June 4, 2009

“ ቤተ ክርስቲያን ከአደንዛዥ እጅ የነፃች ናት”


Selam Deje Selam,
“… የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት ማሪዋናን መጥነው በመጠቀም በቅዳሴ ወቅት ጥቅም ላይ ያውሉታል። ዝቋላና አክሱም ላይ ይህን እንደሚያደረጉ እኔ በግሌ አውቃለሁ። …” (ተስፋዬ ገብረ አብ)
I posted a comment on a book entitled "yegazetgnaw mastawosha" on my blog "Andit Betekirstian". If you can post it in your website, it would be great. If you can't find it on the blog. I have attached the book and my comment.
chur Ensenbit
“ ቤተክርስቲያን ከአደንዛዥ እጅ የነፃች ናት”

በቅርቡ “የጋዜጠኛው ማስታወሻ” በሚል ርዕስ በተስፋዬ ገብረ አብ በተጻፈው መጽሐፍ በገጽ 378 ላይ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ማሪዋናን በመጠኑ በቅዳሴ ላይ ትጠቀማለች” የሚል የሐሰት (ያለማወቅ) ውንጀላ ተፅፎ በማንበባችን በጣም አዝነናል:: ይህ ፍፁም ከእውነት የራቀ ከመሆኑም በላይ በራሱ በፀሐፊውና በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እርምት ሊሰጥበት የሚገባ ጉዳይ ነው::

ቅድስት ቤተክርስቲያን መድኃኔዓለም ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት፣ ሃዋርያት በስብከታቸው፣ ሰማዕታት በተጋድሎዋቸው ያስፋፏት በምድር ሆነን ከሰማያውያን ጋር የምንተባበርባት መንፈሳዊት ቤት ናት:: በዚች ቅድስት የእግዚአብሔር ቤት ያዘኑ ይጽናኑባታል፣የተረበሹ ሰላም ፣ ኃጥአን የኃጢአት ስርየት ያገኙባታል:: ምዕመናን በሙሉ ስለተደረገላቸው ነገር አምላካቸውን ያመሰግኑባታል:: ሊደረግላቸው የሚፈልጉትን ነገር ሁሉ አምላካቸው ያደርገው ዘንድ በጸሎት ይማጸኑባታል:: እግዚአብሔርም በዚያ በረድኤት ይገኛል:: የቀረበውን ጸሎት፣ምስጋና፣ቅዳሴ ተቀብሎ ለሁሉም እንደፍቃዱ ይሰጠዋል:: (1ኛ ነገ 9፥1-3)

እግዚአብሔር የሥርዓት አምላክ ነውና የእግዚአብሔር ቤት በምትሆን በቤተክርስቲያን ሁሉ ነገር በሥርዓት ይፈፀማል:: አንድም ነገር ቢሆን ያለ ሥርዓት
አይደረግም:: ይህ ደግሞ አገልጋዩን (ካህኑን) ምዕመናኑን ለአገልግሎት የሚውሉ ንዋያትን ሁሉ ይመለከታል:: የካህኑና የምዕመናኑን አለባበስ ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች በሙሉ ሥርዓትን የተከተሉ ናቸው:: ለአገልግሎት የሚውሉትም ነገሮች ዕጣኑ፣ መብራቱ፣ መስዋዕቱ፣ ንዋያተ ቅድሳቱ ሁሉ እርሱ ራሱ ለአገልግሎት እንዲውሉ በመጽሐፍ ቅዱስ የሰጠውን ትዕዛዝ መሠረት ያደረጉ እንጂ ሰው ሰራሽ አይደሉም::

ታዲያ ይህን ሰማያዊ አገልግሎት ያልተረዱ እንደ ተስፋዬ ገብረ አብ ያሉ ሰዎች በማያውቁት ገብተው ቤተክርስቲያንን ሲተቹ እንሰማቸዋለን:;

ቤተክርስቲያን በቅዳሴ ሰዓት የምትጠቀመው ዕጣን እንጂ ሌላ ምንም አይነት ነገር አለመሆኑን ቤተክርስቲያንን የሚያውቁ ሁሉ የሚመሠክሩት ጉዳይ ነው:: ይህ እጣን ደግሞ በምድር ባለችው ቤተመቅደስ ብቻ ሳይሆን በሰማይ ያሉ መላእክትም የቅዱሳንን ጸሎት ለማሳረግ የሚጠቀሙበት መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል:: / ራዕ 8 ፥3-4 / ከዚህ ውጭ የጌታን መከራ በምናስብባት በእለተ ዓርብ (ለስቅለት) ቤተክርስቲያን ‘ከርቤ’ ትጠቀማለች:: ይህም የጌታን የመከራውን ጽናት ለማሰብ ሲሆን ሰብአ ሰገል ለጌታ ከሰጡት እጅ መንሻ አንዱ ነው:: /ማቴ 2፥11/

ማሪዋና ግን የሰውን አዕምሮ ለተወሰነ ግዜ በመግዛት ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ እንዲዘነጋና በምኞት ባህር እንዲዋኝ ከሚያደርጉት አደንዛዥ እጾች አንዱ ነው:: ይህንን የመሰሉ አደንዛዥ ዕጾች (ጫት ፣ ሲጋራ ፣ ሀሺሽ ወዘተ.) ተጠቃሚውን በሱስ አስረው እንዳይጾም ፣ እንዳይጸልይ ፣ አምላኩን እንዳያገለግል የሚያከላክሉ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሆነውን የሰው አካል ለሌላ መንፈስ ማደሪያ የሚያደርጉ በመሆናቸው ቤተክርስቲያን ማንኛውም ሰው እራሱን ከእንዲህ ያለ ዕፅ እንዲያርቅ አጥብቃ ታስተምራለች::

እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ጸሐፊው ይህንን የመሰለ የሐሰት ውንጀላ በቤተ ክርስቲያን ላይ ለምን ሰነዘሩ? የሚለውን መመለስ የሚችሉት እራሳቸው ብቻ ቢሆኑም ምን አልባት ቤተክርስቲያንን ጠለቅ ብሎ ካለማወቅ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለኝ:: ስለዚህ ወደ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ቀርበው በመጠየቅ እንዲረዱና በቀጣይ እትማቸው ስህተቱን እንዲያርሙ ካደራ ጭምር ላሳስባቸው እወዳለሁ::

የቤተክርስቲያን ሊቃውንትም ጉዳዩ ቤተክርስቲያንን ያለግብሯ ግብር የሚሰጥ፣ የዋሃን ምዕመናንን የሚያስደነብርና ለመናፍቃኑ የስህተት ትምህርት ልዩ ርዕስ የሚሆን በመሆኑ ባፍ በመጣፍ መልስ ይሰጡበታል ብዬ አምናለሁ::

እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን!
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)