June 4, 2009

ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለፓትሪያርኩ የድረሱልኝ ጥሪ አቀረበ - 1.3 ሚሊዮን ብር ተመዝብሯል

Wednesday, 03 June 2009
ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለፓትሪያርኩ የድረሱልኝ ጥሪ አቀረበ
- 1.3 ሚሊዮን ብር ተመዝብሯል
በታምሩ ፅጌ

(Reporter Newspaper): የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት በደብረ ማርቆስ ንግድ ባንክ በቁጠባ ሂሳብ 16349 እና በተንቀሳቃሽ ሂሳብ ቁጥር 266 ውስጥ ተጠራቅሞ የነበረ ከ1 ሚሊዮን 300ሺ ብር ያላነሰ ገንዘብ በሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ እና ሁለት ሰራተኞች ተመዝብሯል በማለት ለመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤትና ለምሥራቅ ጎጃም ፖሊስ ጽ/ቤት የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች አመለከቱ፡፡ግንቦት 18 ቀን 2001 ዓ.ም የተጻፈና የ14 ሰዎችን ፊርማ የያዘ ማመልከቻ እንደሚያስረዳው በተለያየ አካውንት ተቀምጦ የነበረውን ገንዘብ ባልታወቀ ጊዜና ሰዓት የአስተዳደሩ ጉባኤም ሆነ መላ ሰራተኛው ባላወቁትና ባልተረዱት ሁኔታ በስውርና በሕገወጥ መንገድ ተወስዷል፡፡

የተመዘበረው ከፍተኛ ገንዘብ ሠራተኛው ተረጋግቶ ስራውን እንዳይሠራ ከማድረጉም በተጨማሪ እንዲበተንና የቤተክርስቲያኗን ሕልውና የሚያናጋ መሆኑን ማመልከቻቸው ያስረዳል፡፡

ሠራተኞቹ በፊርማቸው አረጋግጠው የላኩት ማመልከቻ እንደሚያስረዳው የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ወደ አሜሪካ ተዛውረው ሊሄዱ መሆናቸውን በመጥቀስ፤ የደረሰበት ያልታወቀው ገንዘብ ወደ ነበረበት እስከሚመለስ ጉዞአቸው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥላቸው አሳስበዋል፡፡ በተመሣሣይ መንገድ የምሥራቅ ጎጃም ፖሊስ ጽ/ቤትም ትብብር እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡

ተፈጠረ የተባለውን ችግር አስመልክተን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤትን ኃላፊዎች በስልክ አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ባይሳካልንም፣ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የመንበረ ፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ሰራተኛ "ጉዳዩ የጳጳሳት በመሆኑ፣ በሲኖዶስ እንዲታይ ተወስኗል" ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል አባ ዘካርያስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ግንቦት 18 ቀን 2001 ዓ.ም. ለቅዱስ ፓትሪያርኩ በፃፉት ደብዳቤ ለቤተክርስቲያናቸው ይጠቅማሉ ያሏቸውን አንዳንድ ስራዎች ለመስራት በሚሞክሩበት ጊዜ የተለያዩ ችግሮች እንዳጋጠማቸው ገልፀዋል፡፡

ሊቀጳጳሱ በደብዳቤያቸው እንደገለፁት አንድ ግለሰብ ከግብረ አበሮቹ ጋር በመመሳጠር፣ "ወደውጭ አገር ሄጄ ለመኖር ስለወሰንኩኝ ሦስት ሚሊዬን ብር የሚያወጣ ባለ ሦስት ፎቅ ቤት ስላለኝ ግዙኝ" በማለት የሐሰት ካርታ አቅርቦ አንድ ሚሊዮን 600ሺ ብር ቀብድ ይዞ ጠፍቷል፡፡

ገንዘቡ በሀገረ ስብከቱ ለብዙ ጊዜ የተጠራቀመና የሠራተኞችንም ደመወዝ የሚያካትት መሆኑን፣ በሕግም ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው የገለፁት አባ ዘካርያስ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ከሚገኙ ምዕመናን፣ ከበጎ አድራጊዎችና ከግለሰቦች ዕርዳታ በመጠየቅ ገንዘቡን ለመመለስ ይችሉ ዘንድ ቅዱስ ፓትርያርኩና በሲኖዶስ ተፈቅዶ እንዲሰጣቸውና ለሚመለከታቸው ሁሉ ደብዳቤ እንዲፃፍላቸው መጠየቃቸውን በፊርማቸው ተረጋግጦ የተላከው ደብዳቤ ያመለክታል፡፡

3 comments:

Anonymous said...

Hi Ahunis Abezachihut. Find out another issue. Do not make us to hate our fathers.

orthodoxawit said...
This comment has been removed by the author.
orthodoxawit said...

Dear Anonymous
I agree with you some times and think - we, Christian of this generation, have become fault finders. But then I think this patriotism is a result of the continuous assault that the Church and its followers have received from the time its creator, founder and our Lord Jesus Christ was crucified on the cross.
ታሪክንም ስንመለከት አርዮስን አትናቴዮስ ንስጥሮስን ቄርሎስ እንዲሁም ያዕቆን ዘአልበርዲና ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ አናቶቻቸው ላቆዪአት ቤተክርሰቲያን ተጋድሏቸውን ቀጥለዋል፡፡በሀገራችንም ዮዲት ያጠፋችውን አንበሳውድም ደግመው እንዲሠሩ አድርጓል፡፡ቤተ ክርስቲያንን ከግራኝ አሕመድን ጭካኔ የተሞላበት ጥፋት ያሳረፋት አፄ ገላውዲዮስም ከርሱም በኋላ የተነሱ ቅዱሳን አባቶቻችን የሚሰማውን በምክር የማይመለሰውን በውግዘት ለጠላት ድግሞ በሰማዕትነት እራሳችውን በመስጠት ቤተ ክርስቲያንን አዚህ አንድትደርስ አድርገዋል፡፡ ሰለዚህ እኛም እንደ አባቶቻችን መሆን ባንችል እንኳን በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥፋት የሚያድርስን ስናይ እናም እርግጠኛ የሆነ መረጃ ከኖረን ላላወቀ ማሳወቅ ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነው፡፡
ሌላው ድግሞ
በማቴ 24-15 …እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል… ይላል
ይህ ቃል በቤተ ክርስቲያንና ለእግዚአብሔር በተለየ ቦታ ትክክል ያልሆን ሥራ የሚስራን ብናይ(ቢያጋጥመን) እንዳንሰናከል ስፍራችንን እንዳንለቅ የሚያሳስብ ነው ድግሞም እንዲህ ተብሏል
በዕብ 13 – 7 ….የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው..
So our worry should be how we can avoid such incident from happening - discovering a fault is half a solution.
What can we do?
1. Had our Church had a well established financial system (Professionals and IT system) such errors and corruptions could have been easily caught.
2. How can we share the experience from other churches (Copts, Syria, Greek even the catholic and protestants) in improving the work flow of our church.
3. How can we introduce our church to other non Ethiopians
4. How can we preserve the Church wealth and the ancient Clerical Schools?
We should wake up - this is not the time to sit back and watch something goes wrong - it is not time to bite our lips - we have to get up and get involved - give what we have with loyalty and humility.

EgeziAbeHer BeteKristianachenen yetbek
LOM

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)