June 20, 2009

የቅዱስ ሲኖዶስ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የቅዱስ ፓትርያርኩን ጉብኝት ተቃወመ

የቅዱስ ሲኖዶስ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የቅዱስ ፓትርያርኩን ጉብኝት ተቃወመ
(Deje Selam):- በግንቦት 2001 ዓ.ም የቅ/ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ የተመረጠው አዲሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ቅዱስ ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያለ ቅ/ሲኖዶስ ፈቃድ ወደ ውጪ ለጉብኝት መሄዳቸውን በመቃወም ደብዳቤ መጻፉ ተሰማ። “በጂ-8 በሚካሄደው የተለያዩ ሀገራት የሃይማኖት መሪዎች ስብሰባ ላይ እንዲገኙ” የጣሊያኑ ፕሬዚደንት ባቀረቡላቸው ጥሪ እንዲሁም “የኢትዮጵያ ቀን በዓል ላይ ለመገኘት ወደ ጣሊያን” የተጓዙት ቅዱስ ፓትርያርኩ ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ “የፓትርያርኩ ማንኛውም ጉዞ በቅ/ሲኖዶስ ዕውቅና” እንዲሆን ማለቱን ከግምት ውስጥ አለማስገባታቸውን በመንቀፍ እንደጻፈላቸው ምንጮቻችን ገልጸዋል።

በርግጥም ሥራ አስፈጻሚው የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ ለማስከበር ቆርጦ ከተነሣና የተባለውን ደብዳቤ ከጻፈ እርምጃው በቅርብ ጊዜ የቤተ ክርስቲአኒቱ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ለውጥ ሊአስብል አንደሚያስችል ሐሳባቸውን እንዲያካፍሉን የጠየቅናቸው አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።
ከዚህም በተጫማሪ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ያለምንም መመሪያና ደንብ ለቤተ ክርቲያኒቱ የልማት ኮሚሽን ሥራ አስኪያጅነት ሊፈጸም የነበረውን ቅጥር ሕግ ያልጠበቀ ነው በማለት ቅጥሩ እንዳይፈጸም ደብዳቤ መጻፉም ታውቋል። የኮሚሽኑን የበላይ ሥልጣን የሚይዘውን ሰው ለመቅጠር ያለምንም መስፈርት መጠቀም አዲስ አለመሆኑን የገለጹት ምንጮቻችን “አይሆንም፣ ትክክል አይደለም” ሲባል ግን ይህ የመጀመሪያው ነው። ላለፉት ዓመታት ቦታውን በሃላፊነት ይዘው ይሰሩ ለነበሩት ግለሰብ ከ15 ሺህ ብር በላይ የኢትዮጵያ ገንዘብ ይከፈላቸው እንደነበረና ይህም በወቅቱ ቅሬታ አስነስቶ እንደነበር ይታወቃል።Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)