April 27, 2009

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ያካሄዱት ሠላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ


በኃይሌ ሙሉ

(ሪፖርተር Sunday, 26 April 2009)“የሂጃብና የሶላት መብታችን ይከበርልን” ያሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አርብ እለት ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ የሀይል እርምጃ በመውሰድ ሰልፈኞቹን በትኗል፡፡ የተወሰኑ ተማሪዎችም መታሰራቸውንም ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን ገል..ል፡፡

በሠላማዊ ሰልፉ ላይ የተሳተፉ ተማሪዎች ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለጹት በመቶዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በደሴ፣ በኮምቦልቻና በቴፒ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ መልበስና ሶላት ማድረግ መከልከላቸው በመቃወም ሠላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

“እስላም የሠላም ሀይማኖት ነው፣ እኛ አሸባሪዎች አይደለንም፣ ኢትዮጵያዊነታችን እንወዳለን፣ ግለሰቦች በግል ጥላቻ የሚፈፅሙት የመብት ረገጣ ይቁም” የሚሉ መፈክሮች ሲያሰሙ የነበሩት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ መነሻቸውን ያደረጉት ፒያሳ ከሚያገኘው ኑር መስጊድ ነበር፡፡

የአይን እማኞች እንደገለገጹት ሠልፈኞቹ ተማሪዎች መሆናቸውን ለማሳየት እስክርቢቶ በእጃቸው ከፍ አድርገው በመያዝ መፈክር ሲያሰሙ ነበር፡፡ ከኑር መስጊድ የተነሱት እነዚሁ ሙስሊም ተማሪዎች በሲኒማ አምፔር አድርገው፣ ራስ መኮንን ድልድይን ተሻግረው አርባ ደረጃ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት “ሠላማዊ ሠልፉ የተፈቀደ ባለመሆኑ አግባብ አይደለም፣ ሠላማዊ ሰልፉን የማታቆሙ ከሆነ ግን የማስፈጽም ግዴታ ስላለብን ትጎዳላችሁ” የሚል ምክር ቢሰጧቸውም ተማሪዎቹ ሠልፉን ለማቆም ፈቃደኞች አልሆኑም፡፡ ፖሊስ ተማሪዎችን “ተመለሱ” እያለ ሲገፋ ተማሪዎቹ በበኩላቸው “አላሁ አክበር” እያሉ መልሰው ፖሊሶችን እየገፉ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ደረሱ፡፡ ከዚህ በኋላ ነው ፖሊስ የሀይል እርምጃ የወሰደው፡፡ የፖሊስ አባላት ከሠልፉ ፊት ያገኟቸውን ተማሪዎች በዱላ መምታት ሲጀምሩ ሠልፈኞቹ በየቦታው ተበታትነዋል፡፡

ከሠላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች መካከል አንዱ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለጸው ፖሊስ የሀይል እርምጃ መውሰድ ሲጀምር ከጥቃቱ ለማምለጥ የሞከሩ ሴቶች ሲወድቁና ቀሚሳቸው ሲቀደድ ተመልክቷል፡፡

“ያልተፈቀደ ሰላማዊ ሰልፍ ለምን አካሄዳችሁ?” በሚል ላቀረብንለት ጥያቄ ይሄው ተማሪ ሲመልስ “ያልተፈቀደ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄድነው ኃላፊነት ወስዶ ፈቃድ ሊጠይቅ የሚችል ሰው ስለጠፋ ይመስለኛል” ብሏል፡፡ፖሊስ ሰላማዊ ሰልፈኞቹን በሀይል ከበተነ በኋላ በግምት 70 የሚደርሱ ተማሪዎችን ያሰረ መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ የታሰሩት ወንድና ሴት ተማሪዎች ፎቶ ግራፍ በፖሊስ ጣቢያ ፎቶ ግራፍ መነሳታቸውንም ከምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ስንደውል “ጉዳዩ ገና እየተጣራ ነው” የሚል ምላሽ አግኝተናል፡፡

April 20, 2009

ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ?"ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ? የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው፤ ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። " 1ኛቆሮ 15÷ 55
ከመልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ላይ ከፈጸመ በኋላ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ወረደ ÷ ይኸውም በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረትን ሊያስቀር ነው፡፡ በአካለ ነፍስ ደግሞ ወደ ሲኦል ወረደ ÷ ይኸውም በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን ይሰብክላቸው ዘንድ ነው፡፡ መለኮት በተዋሕዶ ከሥጋም ከነፍስም ጋር ነበረ፡፡ ለዚህ ነው መቃብር ሥጋን ሊያስቀረው ያልቻለው ፡፡ ሲኦልም ነፍስን ማስቀረት አልተቻለውም ፡፡ ቅዱስ ዳዊት ፡- « ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተዋትምና ፤ » ያለው ይኽንን ታላቅ ምሥጢር በትንቢት ቃል ሲናገር ነው ፡፡ መዝ 15 ÷ 10 ፡፡


ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም ፡- « ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር (ወደ አብ ÷ ወደ ራሱና ወደ መንፈስ ቅዱስ) እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ( ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት ተላልፎ በመስጠት) ሞቶአልና ፤ በሥጋ ሞተ (በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ለየ) ÷ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ ÷ (ያን ሥጋ ነፍስ እንድተለየችው መለኰት አልተለየውም) ÷ በእርሱም ደግሞ (መለኰት በተዋሐዳት ነፍስ) ሄዶ በወኅኒ ለነበሩት ነፍሳት ሰበከላቸው፤ » ብሏል፡፡ 1ኛ ጴጥ 3 ÷ 18፡፡

ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በመቃብር ፤

ጌታችን በከርሠ መቃብር የቆየው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ነው ፡፡ «ሥጋዬ ደግሞ በተስፋ ታድራለች፤» የሚለው ቃለ ትንቢት የሚያረጋግጥልን ይኽንኑ ነው፡፡ መዝ 15 ÷ 9፡፡ ምሥጢራዊ ትርጉሙ ወደ መቃብር የወረደ ሥጋዬ በተስፋ ትንሣኤ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በመቃብር አደረ ማለት ነው፡፡ ተስፋ ትንሣኤውም በተዋሕዶ ከሥጋ ጋር ወደ መቃብር የወረደ መለኰት ነው፡፡ ነቢዩ ሆሴዕም ፡- « ኑ ÷ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ ፤ እርሱ ሰብሮናልና ÷ (በሞተ ሥጋ ላይ ሞተ ነፍስን ጨምሮ የፈረደብን እርሱ ነው) ÷ እርሱም ይፈውሰናል፤ (መርገመ ሥጋን መርገመ ነፍስን አስወግዶ ከሞት ወደ ሕይወት ያሸጋግረናል) ፤ እርሱ መትቶናል ÷ እርሱም ይጠግነናል፡፡ ከሁለት ቀን በኋላ ያድነናል ፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል፡፡ » በማለት ትንሣኤ ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ሆሴ 6 ÷ 12፡፡ ይልቁንም ጌታችን ራሱ በመዋዕለ ሥጋዌው ፡- ከሽማግሌዎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀመዛሙርቱ በግልጥ ነግሯቸዋል፡፡ ማቴ ፡ 16÷21 ፡፡ በገሊላም ሲመላለሱ፡- «ወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው ÷ ይገድሉትማል ÷ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤» ብሏቸዋል፡፡ ማቴ 17÷20፡፡ ጻፎችና ፈሪሳዊያንም ምልክት በጠየቁት ጊዜ ፡- «ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል ÷ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም፡፡ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደነበረ ÷ እንዲሁ የሰው ልጅ (ወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስ) በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል ፡፡» ብሏቸዋል ፡፡ ማቴ 12÷38 - 40 ፡፡

ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት የሞላው እንዴት ነው;ጌታችን በከርሠ መቃብር የቆየው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ነው ፡፡ «ሥጋዬ ደግሞ በተስፋ ታድራለች፤» የሚለው ቃለ ትንቢት የሚያረጋግጥልን ይኽንኑ ነው፡፡ መዝ 15 ÷ 9፡፡ ምሥጢራዊ ትርጉሙ ወደ መቃብር የወረደ ሥጋዬ በተስፋ ትንሣኤ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በመቃብር አደረ ማለት ነው፡፡ ተስፋ ትንሣኤውም በተዋሕዶ ከሥጋ ጋር ወደ መቃብር የወረደ መለኰት ነው፡፡ ነቢዩ ሆሴዕም ፡- « ኑ ÷ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ ፤ እርሱ ሰብሮናልና ÷ (በሞተ ሥጋ ላይ ሞተ ነፍስን ጨምሮ የፈረደብን እርሱ ነው) ÷ እርሱም ይፈውሰናል፤ (መርገመ ሥጋን መርገመ ነፍስን አስወግዶ ከሞት ወደ ሕይወት ያሸጋግረናል) ፤ እርሱ መትቶናል ÷ እርሱም ይጠግነናል፡፡ ከሁለት ቀን በኋላ ያድነናል ፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል፡፡ » በማለት ትንሣኤ ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ሆሴ 6 ÷ 12፡፡ ይልቁንም ጌታችን ራሱ በመዋዕለ ሥጋዌው ፡- ከሽማግሌዎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀመዛሙርቱ በግልጥ ነግሯቸዋል፡፡ ማቴ ፡ 16÷21 ፡፡ በገሊላም ሲመላለሱ፡- «ወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው ÷ ይገድሉትማል ÷ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤» ብሏቸዋል፡፡ ማቴ 17÷20፡፡ ጻፎችና ፈሪሳዊያንም ምልክት በጠየቁት ጊዜ ፡- «ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል ÷ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም፡፡ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደነበረ ÷ እንዲሁ የሰው ልጅ (ወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስ) በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል ፡፡» ብሏቸዋል ፡፡ ማቴ 12÷38 - 40 ፡፡ጌታ በከርሠ መቃብር የቆየው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ነው፡፡ ይኽንንም ለመረዳት ዕብራውያን ዕለታትን እንዴት እንደሚቆጥሩ ማወቅ ያስፈልጋል ፡፡ እኛ በሀገራችን የሌሊቱን ሰዓት መቁጠር የምንጀምረው ከዋዜማው ከምሽቱ አንድ ሰዓት ነው ÷ የቀኑን ሰዓት መቁጠር የምንጀምረው ደግሞ ከማለዳው አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው ፡፡ የሌሊቱ ሰዓት የሚያልቀው ከማለዳው አሥራ ሁለት ሰዓት ሲሆን የቀኑ ደግሞ ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ነው፡፡ የቀኑም የሌሊቱም ሰዓት ተደምሮ ሃያ አራት ሰዓት ይሆናል፡፡ ሁሉም ሰዓት ዕለቱን ይወክላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው እሑድ ዕለት ከሃያ አራቱ ሰዓት በአንዱ ቢወለድ እሑድ ተወለደ ይባላል ÷ ቢሞትም እሑድ ሞተ ይባላል፡፡ ዕለቱ በሚጀምርበትም ሰዓት ሆነ በሚያልቅበት ሰዓት ድርጊቱ ቢፈጸም ያ ሰዓት እንደ አንድ መዓልትና እንደ አንድ ሌሊት ይቆጠራል ፡፡ አውሮፓውያን አንድ ብለው ሰዓት መቁጠር የሚጀምሩት በእኛ አቆጣጠር ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ነው፡፡ እስከ ሃያ አራት ይቆጥሩና በእኛ አቆጣጠር ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሲሆን ይጨርሳሉ፡፡ ሃያ አራት ሰዓት ሲሆን ዜሮ ይሉና እንደገና አንድ ብለው መቁጠር ይጀምራሉ፡፡ በሌላ አነጋገር ከሌሊት እስከ ሌሊት ይቆጥራሉ፡፡ አሜሪካውያን ደግሞ በእኛ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲሆን አንድ ብለው ይጀምሩና በእኛ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሲሆን አሥራ ሁለት ብለው ይጨርሳሉ፡፡ ከዚያም በእኛ አቆጣጠር ከቀኑ ሰባት ሰዓት እንደገና አንድ ብለው ይጀምሩና በእኛ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሲሆን አሥራ ሁለት ብለው ይጨርሳሉ፡፡ዕብራውያን ግን ዕለትን መቁጠር የሚጀምሩት ከዋዜማው ማለትም በአውሮፓውያን ከአሥራ ሰባት ሰዓት ÷ በአሜሪካውያን ከአምስት ሰዓት (P.M.) ÷ በእኛ ደግሞ ከምሽቱ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው ፡፡ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ድረስ ሃያ አራት ሰዓት ቆጥረው አንድ ቀን ይላሉ ፡፡ ከላይ እንደተገለጠው እያንዳንዱ ሰዓት የዕለቱን መዓልትና ሌሊት ይወክላል ፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ከመስቀል ወርዶ የተቀበረው ዓርብ ቅዳሜ ከመግባቱ በፊት ነው ፡፡ ዓርብ ዕለቱ የሚጀምረው ከዋዜማው ሐሙስ በእኛ አቆጣጠር ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ስለዚህ ጌታ የተቀበረው በዓርብ ሃያ አራት ሰዓት ክልል ውስጥ በመሆኑ እንደ አንድ መዓልትና ሌሊት ይቆጠራል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ዓርብ ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ቀን አሥራ አንድ ሰዓት ያለው ነው ፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ቅዳሜ ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ እሑድ ቀን አሥራ አንድ ሰዓት ያለው ነው፡፡ ከዚህ በኃላ የሰኞ ምሽት ይገባል፡፡ ጌታ የተነሳው በሦስተኛው ቀን እሑድ መንፈቀ ሌሊት ነው፡፡እንዴት ተነሣ ;ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሣው በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ነው፡፡ ይህ ኃይልና ሥልጣን የባሕርይ ገንዘቡ ነው ፡፡ ይኽንንም ፡- « ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ ( ሰውነቴን ከሞት አነሣት ዘንድ ) አኖራለሁና (በፈቃዴ እሞታለሁና ) ፤ ስለዚህ አብ ይወደኛል፡፡ እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ( ነፍሴን በፈቃዴ ከሥጋዬ ለይቼ በገነት ÷ ሥጋዬንም በመቃብር አኖራቸዋለሁ እንጂ ) ከእኔ ማንም አይወስዳትም ፡፡ (ያለ እኔ ፈቃድ የሚፈጸም ምንም ነገር የለም ) ፡፡ላኖራት ( ነፍሴን በገነት ÷ ሥጋዬን በመቃብር ላኖራቸው) ሥልጣን አለኝ ፤ደግሞም ላነሣት (ነፍሴን ከሥጋዬ አዋሕጄ ላነሣት) ሥልጣን አለኝ፡፡ » በማለት አስቀድሞ ተናግሮታል ፡፡ ዮሐ 10 ÷17 - 18 ፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ፡- « ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም ፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት÷ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም፡፡ » በማለት መናገሩ ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ እንደሚሞት የሚያጠይቅ ትንቢት ነበር ፡፡ ኢሳ 53 ÷ 7 ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም ከዚህ የሚመሳሰል ቃል ተናግሯል ፡፡ 1ኛ ጴጥ 2 ÷ 23 ፡፡ በዚህ ዓይነት ነቢያትም ሐዋርያትም የተናገሩለት ኢየሱስ ክርስቶስ በኃይሉ በሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጐ ÷ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ተነሥቷል ፡፡ እርሱ የትንሣኤና የሕይወት ባለቤት ነውና ፡፡ ዮሐ 11 ÷ 25፡፡ይህ እንዲህ ከሆነ ÷ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ፡- « የሕይወትን ራስ ገደላችሁት ፤» በማለት አይሁድን ከወቀሳቸው በኋላ ፡- « እርሱን ግን እግዚአብሔር ከሙታን አስነሣው ፤» ለምን አለ; የሚል ጥያቄ ይነሣ ይሆናል ፡፡ ይኽንን ኃይለ ቃል በመያዝ «አብ አስነሣው እንጂ በራሱ አልተነሣም» ፤ የሚሉ አሉና ፡፡ እነዚህም ትርጓሜውን ያልተረዱ ምሥጢሩን ያላስተዋሉ ናቸው፡፡ሐዋርያው « እግዚአብሔር አስነሣው ፤» ሲል « እግዚአብሔር » የሚለው ስም የሦስቱም መጠሪያ እንጂ የአብ ብቻ አይደለም ፡፡ ወልድም እግዚአብሔር ተብሎ ይጠራል ፡፡ ዮሐ 1 ÷ 1 ፡ የሐዋ 20 ÷ 28 ፡፡ መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር ተብሎ ይጠራል፡፡ ዮሐ 1 ÷ 2፡፡ ስለዚህ ሥላሴ በፈቃድ አንድ በመሆናቸው « አንዲት በሆነች በአብ በራሱና በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድና ሥልጣን ተነሣ ፤ አንድም ወደ መቃብር የወረደ ሥጋ መለኰት የተዋሐደው ስለሆነ ተነሣ ÷ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር በመሆኑ ተነሣ ፤» ተብሎ ይተረጐማል፡፡ ይታመናል፡፡ ትንቢተ ነቢያትም የሚያረጋግጥልን ይኽንኑ ነው ፡፡ « እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ ÷ የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው ፤ ጠላቶቹንም በኃላቸው መታ ፤ » እንዲል፡፡ መዝ 77 ÷ 65 ፡፡ለምን በአዲስ መቃብር ተቀበረ ;በእስራኤል ባሕል የአባቶቻቸው አፅም ካረፈበት መቃብር የመቀበር ልማድ አላቸው ፡፡ ዮሴፍ የእስራኤልን ልጆች ፡- « እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንስታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ፤ » ብሎ ያማላቸው የአባቶቹ የአብርሃም የይስሐቅ የያዕቆብ አፅም ካረፈበት ለመቀበር ፈልጐ ነው፡፡ ዘፍ. 50 ÷ 25 ፡፡ በቤቴል የነበረውም ሽማግሌ ነቢይ ፡- «በሞትሁ ጊዜ የእግዚአብሔር ሰው በተቀበረበት መቃብር ቅበሩኝ ፤ አጥንቶቼንም በአጥንቶቹ አጠገብ አኑሩ ፤ » ብሏል ፡፡ 1ኛ ነገ 13 ÷ 31 ፡፡

ጌታችን የተቀበረው እንደ እስራኤል ባሕል የቅዱሳን አፅም ካረፈበት ሳይሆን ማንም ካልተቀበረበት ከአዲስ መቃብር ነው፡፡ ይኸውም ዮሴፍ ለራሱ ያዘጋጀው ነው፡፡ « ዮሴፍም ሥጋውን ይዞ በንጹሕ በፍታ ከፈነው ÷ ከዓለት በወቀረው በአዲሱ መቃብርም አኖረው ÷ በመቃብሩም ደጃፍ ታላቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ ፤» እንዲል ማቴ 27 ÷ 59 ፡፡ ይህም የሆነው እርሱ ባወቀ በርሱ ጥበብ ነው ፡፡ እንዲህም በማድረጉ አይሁድ ለትንሣኤው ምክንያት እንዳያበጁለት አድርጓቸዋል ፡፡ በብሉይ ኪዳን እንደተጻፈው ከነቢዩ ከኤልሳዕ መቃብር ተቀብሮ የነበረው ሰው የነቢዩ አጥንት በነካው ጊዜ በተአምር ተነሥቷል፡፡ 2ኛነገ 13 ÷ 20፡፡ እንግዲህ ጌታችንም ከአንዱ ቅዱስ መቃብር ተቀብሮ ቢሆን ኖሮ ሞትን ድል አድር ጐ በሚነሣበት ጊዜ «በራሱ አልተነሣም የቅዱሱ አፅም ነው ያስነሣው ፤» ባሉት ነበር ፡፡ ይኸንን ምክንያት ለማጥፋት ነው፡፡ በአዲስ መቃብር የተቀበረው፡፡እንዴት በዝግ መቃብር ተነሣ ;ጌታችንን ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ገንዘው ከቀበሩት በኃላ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ወደ ጲላጦስ ተመልሰው ፡- « ጌታ ሆይ ÷ ያ ሰው ( ክርስቶስ ) ገና በሕይወቱ ሳለ ፡- ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ እንዳለ ትዝ አለን ፡፡ እንግዲህ ደቀመዛሙርቱ መጥተው በሌሊት እንዳይሰርቁት ለሕዝቡም ፡- ከሙታን ተነሣ እንዳይሉ ÷ የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለችና መቃብሩ እስከ ሦስተኛ ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ አሉት፡፡ ጲላጦስም ፡- ጠባቆች አሉአችሁ እንዳወቃችሁ አስጠብቁ አላቸው ፡፡ እነርሱም ሄደው ከጠባቆች ጋር ድንጋዩን አትመው መቃብሩን አስጠብቁ ፡፡ » ማቴ 27 ፡ 63÷66፡፡ በታላቅ ድንጋይ የተገጠመው መቃብር ድንጋዩ እንደታተመ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ተነሥቷል፡፡ ይኸውም ምንም የማይግደው መለኰት በተዋሕዶ ከሥጋ ጋር በመቃብር ስለነበረ ነው ፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ እንደተናገረው በተዋሕዶ የቃል ገንዘብ ለሥጋ የሥጋም ገንዘብ ለቃል በመሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ አይሁድ ብዙ ጊዜ በድንጋይ ቀጥቅጠው ሊገድሉት ሲፈልጉ እያዩት ይሰወርባቸው ከእጃቸውም ይወጣ ነበር፡፡ በመካከላቸው አልፎ ሲወጣ አያዩትም ነበር ፡፡ ዮሐ 8÷59 ፤ 10÷39 ፡፡ ይህም የሆነው እንደ ነፍስና ሥጋ ተዋሕዶ መለኰት ሥጋን በመዋሐዱ ነው፡፡ ከትንሣኤው በኋላም ከአንዴም ሁለት ጊዜ ከተዘጋ ቤት በሩ ሳይከፈት የገባው ለዚህ ነው፡፡ ዮሐ 20÷19 ፤ 26፡፡ በልደቱም ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና እንደታተመች የተወለደው ለዚህ ነው፡፡ ኢሳ 7÷14፡፡ ማቴ 1÷20 - 23 ፣ ሉቃ 2÷ 6-7 ፡፡መቃብሩን ማን ከፈተው ;ጌታችን የተነሣው መግነዝ ፍቱልኝ መቃብሩን ክፈቱልኝ ሳይል ከሆነ መቃብሩን ማን ከፈተው; ለምንስ ተከፈተ ; የሚል ጥያቄ ይነሣ ይሆናል ; በወንጌል እንደተጻፈው የአይሁድ ሰንበት ቅዳሜ ካለፈ በኋላ እሑድ በማለዳ ፀሐይ ሲወጣ መግደላዊት ማርያም ÷ የያዕቆብም እናት ማርያም ሶሎሜም ሽቱ ሊቀቡት ወደ መቃብሩ መጥተው ነበር ፡፡ ትልቁ ጭንቀታቸው « ድንጋዩን ከመቃብሩ ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል ; » የሚል ነበር÷ ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና ፤ አሻቅበውም አይተው ድንጋዩ ተንከባሎ እንደነበር ተመለከቱ ፡፡ ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጐናጸፈ ጐልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ ፡፡ በጐልማሳ አምሳል የተገለጠላቸው የጌታ መልአክ ነው፡፡ እርሱ ግን ፡- « አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን እንደምትፈልጉ አውቃለሁ ፤ ተንሥቷል በዚህ የለም ፡፡» አላቸው፡፡ ማር 16÷1-6፡፡ ጌታችን በዝግ መቃብር ከተነሣ በኋላ ባዶ የነበረውን መቃብር የከፈተው ይህ የጌታ መልአክ ነው ፡፡ የከፈተበትም ምክንያት በእምነት የመጡ እነዚህ ሴቶች ያልተነሣ መስሏቸው ዘወትር በመመላለስ እንዳይቸገሩ ነው፡፡ አንድም ትንሣኤውን እንዳይጠራጠሩ ነው፡፡ በቅዱስማቴዎስ ወንጌልም «በሰንበትም መጨረሻ መጀመሪያው ቀን ሲነጋ መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ፡- ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ ፡፡ እነሆም የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ ፡፡ መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ ፡፡ ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ ፡፡ እንደ ሞቱም ሆኑ፡፡ መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው ፡- እናንተስ አትፍሩ ፤ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንደምትሹ አውቃለሁና ፤ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም ፤» የሚል ተጽፏል፡፡ ማቴ 28÷1-6፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በእርግጠኝነት ትንሣኤውን ያመኑት መልአኩ ወደ ከፈተው መቃብር ገብተው መግነዙን ካዩ በኋላ ነው ዮሐ. 20÷7 ፡፡በኵረ ትንሣኤጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለባሕርይ አባቱ ለአብ ለእናቱ ለድንግል ማርያምም የበኵር ልጅ ነው ፡፡ ዕብ 1÷6 ፣ ሉቃ 2÷7 ፡፡ ለበጎ ነገርም ሁሉ በኵር በመሆኑ የትንሣኤያችንም በኵር እርሱ ነው፡፡ « አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኵራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቷል ፡፡ ሞት በሰው (በቀዳማዊ አዳም) በኵል ስለመጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው (በተዋሕዶ ሰው በመሆኑ ዳግማዊ አዳም በተባለ በክርስቶስ) በኩል ሆኗልና፡፡ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና ፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል ፤ ክርስቶስ እንደ በኵራት ነው ፤» እንዳለ ፡፡ 1ኛ ቆሮ 15÷20-23 ፡፡ በተጨማሪም ፡- « በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥሯልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፡፡ (ከፍጥረታት በፊት የነበረ÷ የፍጥረታት አለቃ÷ የፈጠረውን ፍጥረት የሚገዛ ነው) ፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሯል ፤ እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ፤ (ለዘመኑ ጥንት የሌለው ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት በህልውና የነበረ ነው) ፤ ሁሉም በእርሱ ተጋጥሟል፡፡ እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርሰቲያን ራስ ነው ፤ እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው ፡፡ » የሚል አለ ፡፡ kAላ 1 ÷ 16-18 ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ፡- «ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም ÷ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት÷ ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን ፤» ብሏል፡፡ ራእ 1÷5 ፡፡በብሉይ ኪዳን እነ ኤልያስ÷ እነ ኤልሳዕ ሙት አስነሥተዋል፡፡ 1ኛ ነገ 17÷ 22 ፣ 2ኛነገ 4÷32 - 38፡፡ በአዲስ ኪዳንም ራሱ ባለቤቱ የመኰንኑን ልጅ ÷ የመበለቲቱን ልጅ ÷ አልዓዛርንም ከሞት አንሥቷቸዋል ፡፡ ማቴ 9÷25 ፣ ሉቃ 7÷15 ፣ ዮሐ 11÷44፡፡ ነፍሱን በመስቀል ላይ በፈቃዱ አሳልፎ በሰጠም ጊዜ አያሌ ሙታን ከእግረ መስቀሉ ተነሥተዋል ፡፡ ማቴ 27÷53 ፡፡ እነዚህ ሁሉ በኵረ ትንሣኤ አልተባሉም፡፡ ምክንያቱም አንደኛ በራሳቸው ኃይል የተነሡ አይደሉም፡፡ ሁለተኛ ለተወሰነ ጊዜ ከኖሩ በኋላ ተመልሰው ሞተው ትንሣኤ ዘጉባኤን የሚጠብቁ ሆነዋል፡፡ ሦስተኛ:- ፍጡራን ናቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የባሕርይ አምላክ በመሆኑ በራሱ ኃይልና ሥልጣን ተነሥቷል ፡፡ ዳግመኛም አይሞትም፡፡ ይኽንንም ፡- « ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደፊት እንዳይሞት ሞትም ወደፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና ÷ መሞትን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለኃጢአት ሞቷልና ፡፡» በማለት ሐዋርያው ገልጦታል፡፡ ሮሜ 6÷9 ፡፡ ጌታችንም ፡- «ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርሁ እነሆም ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ ፤» ብሏል፡፡ ራእ 1÷18 ፡፡ከትንሣኤው በኋላ ለምን ተመገበ ;ጌታችን በተዘጋ ቤት ገብቶ ለደቀ መዛሙርቱ በተገለጠ ጊዜ መንፈስ የሚያዩ መስሏቸው ኅሊናቸው ደንግጦ ÷ ልባቸውም ፈርቶ ነበር፡፡ እርሱም ፡- « ስለ ምን ትደነግጣለችሁ ; ስለምንስ አሳብ በልባችሁ ይነሣል ; እኔ ራሴ እንደሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ ፤ በእኔ እንደምታዩት ÷ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ ፤» ካላቸው በኃላ እጆቹንና እግሮቹን አሳይቷቸዋል ፡፡ እነርሱም ከደስታ የተነሣ ገና ስላላመኑ ሲደነቁ ሳሉ ፡- « በዚህ አንዳች የሚበላ አላችሁን ; » አላቸው ፡፡ እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ ከማር ወለላም ሰጡት ፤ ተቀብሎም በፊታቸው በላ ይላል ፡፡ ሉቃ 24÷36-43፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ በጥብርያዶስ በተገለጠላቸውም ጊዜ አብሯቸው ተመግቧል፡፡ ዮሐ፡ 21÷9-14፡፡ ይኽንንም ያደረገው ከትንሣኤ በኋላ መብላት መጠጣት ኖሮ አይደለም፡፡ አለማመናቸውን ለመርዳት ነው ፡፡ ደቀመዛሙርቱ በተዋሐደው ሥጋ ለመነሣቱ እርግጠኞች እንዲሆኑ ነው፡፡ ከወንጌሉ እንደምንረዳው ደቀመዛሙርቱ ይበልጥ እርግጠኞች የሆኑት ስላዩት ሳይሆን ያቀረቡለትን በመብላቱና በመጠጣቱ ነውና፡፡ለምን አትንኪኝ አላት;መግደላዊት ማርያም ገና ሰማይና ምድሩ ሳይላቀቅ በማለዳ ሽቱ ልትቀባው ከመቃብሩ አጠገብ ተገኝታ ነበር፡፡ እንደደረሰችም ድንጋዩ ከመቃብሩ አፍ ተፈንቅሎ አየች፡፡ ይህች ሴት በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ከባለቤቱ ብትሰማም « እንደተናገረ ተነሥቶ ነው፤» ብላ አላመነችም ፡፡ ላለማመኗም ምክንያት የሆነው « እኛ ተኝተን ሳለን ደቀመዛሙርቱ በሌሊት ሰረቁት ፤» የሚለው የጭፍሮች ወሬ ነው ፡፡ ጭፍሮቹ እውነትን በሐሰት ለውጠው ይኽንን ያወሩት በገንዘብ ተደልለው ነው፡፡ ማቴ 28÷11 - 15 ፡፡ ለዚህ ነው ወደ ደቀመዛሙርቱ ሄዳ ፡- «ጌታን ከመቃብር ወስደዉታል ወዴትም እንዳኖሩት አናውቅም ፤» ያለቻቸው ፡፡ ዮሐ 20÷2 ፡፡ ከመቃብሩ ራስጌና ግርጌ ሁለት መላእክት ተገልጠውላት ፡- « አንቺ ሴት ስለምን ታለቅሻለሽ ; » ባሏት ጊዜም « ጌታዬን ወስደውታል ወዴትም እንዳኖሩት አላውቅም ፤»ብላቸዋለች ፡፡ ዮሐ 20÷13 ፡፡ በመጨረሻም ጌታ ራሱ ተገልጦላት ፡- «አንቺ ሴት ስለምን ታለቅሻለሽ ; ማንንስ ትፈልጊያለሽ ; » ሲላት አላወቀችውም ፡፡ ለዚህ ነው አትክልት ጠባቂ መስሏት ፡- «ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ እኔም ወስጄ ሽቱ እንድቀባው ፤» ያለችው ፡፡ ዮሐ. 20÷15 ፡፡ በዚህን ጊዜ « ማርያም » ብሎ በስሟ ቢጠራት በድምፁ አወቀችውና « ረቡኒ ( መምሕር ሆይ ) » አለችው ፡፡ መልኩን አይታ ድምፁን ሰምታ ÷ ትንሣኤውን አረጋግጣ አምላኬ አላላችውም ፡፡ ስለዚህ «ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና ፤ አትንኪኝ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ (ወደ ደቀመዛሙርቴ) ሄደሽ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ÷ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ አርጋለሁ ብሏል ብለሽ ንገሪያቸው አላት፡፡» እንዲህም ማለቱ የእርሱ የእግዚአብሔር ልጅ መባልና የእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች መባል ፍጹም የተለያየ በመሆኑ ነው ፡፡ እርሱ « አባቴ » ቢል የባሕርይ ልጅ በመሆኑ ነው ፡፡ ነርሱ ግን የጸጋ ልጆች ናቸው፡፡ እርሱ « አምላኬ » ቢል ስለተዋሐደው ሥጋ ነው ፡፡ የተዋሐደው የፈጠረውን ሥጋ ነው ፡፡ እነርሱ ግን « አምላካችሁ » ቢባሉ ፍጡራን ስለሆኑ ነው ፡፡ በዚህም እርሱ ፈጣሪ እነርሱ ፍጡራን መሆናቸውን አስረግጦ ተናግሯል፡፡ ቶማስን ግን ፡- « ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው ፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን ፤» ብሎታል ፡፡ ዮሐ 20 ÷ 27 ፡፡ ምክንያቱም አይቶ ዳስሶ « ጌታዬ አምላኬም » ብሎ የሚያምን ነውና ፡፡ አንድም ሥጋውንና ደሙን ለመዳሰስ÷ ለመፈተት የተጠራ የተመረጠም ካህን ነውና፡፡

ተስፋ ትንሣኤበብሉይ ኪዳን ዘመን ሁሉም በአዳም ኃጢአት ምክንያት እየተኰነኑ በሞተ ነፍስ ተይዘው ወደ ሲኦል ይወርዱ ነበር ፡፡ 1ኛ ቆሮ 15÷ 22 ፡፡ « ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ( እስከ ክርስቶስ ) ድረስ ሞት ነገሠ ፤ » እንዲል፡፡ ሮሜ 5÷ 14 ፡፡ ከዚህ የተነሣ እነ አብርሃም እንኳ ሳይቀሩ የወረዱት ወደ ሲኦል ነው ፡፡ እነ ኢሳይያስ ፡- «ጽድቃችንም ሁሉ እንደመርገም ጨርቅ ነው ፤ » ያሉት ለዚህ ነው ፡፡ ኢሳ 64÷ 6፡፡ እነ ኤርምያስም ፡- « ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም ፡፡ ስንዴን ዘሩ እሾህንም አጨዱ፡፡» ብለዋል ፡፡ ኤር 12÷ 13 በዚህ ምክንያት የብሉይ ኪዳን ዘመን ዘመነ ፍዳ ÷ ዘመነ ኵነኔ ÷ ዘመነ ጽልመት ተብሏል ፡፡ በዚህ ዘመን እነ ቅዱስ ዳዊት ፡- «አንሥእ ኃይለከ÷ ወነዓ አድኅነነ ፤ ኃይልህን አንሣ÷ እኛንም ለማዳን ና ፤ ( በሥጋ ተገልጸህ÷ ሰው ሁነህ አድነን ) ፤» እያሉ ወልድን ተማጽነዋል ፡፡ መዝ 79÷ 2 ፡፡ « ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ ፤ ብርሃንህንና እውነትህን ላክልን ፤( ብርሃን ወልድን ÷ እውነት መንፈስ ቅዱስን ላክልን ፤ እነርሱ ይምሩን÷ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ÷ ወደ ገነት መንግሥተ ሰማያት ይውሰዱን ) » ፤ እያሉም አብን ተማጽነዋል ፡፡ መዝ.40 ÷3 ፡፡ ይህም የሚያመለክተው በዚያ በጨለማ ዘመን ሆነው ተስፋቸው የክርስቶስ ትንሣኤ ስለነበር ነው ፡፡ በሞት አጠገብ ሕይወት÷ በመቃብር አጠገብ ትንሣኤ እንዳለ ተስፋ እንዲያደርጉ የሚያደርጋቸው የክርስቶስ ትንሣኤ ነውና ፡፡ ያንጊዜ ከሲኦል እንደሚወጡ የተዘጋች ገነትም እንደምትከፈትላቸው ያውቃሉና ፡፡

የክርስቶስ ትንሣኤ የአዳም ልጆች በጠቅላላ ትንሣኤ ዘጉባኤን በተስፋ እንዲጠብቁ አድርÑEቸዋል ፡፡ ይህም ተስፋ ሃይማኖት እንዲይዙ÷ ምግባር እንዲሠሩ አጽንቷቸዋል ፡፡ ምድራዊውን እንዲንቁ ሰማያዊውን እንዲናፍቁ አድርÑEቸዋል ፡፡ « ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን ፡፡» እንዲል ፡፡ 2ኛ ጴጥ 3 ÷13 ፡፡ ቅዱሳን በሃይማኖት አይተዋታል ፡፡ « አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ÷ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና÷ ባሕርም ወደፊት የለም፡፡ ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለባልዋ እንደተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ ፡፡» እንዲል ፡፡ ራእ 21÷ 1 - 3፡፡ እግዚአብሔርም ፡- « እነሆ ÷ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እፈጥራለሁና የቀደሙትም አይታሰቡም÷ ወደ ልብም አይገቡም ፡፡ ነገር ግን በፈጠርሁት ደስ ይበላችሁ ለዘላለምም ሐሴት አድርጉ ፤ እነሆ ÷ ኢየሩሳሌምን ለሐሴት ÷ ሕዝቧንም ለደስታ እፈጥራለሁና ፡፡» ብሏል ፡፡ ኢሳ ፡ 65 ÷17 ፡፡

ሙታን እንዴት ይነሣሉ;እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሲፈጥረው የሚያንቀላፋና የሚነቃ አድርጐ ፈጥሮታል ፡፡ ማንቀላፋቱ የሞት መንቃቱ ደግሞ የትንሣኤ ምሳሌ ነው፡፡ አቤል ከሞተ በኋላ በደሙ መናገሩም የትንሣኤ ምሳሌ ነው፡፡ ዘፍ ፡ 4÷10 ፡፡ የሄኖክም ከዓይነ ሞት ተሰውሮ በእግዚአብሔር መወሰድ የትንሣኤ ምሳሌ ነው፡፡ ዘፍ፡ 5÷24 ፡፡ ፍጥረታት በጠቅላላም ትንሣኤን የሚሰብኩ ናቸው፡፡ የፀሐይ መውጣት የመወለድ÷ የፀሐይ መጥለቅ የመሞት÷ ከጠለቀች በኋላም እንደገና መውጣት የትንሣኤ ምሳሌ ነው፡፡ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙታን እንደሚነሡ በቃልም በተግባርም አስተምሯል ፡፡ በቃል ፡- « በመቃብር ያሉት ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል ፤ መልካምም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ÷ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ ፡፡ » ሲል አስተምሯል፡፡ ዮሐ 5÷29 ፡፡ በተግባርም የአራት ቀን ሬሳ አልዓዛርን አስነሥቷል ፡፡ ዮሐ 11÷43 ፡፡ ቅዱሳን ነቢያት ፡- እነ ኢሳይያስ « ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ ሬሳዎችም ይነሣሉ፡፡ » ብለዋል ፡፡ ኢሳ 26÷19 ፡፡ እነ ዳንኤልም ፡- « በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉት ብዙዎች ( ሁሉም ) ይነቃሉ፤ እኵሌቶችም ወደ ዘላለም ሕይወት÷ እኵሌቶችም ወደ እፍረትና ዘላለም ጉስkCልና ፡፡» ብለዋል፡፡ ዳን 12÷2፡፡ በተለይም ለነቢዩ ለሕዝቅኤል ፡- እግዚአብሔር በአፅም የተሞላ ታላቅ ሸለቆ ካሳየው በኋላ ፡- « እነዚህ የደረቁ አጥንቶች ተመልሰው በሕይወት የሚኖሩ ይመስልሃልን ; » ሲል ጠይቆታል፡፡ ሕዝቅኤልም፡- «እግዚአብሔር ሆይ÷ አንተ ታውቃለህ ፤ » የሚል መልስ ሰጥቶቷል ፡፡ በመጨረሻም እነዚህ ሁሉ ሕይወት ዘርተው ሲነሡ አይቷል፡፡ ይኸንንም፡- « እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ÷ ትንፋሽም ገባባቸው ሕያዋንም ሆኑ÷ እጅግም ታላቅ ሠራዊት ሆነው በእግራቸው ቆሙ ፡፡» በማለት ገልጦታል፡፡ ሕዝ 37÷ 1 - 10 ፡፡ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ሙታን ትንሣኤ በሚገባ ቋንቋ አብራርቶ በምሳሌ ሲያስተምር « ነገር ግን ሰው ፡- ሙታን እንዴት ይነሣሉ ; በምንስ ዓይነት አካል ይመጣሉ ; የሚል ይኖር ይሆናል ፡፡ » ብሎ ከጠየቀ በኋላ ፡- « አንተ ሞኝ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም ፡፡ » ብሏል ፡፡ ከዚህም አያይዞ « የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲሁ ነው ፡፡ በመበስበስ ይዘራል÷ ባለመበስበስ ይነሣል ፤ በውርደት ይዘራል በክብር ይነሣል ፤ በድካም ይዘራል÷ በኃይል ይነሣል ፤ ፍጥረታዊ አካል ይዘራል÷ መንፈሳዊ አካል ይነሣል ፤ ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ ፡፡ እንዲሁ ደግሞ ፡- ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል ፤ ኋለኛው አዳም ( ክርስቶስ ) ሕይወትን የሚሠጥ መንፈስ ሆነ ፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ ፍጥረታዊው ቀጥሎም መንፈሳዊው ነው እንጂ መንፈሳዊው መጀመሪያ አይደለም ፡፡ የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው ፡፡ ሁለተኛው ሰው ( ክርስቶስ ) ከሰማይ ነው፡፡ መሬታዊው እንደሆነ መሬታውያን የሆኑት ደግሞ እንዲህ ናቸው÷ ሰማያዊው እንደ ሆነ ሰማያውያን የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው ፡፡ የዚያንም የመሬታዊውን መልክ

እንደ ለበስን የሰማያዊውን መልክ ደግሞ እንለብሳለን፡፡» ብሏል ፡፡ 1ኛቆሮ 15÷ 35-49፡፡ በፊልጵስዩስ መልእክቱም፡- «ክቡር ሥጋውን እንደሚስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል፡፡» ብሏል፡፡ ፊል 3÷ 21 ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም ፡- « እርሱን እንድንመስል እናውቃለን ፤ ብሏል፡፡ 1ኛ ዮሐ 3÷ 2 ፡፡

የትንሣኤ ጸጋ

በክርስቶስ ትንሣኤ ያገኘነው ጸጋ ታላቅ ነው ፡፡ ከጨለማ ወደ ብርሃን ወጥተናል ÷ ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋግረናል ፡፡ ሙታን የነበርን ሕያዋን ÷ ምድራውያን የነበርን ሰማያውያን ÷ ሥጋውያን የነበርን መንፈሳውያን ሆነናል፡፡ « ሞት ሆይ÷ መውጊያህ የት አለ ; ሲኦል ሆይ÷ ድል መንሣትህ የት አለ ; » የምንል ሆነናል፡፡ ሆሴ 13÷ 14 1ኛቆሮ 15÷ 55 ፡፡ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ « እኛ አገራችን በሰማይ ነውና÷ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን ፤ እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል ፡፡ » የምንል ሆነናል ፊል 3÷20 - 21 ፡፡ ናፍቆታችን ሁሉ በትንሣኤ ያገኘነውን ጸጋ እውን ማድረግ ነው ፡፡ « ድንኳን የሚሆነው ምድራዊው መኖሪያችን ቢፈርስ ÷በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘላለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ እንዳለን እናውቃለንና ፡፡ በ፡፡ ዚህ ውስጥ በእውነት እንቃትታለንና ÷ ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድንለብስ እንናፍቃለንና ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም፡፡ » እንዲል ፡፡ 2ኛቆሮ 5÷1 - 2 ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም ፡- «ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ÷ እድፈትም ለሌለበት÷ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ይባረክ ፤ » ብሏል፡፡ 1ኛ ጴጥ 1÷3 ፡፡ ቅዱስ ጳውለሮስም ፡- « በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳየን ዘንድ ከእርሱ ጋር አስነሣን ፤ በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊው ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን ፡፡ » ብሏል፡፡ ኤፌ 2÷6 - 7፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን አሜንApril 15, 2009

አማኒያን (ምዕመናን) ላይ የእሥር ትዕዛዝ ሊወጣ ነው

አዲስ አባባ (ECADF) - ከሀይማኖት ጋር በተያያዘ ግጭቶችን የሚፈጥሩ ስራዎችን ሰርተዋል በሚል አማንያን ላይ የእስር ትእዛዝ ሊወጣ መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ገለጹ፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተከሰቱ ባሉት የክርስትና እና የእስልምና ሀይማኖት አስተምህሮቶች ላይ አንዳንድ ሰባኪያን ግጭት የሚፈጥሩ ቃላቶችን በመጠቀማቸው መንግስት በሀይማኖቶች ጉዳይ ጣልቃ የገባ ሲሆን ይህ ጣልቃ ገብነት ወደ እስራት ደረጃ ማደጉን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡ ሪፖርተራችን ያነጋገራቸው የሁለቱም ሀይማኖቶች የካሴት ሲዲ፣ ቪሲዲና መጽሀፍት አከፋፋዮች እንደገለጹት ወሬው እስካሁን ባይደርሳቸውም የሚጠብቁት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡


አንድ የእስልምና ሀይማኖት የሀይማኖታዊ ነክ መጽሀፍትና ካሴቶች አከፋፋይ እንዳሉት “መንግስት በግብታዊነት እርምጃ ሊወስድ አይገባውም፡፡ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች በጉዳዩ ዙሪያ ጠርቶ አነጋግሮን ምላሽ ሰጥተንበታል፡፡ በቅርቡም ከጠቅላይ ምክርቤቱ የተላለፈ መመሪያ ነው በሚል ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች መጅሊሱ ሳያውቀው እንዳይደረግ ተብሏል፡፡ በዚህ ሁሉ ቅሬታ እያለን የእስር ትእዛዝ የሚወጣ ከሆነ ችግሩ በቀላሉ የሚበርድ አይመስለኝም” ብለዋል፡፡

በቅድስት ሥላሴ መንፈሣዊ ኮሌጅ መምህር የሆኑ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ “በጭምጭምታ ደረጃ ነገሩን ሰምቸዋለሁ መንግስት ይህን ያደርጋል ብዬ አልጠብቅም፡፡ ሆኖም እየተደረጉ ያሉት “ሊደረጉ አይችሉም” የተባሉ ነገሮች ናቸውና ይህም ወደዚያው ማምራቱ አይቀርም፡፡ የሚሰማውም ከዚህ በላይ ነው መንግስት ነገር ማብረድ እንጂ ማባባስ የለበትም” ብለዋል፡፡

መንግስት በሀይማኖት ጉዳዮች ግጭት እንዲፈጠር ሙከራ አድርገዋል በሚል ሊያስርና ሊከስ የሚፈልጋቸው በቪሲዲ፣ በሲዲ፣ በመጽሀፍትና በመጽሄት ስራ ላይ የተሰማሩ አሳታሚዎች ሰባኪያን አከፋፋዮች ብቻ ሳይሆን በጉዳዩ ዙሪያ ተጠርጣሪ ናቸው ያላቸውን በሙሉ እንደሆነ ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡

በተያያዘ ዜና መንግስት ሀይማኖት ነክ ግጭት የሚመክት ዓመታዊ እቅድ በቅርቡ አሰራጭቷል፡፡ ይኸው ከየካቲት 2001 እስከ መጋቢት 2002 ዓ.ም የሚያገለግለው እቅድ “ሀይማኖት ነክ ግጭትና አክራሪነትን ለመመከት. . .” የሚል ርእስ ያለው ነው፡፡ ሃያ ገጾች ያሉት ይኸው እቅድ በመጪው የ2002 ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ያግዛል በሚል እምነት የተዘጋጀ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ እቅዱ ለክልል መንግስታት እና ለሀይማኖት ተቋማት የተሰራጨ ሲሆን ክልሎች ከእቅዱ በመነሳት የየራሳቸውን አሰራር እንዲያወጡ የሚያዝ ነው፡፡ በዚሁ እቅድ ቁጥር 2.1.1 “ከቀጣይ ሀገር አቀፍ ምርጫ በፊት /ግንቦት 2002 በፊት/ በሀይማኖት ዙሪያ ግጭትና አለመረጋጋት የማይፈጠርበት አስተማማኝ ሁኔታ መፍጠር” የሚል አላማ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል፡፡
Source: http://ecadforum.com/blog/2009/04/11/103-ecadf-news-addis-ababa/

April 8, 2009

Trip to Ethiopia includes rare, religious blessing


By Janice Law | April 6, 2009
LALIBELA, Ethiopia — On the flight here, reading of the golden cross, known as Afro Ayigeba, perhaps the most sacred object in this East African country, I had no concept that in a few hours, a priest would be pressing the same cross against my face.

Eleven rock-hewed churches, so remote that electricity arrived only a few years ago, are a World Heritage site, known as Africa’s Petra, visited by thousands of adventuresome international tourists annually.

The monolithic churches, carved out of a 2,600-square-foot rock in the 12th century, were either created overnight by angels in a miracle or by 40,000 workers under King Lalibela, depending on which historical version you accept.

We were visiting during the three days of Timkat (Epiphany), the biggest annual religious festival in a country where Christianity is the official state religion.

As we stumbled shoeless into the church Bet Medhane Alem, the House of the Redeemer of the World, our eyes adjusting from the harsh, desert glare to the cool, dark recesses of 6-foot-thick walls, our guide said: “Look. The priest is blessing pilgrims with the Lalibela Cross. It’s taken out of hiding only rarely and usually during Timkat. It’s extremely rare to see it. You’re very lucky.”

“May anyone be blessed?” I asked our guide.

“Of course.”

I got in line. Soon, the priest in a shimmering white Orthodox robe was pressing this world famous cross against my cheek.

Ethiopians are understandably protective of this revered, ornate icon known as “the soul of Ethiopia.”

It was stolen in 1997, sold to a Belgian antiquities dealer who eventually returned it to Ethiopia years later. Now, two men guard it 24/7.

Visiting the churches, in two locations connected by a series of pitch dark tunnels, precipitous ledges, steep rock stairs to trap doors, is particularly challenging since shoes must be removed outside each church. Industrious locals provide assistance.

The next afternoon, we joined hundreds thronging the famous Timkat procession, where priests hold high the Tabot symbolizing the Ark of the Covenant, containing the Ten Commandments.

Traditional dress of dazzling white, contrasts against jewel colors of velvet and satin worn by the priests.

I purchased a colorful, sequined fringed umbrella, pumping it up and down gleefully as we marched and danced en masse in the blazing sun along the only “paved” street, drums beating, people chanting, bells ringing, horns trumpeting.

Periodically, as a planned part of the ceremony, groups of young men brandishing sticks mock-charged us from vendors’ tents on the sidelines.

It was magic, glorious, and spectacular. A once-in-a-lifetime memory.

Our destination was Tablot Maderia about a half-mile away on a promontory encampment with a specially built sacred pool of water to be used the next morning for blessing.

We visited the encampment again in the night of flickering lamps where the Tabot is kept in a special tent and the faithful picnic, sing and dance in the smoldering incense until and after the 2 a.m. Mass. At dawn, the procession returns the Tabot to the church for another year, where only priests can see it.

Timkat has been described as “opening a window on the authentic world of the Old Testament.”

Inexplicably for such a visited site, Lalibela’s tourist infrastructure is basic at best.

The only paved road is to the airport. Electricity is rationed, so it could go off or on at any time.

There are no banks. The food in our hotel was good; however, it was greatly influenced by the Italian occupation decades ago.

Ethiopians are extremely friendly and gracious. English is widely spoken.

When Texas’ summer heat hits, I’m getting out my green-, pink- and blue-sequined umbrella from Ethiopia.
---
Source: Galveston County Daily News

April 2, 2009

ላሉት የሕልውና ጥንካሬን፤ ለጠፉት ትንሣኤን የሚሰጥ ተስፋ

ላሉት የሕልውና ጥንካሬን፤ ለጠፉት ትንሣኤን የሚሰጥ ተስፋ
የደብረ አሜን ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ የሚገኘው ትንሽ አዳራሽ በምእመናን ተጨናንቋል፡፡ እሁድ ኅዳር 21 ቀን 2001 ዓ.ም፡፡ የመለከት መጽሔት ኅትመት የጀመረበት 17ኛ ዓመት ለማክበር ነው፤ የምእመናኑ የመሰብሰብ ምክንያት፡፡ እናም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተወካይ ላዕከ ወንጌል በዕደ ማርያም ለክብረ በዓሉ የተዘጋጀውን ሻማ ከለኮሱ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት የተጀመረው ይህ በዓል በጸሎት፣ በውይይት፣ በምስጋናና በዝማሬ ደምቆ ነበር፡፡ መለከት መጽሔት በነዚህ ዓመታት የእግዚአብሔርን ቃል ለምእመናን ለማድረስ ባደረገው ጥረት ብዙዎች በእምነታቸው እንዲጸኑ፣ ስለ ሃይማ ኖታቸው ጠንቅቀው እንዲረዱ፣ በተኩላዎች እንዳይነጠቁ፣ ለሥጋዊ እና መንፈሳዊ ሕይወታቸው ስንቅ የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃልን እንዲያውቁ አስችሏል፡፡
በዚህ ክብረ በዓል ላይ በተሳታፊዎች ሲሰጥ በነበረው አስተያየት መጽሔቱ መጠንከር፣ የአንባቢያን ቁጥሯን ማሳደግ ብቻ ሳይሆን ያሉባትንም መጠነኛ ድክመቶች አርሞ የሃይማኖታዊ አስተምህሮ ተልዕኮዋን መወጣት እንዳለባት ነው፡፡ በእለቱ የቀረቡ ሁለት ጥናታዊ ጽሑፎችም ይህንኑ መልዕክት አጠናክረው የሚናገሩ ነበሩ፡፡
በተለይ በወ/ሪት መሠረት ከበደ የቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ የመጽሔቱን አጠቃላይ ድክመትና ጥንካሬ የዳሰሰ ሲሆን ወደፊት መከተል የሚ ኖርበትን አቅጣጫም ጠቁሟል፡፡
የዚህ ጽሑፍ ዓላማ በመጽሔቱ ላይ የቀረበውን ጥናት መቃኘት አይደለም፡፡ በዚህ እለት «የመንፈሳዊ መጽሔቶችና ጋዜጦች የንባብና ሥርጭት ችግር» በሚል ርዕስ በአቶ ነፃነት ተስፋዬ የቀረበውን ጥናት በስሱ ለመዳሰስና በቅርቡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በዚሁ ጉዳይ ላይ የተወያዩበትንና የአቋም መግለጫ ለማመላከት እንጂ፡፡
እንደሚታወቀው የመንፈሳዊ ጋዜጦች ኅትመት 8 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡ በ1939 ዓ.ም መንፈሳዊ የኅትመት ውጤቶች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር መታተም ከጀመሩ ወዲህ ዜና ቤተ ክርስቲያን፣ ድምፀ ተዋሕዶ እና ሌሎችም ጥቂት መንፈሳዊ ጋዜጦችና መጽሔቶች ለኅትመት በቅተው እንደነበር ይታወቃል፡፡
በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥር ከታተሙት በተጨማሪ መለከት እና ሐመር መጽሔት፣ ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣና ሌሎችም መንፈሳዊ የኅትመት ውጤቶች ዛሬ ድረስ ምዕመናንን ሲያስተምሩና ሲያነቁ መቆየታቸው እሙን ነው፡፡
ጥናት አቅራቢው በጽሑፋቸው እንዳሰፈሩት እነዚህ የኅትመት ውጤቶች ቃለ እግዚአብሔርን በማስፋፋት ረገድ እየተጫወቱት ያለውሚና ቀላል የሚባል አይደለም፡፡
የመንፈሳዊ ጋዜጦች ኅትመት 8 ዓመት ታሪክ ቢኖረውም፤ ከአጀማ መሩ አንፃር ሲታይ ሂደቱ እጅግ አዝጋሚ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ከክርስቲያኑ ሕዝብ ቁጥርና ፍላጎት ጋር ሲታይ የኅትመት ብዛቱ፣ ዓይነቱም ሆነ ሥርጭቱ የሰማይና የምድር ያህል ነው ቢባል አልተጋነነም፡፡ ዛሬ ከሰባ ሦስት ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ከሚገመተው የሀገሪቱ ሕዝብ ቁጥር በአብዛኛው ክርስቲያን ነው፡፡ በዚህ ውስጥ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ቁጥርም እጅግ ከፍተኛ እንደሆነም ይታመናል፡፡
አቶ ነፃነት የኅትመት ውጤቶችን በንፅፅር ሲያስቀምጡም በአሁኑ ወቅት የመንግሥትን ሳይጨምር ከ 22 በላይ ጋዜጦች በኅትመት ላይ ይገኛሉ፡፡ በውል የሚታወቁት መንፈሳዊ ጋዜጣዎችና መጽሔቶች ግን ከ6 አልበለጡም፡፡ እነዚም መንፈሳዊያን ጋዜጦችና መጽሔትም በወር በአማካኝ ከሃምሳ እስከ ሰባ ሺህ ቅጂዎች ብቻ ሲታተሙ ዓለማዊ ጋዜጦች ግን ዘጠኝ መቶ ሰባ ሁለት ሺህ ቅጂዎች ታትመው ለሥርጭት ይበቃሉ፡፡
እንደ ጥናቱ ዝርዝር ሠላሳ ስድስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ለሚሆኑ ምእመናን የሚደርሰው ከ70ሺ ያልበለጠ ኮፒ ነው፡፡ ይህ ኮፒ ለምእመናን ቃለ እግዚአብሔርን ማድረስ አስችሏል ብሎ ለመናገር የሚደፍር አይኖርም፡፡
ዛሬ ዛሬ የንባብ ባህል ቢያድግም በአሠረጫጨት ችግር ምክንያት የምእመናንን ፍላጎት ማሟላት አልተቻለም፡፡ መንፈሳዊ ምግብን የመቋደስ እድል በጥቂት ዋና ዋና ከተሞች ብቻ መወሰኑም ይኸው የአሰረጫጨት ችግር መሆኑ በዚሁ ወቅት ተነግሯል፡፡
በቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደር መዋቅር ከሀገረ ስብከት እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ወጥ የሆነ የሥርጭት መስመር አለመኖር፣ የመጽሔትና ጋዜጣቹ ዝግጅት ሳቢ አለመሆን፣ ምእመናን ለዓለማዊ የኅትመት ውጤቶች ትኩረት መስጠት፣ የኅትመት ዋጋ ንረት እና የመሳሰሉት ምክ ንያቶች የመንፈሳዊ ኅትመቶች ወደ ምእመናን ዘንድ እንዳይደርስ እንቅፋት ሆነዋል፡፡
ለተጠቀሱት ችግሮች በጥናታዊ ጽሑፉ እንደ መፍትሔ የተቀመጡ ነጥቦችም አሉ፡፡ የጋዜጦቹንና የመጽሔቶችን አቀራረብ ይዘት እንደ ዘመኑ ሁኔታ ማስተካከል፣ ማሻሻል፣ በምእመናን ዘንድ የንባብ ባህልን ለማሳደግ መጣር ይገባል፡፡ በዚህም የሰርክ ጉባኤ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ የርዕሰ አድባራት፣ የጽዋና የጉዞ ማኅበራት እንዲሁም ሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት አስተዋጽዖአቸው ከፍተኛ እንደሆነ በማሰብ እነርሱን መጠቀምም ተገቢ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱ በራሷ መዋቅር መጽሔቶችና ጋዜጦች የሚሰራጩበትን መንገድ መፍጠር፣ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ያሉ የንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቆችን አጠናክሮ መጠቀም፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በሥርጭቱ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማመቻቸትና የኅትመት ውጠ@ቶችን ለሚያድሉ ማስታወቂያ ማውጣት ችግሮቹን ለመቅረፍ እንደ መፍትሔ በጥናታዊ ጽሑፉ ተመልክቷል፡፡
ይህን ጥናታዊ ጽሑፍ መሠረት በማድረግ በእለቱ የተደረገው ውይይት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ጋር ለመ ድረስ ቤተ ክርስቲያኒቱ ቃለ እግዚአብሔርን የያዙ የኅትመት ውጤቶችን በዓይነትና በስፋት ማብዛት እንዳለባት ነው የተጠቆመው፡፡
ዛሬ በገበያ ላይ አሉ የተባሉት የኅትመት ውጤቶች ከሌሎች የሃይማኖት ድርጅቶች ኅትመቶች ጋር ሲነፃፀር ኢምንት መሆኑም ይታወቃል፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ ምእመናንን ወደ ሌላ ሃይማኖት የሚሳቡበትን ሁኔታም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያባባሰው መምጣቱን በወቅቱ አንዳንድ ተሳታፊዎች ከሰጡት አስተያየት ለመረዳት ተችሏል፡፡
ይህ የመንፈሳዊ የኅትመት ውጤት የንባብና ሥርጭት ችግር መፍትሔ ያገኝ ዘንድ በተለያዩ መድረኮች መነሳቱ አልቀረም፡፡ በቅርቡ በኢትዮ ጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ¬ትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በተካሄደው የሁለት ቀን ሀገር አቀፍ የሰበካ ጉባኤ ሴሚናር ላይ የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዋና አዘጋጆ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍም ይህንኑ የሚያስገነዝብ ነው፡፡
«ከሰባት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶችን ያቀፈች፣ በየደብሩ አያሌ የአብነት መምህራን ያላት፣ ከመንፈሳዊ ኮሌጆች በድግሪና በዲፕሎም የተመረቁ፣ በተለያዩ ልሳናት የሚናገሩ የሥነ ጽሑፍ ችሎታ ያላቸውና የየራሳቸውን መጽሐፍ በመጻፍ ችሎታቸውን ያስመሰከሩ በርካታ ዘመናውያን ልጆች ያሏት ቤተ ክርስቲያን የሰው ኃይልና የገንዘብ አቅም እጥረት ሳይኖርባት በአስተዳደር ድክመት፣ የመደራጀትና የማደራጀት ክህሎት በማጣት ብቻ እንዴት በጋዜጣና መጽሔት ድርቅ ትመታ)» ሲሉ በጥናታዊ ጽሑፋቸው አምረው የገለጹት መጋቤ ምስጢር፤ የሴሚናሩ ተሳታፊዎች በጉዳዩ አንድ መፍትሔ ይፈልጉ ዘንድ የተማጽንኦ ቃላትም ሰንዝረዋል፡፡
የዚህ ሴሚናር ማጠቃለያ ላይ የተነበበው የአቋም መግለጫ ላይ ይህን ኅትመትን በማስመልከት የሰፈረው ነጥብ ተሳታፊዎቹ ጉዳዩን በጥልቀት የተገነዘቡት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአቋም መግለጫው ቁጥር አራት የሰፈረው ቃል እንዲህ ይላል፡፡
«በመንበረ ¬ትርያርኩ የሚታተመው ጋዜጣና መጽሔት ውስን መሆኑ ተነግሯል፡፡ እነዚህ ጋዜጦችና መጽሔቶች ሥርጭታቸውም ችግር እንዳለበት ታውቋል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ ተልዕኮ ይሳካ ዘንድ ጋዜጦችና መጽሔቶች ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ጋዜጦችና መጽሔቶች በሰው ኃይል በሊቃውንትም ተጠናክረው በብዛትና በጥራት እንዲታተሙ እስከ ቅርብ ዓመታትም እየታተሙ ለአንባቢዎች ይሰራጩ የነበሩ በአሁኑ ጊዜ የተቋረጡ መጽሔቶችና ጋዜጦች ኅትመታቸው እንዲቀጥል፣ አቅም ያላቸው የአህጉረ ስብከት ጽ/ቤት አብያተ ክርስቲያናት የሊቃውንት ተሳትፎ ያልተለያቸው ትምህርታዊ ጽሑፎችን እያሳተሙ እንዲያሰራጩ ጉባኤው አበክሮ ይጠይቃል፡፡» ይህ አቋም ላሉት የሃይማኖት መጽሔቶች ህልውና መጠንከር፤ ለጠፉትም ትንሳኤን የሚያስገኝ ተስፋን ይሰጣል፡፡ በዚህ ረገድ የምእመናኑ ፍላጎት ከፍተኛ ነው፡፡ በሃይማኖቱ እንዲጸና፣ እንዲጠነክር፣ እንዲበረታ፣ በእግዚአብሔር ቃል እየተጽናና፣ ነሕይወቱን እንዲያለመልም ብቃት፣ ጥራትና ብዛት ያላቸው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅትመት ውጤቶች ያስፈልጉታል፡፡ ለዚህ ደግሞ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ እያንዳንዱ ደብር እንቅስቃሴ ሊያደርጉ ይገባል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ከቡር፡፡
Source: Mahibere Kidusan WebsiteApril 1, 2009

በሃይማኖት መቻቻል የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ደካማ መሆኑ ተጠቆመ

በሃይማኖት መቻቻል የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ደካማ መሆኑ ተጠቆመ
በሰለሞን ጎሹ

(Wednesday, 01 April 2009)ኢትዮጵያ የዳበረ የሃይማኖት መቻቻል ባህል ያላት ቢሆንም የተሰራው ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ደካማ መሆኑ የተለያዩ ሃይማኖቶች ተከታዮች ባደረጉት ውይይት ላይ ተገለፀ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማስታወቂያ ቢሮ ማስታወቂያና ህዝብ ግንኙነት ወሳኝ የሥራ ሒደት ከፎረም ፎር ፌዴራሊዝምና ዲሞክራሲ ጋር በመተባበር በትላንትናው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ "የሃይማኖት እኩልነትና ነፃነት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የፓናል ውይይት የመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ ምሁራንንና የተለያዩ ሃይማኖቶችን ተከታዮች በጋራ ማወያየት እና ሃሳብ መለዋወጥ አስችሏል፡፡
አንዳንድ ጥቃቅን ምክንያቶች ለከፍተኛ ግጭትና አለመግባባት የሚዳረጉት ተከታታይ የሃይማኖት መቻቻል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ባለመሠራታቸው መሆኑን የተቹ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች አንዳንዶች የሃይማኖት ነፃነትና እኩልነት መብት ብቻ እንጂ ግዴታ ያለበት መብት መሆኑን እንደማይቀበሉ ተችተዋል፡፡

በእለቱ በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር የሆኑት አቶ ሱልጣን ቃሲም "የሃይማኖት እኩልነት፣ ነፃነትና መቻቻል ዓለም አቀፍ ገፅታ" በተሰኘ ርዕስ ጥናት ያቀረቡ ሲሆን በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ የህግ መምህር የሆኑን አቶ ፀጋዬ ረጋሳ "የሃይማኖት እኩልነትና ነፃነት በኢትዮጵያ ህግ" በሚል ርዕስ ሌላ የጥናት ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡ ውይይት ከሰዓት ሲቀጥል የሃይማኖት ሚና ሰላምን በመገንባት ረገድ በሚል ርዕስ የፎረም ፎር ፌዴራሊዝምና ዴሞክራሲ ፀሐፊ አቶ ልዑልሰገድ ታደሰ ጥናታቸውን ሲያቀርቡ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የመንግሥት ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ "የሃይማኖት መቻቻል በኢትዮጵያ፣ ተግዳሮቶችና መፃኢ እድል" በሚል ርዕሰ ጥናት አቅርበዋል፡፡

ከተሳታፊዎቹ በአፅንኦት የተነሳው ነገር የኢትዮጵያ የዳበረ የሃይማኖት መቻቻል እንዳይበረዝና የተለያየ የኢኮኖሚና የፖለቲካ አጀንዳ ያላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች መጠቀሚያ እንዳይሆን ለማድረግ መንግሥት፣ የሃይማኖት ተቋማትና የሃገር ሰላምና ስሜት የሚያሳስባቸው ወገኖች በሙሉ በግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራው በቀጣይነትና በተከታታይነት መሳተፍ እንዳለባቸው ነው፡፡

የጥናት አቅራቢዎቹን ሃሳብ ተከትሎ ተሳታፊዎቹ የየራሳቸውን ሃይማኖት ምሳሌ በማድረግ ልምዳቸውን ያካፈሉት ተሳታፊዎች መንግሥት ከሃይማኖት የተለየ መሆኑን ህገ መንግሥቱ ያረጋገጠ ቢሆንም ጥቃቅን ምክንያቶች ለትልቅ ግጭትና ብጥብጥ እየዳረጉ በሚገኙበት ሁኔታ የመንግሥት ዝምታ ወይም ግዴለሽነት አደገኛ ሁኔታን ሊፈጥር ስለሚችል በሃይማኖት ነፃነትና እኩልነት መብት ላይ የተቀመጡትን ገደቦች መንግሥት በአሳማኝ ሁኔታ፣ ነፃና ገለልተኛ ሆኖ ሊፈፅማቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በሃይማኖት ጉዳይ - ተቃዋሚዎች ላይ ጣት ተቀሥሯል

በጌታቸው ንጋቱ
በኢትዮጵያ ባልተለመደ መልኩ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እዚህም እዚያም የሃይማኖት ግጭቶች ደረሱ ሲባል ምንድነው ነገሩ የሚል ጥያቄ በሁሉም ሕሊና ውስጥ ይነሳል፡፡ ኢሕአዴግ ሃይማኖትን ሽፋን ያደረጉ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች መበራከታቸውን ሲገልፅ ሃይማኖትን መደበቂያ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ፖለቲከኞች እንዳሉም ይገልፃል፡፡ ተቃዋሚዎች ሃይማኖትን ለፖለቲካ መጠቀሚያ እንደማያደርጉ ሲገልፁ የኢሕአዴግንም አገላለፅ "ጅምላ" ፍረጃ በማለት ይቃወማሉ፡፡
ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ይንቀሳቀሳሉ ያላቸውን የፖለቲካ ኃይሎችንም ኢሕአዴግ "የከሠሩ ፖለቲካኞች" ሲል ይገለፃቸዋል፡፡ ፓርቲው ልሣኑ በሆነው አዲስ ራዕይ መፅሄት ላይ እንደገለፀው "ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች አክራሪና የከሠሩ ፖለቲከኞች ሃይማኖትን በሽፋንነት በመጠቀም ግጭት ለመቀስቀስ ሲሞክሩ ማየትና መስማት የተለመደ ነው፡፡ ሃይማኖትን በሽፋንነት ለመጠቀም የቆረጡት እነዚህ ወገኖች በአገራችን ለሃይማኖት እኩልነትና ነፃነት የተፈጠረውን አመቺ ሕጋዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ በመጠቀም የመንግሥትን ቻይነት እንደድክመት በመቁጠር በአደባባይ ሕግን ተላልፈው እስከመንቀሳቀስ ደርሰዋል" ሲል ያስረዳል፡፡

"ሃይማኖትን በሽፋንነት ለመጠቀም ሲደረግ የቆየው ሙከራ ከተጀመረ የሠነባበተ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የክርስትናንም ሆነ የእስልምና ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሚካሄደው ቅስቀሳና ማነሳሳት ገደቡን አልፎ ሲገለፅ ሠንብቷል" የሚለው ፓርቲው ጠብ ያለሽ በዳቦ ዓይነት አካሄድ በክርስትናም፤ በእስልምና ሃይማኖትም ውስጥ ሰርገው በገቡ ተቃዋሚዎች እየተፈፀመ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ተቃዋሚዎች በአንድ ቃል ይህንን የኢሕአዴግ ፍረጃ እንደማይቀበሉት ይገልፃሉ፡፡ ይሁን እንጂ ኢሕአዴግ ከምርጫ 97 በኋላ ተስፋ የቆረጡ ተቃዋሚዎች ፖለቲከኞች ሃይማኖትን በመጠቀም አጀንዳቸውን እያራመዱ እንደሆነ ይገልፃል፡፡

በሃይማኖት ሽፋን ግጭት ለመቀስቀስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በብቃት ለመመከት የሚቻለው መንስዔውን በትክክል መገንዘብ ሲቻል መሆኑን የሚገልፀው ፅሁፍ ለግጭት መንሥዔ ሊሆኑ አይችሉም ብሎ የሚያምንባቸውን ጉዳዮች በመጀመሪያ ይለያል፡፡ የመጀመሪያው አመለካከትም "ሃይማኖት መቼም ቢሆን የግጭት መንስዔ ሊሆን አይችልም" የሚል ነው፡፡ ይህም መነሻውን ያደገው ሃይማኖት ፍቅርና ሠላምን፤ ትዕግሥትና መቻቻልን እንጂ ጥላቻና ግጭትን የሚሰብክ ይዘት የለውም የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው መነሻ "ሕገ መንግሥታዊ ስርዓታችን ለሃይማኖት ግጭት ቦታ የለውም" የሚል ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱ የሃይማኖት የግል እንደሆነና በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ሃይማኖቶች እኩል እንደሚታዩ ቢደነገግም "የከሰሩ ፖለቲካኞች ይህንን የሃይማኖት እኩልነት የረባ ሕጋዊና ፖለቲካዊ ምክንያት በሌለበት ወቅት የሚካሄዱ ግጭቶች የመቀስቀስ ሙከራዎች መንስዔያቸው አሁንም ፍላጐታቸውን በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ ማራመድ የተሳናቸው ወገኖች እንደሆኑ አመላካች ነው" ይላል፡፡

በእርግጥ ኢሕአዴግ እንደሚለውና እንደሚያምነው ተቃዋሚዎች በሃይማኖት ግጭት እናተርፋለን ብለው ያስባሉ? ወይስ ኢሕአዴግ ትክክለኛ ባልሆነ መልኩ እየፈረጃቸው ነው? በትክክል በእንደዚህ ዓይነት የወንጀል ተግባር የተሰማሩ ተቃዋሚዎች ካሉስ የትኞቹ ናቸው? ካለስ ተለይተው ለምን ለፍርድ አይቀርቡም? የሚሉና ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡

ተቃዋሚዎቹ በዚህ ዙሪያ በሚሰጡት ምላሽ ኢሕአዴግ ሕዝቡን ለማሸማቀቅና ከተቃዋሚዎች ጋር የሚሰለፍ ኃይል እንዲጠፋ ሆን ብሎ የሚነዛው ፕሮፖጋንዳ ነው በማለት ይቃወማሉ፡፡ የፈንጂ አደጋ፣ የሃይማኖት ግጭት፣ የኤርትራ ጉዳይ በተነሱና በደረሱ ቁጥር ተቃዋሚዎች እጃቸው እንዳለበት ኢሕአዴግ መግለፁ የተቃዋሚውን ኃይል ከሕዝቡ ለመለየትና የራሱን አቅም ለማደራጀት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ኢሕአዴግ የፖለቲካ መድረኩን እያጠበበ መምጣቱን ከሚታይበት መንገድ አንዱ የሆነው እንደዚህ ዓይነቱ ፍርጃ ነው ይላሉ፡፡ ተቃዋሚዎቹ በአገሪቱ ሠላምና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ለማድረግ እንጂ ለብጥብጥ እንዳልተደራጁም ይናገራሉ፡፡

"የአገር ውስጥ የከሠሩ ፖለቲከኞች ሃይማኖትን እንደ ምሽግ መጠቀም መርጠዋል" የሚለው የኢሕአዴግ ልሳን የሆነው አዲስ ራዕይ "በአገሪቱ የሃይማኖት እኩልነትን በሕግና በተግባር ለማረጋገጥ በተካሄደ ትግል የተሳካ ውጤት ለማምጣት ብንችልም የከሠሩ ፖለቲከኞች በሃይማኖት ዙሪያ ሁከትና ብጥብጥን ለመቀስቀስ የማይሞክሩት ነገር የለም" ሲል ይወነጅላል፡፡

እነዚህ ሃይሎችም በሁሉም ሃይማኖቶች ውስጥ ሠርገው በመግባት ሃይማኖቱን በፖለቲካ ለመበረዝ የተለያዩ ጥረቶች እንደሚያደርጉ የሚገልፀው ኢሕአዴግ "የከሠሩ ፖለቲከኞች የወቅቱ ስልት በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ሠርገው በመግባት ሃይማኖትን የፖለቲካ አላማቸው ማራመጃ ማድረግ ሆኗል" ይላል፡፡

የከሠሩ ፖለቲከኞች ተብለው የተፈረጁትም በምርጫ 97 ተወዳድረው የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምርጫን አሸንፈውና በፓርላማና በክልል መቀመጫ አግኝተው፤ ሙሉ በሙሉ ስልጣን ካልያዝን ብለው ወደ አመፅ ያመሩት ኃይሎች፤ የአመፅ መንገዳቸው ስለተዳፈነ የመረጡት አዲስ የትግል ስልት መሆኑን ኢሕአዴግ ይገልፃል፡፡ ተበታትኖና ተከፋፍሎ ያለቀው የምርጫ 97 ዋነኛ ተቃዋሚ ቅንጅት አባላት የነበሩ ሰዎች አሁን እዚህም እዚያም ለሚታዩ የተለያዩ የሃይማኖት ተከታዮች ግጭት አንቀሳቃሾች እንደሆኑም ይገልፃል፡፡

"ሃይማኖትን በሽፋንነት ለመጠቀም የሚሹት እነዚህ ኃይሎች በኦርቶዶክስም ሆነ በእስልምና ሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ቀላል በማይባል ደረጃ ሰርገው ለመግባት ችለዋል፡፡ አንዳንድ የሃይማኖት መሪዎችም ከመንፈሳዊ ግዴታቸው ባፈነገጠ አኳኋን አለማዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ እስከመግባት ሲደርሱ መመልከት የተለመደ ሆኗል" የሚለው ልሳኑ "የከሠሩ ፖለቲከኞች" የሚላቸው ወገኖች "በሃይማኖት ተቋማት ዙሪያ ሠርጐ በመግባት ብቻ ሳይወሰኑ የመንግሥት ተቋማትንም በሃይማኖት አስተሳሰብና ወገናዊ ተግባር በመበከል የሚፈልጉትን የገበያ ግርግር ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ" መምጣታቸው የተለመደ ተግባር መሆኑን ያትታል፡፡

"የከሠሩ ፖለቲከኞች" ሰርገው ለገቡበት ወይም ደግሞ ለብጥብጥ መፍጠሪያ በሽፋንነት ለሚጠቀሙበት ሃይማኖት አክብሮት እንደሌላቸው የሚገልፀው ኢሕአዴግ "በዚህ ረገድ ከሚታዩት እውነታዎች ቀዳሚው የአገራችን የጥፋት ፖለቲከኞች ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ትግል በከፍተኛ ደረጃ መጋለጣቸውና መሸነፋቸው ነው፡፡ ስልጣንን ከተቻለ በምርጫ ካልተቻለ ደግሞ በሃይል ለመያዝ አልመው የተነሱት ኃይሎች በሁለቱም መንገድ እንደተሸነፉ በግልፅ ይታወቃል፡፡ በምርጫ የተወሰነ ወንበር ለመጨመርና አዲስ አበባንም ለማሸነፍ ችለው የነበሩት ተቃዋሚዎች ሁሉንም ስልጣን ካልጠቀለልን ብለው ወደ አመፅ ካመሩ በኋላ አመፁ በቁጥጥር ሥር ውሎ በሕጋዊ ትግልም ተረትተው ክፉኛ ተጋልጠዋል" ይላል፡፡

ኢሕአዴግ በዚህ መልኩ ያስቀመጠው ቅንጅትን ሲሆን በዚህ ሥም ደግሞ በሕጋዊ መልኩ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ አለ፡፡ በአቶ አየለ ጫሚሶ የሚመራው ቅንጅት በፊት አባል የነበሩትንና ሌሎችንም አሰባስቦ በአዲስ መልክ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ይገልፃል፡፡ የቀድሞው የቅንጅት ሊቀመንበር አቶ ኃይሉ ሻውል መኢአድ (የመላው ኢትዮጵያዊያን አንድነት ድርጅት) ፕሬዚዳንት ሆነው እየሠሩ ነው፡፡ ዕጩ ከንቲባ ሆነው የነበሩት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከባህር ማዶ መታገልን መርጠዋል፡፡ ወ/ሪት ብርቱካን የሚመሩት አንድነት ፓርቲ በአዲስ መልኩ ቢደራጅም ሊቀመንበሯ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ወሕኒ ቤት ይገኛሉ፡፡ አቶ ልደቱ ኢዴፓን በፕሬዚዳንትነት በመምራት ይገኛሉ፡፡

ኢሕአዴግ ከሃይማኖት ግጭቶች ጀርባ አሉ የሚላቸው የትኞቹን ኃይሎች እንደሆነ በግልፅ ባያስቀምጥም ከምርጫ 97 በኋላ "የከሠሩ ፖለቲከኞች" ያመጡት እንደሆነ ይገልፃል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኢሕአዴግ ሆነ ብሎ እንዲሸማቀቁ ለማድረግና የተዳከመ የተቃዋሚ እንቅስቃሴ እንዲኖር ለማድረግ እንጂ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት የፖለቲካ ትርፍ የማግኘት ሃሳብን ሙሉ በሙሉ እንደማይቀበሉትና እንደማይደግፉ ያስረዳሉ፡፡ ተቃዋሚዎች በዚህ መልኩ ከተፈረጁ አባላት ለማሰባሰብ ይቸገራሉ፤ የሕዝብ ድጋፍ ያጣሉ በሚል ስሌት ሆን ብሎ ኢሕአዴግ እያጠቃቸው መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ኢሕአዴግ ከተቃዋሚዎች በመቀጠል በተለያዩ ቦታዎች ለሚታዩ የሃይማኖት ግጭቶች ምክንያት የሆኑና ያባባሱ ያላቸውን ኃይሎች ዘርዝሯል፡፡ የየራሳቸው አጀንዳ ያላቸው የውጭ ኃይሎችም እጃቸው እንዳለበት፣ የሚገልፀው ልሳኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው ዘመናዊ የመስቀል ጦርነት ኢትዮጵያ አንድ አካል እንድትሆን የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እንደሚደረጉ ያመለክታል፡፡ በሃይማኖት ሽፋን ለሚፈጠር ግርግር አመቺ ሁኔታ የሚፈጥሩ ተጨማሪ ጉዳዮች ተብለው ከቀረቡትም በላይ ሁሉ ግን "የከሠሩ ፖለቲከኞች" የተባሉት ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

"በሃይማኖት ሽፋን ግጭትን ለመቀስቀስ የሚደረገው ሙከራ በዋነኛነት በአገር ውስጥ ካሉ የከሠሩ ፖለቲከኞች ከዚሁ ጋር በተያያዘ አኳኋን ደግሞ ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ አክራሪዎች ሽኩቻ መናሃሪያ ለማድረግ በሚፈልጉ የውጭ ኃይሎች የተጠነሰሰና የሚራመድ ቢሆንም ለዚህ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ውስጣዊ ድክመት የለንም ማለት አይቻልም" የሚለው ልሳኑ የሃይማኖት ተቋማትም ያለባቸውን ድክመት ያስቀምጣል፡፡

እንደ ኢሕአዴግ እምነት በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄድ የፖለቲካ ግጭት ስልት ለማምከን መውሰድ ያለባቸው እርምጃዎች አሉ፡፡ "ታግሎ ማሸነፍ የሚቻለው በአንድ በኩል መላውን የድርጅታችንን አቅም በፖለቲካዊ ትግሉ ላይ በማረባረብና ተፈላጊውን ውጤት በማምጣት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሰላም ወዳጅ የአገራችን ሕዝብ በጉዳዩ ላይ ግልፅነት እንዲኖረው በማድረግ የመፍትሔው አካል ሆኖ እንዲታገል በማድረግ ነው" ይላል፡፡ በመሆኑም ኢሕአዴግ የከሠሩ ፖለቲከኞች የሚላቸውንና የራሳቸው አጀንዳ ያላቸው የውጭ ወገኖች ለሚያካሂዱት አፍራሽ እንቅስቃሴ ለም አፈር ሆነው የሚያገለግሉ የፓርቲውን ችግሮች አንድ በአንድ ነቅሶ ማወጣት እንደሚያስፈልግ ይገልፃል፡፡ በዚህም የመንግሥት ኃላፊዎችንና የከተማ ከንቲባዎችን ጭምር ገለልተኛ ባለመሆን ተችቷቸዋል፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኢሕአዴግ የተለያዩ ችግሮች ሲፈጠሩበት ጥፋቱን በተቃዋሚዎች ላይ በማስቀመጥ መፈረጁን የማቃወሙ ፖለቲከኞች አሁንም በሃይማኖት ሽፋን ይንቀሳቀሳሉ መባላቸውን አይቀበሉትም፡፡ የሃይማኖት ግጭት የሃገሪቱ ታሪክ እንዳልሆነና ይህንንም አጥብቀው እንደሚታገሉት ያስረዳሉ፡፡

የኢትዮጵያ ቅርሶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሰዋል


በሔኖክ ያሬድ

የአገር ሥልጣኔ፣ የአገር ታሪክ፣ የአገር ሥነ ጥበብ አመልካች የሆኑት የኢትዮጵያ ቅርሶች በመጥፋትና በመሰረቅ እየጠፉ መሆናቸው ተጠቆመ፡፡
ከዘመነ አክሱም ጀምሮ ተሰባስበው የነበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ቅርሶች በአውሮፓና በአሜሪካ የቅርስ ገበያዎች ላይ እየተሸጡ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
በብሔራዊ ሙዚየም መጋቢት 5 ቀን 2001 ዓ.ም. በተዘጋጀውና “ቅርሶች እንዴት ይጠበቁ?” በሚል ርእስ በማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማዕከል በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ፣ አርኪዮሎጂስቱ አቶ ተክሌ ሐጎስ እንደተናገሩት፣ የኢትዮጵያ ቅርሶች በአሁን ጊዜ በጣም አሳሳቢ ችግር እየገጠማቸው ነው፡፡
“ቅርሶች የታሪክ መረጃዎች ናቸው፡፡ ቅርሶች ከሌሉ የአገራችን ታሪክ ተረት ሆኖ ነው የሚቀረው፡፡ መረጃው ያለው በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ መረጃው እየተሸረሸረ እየተናደ እየጠፋና እየወደመ ነው፡፡” ያሉት አቶ ተክሌ፣ የችግሩን ምንጭ አመልክተዋል፡፡

የሕገ ወጥ የቅርስ ዝውውር በአገራችን በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በዓለም አቀፍም፣ በገጠርም በከተማም በስፋት እየተካሄደ ነው፡፡ በአሜሪካ ኢቤይ በሚባል ድረ ገጽ የቅርሶቹ የጨረታ ሽያጭ ይፈጸማል፡፡ ድረ ገፁ ለ48 አገሮች ሽያጭ የሚያካሂደው በኢትዮጵያ ቅርሶች ላይ ሲሆን፣ በከፍተኛ ደረጃ የሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቅርሶች የሆኑት የብራና መጻሕፍት ናቸው፡፡

መጻሕፍቱ ታሪኩንም፣ ንባቡንም፣ ጥበበ ዕዱንም፣ ፊደሉንም የያዙ መሆናቸውና ከብረታ ብረትና ከእንጨት የተሰሩ መስቀሎችም እየተቸበቸቡ ናቸው፡፡

በአቶ ተክሌ አነጋገር፣ “ሁላችንም ልናስብ ልንቆረቆር ይገባናል፡፡ በባለቤትነት የቤተክርስቲያን ይሁን እንጂ ቅርስ የሕዝብ ነው፡፡ ሌላው ቅርሶችን አደጋ ላይ የከተታቸው ሕገወጥ ቁፋሮ ነው፡፡ በመሬት ውስጥ ብዙ የአርኪዮሎጂ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡ በመቃብርና በቤተ እምነት ቦታዎች የተቀበሩ ንዋየ ቅድሳት ለማውጣት እየተባለ የቁፋሮ ጥበብ በሌላቸው ሰዎች ቁፋሮ እየተካሄደ በመሆኑ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው፡፡”

ቅርስን፣ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናትን ለመጠገን፣ ጥንት የተሰሩትንም ለማደስ በሚደረግ አዝማሚያ፣ መልካቸውና ጥንታዊ ታሪካዊ ይዘታቸውንና የሥነ ጥበብ ውበታቸው ያጡና ዘመናዊ ቤት ይሆናል ያሉት አርኪዮሎጂስቱ በምሳሌነት ያቀረቡት በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ላይ የተፈጸመውን ጥገና ነው፡፡

“ቤተ መርቆሪዎስ ላይ ከአለት በተፈለፈለ ቤተ ክርስቲያን ላይ እንጠግናለን ብለው ዘመናዊ የሆነ ብሎኬት ተክለዋል፡፡ በዚያ ጥበብ ላይ ባዕድ የሆነ የዘመኑ ቁስ ሲደረግበት አስቀያሚና ከባድ አዝማሚያ ስለሆነ ልናስወግደው ይገባል፡፡”

አሮጌ ሕንፃን አፍርሶ በአዲስ መሥራት እየታየ ያለ አደገኛ አዝማሚያ መሆኑን ያወሱት ባለሙያው በተለይ በዘመነ አክሱም ሆነ በኋላ የተሰሩትን ጥንታውያን ሕንፃዎች አፍርሶ በአዲስ ለመተካት የሚንቀሳቀሱበት መንገድ አሳሳቢ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

“በ4ኛው መቶ ዘመን የተሰራችውና በትግራይ የምትገኘውን አንዛ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አፍርሰን ሌላ ሕንፃ እንሰራለን ይባላል፡፡ ያ የጥንቱ የአርኪዮሎጂ መረጃ፣ የቤተ ክርስቲን ታሪኳ በሙሉ ፈጽሞ ይጠፋል፡፡ አደገኛ አካሄድ ስለሆነ ሊገታ ይገባዋል” ብለዋል፡፡

ያሉት ቅርሶች አጠባበቅና አያያዝ ሌላው አሳሳቢና አሳዛኝ መሆኑም በተጠቀሰበት የውይይት መድረክ የብራና መጻሕፍቱ አቀማመጥ፣ የዕቃ ቤቱ ገጽታ፣ መስቀሉ፣ ብራናው፣ ሥዕሉ፣ ከብረት፣ ከእንጨት የተሰራው አንድ ላይ መነባበሩ ለጥፋት እየዳረገው መሆኑ ተመልክቷል፡፡ “አንዱ ለአንዱ ጠር ነው፡፡ በሥነ ሥርዓት እንኳን አልተቀመጡም፡፡ ቅርሶቹ ሲቀመጡ አየርም አያገኙም፡፡ ለምስጥ፣ ለተባይ፣ የተጋለጡ ናቸው” ያሉት ባለሙያው የ14ኛውን 15ኛ መቶ ዘመን ብራናዎች የሚገኙበት የጣና ሐይቅ ደሴቶች ገዳማትና በአዲስ አበባም በሚያሳስብ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ አመልክተዋል፡፡

የብራና መጻሕፍት አጠቃቀም ላይም ተመሳሳይ ችግር ይታያል፡፡ በአብዛኛው አያያዙ ሥርዓት የለውም፡፡ በትግራይ በሚገኘው የአባ ገሪማ ገዳም ረዥም ዕድሜ ያስቆጠረ ረ1,500 ዓመትሪ የብራና መጽሐፍ ቢኖርም ባለሥልጣኖችና ፈረንጆች ሲመጡ እያወጡ በማሳየትና በእጅ ሲያገላብጡት ለአደጋ እየተጋለጠ በመሆኑ በሥርዓት ሊያዝ እንደሚገባና ሥዕሎቹንም በፍላሽ ፎቶ ግራፍ በማንሳት በመደብዘዝ ላይ በመሆናቸው የሚመለከተው ክፍል ትኩረት እንዲሰጥበት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

በላሊበላም በመኪና መድኃኔ ዓለም ዐምዶች ላይ ያሉት ሥዕሎች ላይ ሰዎች እየተደገፉ፣ ሻማ፣ ጧፍ እያነደዱ እየጠፉ በመሆናቸው በሁሉም አካባቢ ተገቢው ትኩት ካልተሰጠው የቅርሶቹ ሕልውና አሳሳቢ እንደሚሆን ተመልክቷል፡፡

“በአገሪቱ ላሉት ችግሮች መንስኤው አንደኛው በአንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን ያለው ቅርስ በቅጡ አይታወቅም፡፡ እንዲታወቅም አይፈለግም፡፡ ያለው አካሄድ ይህ ነው፡፡ ካላወቅነው አንቆጣጠረውም፡፡ ስለማይታወቅ በየጊዜው ወደ አሜሪካ እየሄደ እየተቸበቸበ ነው፡፡ ስለዚህ በየቦታው ያለው ቅርስ ተቆጥሮ ከተመዘገበ የጎደለው ይታወቃል ያሉት አቶ ተክሌ፣ የቤተ ክርስቲያን ቅርስ ጠባቂዎች በቅርስ ላይ ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛና ተቆርቋሪነትም ስማይታይ የማስገንዘቢያ መድረክ በተከታታይ ማዘጋጀት አስፈላጊነቱን ጠቁመዋል፡፡

በመንግሥት በኩልም ለቅርሶች ትኩረት ተሰጥቶ ልዩ ልዩ አዋጆችና ድንጋጌዎች፣ ስምምነቶችም ቢወጡም ችግሮች እየታዩ በመሆኑ ጊዜ ሊሰጠውም ስለማይገባ ቅርሶች በየቤተክህነቱ በተከታታይ ምዝገባ በማካሄድ ያለውን ቁጥር ማወቅና ቄሰ ገበዙም ሆነ የሰበካው ጉባኤ መረጃውን አጠናቅሮ መያዝ እንደሚገባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

ቅርስ ከተመዘገበ በፖሊሲም በፍርድ ቤትም ከታወቀ ውጭ አገር ቢሄድም በማስረጃ ማስመጣት ይቻላል፡፡ የላሊበላው ፣አፍሮ አይገባ፣ መስቀል በመመዝገቡ ተዘርፎ ከተወሰደበት አገር ማስመለስ መቻሉን በመድረኩ አጽንኦት ተሰጥቶበታል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ ባቀረቡት መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ቅርሶች በዓይነትና በብዛት የትየለሌ መሆናቸው፣ የአብያተ ክርስቲያን ሕንፃዎች፣ መካናተ መቃብር፣ ጥንታውያን ሥዕሎች የብራና መጻሕፍት፣ ያሬዳዊ ዜማና መንፈሳዊ በዓላት የመሳሰሉት ተጠቃሽ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ቅርሶች የማንነት መገለጫዎችና የታሪክ የመረጃ ምንጮች ከመሆናቸው ባሻገር ማኅበራዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ ጠቀሜታ አላቸው፡፡ ከታሪክ መረጃነት ሌላ አገራዊ ስሜትን ለመገንባት አንድ አገርና ሕዝብ ከሌላው የሚለይበትን ነገር የሚያሳዩ የማንነት መገለጫዎች በመሆናቸው በክብር ተጠብቀውና ተይዘው ወደትውልድ ለማስተላለፍ አፋጣኝ የመፍትሔ ሃሳብ ተብሎም የተጠቆሙት በሚመለከታቸው ተቋማት አማካይነት ግንዛቤን መፍጠር፣ ምዝገባና ቆጠራ ማካሄድ፣ ጠንካራ ሕጎችን በማውጣት ተግባራዊ ማድረግ፣ ተገቢ ካልሆነ የዕድሳት ሥራ መቆጠብ ናቸው፡፡

በውይይቱ መድረክ እንደተመለከተው ሕገ ወጥ ዝውውር የሚከናወንባቸው አንዳንድ የገጸ በረከት መሸጫ መደብሮች፣ በአንዳንድ ከተሞች ድብቅ ቤቶች ውስጥ የቅርስ ሽያጭ የሚፈፀምባቸውን ቦታዎች እንዲገቱ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡ በውይይቱ ላይ የተሳተፉ አንዲት ባለሙያ በሐረር ከተማ ውስጥ በድብቅ ቅርሶች የሚሸጡበትና ቱሪስቶች እየተመሩ የሚሄዱበት ቦታ መኖሩንም ጠቁመዋል፡፡

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ተወካይ ሕገወጥ ዝውውርን ለመግታት ተቋሙ ባደረገው ጥብቅ ቁጥጥር፣ በአየርና በየብስ መውጪያ ኬላዎች ላይ ሊሾልኩ የነበሩ 1925 ቅርሶች በመያዝ ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ማስረከቡን ተናግረዋል፡፡

በተያያዘ ዜና በአሜሪካ ኮሌጅ ቪል በሚገኘው የቅዱስ ዮሐንስ ዩኒቨርሲቲ በአደጋ ላይ ስላሉት የኢትዮጵያ ቅርሶች ንግግር እንደሚካሄድ የሒል ሙዚየም ኤንድ ማኑስክራፕት ላይብረሪ (ኤች.ኤም.ኤም.ኤል) አስታውቋል፡፡

የፊታችን ማክሰኞ መጋቢት 22 ቀን 2001 ዓ.ም. በሚኖሶታ በሚካሄደው መሰናዶ ንግግሩን የሚያደርጉት ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ሲሆኑ፣ ርእሳቸውም “ኢትዮጵያ ኢንዳንጀርድ ጋርደን ኦፍ ክርስቲያኒቲስ ኢርሊየስት ትራዲሽንስ” መሆኑ ከዩኒቨርሲቲው ድረ ገጽ ዘገባ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኢትዮጵያ ክርስትናን በይፋ ሃይማኖትነት በ4ኛው ምእት ዓመት በመቀበል ሁለተኛዋ አገር መሆኗንና ቅድመ ክርስትና የእምነተ አይሁድ ሥርዓት መኖሩን ያስታወሰው ዩኒቨርሲቲው፣ ያካበታቸውን ጥንታዊ የአይሁድና ክርስትና ሥርዓቶች፣ ልምዶችና ትውፊቶች በየትም አገር እንደማይገኙና ከነዚህም መካከል በእጅ የተጻፉ ቀዳሚ ሃይማኖታዊ የብራና መጻሕፍት እንዳሉበት አመልክቷል፡፡ ጥንታውያን የዕብራውያንና የክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍት በሌሎቹ ጠፍተው በብቸኝነት ተጠብቀው የሚገኙት በኢትዮጵያ ትውፊት ውስጥ እንደሆነ ያመለከተው ዘገባ፣ በአሁን ጊዜ ቁጥራቸው የማይታወቁ የኢትዮጵያ ብራናዎች እየተሰረቁ ወይም እየጠፉ መሆናቸው ለዚህም ድህነትና አካባቢያዊ አለመረጋጋት ምክንያቱ እንደሆነ አመልክቷል፡፡ የሒል ሙዚየምና ብራናዎች ቤተ መጻሕፍት ከ1960ዎቹ ጀምሮ ከኢትዮጵያውያን ምሁራንና ከቤተክህነት ሹማምንት ጋር በመተባበር የብራና መጻሕፍትን ጠብቆ ለማቆየት በማይክሮ ፊልም ባስነሳበት ጊዜ ከተሳተፉትና ካስተባበሩት ታዋቂ ምሁራን መካከል ፕሮፌሰር ጌታቸው አንዱ ነበሩ፡፡

የኢትዮጵያ ብራና መጻሕፍት ልዩ ልዩ ይዘት ወደተለያዩ ቋንቋዎች በመተርጎምና እሴታቸውን በማስተዋወቅ የሚታወቁት ፕሮፌሰሩ በሚያደርጉት ንግግር ኢትዮጵያ በዓለም ታሪክ ውስጥ ያላትን ልዩ ስፍራ የሚያጋሩበት እንደሆነ ተቋሙ አመልክቷል፡፡

Last Updated ( Sunday, 29 March 2009 )

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)