesitate from harming any one they don’t like and that they also have an accomplice who were or are working with in the governments security force (dehenenet).Some inner sources say that they were either bribed or given commercial houses own by the church or are relatives of the Patriarch.

In the evidences listed on the agenda, addressing the Patriarch corruptive administration, presented to the Holy Synod says “By making former employees of the government who were found to be guilty of corruption and other various predicaments, part of the administration has made the church a hiding place of vagabonds and traitors”. Some are concerned that if realistically the government does not have a means of controlling its security officials from executing any kind of crime and offense, the country is soon to face similar South Africa’s post-apartheid crisis. It is also know that the Patriarch uses the government to threaten people.

Cher wera yaseman
Amen

የቤተ ክህነቱ ማፊያ ቡድን አሁንም አልተያዘም፤ የመንግሥት ደህንነቶች ሳይኖሩበት አልቀሩም

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 17/2009)

ረቡዕ ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው ያለውን የመብራት መጥፋት ተገን ባደረጉ ሰዎች በብፁዓን አባቶች ላይ አደጋ ለመጣል በተደረገውና በንብረት ውድመትና አባቶችን በማጎሳቆል እንዲሁም አፍኖ በመውሰድና በማስፈራራት በተፈጸመው ወንጀል ቤተ ክህነቱን የተቆጣጠረው የፓትርያርኩ “ቤተ ዘመዶች ቡድን” እንዲሁም በጉቦ የተገዙ “የመንግስት ደህንነት ሠራተኞች” እንደሚገኙበት ውስጥ አዋቂዎች እየተናገሩ ነው።

“ሊቀ ኅሩያን” የሚል የማዕረግ ስም ተሰጥቶት ታላቁን የቤተ ክርስቲያኒቱን የሰበካ ጉባዔ ማደራጃ መምሪያ ሃላፊነት የተቆጣጠረው የፓትርያርኩ እህት ልጅ በሆነው በአቶ ያሬድ ከበደው መሪነት የሚንቀሳቀሰው የማፊያ ቡድን የተጠናከረና መሳሪያ የታጠቀ ሲሆን አደጋ በመጣልና በማስፈራራት ከዚህ በፊትም ልምድ አለው። ከዓመታት በፊት በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ሕጉ በቆመበት የአንድ ባህታዊ ነፍስ በጠፋባት ዕለት “ጥይቲቱን ያስወነጨፈው እርሱ ነው” እየተባለ ሲታማ የኖረው ያሬድ የቤተ ክህነቱ ቁጥጥር ክፍል ሀላፊ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱ የጀርባ አጥንት የሆነው የሰበካ ጉባዔ መምሪያ የበላይ ነው። ይህ መምሪያ በተወዳጁ መንፈሳዊ አባት በሊቀ ጉባዔ አባ አበራ በቀለ መሪነት ለአስርት ዓመታት ሲተዳደር የነበረ ሲሆን አባ አበራ ከፓትርያርኩ በደረሰባቸው መገፋት የሕክምና ርዳታ ሳያገኙ፣ በአንዲት ቆርቆሮ በቆርቆሮ ቤት ውስጥ ኖረው በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ሊለዩ በቅተዋል።


ስለ ረቡዑ አደጋ አስተያየት የጠየቅናቸው የቤተ ክህነት ሠራተኞች እንደሚናገሩት “እነ ያሬድ የጠሉትን ሰው በማንኛም መልኩ ከማጥቃት ወደ ሁዋላ” እንደማይሉ ገልጸው በዚህ ወንጀላቸው ደግሞ በመንግስት ደህንነት ውስጥ የሚሰሩ ወይም ይሰሩ የነበሩ ሰዎች እንደሚተባበሯቸው ተናግረዋል። ደህንነቶቹ ለምን በዚህ ወንጀል እንደሚሳተፉ ምክንያታቸውን የሚዘረዝሩት ውስጥ አዋቂዎቹ “ሰዎቹ በገንዘብ ይደለላሉ፣ የቤተ ክህነት ቤቶች ይሰጧቸዋል፣ ወይም ፓትርያርኩ የሥጋ ዘመዶች ይሆናሉ” ሲሉ አብራርተዋል።

በግንቦት 2001 ዓ.ም ለቅዱስ ሲኖዶስ በቀረበና የፓትርያርኩን አስተዳደራዊ በደሎችና ወንጀሎች በዘረዘረ አንድ መረጃ ላይ ፓትርያርኩ “በሙስናና በተለያዩ ከፍተኛ ችግሮች በደል ተገኝቶባቸው ከመንግሥት በግምገማ የሚባረሩ አካላትን ከጥፋታቸው ሳይታረሙ ከነችግራቸው በማቅረብ ቤተ ክርስቲያኒቱን የዘራፊዎች ዋሻ አድርገዋልታል፡፡” የሚል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበረ ታውቋል።
በርግጥም መንግስት የደህንነት ሃይሎቹ በፈለጉት መልክ ወንጀል ሲሰሩ ሊቆጣጠር የሚችልበት ዘዴ ከሌለው አገራችን የድህረ-አፓርታይድ ደቡብ አፍሪካ ዕጣ እየገጠማት ነው የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ ፈጥሯል። ፓትርያርኩ ከዚህ በፊትም የሚቃወሟቸውን ሰዎች በመንግስት ስም እንደሚያስፈራሩ ይታወቃል።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

July 16, 2009

አባቶች አካላዊ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ታወቀ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 16/2009)

ረቡዕ ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው ያለውን የመብራት መጥፋት ተገን ያደረጉ ሰዎች በብፁዓን አባቶች ላይ አደጋ ለመጣል በተደረገው ሙከራ ከንብረት ውድመትና አባቶችን ከማጎሳቆል ባለፈ አካላዊ ጉዳት በሚያደርስ መልኩ አደጋ የደረሰበት አባት እንደሌለ ታወቀ።

ብዙ የጥበቃ ሠራተኞች በሚተራመሱበት የቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የብፁዓን አበው መኖሪያ ሕንጻ ላይ በተሰነዘረው በዚህ አደጋ የቅዱስ ሲኖዶስ መብት አስጠባቂነቱን ስብሰባ በመምራት ላይ የሚገኙት የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ቤት በሮች ከተሰባበሩ በሁዋላ እርሳቸው ግን በእግዚአብሔር ቸርነት ሲተርፉ በተመሳሳይ መልኩም የብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ቤት በር ተሰባብሯል ተብሏል።

ከሌሎቹ በተለየ የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ቤት ለአደጋ የተጋለጠበት ምክንያት የአባቶች ፊርማ ያረፈበት ቃለ ጉባዔ እርሳቸው ዘንድ ስለሚገኝ ሊሆን እንደሚችል ምንጮቻችን አብራርተዋል። ከርሳቸው በተጨማሪ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ለተወሰነ ጊዜ “ታፍነው፣ ማስፈራሪያና ዛቻ” ደርሶባቸው ተለቀዋል የተባለ ሲሆን ሌሎች ምንጮች በበኩላቸው ምንም እንዳልደረሰባቸው ይናገራሉ።

ይህ ሁሉ ሲሆን የግቢው የጥበቃ ክፍል ምን ይሠራ እንደነበር፣ የት እንደነበር ገና ምርመራ ያስፈልገዋል። አደጋውና በር- ሰበራው ለጆሮም ለዓይንም የማይሰወር፣ እንኳን የጥበቃ ሠራተኞች ራሳቸው ፓትርያርኩም ሊሰሙት የሚችሉት እንደሆነ ተገልጿል። አባቶች ስለ ቤተ ክርስቲያን ያላቸውን አቋም በመግለጻቸው ብቻ ጥበቃ ሊደረግላቸው ሲገባ ለአደጋ በሚጋለጡበት ሁኔታ መተዋቸው የተደፈረችው ቤተ ክርስቲያን መሆኗን ያሳያል ተብሏል። አደጋው መድረሱን ያወቁ አንድ አባት ለጥበቃ ሰዎች ቢናገሩም የሚደርስ ሰው አለመገኘቱ ሲታወቅ መንግሥት በእምነት ደረጃ የሃይማኖት አባቶች፣ በዜግነት ደረጃ አረጋውያን የሆኑ አቅመ ደካማ ዜጎቹን ለመጠበቅ አለመቻሉ አነጋግሯል።

ዛሬ ጠዋት አባቶች በአካል በተገናኙበት ወቅት ስለ ጤንነታቸውና ስለ አጠቃላዩ ሁኔታ ሲነጋገሩ መታየታቸው ታውቋል። በዚህ የመንፈስ መረበሽና የሴኪዉሪቲ እጦት መንፈስ ምን ዓይነት ስብሰባ ሊያኪያሂዱ እንደሚችሉ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል። በዚህ ወንጀል ውስጥ ሊሳተፉና ሊመሩ የሚችሉ እነማን ሊሆኑ ይችላሉ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የራሳቸውን መላምት የሚሰጡ ምንጮቻችን እንደሚናገሩት በፓትርያርኩ መሪነት እርሳቸውን ተገን አድርገው የሚንቀሳቀሱት ማፊያ ቡድኖች፣ በተለይም የእጅጋየሁ በየነና የቅዱስነታቸው የወንድም ልጅ የሆነው የያሬድ ጋሻ ጃግሬዎች ሳይሆኑ አልቀሩም ይላሉ። ሌሎችም በበኩላቸው መንግሥት የሚጫወተው ድራማ ወይም በቁልቢ ብር የተገዙ የደህንነት ሠራተኞች የሚሰሩት ሕገ ወጥ ድርጊት ይሆናል ሲሉ ግምታቸውን ይናገራሉ።

በትናንት ረቡዕ ስብሰባ ፓትርያርኩ “ሕገ ቤተ ክርስቲያን የምትሉትን አልቀበልም፣ የማንም ዱርዬ የሠራው ነው፣ … ሲኖዶሱ ተጠሪነቱ ለፓትርያርኩ ነው” የሚለው ክርክራቸው ከከሸፈ ወዲህ በትልቅ የተስፋ መቁረጥ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። ነገሩ በዚህ ካለቀ ችግር ውስጥ የሚገባው የፓትርያርኩና የማፊያዉ ቡድን ወደ ጥቃት የተሸጋገረው ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ተብሎ ተገምቷል። ሲኖዶሱ በመንግሥት ባለሥልጣናት አሸማጋይነት የጀመረው ስብሰባ ዛሬም ቀጥሎ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እግድና በሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ ለመነጋገር ቀጠሮ ነበረው።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

(ሰበር ዜና፣ Breaking News) ብፁዓን አባቶች ላይ አደጋ ተጣለ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 15/2009)

ዛሬ ረቡዕ ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው ያለውን የመብራት መጥፋት ተገን ያደረጉ ሰዎች በብፁዓን አባቶች ላይ አደጋ መጣላቸው ተሰማ።

የደጀ ሰላም ምንጮች እንደተናገሩት ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ባለፈው ጊዜ ማንነታቸው ለጊዜው ያልታወቀ ሰዎች የብፁዓን አባቶችን መኖሪያ በመደብደብ፣ በር ገንጥሎ በመግባት አደጋ ለማድረስ መሞከራቸው ሲታወቅ ይህ ዜና በተጠናቀረበት ወቅት አባቶች ላይ የደረሰው አደጋ ምን እንደሆነ፣ የተጎዱትስ አባቶች ምን እንደገጠማቸው አልታወቀም። ምንጮቻችን እንደተናገሩት ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ሳይሆኑ አይቀሩም፣ ሲጮሁና “አድኑኝ” ሲሉ ተሰምተዋል ተብሏል።

ፓትርያርኩን በመቃወሙ ዘርፍ ስብሰባዎችን ሲመሩ የሰነበቱት የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ መኖሪያ በር ከተሰበረ በሁዋላ ብፁዕነታቸው የመኝታ ቤታቸውን በር ቆልፈው ከአደጋው አምልጠዋል ተብሏል። ማንነታቸውን ለጊዜው ያላወቅነው አንድ አባት ግን ችግር ሳይደርስባቸው አልቀረም። እኚሁ አባት “ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ናቸው፤ ታፍነው ሳይወሰዱ አልቀሩም” ሲሉ ምንጮቻችን ጥቆማ ሰጥተዋል። ይህንኑ ያወቁ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መግባታቸውም ታውቋል።

በሌላም በኩል ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ውጪ ቃሊቲ አካባቢ ባለው መኖሪያቸው የሚኖሩት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የጥቃቱ ኢላማ የነበሩ ሲሆን አደጋ ጣዮቹ በራቸውን በተደጋጋሚ ከደበደቡ በሁዋላ፣ በጥበቃ ሠራተኞቻቸው መኖር ከአደጋው አምልጠዋል ተብሏል። ብፁዕነታቸውም ወደ ፖሊስ ዘንድ በመሄድ ቃላቸውን ሰጥተው ተመልሰዋል።

የዛሬው አደጋ ኢላማ የሆኑት አባቶች የፓትርያርኩ ተቃዋሚዎችና በዛሬው ስብሰባ ላይ ጠንካራ ሐሳብ የሰነዘሩት ናቸው ተብሏል። ነገሩ በርግጥም በተባለው መልኩ ተፈጽሞ ከሆነ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ አደጋ ላይ የመሆኗ የመጨረሻ ምልክት ይሆናል ማለት ነው።
ቀሪውን እንደደረሰን እናቀርባለን።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜንJuly 15, 2009

የሥራ አስፈጻሚው ዕገዳ ተነሣ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 15/2009)
በመንግሥት አደራራሪነት ዛሬ ዝግ ስብሰባ ተቀምጦ የዋለው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የሥራ አስፈጻሚውን ዕገዳ በማንሳት ለዛሬ እረፍት አደረገ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ላይ የተጣለው ዕገዳ ላይ መነጋገር የተጀመረ ቢሆንም የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በስብሰባው ላይ ባለመገኘታቸው ጉዳዩ ንግግር እንዳይደረግበት አባቶች በመጠየቃቸው ለነገ ተላልፏል። ብፁዕነታቸው በዛሬው ስብሰባው ያልተገኙት እንዳለፈው ሳምንት “ለደህንነታቸው” በሚል እገታ ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል። ስለዚሁ ጉዳይ በአባቶች የተጠየቁት የመንግሥት ባለሥልጣናት ስለ ነገሩ እንደማያውቁ መልሰዋል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዱስ ፓትርያርኩ አሁን በመካሄድ ላይ ያለው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ እንዲደናቀፍና ወደ ጥቅምት እንዲሸጋገር በመታገል ላይ ናቸው። ቅዱስነታቸው ይህንን የሚያደርጉት በተጠና ዝግጅት ለመቅረብ ዕድል ስሊሚሰጣቸው እንደሆነ የጉዳዩ ተንታኞች መስክረዋል። ፓትርያርኩ ራሳቸውን ከሕገ ቤተ ክርስቲያን በላይ እንደሚያደርጉ ትናንት ማክሰኞ የዘገበው የአሜሪካ ድምጽ ሲያቀርብ የደጀ ሰላም ምንጮች ደግሞ ሲኖዶሱም ተጠሪነቱ ለእርሳቸው እንደሆነ አድርገው መናገራቸውን መስክረዋል።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

በመንግሥት አደራዳሪነት ዝግ ስብሰባ እየተደረገ እንደነበረ ታወቀ

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 15/2009)
ለብዙ ቀናት በመስማማትና ባለመስማማት መካከል ሲንከባለል የነበረው አጀንዳ በአባቶች መፈረሙን ተከትሎ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሁለት በመከፈላቸው ይህንኑ ለአንዴም ለመጨረሻውም እልባት ለመስጠት ዛሬ በመንግሥት ባለ ሥልጣናት ሰብሳቢነት የተጠራ ስብሰባ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ (ከሰዓት በሁዋላ) መካሄዱ ታውቋል። ስብሰባው ይህንን ዘገባ እስካዘጋጀንበት ጊዜ ድረስ የቀጠለ ሲሆን ውጤቱ ምን እንደሆነ ለማወቅ አልቻልንም። የፓትርያርኩ ቡድንም ሆነ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑ አባቶች በሌላ በኩል በገቡት ፍጥጫ አንዱ የሌላውን ቁጥር ዝቅ ለማድረግ አድፍጠው እየሠሩ ነው ተብሏል። የዚህ ስብሰባ ውጤት ትልቅ ትርጉምና ወሳኝነት እንደሚኖረው ይጠበቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በትናንትናው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትርት በረከት ስምዖን መንግሥት ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተለ መሆኑን ተናግረዋል። በረከት ለቤተ ክርስቲያን ጤናማ አመለካከት ከሌላቸው ባለስልጣናት መካከል አንዱ መሆናቸው መዘገቡ ይታወቃል።
የስብሰባውን ሂደትና ውጤት እንደደረሰን እናቀርባለን።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

ሪፖርተር ጋዜጣ የተሳሳተ መረጃ እያሰራጨ ነው

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 15/2009)
• አውራምባ ታይምስ፣ ኢትዮፕያፈርስትና ሌሎች ጋዜጦችም ተሳስተዋል
ትናንት ተሰብስበው ቃለ ጉባዔውን ያጸደቁት በቁጥር ከ21 የማያንሱ አባቶች ሆነው ሳለ 13 እንደሆኑ አድርጎ በዛሬ የረቡዕ እትሙ የዘገበው የሪፖርተር ጋዜጣ ዜና የተሣሣተ መሆኑ ታወቀ። ባለፈው እሑድ እትሙም የአንዱን ወገን ብቻ በማነጋገር ነገሩን ለማራገብ የሞከረው ሪፖርተር ጋዜጣ ፓትርያርኩ ሁሉንም ጉዳይ በቁጥጥር ስራቸው እንዳደረጉ፤ ይልቁንም የተወሰኑ አባቶች እንደተነሱባቸው ለማስመሰል ሲሞክር ተስተውሏል።


ከዚህ በፊትም ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ይቅርታ ጠይቀዋል ማለቱ ይታወሳል። ሪፖርተር ይህንን አቋም የያዘበት ምክንያት ለጊዜው ግልጽ ባይሆንም ከቁልቢ ገብርኤል በፓትርያርኩ ቀጥተባ ትዕዛዝ ወጪ ተደርጓል የተባለው ከሁለት ሚሊዮን በላይ ብር “በረከት ተቋዳሽ” ሳይሆን እንዳልቀረ ምንጮቻችን አስረድተዋል። በዚሁ መልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ብር ከተረጨላቸው ሚዲያዎች መካከል አንደኛው የሆነው የዋሺንግተን ዲሲው ሀገር ፍቅር ሬዲዮ $10 000 (አሥር ሺህ ዶላር) ማግኘቱ ይታወቃል። በሌላ በኩል ደግሞ www.ethiopiafirst.com የተባለውና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለሼህ አላሙዲን በሚያሳየው ጥብቅና “አላሙዲን ፈርስት” የሚል ቅጽል የተሰጠው ድረ ገጽ ይገኝበታል። ድረ ገጹ የቅዱስ ሲኖዶስን አባቶች ሳይስማሙ መበተን “ካርታው ተናደ” ሲል እስከ መዘገብ ደርሷል፤ ፓትርያርኩንም ከ45 ደቂቃ ያላነሰ ቃለ ምልልስ ሽፋን በመስጠት የተቀሩትን አባቶች ሲያሳጣ ሰንብቷል።

Question And Answers About the Holy Synod Meeting: Two Articles

Dear Deje Selamaweyan,
Here you have two interesting articles. Article 1 is written by Dan, and Article 2 is by Matiwos. Enjoy.
Deje Selam
+++++++++++++++++++++++

1. (Article By Dan)
I have tried to follow what is taking place for some times but with regards to the synod what I find amusingly or sadly strange is not knowing, particularly in the last three or more synods.

In the last synod what was the agenda? (The issues brought to the meeting?)
What is the total number of the bishops? Are they all members of the synod?

Was the meeting the General Synod or permanent synod, if there is one?

How many of them attend this synod? Do they have OBLIGATION to attend?

What is the quorum for the meeting to take place?
Did the synod discuss the issues, heard HEARINGS?

Who voted for (again not knowing what the issues brought to the meeting) and who voted against?
What is the vote number for yes and no?

Those who refused to meet with an excuse of going to church to celebrate the Holy Trinity, in the Gospel Christ said First go and make peace first True Peace, Love, charity is so much better than all burnt-offerings and sacrifice. They have put the Church in crisis and it is trying time with no peace among them
In Matthew 5:24 we read “leave your offering there before the altar and go; first be reconciled to your brother, and then come and present your offering.

Other points I want to express: the patriarch is the first among equals. Not a monarch. There are only three Holy Orders:
Bishop, Priest and Deacon. Patriarch, Arch Bishop etc is Ecclesiastical Titles. Also NOT ALL orthodox churches call their Patriarch “Holy”. Under the current circumstance it is a mockery of the word Holy and ridiculous to call the current patriarch “Holy”. I think they should be addressed as “Your Beatitude, "Your Grace", or Your Eminence. Like in all orthodox churches they all dress the same way. (Since when an orthodox Patriarch wear white robe? He is not catholic or the pop. – Take a look at the way the Copts –Egypt, and the other Oriental
hierarchy dress. http://malankaraorthodoxchurch.in/index.php?option=com_content&task=view&id=99&Itemid=265

Ours like to be different and like a monarch with a crown.
In contrast take a look at the life and service of Aba Shenuda, the patriarch of Egypt. He is Obedient to Christ, his Church the people of God. His is loved by his people as a Disciple of Christ. Look at his joy in being among his people, look at the seat he takes, a simple pew –wooden bench, unlike aba Paulos who require a throne. You hear Shenuda CRY FOR HIS CHURCH AND PEOPLE.
http://www.youtube.com/watch?v=tGGeSTGUoiU&feature=related.

Yes Egyptians were not good for our church and us. That is our Weakens, which we still exhibit 50 years after we free ourselves from their rule

Has anyone witnessed aba Paulos with such humility and spirituality (For that mater do any of the Ethiopian Bishops?)? In other churches bishops stand with their people & serve their people, ours get serviced by the church people; serve the rich and those with power.

WE SHOULD PRAY. We should pray to Christ so that our action is guided by his words. In action is not acceptable at times of crisis.


++++++++++++++++++++
2. Article 2 By Matiwos
In the name of the Father, and of the Son and of the Holy Spirit, One God Amen.

Mr Dan, by the Will of God, I am member of the Ethiopian Orthodox Tewhadeo Church.

Concerning your comment: "Also NOT ALL orthodox churches call their Patriarch “Holy”. Under the current circumstance it is a mockery of the word Holy and ridiculous to call the current patriarch “Holy”"

My reaction to this is: the reason the EOTC calls the Patriarch 'Holy' is because the seat/position (Patriarch) he is occupying is the Holy Seat of Saint Mark, the first Patriarch.

In addition, you mention, "I think they should be addressed as “Your Beatitude, "Your Grace", or Your Eminence." Yet you address the Patriarch Bitsue Abune Paulos as, "aba Paulos". Again, addressing the Patriarch has nothing to do with his personality, its because his POSITION demands it.

Yet again, "Yes Egyptians were not good for our church and us. That is our Weakens, which we still exhibit 50 years after we free ourselves from their rule."

My question to this statement is, is it our weakness that the Egyptians for 1600 years did not contribute to the real development of the EOTC to be self sufficient? Is it our weakness that the Egyptians demanded an excessive amount of $$$ in gold, elephant tusks, etc, for them to send our Bishops, is this what is called 'spiritual'?; is it our fault that Copts did not take Ethiopians to Egypt and train them their language, as well as Church canons and dogma, so we could communicate with them better? Do we know for certain the EOTC fathers at the time of Copt 'leadership' did not attempt to have autonomy, which is a sign of strength? I tell you they did, but were refused because they were not seen worthy!!! And this feeling of 'holy' superiority complex still exists among them today. There are books that can help us see this, we can start with the late Abune Gorgorios' book on Church History. Again, nothing against the Copts, they have done an amazing job with THEIR OWN CHURCH progress, but when it comes to the EOTC, their contribution is questionable and this cannot be ignored as history can attest to this truth.

Two more things I would like to bring to attention. One is that the EOTC is young in terms of administrating its own affairs from top to bottom. This means there will be mistakes along the way of our growth. If we research the development history of ancient Churches like Copts, Rome, Greek, Russian, we will find out they had similar issues, and at times worse situations, this is part of growth.

The question we as EOTC servants should ask is how is MY service to the Church looking? What is God's expectation for me? What do others expect from me? The whole point is for us to look within ourselves in order to know who we are in relation to our relationship with God. Which brings me to my last point, it is terrible to compare the fathers of the EOTC with the Copts, first of all its not Christian to reveal another persons weakness openly like this. Our fathers should not be subjected to our judgments, let lone our Bishops and Priest, who have the position of leadership in the Kingdom of God, we should not place judgments on ANY soul. Our Fathers have been given their position by God, He will monitor their affairs. We are not the boss, He is. The responsibility of the laity/meamen, is serving God in what ever capacity given to us, along with RESPECTING our fellow workers of the Kingdom of God. In short, lets know our place if we want to work within the Kingdom of God and please God. Lets concentrate on OUR OWN responsibilities within the Kingdom, judgment is only reserved to the King and ruler of the Kingdom of Heaven, God Himself. Lets not squander our calling by straying away from the Word.

All the Glory be to the Father and the Son and the Holy Spirit, One God, who made taught me what I wrote. May the prayers of our Mother Holy Mary and all the Saints be with us

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)