June 30, 2009

ፓትርያርኩ በቅ/ሲኖዶስ የተሠየመውን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አገዱ

(DEJE SELAM):-
(አዲስ ነገር ጋዜጣ፤ አብርሃም በጊዜው):- ግንቦት 26/2001 ዓ.ም በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ የተቋቋመውና ሰባት ሊቃ ነጳጳሳት የሚገኙበት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በብፁዕወቅዱስ ቡነ ጳውሎስ በተጻፈ ደብዳቤ ታገደ።
ፓትርያርኩ በፊርማቸው ሐሙስ ዕለት (June 25/2009) ያወጡት የእግድ ደብዳቤ በአድራሻ ለኮሚቴው ሰብሳቢ ለብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የተጻፈ ቢሆንም የኮሚቴው አባላት ለሆኑት ጳጳሳት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚ/ር፣ ለብሔራዊ ደህንነት መረጃ አገልግሎት፣ ለፌዴራል እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች በግልባጭ እንዲደርሳቸው መደረጉን የአዲስ ነገር ምንኞች አረጋግጠዋል። ፓትርያርኩበዚህ ደብዳቤ “ግንቦት 26 ቀን 2001 ዓ.ም የተሰየመው ኮሚቴ ከዛሬ ሰኔ 18 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ ከሥራ አስፈጻሚነቱ ተግባር ታግዷል” ሲሉ አሳውቀዋል።
በደብዳበኔ ቁጥር ል/ጽ/637/2001 የተበተነው የፓትርያርኩ የእግድ ትእዛዝ ውሳኔው የተላለፈው ረቡዕ ዕለት በተካሄደው “የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባዔ” መሆኑን ይገልጻል። በዚህ ጉባኤ ላይ ውሳኔ የተላለፈባቸው የኮሚቴው አባላትም ሆኑ በርካቶች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አለመገኘታቸውን በስብሰባ የተሳተፉ ታዛቢዎች ለአዲስ ነገር ገልጸዋል። በጉባኤው የተሳተፉት የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች መሆናቸው ቢታወቅም ትክክለኛ ቁጥራቸውን ለማረጋገጥ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

የቅዱስ ፓትርያርኩ ደብዳቤ ኮሚቴው የተቋቋመው “የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊ አስተዳደር የማስፈጸም አቅም ለማጎለበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንዲሠራ” እና እስከ ሐምሌ ወር ውስጠ ደንብ እንዲዘጋጅለት፤ እስከዚያው ግን “በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤና በቋሚ ሲኖዶስ ደንብ እንዲዘጋጅለት፤ እስከዚያው ግን “በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤና በቋሚ ሲኖዶስ ተወስነው የተጓተቱ ጉዳዮችን እየተከታተለ” እንዲያስፈጽም እንደነበር ይገልጻል። ይሁንና ኮሚቴው “ቤተ ክርስቲያኒቱ ከምትደዳርባቸው ከሕገ ቤተ ክርስቲያን፤ ከቃለ ዓዋዲውና ከሠራተኞች አስተዳደር ሕጎች ውጭ የሆነ አሠራር በመፈጸም ያልተጠበቀ ችግር በመፍጠር አላስፈላጊ ጽሑፎችን ያስተላልፋል ብለን አልገመትንም ነበር” ሲል ለእግዱ ምክንያት የሆኑተርን ችግሮች ይዘረዝራል።
ለዚህም በቀዳሚነት የሚነሣው ኮሚቴው ባለፈው ሳምንት የፓትርያርኩን የጣልያን ጉዞ፣ የሠራተኞች ዝውውርና ድልድል እንዲሁም አዲስ ሹመት በተመለከተ ማብራሪያዎች እንዲሰጡትና እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ያጻፋቸውን ደብዳቤዎች ነው። ይኸው ደብዳቤ የሥራ አስፈጻሚውን ተግባር “የሥልጣን ተዋረዱን ያልጠበቀ” ነው ብሎታል። “የሥራ አስፈጻሚው ተግባር የተጓተቱ ጉዳዮችን እንዲያስፈጽም እንጂ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላኢ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የተሰጠውን ሐላፊነት ድርሻ በመጋፋት ወይም የበላይነቱን ሥልጣን በመያዝ ቤተ ክህነቱን ተክቶ እንዲሠራ ኤኢደለም” ሲል ከሷል።
በዚህ ተግባሩ “የአስተዳደር ጉባኤው” ስድስት ውሳኔዎችን በማስተላለፍ እንዲፈጸሙ አዟል። በውሳኔው መሠረትም ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የከፈተው ጽሕፈት ቤት በአስቸኳይ እንዲዘጋ፣ ኮሚቴው ያሳተማቸው ክብ ማህተም፣ ቴተርና ሄዲንግ ማዘዣ ወረቀቶች የቤተ ክርስቲያኒቱን ቃለ ዓዋዲ እና ሕገ ቤተ ክርሲያኑን የጣሱ በመሆኑ በሥራ ላይ እንዳይውሉ ይላል።
በተጨማሪም ሥራ አስፈጻሚው “በሚያከናውነው ሕገ ወጥ ተግባር” ከጀርባው “የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና ደንብ መዋቅርንም ጭምር ለማፍረስ የተዘጋጀ አካል እንዳለ ስለሚያመለክት አስፈላጊ ክትትል እንዲደረግበት” ይላል። በአራተኛው ውሣኔው ላይ በሥራ አስፈጻሚው የተላለፉት “ሕገ ወጥና ፀረ ሰላም ጽሑፎች” በኢንተርኔት እና በአዲስ ነገር ጋዜጣ በመውጣታቸው የኮሚቴው አባላት እንዲጠየቁ እና የአዲስ ነገር አዘጋጅም በሕግ እንዲጠየው ሲል ጠይቋል።
በማያያዝም ሥራ አስፈጻሚው ባለፈው ሳምንት ማብራሪያ የጠየቀበትና ከሕግ ውጭ ተካሄደ ያለው የፓትርያርኩ የውጭ አገር ጉዞ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ዕውቅና የሚጠቅም በመሆኑ “ቀጣይነት እንዲኖረው የአስተዳደር ጉባኤው አምኖበታል” ሲል የኮሚቴውን ውሳኔ ተቃውሟል። በመጨረሻም የኮሚቴው አባላት ላሳዩት እንቅስቃሴና ለፈጠሩት ውዥንብር “በሕግ ፊት እንዲቀርቡና እንዲጠየቁ” መወሰኑን አስታውቋል። የኮሚቴው አባላት የሆኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ይህንኑ በመረዳት በአስቸኳይ በተመደቡበት ሀገረ ስብከት ተገኝተው መደበኛ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ሲል ደብዳቤው ትእዛዝ አስተላልፏል።
እርምጃው በፓትርያርኩ እና በኮሚቴው መካከል ሲብላላ የቆየው ሽኩቻ ከፍተኛ መገለጫ ተደርጎ ተወስዷል። ቀደም ሲል ባቀረብናቸው ተከታታይ ዘገባዎች ቅዱስ ሲኖዶስ ያቋቋመው አዲስ የ ራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ፓትርያርኩን በአስተዳደራዊ ሥራዎች የሚኖራቸውን ሥልጣን ይገድባል የሚል ግምት መኖሩን መግለጻችን ይታወሳል።

June 29, 2009

የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀጳጳስ አቡነ ሣሙኤል እና አቡነ ጢሞቲዎስ ከኃላፊነታቸው ታገዱ

(Reporter Sunday, 28 June 2009)
የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀጳጳስ አቡነ ሣሙኤል እና አቡነ ጢሞቲዎስ ከኃላፊነታቸው ታገዱ
የሐገረ ስብከቱ የባንክ ሒሳብ ታግዷል

በታምሩ ጽጌ

(DEJE SELAM) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀጳጳስ አቡነ ሣሙኤል እና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ አቡነ ጢሞቲዎስ ከሰኔ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ከኃላፊነታቸውና ከሥራቸው መታገዳቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ጋዜጣ ገለፁ፡፡

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኙ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና ከሊቃውንት ጉባኤ ዕውቅና ውጭ መንፈሳዊ አገልግሎትን ስለማስተላለፍ የተሰራጨው ትምህርተ ቀኖና፤ ቤተ ክርስቲያንን የሚያፋልስና በቤተ ክርስቲያን ላይ የተሰነዘረ የድፍረት ድርጊት መፈፀማቸውን በመግለፅ፣ ጉባኤው ተጠንቶ በቅዱስ ሲኖዶስ እርማት እስከሚሰጥበት ድረስ ረዳት ሊቀ ጳጳሱ ከኃላፊነታቸውና ከሥራቸው ታግደው እንዲቆዩ በሚል ባስተላለፉት ጥሪ መሠረት መታገዳቸውን ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡፡

በብፅዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ሰኔ 18 ቀን 2001 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ፀሐፊዎች ለአንድ ቀን ባደረጉት ስብሰባ፣ ለቤተ ክርስቲያኗ ሠራተኞች እየተላለፈ ያለ ህገወጥ ደብዳቤ በመኖሩ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ መሆኑን፣ በሐገረ ስብከቱ በኩል ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ የእምቢተኛነት መንፈስ ከመታየቱም በተጨማሪ፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሚተላለፉ መመሪያዎችም ሆኑ ውሳኔዎች ምላሽ በማይሰጥባቸው ደረጃ ላይ መደረሱን መግለፃቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤና በቋሚ ሲኖዶስ ተወስነው ያልተፈፀሙ ጉዳዮችን እየተከታተለ የሚያስፈፅም አንድ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ቢቋቋምም የሐገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በኮሚቴው ስም ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ፣ ለመምሪያዎች፣ ድርጅቶችና ለሠራተኞች ባስተላለፏቸው ተደጋጋሚ ደብዳቤዎች፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቃለ ዓዋዲ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑና የመሥሪያ ቤቱ መዋቅር እንዲጣስ መደረጉን በስብሰባው ወቅት ትኩረት የተሰጣቸው ነጥቦች መሆናቸውን ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ረዳት ሊቀ ጳጳስ በኩል እየታየ ያለው ችግር በቅርብ የተከሰተ አለመሆኑን የገለፁት የጉባኤው ተሳታፊዎች፣ ድርጊቱ የቆየና የኖረ መሆኑን፣ ከላይ የመጣ መመሪያን ያለመቀበል ብቻ ሳይሆን ከታችም መመሪያን ተቀብሎ ማስተናገድ ባለመቻሉ፤ የአብያተ ክርስቲያናቱ አገልጋዮች ኑሮአቸው የሰቀቀንና "ነገ ምን ይገጥመን ይሆን?" የሚል የሥጋት ኑሮ መሆኑ በምሬት መወሳቱን ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡፡

የጉባኤው ተሳታፊዎች ጨምረው እንዳስረዱት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ሀገረ ስብከት መሆኑ በሕግ መደንገጉን አስታውሰው "ፓትርያርኩም ሆኑ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ቢጠሯችሁ፣ መመሪያ ቢሰጣችሁም እንዳትቀበሉ" በማለት ከሐገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሕገ ወጥ ደብዳቤ ቢተላለፍላቸውም፤ ትዕዛዙን ጥሰው በጉባኤው ላይ ሊገኙ መቻላቸውን መግለፃቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

በሀገረ ስብከቱ በየአብያተ ቤተ ክርስቲያናቱ የተመደቡ ሠራተኞች፤ ለመዳቢዎቻቸው ጥቅም አሰባሳቢ ሆነው ካልተገኙ አኗኗራቸው አደጋ ላይ የወደቀ መሆኑን እንደሚገለፅላቸው የተናገሩት የስብሰባው ተሳታዎች፣ በሀገረ ስብከቱ የሕንፃ ግንባታና በሌሎችም ሙስና በተካሄደባቸው ዘርፎች ጥያቄ እንዳላቸው በመግለፅ ቅዱስ ሲኖዶሱ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

የጉባኤው ተሳታፊዎች በሀገረ ስብከቱ እየተከናወነ ያለውንና የእምነቱ ተከታዮች ምዕመናንን ያሳዘነ በርካታ አሳፋሪ ተግባራትና የስነ ምግባር ጉድለት በተለይም የጥንታዊ ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት በሚቃረን መልኩ ቅዳሴን፣ ፀሎትና ትምህርት በኢንተርኔት መረብ መከታተልና መፈጸም እንደሚቻል ያስተላለፉትን መልዕክት አበክረው እንደሚቃወሙት መግለፃቸውን ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ እና ንቡረዕድ አብርሃ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረው የአንድ ቀን ውይይት ሰባት ነጥብ ያለው የአቋም መግለጫ በማውጣት መጠናቀቁን ምንጮች ገልፀዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ጋር የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ አቡነ ጢሞቲዎስም የታገዱ መሆናቸውን፣ ነገር ግን ሰኔ 19 ቀን 2001 ዓ.ም. ወደ ቅዱስ ፓትርያርኩ በመመለስ ይቅርታ ጠይቀው በመታረቃቸው ምናልባት እግዱ ሊነሳላቸው እንደሚችል ምንጮቹ ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሣሙኤልን አግኝተን ለማነጋገር በተደጋጋሚ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ላይ ብንደውልም ሊያነሱልን ባለመቻላቸው ሳይሳካልን ቀርቷል፡፡

June 26, 2009

ፓትርያርኩ የቅ/ሲኖዶሱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ላይ ጦርነት ከፈቱ(DEJE SELAM)ከሮም ጣሊያን ጉብኝታቸው ባለፈው ረቡዕ ወደ አዲስ አበባ የተመለሱት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ መጓዛቸውን ተቃውሞ ደብዳቤ የጻፈባቸው የቅዱስ ሲኖዶስ ሥራ አስፈጻሚ ላይ “ጦርነት መጀመራቸውን” የአዲስ አበባ ምንጮቻችን ገለጹ።
ለጂ-8 ጉባዔና ለ”ኢትዮጵያ ቀን” ዝግጅት ሮም የሰነበቱት ፓትርያርኩ በራሳቸው ፈቃድ ካደረሱት ጉዞ በተመለሱበት ዕለት የአዲስ አበባ ሊቃውንት ከ6ኤ.ኤም ጀምረው ተሰልፈው እንዲጠብቋቸው የተደረገ ሲሆን ተቃዋሚዎቻቸው የተባሉ ብፁዓን አባቶችንና ዜናዎች ያወጡ ጋዜጦችን የሚሰድቡ ዘለፋ አዘል “ቅኔዎች” ሲቀርቡ ተሰምቷል። በብዙ ሚሊዮን ብር የሙስና ተግባር ከተራ ግለሰብነት ወደ ሀብታምነት ተሸጋግሯል በሚባለው በወንድማቸው ልጅና የቤተ ክርስቲአን ሕንጻዎችን በትንሽ ገንዘብ በመከራየት መልሰው በብዙ ትርፍ በማከራየት ሀብት በማግበስበስ ላይ ናቸው በሚባሉት በወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ አስተባባሪነት በነቂስ እንዲወጡና ፓትርያርኩን እንዲቀበሉ የተደረጉት ሊቃውንቱ “ከርስዎ ጋር ነን” የሚል መልእክት እንዲያስተላልፉ መገደዳቸውን ምንጮቻችን ዘግበዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቅ/ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከወደቀችበት የሙስናና የዘረኝነት አዘቅት ወጥታ የተሰጣትን ሐዋርያዊ አገልግሎት ለመፈጸም ትችል ዘንድ አንድ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ማቋቋሙ የሚታወስ ሲሆን የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብት በመዝረፍ ላይ የሚገኙ ወገኖች ከሚቴው ሥራውን እንዳይጀምር ከፍተኛ ዘመቻ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የዚህ ፀረ-ሲኖዶስና፣ ፀረ ብፁዓን አባቶች እንቅስቃሴ መሪ ናቸው የሚባሉት የጥንቷ የአርቲስት መሐሙድ አሕመድ ባለቤት፣ የዛሬዋ የፓትርያርኩ አወዳሽ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ሲሆኑ ወ/ሮዋ አሜሪካን ሀገር በሚዘጋጀው በሀገር ፍቅር ራዲዮ ሳይቀር ቃለ ምልልስ በመስጠት የአባቶችን ክብር በመጋፋት ላይ ይገኛሉ። ይሄው ፀረ-ሲኖዶስ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ሐሙስ ዕለት የመላው አዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ያለ ሀ/ስብከቱ ዕውቅና ተሰብስበው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባል የሆኑት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልንና የኮሚቴው ሊቀመንበር የሆኑትን የ ቅ/ሥላሴ ዲን ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስን እንዲያወግዙ ሲነገራቸው ውሏል። የስብሰባው ጥሪ ሕጋዊ እንዳልሆነ የተነገራቸው አስተዳዳሪዎች በስብሰባው ሳይገኙ ሲቀሩ የፓትርያርኩን ብቀላ ፈርተና ል ያሉና በዝምድናና በጥቅም ተሿሚነት የሚታወቁ ምንደኞች ደግሞ በሥፍራው በመገኘት ሲያሟሙቁ መዋላቸው ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሮም ጉብኝታቸው ቤኔዲክት 16ኛን ያገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ታቦተ ሙሴን በሙዚየም አስቀምጬ ለዓለም አሳያለሁ ማለታቸውን “ወርልድኔት ዴይሊ” የተባለ የዜና ተቋም መዘገቡ ታውቋል። ዛሬ አርብ ታቦተ ጽዮንን እንደሚያሳዩ መናገራቸው የተጠቀሰው ፓትርያርኩ ራሳቸውም ታቦተ ጽዮንን እንዳዩ ተናግረዋል ተብሏል። ዜናው በታዋቂ ዓለማቀፋዊ የዜና አውታሮች ያልተዘገበ ሲሆን ነገሩን በብቸኝነት ያቀረበው “ወርልድኔት ዴይሊ” ብቻ ነው። ዜናው ትክክለኛ ይሁን ወይም ሆን ተብሎ የፓትርያርኩን ስም ለማጉደፍ የተደረገ ወደፊት የሚታወቅ ይሆናል።

June 20, 2009

የቅዱስ ሲኖዶስ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የቅዱስ ፓትርያርኩን ጉብኝት ተቃወመ

የቅዱስ ሲኖዶስ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የቅዱስ ፓትርያርኩን ጉብኝት ተቃወመ
(Deje Selam):- በግንቦት 2001 ዓ.ም የቅ/ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ የተመረጠው አዲሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ቅዱስ ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያለ ቅ/ሲኖዶስ ፈቃድ ወደ ውጪ ለጉብኝት መሄዳቸውን በመቃወም ደብዳቤ መጻፉ ተሰማ። “በጂ-8 በሚካሄደው የተለያዩ ሀገራት የሃይማኖት መሪዎች ስብሰባ ላይ እንዲገኙ” የጣሊያኑ ፕሬዚደንት ባቀረቡላቸው ጥሪ እንዲሁም “የኢትዮጵያ ቀን በዓል ላይ ለመገኘት ወደ ጣሊያን” የተጓዙት ቅዱስ ፓትርያርኩ ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ “የፓትርያርኩ ማንኛውም ጉዞ በቅ/ሲኖዶስ ዕውቅና” እንዲሆን ማለቱን ከግምት ውስጥ አለማስገባታቸውን በመንቀፍ እንደጻፈላቸው ምንጮቻችን ገልጸዋል።

በርግጥም ሥራ አስፈጻሚው የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ ለማስከበር ቆርጦ ከተነሣና የተባለውን ደብዳቤ ከጻፈ እርምጃው በቅርብ ጊዜ የቤተ ክርስቲአኒቱ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ለውጥ ሊአስብል አንደሚያስችል ሐሳባቸውን እንዲያካፍሉን የጠየቅናቸው አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።
ከዚህም በተጫማሪ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ያለምንም መመሪያና ደንብ ለቤተ ክርቲያኒቱ የልማት ኮሚሽን ሥራ አስኪያጅነት ሊፈጸም የነበረውን ቅጥር ሕግ ያልጠበቀ ነው በማለት ቅጥሩ እንዳይፈጸም ደብዳቤ መጻፉም ታውቋል። የኮሚሽኑን የበላይ ሥልጣን የሚይዘውን ሰው ለመቅጠር ያለምንም መስፈርት መጠቀም አዲስ አለመሆኑን የገለጹት ምንጮቻችን “አይሆንም፣ ትክክል አይደለም” ሲባል ግን ይህ የመጀመሪያው ነው። ላለፉት ዓመታት ቦታውን በሃላፊነት ይዘው ይሰሩ ለነበሩት ግለሰብ ከ15 ሺህ ብር በላይ የኢትዮጵያ ገንዘብ ይከፈላቸው እንደነበረና ይህም በወቅቱ ቅሬታ አስነስቶ እንደነበር ይታወቃል።June 13, 2009

Deir Sultan Facebook Site Hacked?

(DEJE SELAM)
Dear Dejeselamaweyan,
Here is a message we got from a group concerned with "Deir Sultan". Please take a look at it and visit their website.
Cher Werre Yaseman,
Deje Selam

Dear frinds of Deir Sultan,
You may have noticed that our facebook group name was changed, from “Save Our Monastery”-to “Burn Our Monastery”. Please be advised that the Deir Sultan team did not change this name and we do not agree to the change.
Three days ago our facebook account was hacked into and our administrative ability was taken. While we are working to resolve the problem, please be advised that an irresponsible person has taken control of the discussion forum and is using it for his personal/institutional indulgence.
As you are well aware of the importance of Deir Sultan, you can appreciate that there are some groups that are trying to disrupt our movement. As the film is very critical and brings out the bare naked truth, such act is expected and might even escalate. So please be patient with us until we resolve this problem. If you get a chance, please also report this action as an abuse to facebook to pressure them to act quickly.
This is not the first time such an attempt was made to hinder our effort. We have received several demonizing e-mails trying to undermine our efforts. We have faced obstacles at every step of our activities. We knew how challenging and difficult embarking on this journey would be, but we believe that together we can make a difference and save our monastery, whether they like it or not!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

May God Bless you for your Efforts!!!
P.s.the screening is as scheduled for Sunday June 07 2 4:00 p.m. at Bloor cinema


SAVE OUR MONASTERY!!!!!!
www.deirsultan.com
www.orthodoxfilm.com
http://www.youtube.com/watch?v=2NdHTVx2hT0
http://www.facebook.com/group.php?gid=119888385622

June 12, 2009

Ethiopian Muslim Professor Died


Ethiopian muslim professor, ardent supporter of Islam in the country is dead. Professor Hussein Ahmed was history professor at the Addis Ababa university and strong critic of Ethiopian Christianity. The professor was an accademic corner stone for their cause.

The following is an article taken from hardliner Negashi website.
"ፕሮፈሰር ሁሴን አህመድ ከአባታቸው አቶ አህመድ ሀጂና ከእናታቸው ከወ/ሮ አሚናት ሲራጅ በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ልዩ ስሙ ገዳም አንቻሮ በሚባለው ስፍራ መስከረም 12 ቀን 1945 ዓ.ም ተወለዱ። እድሚያቸው ለትምህርት ሲደርስም የቁርዓን ትምህርታቸውን በዚያው በተወለዱበት ቦታ አጠናቀዋል። ከዚያም መደበኛ ትምህርታቸውን አንቻሮ ከጀመሩ በኋላ ወደ ደሴ በመሄድ በእቴጌ መነን ትምህርት ቤት የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተምረዋል። ከዚያም ወ/ሮ ሲሂን ሁለተኛ ትምህርት ቤት ገብተው እስከ 11ኛ ክፍል ከተማሩ በኋላ በነበራቸው ከፍተኛ ዉጤት በወቅቱ በዕደማርያም ይባል ወደነበረው ትምህርት ቤት የመግባት እድል አግኝተው ወደ አዲስ አበባ መጡ። ከዚያም የተሰጣቸውን ትምህርት በሚገባ አጠናቀው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ክፍል ፋካልቲ በመግባት የታሪክ ትምህርት ተምረው በ1969 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ማዕረግ አግኝተዋል።

በዉጤታቸው ከፍተኛነት የተነሳ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማስተማር ዕድል አግኝተው ከመስከረም 1970 ህይወታቸው እስካለፈበት ግንቦት 30 ቀን 2001 ዓ.ም ድረስ ለ31 አመታት ከፍተኛ ዉጤት ያመጣ የማስተማርና የምርምር ስራ አከናውነዋል።

ፕሮሰር ሁሴን አህመድ የነበራቸውን እውቀት ለማሻሻልና ለአገራቸና ህብረተሰባቸው የሚኖራቸውን አገልጋሎት ለማሳደግ በነበራቸው ልዩ ፍላጎትና ለዚህም ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት በእንግሊዝ አገር ከሚገኘው በርሚንግሃም ዩኒቨርሲቲ በ1974 ዓ.ም በታሪክ የማስትሬት ዲግሪያቸውን ከዚያም በታህሳስ ወር 1978 ዓ.ም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል።

ፕሮፌሰር ሁሴን በተለይ የእስልምና ሀያማኖት በወሎ ስለነበረውና አሁንም ስላለው ሁኔታ ሰፋ ያለ ጥናት በማካሄድ ከ35 የጥናት ዉጤቶችን እዉቅ በሆኑ የጥናት መጽሄቶች (ጁርናል) ላይ ያሳተሙ ሲሆን በ1995 ዓ.ም. ባሳተሙት Islam in the 19th Century Wallo - Revival, Reform and Reaction በሚለው መጽሀፋቸው አለም አቀፍ እዉቅናን በማግኘት ታላቅ ምሁረታቸውን አስመስክረው አልፈዋል። በተለያዩ አገሮች በተዘጋጁ የኢትዮጵያና የታሪክ ጥናት ጉባኤዎች ላይ የምርምር ውጤታቸውን በማቅረብ ንቁና ውጤታማ ተሳታፊ ከመሆን አልፈው ለኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር መጎልበት ሌት ተቀን ይሰሩ የነበሩ መሆናቸውን የስራ ባልደረቦቻቸውና የጥናት ውጤታቸውን የተከታተሉ ይናገራሉ። ፕሮፌሰሩ በማስተማርና የምርምር ስራቸው ያሳዩትን ታታሪነትና ትጋት እንደዚሁም በየጊዜው ላሳተሟቸው የጥናት ዉጤቶች ከፍተኛ እውቅና በማግኘት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በየካቲት 1995 የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ተረክበዋል።

ከማስተማርና የምርምር ስራቸው በተጨማሪ ፕሮፌሰር ሁሴን የቅድመና ድህረ ምረቃ በአገር ዉስጥና በውጭ ሀገር ተማሪዎችን የማማከር አገልግሎት በመስጠት ለአገራቸው እንደዚሁም ለታሪክ ትምህርት እድገት የራሳቸውን አስተዋጾን አበርክተው አልፈዋል። በዩኒቨርሲቲው ባገለገሉበት ወቅት ከመደበኛ ስራቸው በተጨማሪ የአስተዳደር ሀላፊነቶችንም በመረከብ የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ ሳይንስ ፋካልቲ ረዳት ዲንና የታሪክ ትምህርት ክፍል ሊቀመንበር በመሆን አገልግለዋል።

ፕሮፌሰር ሁሴን በህይዎት ዘመናቸው ትሁት፣ ስራ ወዳድና ተግባቢ የነበሩ ሲሆን የእስልምና ሀይማኖት ግደታ የሚያደርገውን የሀጂ ጉዞ በህዳር ወር 2000 ዓ.ም ወደ መካ በመጓዝ አከናውነው ተመልሰዋል።

ፕሮፌሰር ሁሴን ከወ/ሮ ፋጡማ ሀሰን ጋር ትዳር መስርተው ሶስት ሴቶችና አንድ ወንድ ልጅ አፍርተዋል።

ፕሮፌሰሩ በድንገት ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት በጥቁር አምበሳ ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት ሲደረግላቸ ቆይቶ በተወለዱ 56 አመታቸው ግንቦት 30 ቀን 2001 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። የቀብራቸው ስነ ስርዓትም እሁድ ሰኔ 01 2001 በኮልፌ በሚገኘው የሙስሊሞች መካነ መቃብር ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ፣ የስራ ባልደረቦትቻችውና ተማሪዎቻቸው በተገኙበት ተፈጽሟል።"

June 9, 2009

ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ድረ ገጾች የተለያየ ዘገባ እያቀረቡ ነው

ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ “የቅዱስ ፓትርያርኩን ስልጣን በመገደብ” ሥራውን ሊሠራ የሚችል የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ማቋቋሙን መዘገባችን ይታወሳል። ከዚያ በሁዋላ ዜናው በሁለት መልኩ ተተርጎሞ በመሠራጨት ላይ መሆኑን ለመረዳት ችለናል። “ኢትዮ ሚዲያ ፎረም” (EMF) የተባለው ፀረ መንግሥት ድረ ገጽ “(29 May 2009) Abune Paulos, a political appointee of the Ethiopian Orthodox Church, is removed from his administrative power” ሲል የመንግሥት ደጋፊ እና የሼህ አላሙዲን ጠበቃ ነው የሚባለው ethiopiafirst (ኢትዮጵያ ትቅደም?) በበኩሉ “The Patriarch of Ethiopia is still Abuna Paulos” የሚል ዘገባ አቅርቧል።
EMF ምንጮቼ እንደነገሩኝ ብሎ እንደዘገበው “ፖለቲካ ሹመኛው አቡነ ጳውሎስ” ከሥልጣናቸው ተወግደው በምትካቸው “የትናንቱ አባ ተከስተ ወልደ ሳሙኤል የዛሬው ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፣ ትግሬው፣ እና ከዋልድባ ጀምሮ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ሰላይ” ሊተኩ እንደሚችሉ ሲዘግብ ethiopiafirst በበኩሉ ይህንን ዜና ትክክል አለመሆኑን በመጥቀስ ምእመናን እንዲረጋጉ ጠይቋል።
በዚህ ረገድ “ደጀ ሰላም” ከመጀመሪያው ጀምሮ ዜናውን ለአንባብያን ያቀረበች ሲሆን በዚህ ረገድ የሚኖሩ ተጨማሪ ለውጦችን በማቅረብ ትቀጥላለች። ከላይ ተጠቀሱትን ሁለት ጽንፍ የያዙ ድረ ገጾች ዜናዎች ስንመለከታቸው ሁለቱም የተሳሳቱ መረጃዎች እንዳላቸው እንገነዘባለን። EMF የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ አውርዶ የአቡነ ሳሙኤል በማድረጉ፣ ethiopiafirst ደግሞ ነገሩን ሙሉ በሙሉ በመካድ ምንም እንዳልተፈጠረ ማድረጉ ትክክል እንዳልሆነ መግለጽ እንወዳለን።

June 5, 2009

NEW STUDY SHOWS HOW SAUDI TEXTBOOKS TEACH CHILDREN TO HATE JEWS AND CHRISTIANS

Washington, DC 06.03.09– With President Barack Obama in Saudi Arabia today, a new study shows how textbooks currently used in middle and high schools in the Kingdom are teaching children to hate Jews and Christians and to use violent means against them.Representatives Anthony D. Weiner (D – Brooklyn and Queens), Joseph Crowley (D – Queens and Bronx), and Shelley Berkley (D – Las Vegas) released the report of translated 2009 Saudi textbooks, documenting an on-going pattern of hate, anti-Semitism, and violence taught in Saudi Arabian schools.

In a letter to President Obama, Weiner condemned the hate-filled teachings and urged the President to address the issue during his meetings with Saudi officials this week.

Textbooks used in Saudi Arabian schools are not widely available to the West. In fact, the Saudi Arabian government and its Ministry of Education do not share the textbooks used in their schools and have ignored requests from U.S. officials to receive copies of the textbooks.

The Institute for Gulf affairs, a nonpartisan organization that studies the Gulf region, worked with a resident of Saudi Arabia to smuggle the text books out of Saudi Arabia to the United States and then translate them for this report.

Hateful Teachings in Saudi Textbooks

1. Students are taught: “The Prophet said, “The hour [of judgment] will not come until the Muslims fight the Jews and kill them. [It will not come] until the Jew hides behind rocks and trees. [It will not come] until the rocks of the trees say, ‘O Muslim! O Servant of God! There is a Jew behind me. Come and kill him.” [Source: Al Hadeeth wa Athaqafah (Sayings of the Prophet and Islamic culture.) Page 148, 2009. Taught in 9th grade, age 14.]

2. In Grade 10, students are taught: “The blood money for a Muslim woman is half of the blood money for a male Muslim, and the blood money for an infidel woman is half of the blood money for a male infidel.” [Source: Fiqh (Jurisprudence.) Page 65, 2009. Taught in 10th grade, age 15.]

3. “The punishment for homosexuality is death….” [Source: Fiqh (Jurisprudence) Page 100, 2009, Age 16.]

4. “The apostate (Muslims who convert, question or doubt Islam) is required to repent to the ruler. If he repents and returns to Islam, it is accepted and he is left alone. If he refuses it is mandatory that the ruler kill him.” [Source: Towheed (Monotheism.) Page 33, 2009. Taught in 12th grade, age 17.]

5. “The Goals of Zionist-Movement: Instill a fighting spirit among the Jews, as well as religious and nationalist fanaticism to challenge [other] religions, nations, and peoples; Establish Jewish control over the world; Incite rancor and rivalry among the great powers so that they fight one another, and kindle the fire of war among states so that all states are weakened and their state arises.” [Source: Al Hadeeth wa Athaqafah (Sayings of the Prophet and Islamic culture.) Page 114, 2009. Taught in 10th grade, age 15.]

The Saudi Arabian school system maintains nearly 32,000 schools, with over 400,000 academic staff educating over 5 million students. In addition, Saudi Arabia runs academies in 19 world capitals and distributes texts worldwide to Islamic schools and madrassas.

For years, the Saudi leadership has said that they are working to reform their education system and remove examples of hateful teachings. And yet, the current 10th grade textbook, Towheed, which translates to “Monotheism,” was written by a Wahabi extremist named Sheikh Saleh Al-Fawazan who was quoted as saying “slavery is a part of Islam” and whoever wants it abolished is “an infidel.”

Weiner, a long-time critic of Saudi Arabia, is the author of the Saudi Arabia Accountability Act of 2009, a bill that encourages the Saudis to cooperate with the U.S. the investigation of terror groups and close all organizations in Saudi Arabia that fund, train, encourage, or in any way aid terrorism anywhere in the world.

Ali Al-Ahmed, Director of The Institute for Gulf Affairs, said, “The Saudi textbooks agree more with Al-Qaeda’s ideology more than it agrees with the values of Islam. Their education system must respect the diversity in Saudi Arabia, the Muslim world and world cultures and faiths, especially Judaism and Christianity.”

Rep. Berkley said, “The Saudis continue to instruct students in the ABC’s of hatred and violence, even after pledging to stop the spewing of this venom aimed at Jews, Christians and other non-Muslims. Until ‘killing the infidel’ in no longer a part of the Saudi lesson plan, we will remain skeptical about their interest in ending bloodshed in their region. The Saudis must show their commitment to peace by putting an end to these dangerous, hate-filled lessons that serve only to foster intolerance and promote violence.”

Rep. Weiner said, “The Saudis teach hate and violence. They fund and export terror. They obstruct Middle East peace. Turning over a new page with the Saudis must start with them reforming their education system.”

June 4, 2009

ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለፓትሪያርኩ የድረሱልኝ ጥሪ አቀረበ - 1.3 ሚሊዮን ብር ተመዝብሯል

Wednesday, 03 June 2009
ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለፓትሪያርኩ የድረሱልኝ ጥሪ አቀረበ
- 1.3 ሚሊዮን ብር ተመዝብሯል
በታምሩ ፅጌ

(Reporter Newspaper): የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት በደብረ ማርቆስ ንግድ ባንክ በቁጠባ ሂሳብ 16349 እና በተንቀሳቃሽ ሂሳብ ቁጥር 266 ውስጥ ተጠራቅሞ የነበረ ከ1 ሚሊዮን 300ሺ ብር ያላነሰ ገንዘብ በሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ እና ሁለት ሰራተኞች ተመዝብሯል በማለት ለመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤትና ለምሥራቅ ጎጃም ፖሊስ ጽ/ቤት የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች አመለከቱ፡፡ግንቦት 18 ቀን 2001 ዓ.ም የተጻፈና የ14 ሰዎችን ፊርማ የያዘ ማመልከቻ እንደሚያስረዳው በተለያየ አካውንት ተቀምጦ የነበረውን ገንዘብ ባልታወቀ ጊዜና ሰዓት የአስተዳደሩ ጉባኤም ሆነ መላ ሰራተኛው ባላወቁትና ባልተረዱት ሁኔታ በስውርና በሕገወጥ መንገድ ተወስዷል፡፡

የተመዘበረው ከፍተኛ ገንዘብ ሠራተኛው ተረጋግቶ ስራውን እንዳይሠራ ከማድረጉም በተጨማሪ እንዲበተንና የቤተክርስቲያኗን ሕልውና የሚያናጋ መሆኑን ማመልከቻቸው ያስረዳል፡፡

ሠራተኞቹ በፊርማቸው አረጋግጠው የላኩት ማመልከቻ እንደሚያስረዳው የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ወደ አሜሪካ ተዛውረው ሊሄዱ መሆናቸውን በመጥቀስ፤ የደረሰበት ያልታወቀው ገንዘብ ወደ ነበረበት እስከሚመለስ ጉዞአቸው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥላቸው አሳስበዋል፡፡ በተመሣሣይ መንገድ የምሥራቅ ጎጃም ፖሊስ ጽ/ቤትም ትብብር እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡

ተፈጠረ የተባለውን ችግር አስመልክተን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤትን ኃላፊዎች በስልክ አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ባይሳካልንም፣ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የመንበረ ፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ሰራተኛ "ጉዳዩ የጳጳሳት በመሆኑ፣ በሲኖዶስ እንዲታይ ተወስኗል" ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል አባ ዘካርያስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ግንቦት 18 ቀን 2001 ዓ.ም. ለቅዱስ ፓትሪያርኩ በፃፉት ደብዳቤ ለቤተክርስቲያናቸው ይጠቅማሉ ያሏቸውን አንዳንድ ስራዎች ለመስራት በሚሞክሩበት ጊዜ የተለያዩ ችግሮች እንዳጋጠማቸው ገልፀዋል፡፡

ሊቀጳጳሱ በደብዳቤያቸው እንደገለፁት አንድ ግለሰብ ከግብረ አበሮቹ ጋር በመመሳጠር፣ "ወደውጭ አገር ሄጄ ለመኖር ስለወሰንኩኝ ሦስት ሚሊዬን ብር የሚያወጣ ባለ ሦስት ፎቅ ቤት ስላለኝ ግዙኝ" በማለት የሐሰት ካርታ አቅርቦ አንድ ሚሊዮን 600ሺ ብር ቀብድ ይዞ ጠፍቷል፡፡

ገንዘቡ በሀገረ ስብከቱ ለብዙ ጊዜ የተጠራቀመና የሠራተኞችንም ደመወዝ የሚያካትት መሆኑን፣ በሕግም ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው የገለፁት አባ ዘካርያስ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ከሚገኙ ምዕመናን፣ ከበጎ አድራጊዎችና ከግለሰቦች ዕርዳታ በመጠየቅ ገንዘቡን ለመመለስ ይችሉ ዘንድ ቅዱስ ፓትርያርኩና በሲኖዶስ ተፈቅዶ እንዲሰጣቸውና ለሚመለከታቸው ሁሉ ደብዳቤ እንዲፃፍላቸው መጠየቃቸውን በፊርማቸው ተረጋግጦ የተላከው ደብዳቤ ያመለክታል፡፡

“ ቤተ ክርስቲያን ከአደንዛዥ እጅ የነፃች ናት”


Selam Deje Selam,
“… የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት ማሪዋናን መጥነው በመጠቀም በቅዳሴ ወቅት ጥቅም ላይ ያውሉታል። ዝቋላና አክሱም ላይ ይህን እንደሚያደረጉ እኔ በግሌ አውቃለሁ። …” (ተስፋዬ ገብረ አብ)
I posted a comment on a book entitled "yegazetgnaw mastawosha" on my blog "Andit Betekirstian". If you can post it in your website, it would be great. If you can't find it on the blog. I have attached the book and my comment.
chur Ensenbit
“ ቤተክርስቲያን ከአደንዛዥ እጅ የነፃች ናት”

በቅርቡ “የጋዜጠኛው ማስታወሻ” በሚል ርዕስ በተስፋዬ ገብረ አብ በተጻፈው መጽሐፍ በገጽ 378 ላይ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ማሪዋናን በመጠኑ በቅዳሴ ላይ ትጠቀማለች” የሚል የሐሰት (ያለማወቅ) ውንጀላ ተፅፎ በማንበባችን በጣም አዝነናል:: ይህ ፍፁም ከእውነት የራቀ ከመሆኑም በላይ በራሱ በፀሐፊውና በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እርምት ሊሰጥበት የሚገባ ጉዳይ ነው::

ቅድስት ቤተክርስቲያን መድኃኔዓለም ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት፣ ሃዋርያት በስብከታቸው፣ ሰማዕታት በተጋድሎዋቸው ያስፋፏት በምድር ሆነን ከሰማያውያን ጋር የምንተባበርባት መንፈሳዊት ቤት ናት:: በዚች ቅድስት የእግዚአብሔር ቤት ያዘኑ ይጽናኑባታል፣የተረበሹ ሰላም ፣ ኃጥአን የኃጢአት ስርየት ያገኙባታል:: ምዕመናን በሙሉ ስለተደረገላቸው ነገር አምላካቸውን ያመሰግኑባታል:: ሊደረግላቸው የሚፈልጉትን ነገር ሁሉ አምላካቸው ያደርገው ዘንድ በጸሎት ይማጸኑባታል:: እግዚአብሔርም በዚያ በረድኤት ይገኛል:: የቀረበውን ጸሎት፣ምስጋና፣ቅዳሴ ተቀብሎ ለሁሉም እንደፍቃዱ ይሰጠዋል:: (1ኛ ነገ 9፥1-3)

እግዚአብሔር የሥርዓት አምላክ ነውና የእግዚአብሔር ቤት በምትሆን በቤተክርስቲያን ሁሉ ነገር በሥርዓት ይፈፀማል:: አንድም ነገር ቢሆን ያለ ሥርዓት
አይደረግም:: ይህ ደግሞ አገልጋዩን (ካህኑን) ምዕመናኑን ለአገልግሎት የሚውሉ ንዋያትን ሁሉ ይመለከታል:: የካህኑና የምዕመናኑን አለባበስ ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች በሙሉ ሥርዓትን የተከተሉ ናቸው:: ለአገልግሎት የሚውሉትም ነገሮች ዕጣኑ፣ መብራቱ፣ መስዋዕቱ፣ ንዋያተ ቅድሳቱ ሁሉ እርሱ ራሱ ለአገልግሎት እንዲውሉ በመጽሐፍ ቅዱስ የሰጠውን ትዕዛዝ መሠረት ያደረጉ እንጂ ሰው ሰራሽ አይደሉም::

ታዲያ ይህን ሰማያዊ አገልግሎት ያልተረዱ እንደ ተስፋዬ ገብረ አብ ያሉ ሰዎች በማያውቁት ገብተው ቤተክርስቲያንን ሲተቹ እንሰማቸዋለን:;

ቤተክርስቲያን በቅዳሴ ሰዓት የምትጠቀመው ዕጣን እንጂ ሌላ ምንም አይነት ነገር አለመሆኑን ቤተክርስቲያንን የሚያውቁ ሁሉ የሚመሠክሩት ጉዳይ ነው:: ይህ እጣን ደግሞ በምድር ባለችው ቤተመቅደስ ብቻ ሳይሆን በሰማይ ያሉ መላእክትም የቅዱሳንን ጸሎት ለማሳረግ የሚጠቀሙበት መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል:: / ራዕ 8 ፥3-4 / ከዚህ ውጭ የጌታን መከራ በምናስብባት በእለተ ዓርብ (ለስቅለት) ቤተክርስቲያን ‘ከርቤ’ ትጠቀማለች:: ይህም የጌታን የመከራውን ጽናት ለማሰብ ሲሆን ሰብአ ሰገል ለጌታ ከሰጡት እጅ መንሻ አንዱ ነው:: /ማቴ 2፥11/

ማሪዋና ግን የሰውን አዕምሮ ለተወሰነ ግዜ በመግዛት ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ እንዲዘነጋና በምኞት ባህር እንዲዋኝ ከሚያደርጉት አደንዛዥ እጾች አንዱ ነው:: ይህንን የመሰሉ አደንዛዥ ዕጾች (ጫት ፣ ሲጋራ ፣ ሀሺሽ ወዘተ.) ተጠቃሚውን በሱስ አስረው እንዳይጾም ፣ እንዳይጸልይ ፣ አምላኩን እንዳያገለግል የሚያከላክሉ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሆነውን የሰው አካል ለሌላ መንፈስ ማደሪያ የሚያደርጉ በመሆናቸው ቤተክርስቲያን ማንኛውም ሰው እራሱን ከእንዲህ ያለ ዕፅ እንዲያርቅ አጥብቃ ታስተምራለች::

እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ጸሐፊው ይህንን የመሰለ የሐሰት ውንጀላ በቤተ ክርስቲያን ላይ ለምን ሰነዘሩ? የሚለውን መመለስ የሚችሉት እራሳቸው ብቻ ቢሆኑም ምን አልባት ቤተክርስቲያንን ጠለቅ ብሎ ካለማወቅ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለኝ:: ስለዚህ ወደ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ቀርበው በመጠየቅ እንዲረዱና በቀጣይ እትማቸው ስህተቱን እንዲያርሙ ካደራ ጭምር ላሳስባቸው እወዳለሁ::

የቤተክርስቲያን ሊቃውንትም ጉዳዩ ቤተክርስቲያንን ያለግብሯ ግብር የሚሰጥ፣ የዋሃን ምዕመናንን የሚያስደነብርና ለመናፍቃኑ የስህተት ትምህርት ልዩ ርዕስ የሚሆን በመሆኑ ባፍ በመጣፍ መልስ ይሰጡበታል ብዬ አምናለሁ::

እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን!
Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)