April 15, 2009

አማኒያን (ምዕመናን) ላይ የእሥር ትዕዛዝ ሊወጣ ነው

አዲስ አባባ (ECADF) - ከሀይማኖት ጋር በተያያዘ ግጭቶችን የሚፈጥሩ ስራዎችን ሰርተዋል በሚል አማንያን ላይ የእስር ትእዛዝ ሊወጣ መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ገለጹ፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተከሰቱ ባሉት የክርስትና እና የእስልምና ሀይማኖት አስተምህሮቶች ላይ አንዳንድ ሰባኪያን ግጭት የሚፈጥሩ ቃላቶችን በመጠቀማቸው መንግስት በሀይማኖቶች ጉዳይ ጣልቃ የገባ ሲሆን ይህ ጣልቃ ገብነት ወደ እስራት ደረጃ ማደጉን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡ ሪፖርተራችን ያነጋገራቸው የሁለቱም ሀይማኖቶች የካሴት ሲዲ፣ ቪሲዲና መጽሀፍት አከፋፋዮች እንደገለጹት ወሬው እስካሁን ባይደርሳቸውም የሚጠብቁት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡


አንድ የእስልምና ሀይማኖት የሀይማኖታዊ ነክ መጽሀፍትና ካሴቶች አከፋፋይ እንዳሉት “መንግስት በግብታዊነት እርምጃ ሊወስድ አይገባውም፡፡ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች በጉዳዩ ዙሪያ ጠርቶ አነጋግሮን ምላሽ ሰጥተንበታል፡፡ በቅርቡም ከጠቅላይ ምክርቤቱ የተላለፈ መመሪያ ነው በሚል ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች መጅሊሱ ሳያውቀው እንዳይደረግ ተብሏል፡፡ በዚህ ሁሉ ቅሬታ እያለን የእስር ትእዛዝ የሚወጣ ከሆነ ችግሩ በቀላሉ የሚበርድ አይመስለኝም” ብለዋል፡፡

በቅድስት ሥላሴ መንፈሣዊ ኮሌጅ መምህር የሆኑ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ “በጭምጭምታ ደረጃ ነገሩን ሰምቸዋለሁ መንግስት ይህን ያደርጋል ብዬ አልጠብቅም፡፡ ሆኖም እየተደረጉ ያሉት “ሊደረጉ አይችሉም” የተባሉ ነገሮች ናቸውና ይህም ወደዚያው ማምራቱ አይቀርም፡፡ የሚሰማውም ከዚህ በላይ ነው መንግስት ነገር ማብረድ እንጂ ማባባስ የለበትም” ብለዋል፡፡

መንግስት በሀይማኖት ጉዳዮች ግጭት እንዲፈጠር ሙከራ አድርገዋል በሚል ሊያስርና ሊከስ የሚፈልጋቸው በቪሲዲ፣ በሲዲ፣ በመጽሀፍትና በመጽሄት ስራ ላይ የተሰማሩ አሳታሚዎች ሰባኪያን አከፋፋዮች ብቻ ሳይሆን በጉዳዩ ዙሪያ ተጠርጣሪ ናቸው ያላቸውን በሙሉ እንደሆነ ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

በተያያዘ ዜና መንግስት ሀይማኖት ነክ ግጭት የሚመክት ዓመታዊ እቅድ በቅርቡ አሰራጭቷል፡፡ ይኸው ከየካቲት 2001 እስከ መጋቢት 2002 ዓ.ም የሚያገለግለው እቅድ “ሀይማኖት ነክ ግጭትና አክራሪነትን ለመመከት. . .” የሚል ርእስ ያለው ነው፡፡ ሃያ ገጾች ያሉት ይኸው እቅድ በመጪው የ2002 ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ያግዛል በሚል እምነት የተዘጋጀ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ እቅዱ ለክልል መንግስታት እና ለሀይማኖት ተቋማት የተሰራጨ ሲሆን ክልሎች ከእቅዱ በመነሳት የየራሳቸውን አሰራር እንዲያወጡ የሚያዝ ነው፡፡ በዚሁ እቅድ ቁጥር 2.1.1 “ከቀጣይ ሀገር አቀፍ ምርጫ በፊት /ግንቦት 2002 በፊት/ በሀይማኖት ዙሪያ ግጭትና አለመረጋጋት የማይፈጠርበት አስተማማኝ ሁኔታ መፍጠር” የሚል አላማ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል፡፡
Source: http://ecadforum.com/blog/2009/04/11/103-ecadf-news-addis-ababa/

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)