June 26, 2009

ፓትርያርኩ የቅ/ሲኖዶሱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ላይ ጦርነት ከፈቱ(DEJE SELAM)ከሮም ጣሊያን ጉብኝታቸው ባለፈው ረቡዕ ወደ አዲስ አበባ የተመለሱት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ መጓዛቸውን ተቃውሞ ደብዳቤ የጻፈባቸው የቅዱስ ሲኖዶስ ሥራ አስፈጻሚ ላይ “ጦርነት መጀመራቸውን” የአዲስ አበባ ምንጮቻችን ገለጹ።
ለጂ-8 ጉባዔና ለ”ኢትዮጵያ ቀን” ዝግጅት ሮም የሰነበቱት ፓትርያርኩ በራሳቸው ፈቃድ ካደረሱት ጉዞ በተመለሱበት ዕለት የአዲስ አበባ ሊቃውንት ከ6ኤ.ኤም ጀምረው ተሰልፈው እንዲጠብቋቸው የተደረገ ሲሆን ተቃዋሚዎቻቸው የተባሉ ብፁዓን አባቶችንና ዜናዎች ያወጡ ጋዜጦችን የሚሰድቡ ዘለፋ አዘል “ቅኔዎች” ሲቀርቡ ተሰምቷል። በብዙ ሚሊዮን ብር የሙስና ተግባር ከተራ ግለሰብነት ወደ ሀብታምነት ተሸጋግሯል በሚባለው በወንድማቸው ልጅና የቤተ ክርስቲአን ሕንጻዎችን በትንሽ ገንዘብ በመከራየት መልሰው በብዙ ትርፍ በማከራየት ሀብት በማግበስበስ ላይ ናቸው በሚባሉት በወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ አስተባባሪነት በነቂስ እንዲወጡና ፓትርያርኩን እንዲቀበሉ የተደረጉት ሊቃውንቱ “ከርስዎ ጋር ነን” የሚል መልእክት እንዲያስተላልፉ መገደዳቸውን ምንጮቻችን ዘግበዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቅ/ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከወደቀችበት የሙስናና የዘረኝነት አዘቅት ወጥታ የተሰጣትን ሐዋርያዊ አገልግሎት ለመፈጸም ትችል ዘንድ አንድ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ማቋቋሙ የሚታወስ ሲሆን የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብት በመዝረፍ ላይ የሚገኙ ወገኖች ከሚቴው ሥራውን እንዳይጀምር ከፍተኛ ዘመቻ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የዚህ ፀረ-ሲኖዶስና፣ ፀረ ብፁዓን አባቶች እንቅስቃሴ መሪ ናቸው የሚባሉት የጥንቷ የአርቲስት መሐሙድ አሕመድ ባለቤት፣ የዛሬዋ የፓትርያርኩ አወዳሽ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ሲሆኑ ወ/ሮዋ አሜሪካን ሀገር በሚዘጋጀው በሀገር ፍቅር ራዲዮ ሳይቀር ቃለ ምልልስ በመስጠት የአባቶችን ክብር በመጋፋት ላይ ይገኛሉ። ይሄው ፀረ-ሲኖዶስ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ሐሙስ ዕለት የመላው አዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ያለ ሀ/ስብከቱ ዕውቅና ተሰብስበው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባል የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልንና የኮሚቴው ሊቀመንበር የሆኑትን የ ቅ/ሥላሴ ዲን ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስን እንዲያወግዙ ሲነገራቸው ውሏል። የስብሰባው ጥሪ ሕጋዊ እንዳልሆነ የተነገራቸው አስተዳዳሪዎች በስብሰባው ሳይገኙ ሲቀሩ የፓትርያርኩን ብቀላ ፈርተና ል ያሉና በዝምድናና በጥቅም ተሿሚነት የሚታወቁ ምንደኞች ደግሞ በሥፍራው በመገኘት ሲያሟሙቁ መዋላቸው ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሮም ጉብኝታቸው ቤኔዲክት 16ኛን ያገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ታቦተ ሙሴን በሙዚየም አስቀምጬ ለዓለም አሳያለሁ ማለታቸውን “ወርልድኔት ዴይሊ” የተባለ የዜና ተቋም መዘገቡ ታውቋል። ዛሬ አርብ ታቦተ ጽዮንን እንደሚያሳዩ መናገራቸው የተጠቀሰው ፓትርያርኩ ራሳቸውም ታቦተ ጽዮንን እንዳዩ ተናግረዋል ተብሏል። ዜናው በታዋቂ ዓለማቀፋዊ የዜና አውታሮች ያልተዘገበ ሲሆን ነገሩን በብቸኝነት ያቀረበው “ወርልድኔት ዴይሊ” ብቻ ነው። ዜናው ትክክለኛ ይሁን ወይም ሆን ተብሎ የፓትርያርኩን ስም ለማጉደፍ የተደረገ ወደፊት የሚታወቅ ይሆናል።

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)