March 20, 2009

ከሃይማኖት አባቶች ጋር የተደረገው ተከታታይ የምክክር መድረክ ውጤታማ እንደነበር ተጠቆመ

ሰሞኑን በተከታታይ ከሃይማኖት አባቶች ጋር የተደረገው የምክክር መድረክ ውጤታማ እንደነበር የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታ ወቀ፡፡ በቀጣይም ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ይደረጋል፡፡ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ሰሞኑን ከተለያዩ የሃይማኖት አባቶች ጋር የተካሄደውን የምክክር መድረክ በተመለከተ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰ ጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፤ ከሃይ ማኖት አባቶች ጋር የተካሄደው ውይይት አበረታች ውጤት የታየበት እንደነበር አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ሁሉም የሃይማኖት አባ ቶች በተነሱት የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ አቋም ማሳየታቸውም የውይይቱን ውጤታማነት ያሳያል ብለ ዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የተካፈሉት የሃይማኖት አባቶች በተነሱት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ተመሳሳይ አቋም መያዛቸው ለወደፊት ለሚደረገው ቀጣይ መድ ረክ ትልቅ መነሳሳትን ፈጥሯል ያሉት ሚኒስትሩ፤ በውይይቱ ችግሮችን በመለየትና መፍትሔ በማፈላለጉ ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን አመልክተዋል፡፡
የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትን ወክለው በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የሃይማኖት አባቶች በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደውን የፅንፈኞች እንቅስቃሴ በመከላከል ረገድ የሃይማኖት አባቶች ከመንግሥት ጋር አብሮ ለመሥራት ያላቸውን ሙሉ ዕምነት ፈቃደኝነት ማሳየታቸውን ሚኒስትሩ ግልጽ አድርገዋል፡፡
ከሃይማኖት አባቶች ጋር በተደረገው ውይይት የተነሱትን ችግሮች በሙሉ ለመቅረፍ የመፍትሔ ርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ተቋማዊ የሆነ የሰላምና የመቻቻል ኮሚቴ በራሳቸው በተቋማቱ ውስጥ መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አመልክተዋል፡፡ ሚኒስትሩ አያይዘውም በግል የሚፈጠረውን ተቋማዊ አሠራር በመጠቀም የጋራ የሆነ ኮሚቴ ማዋቀር ይቻላል ብለዋል፡፡
የሃይማኖት ተቋማቱ የሚፈጥሩት የሰላምና የመቻቻል ኮሚቴ ኃላፊነት በዋነኛነት በተቋማቱ ውስጥ የተመረጡ ሥራዎችን የማቀድና የመፈጸም፣ የሕግ የበላይነት የማስከበር፣ ሃይማኖቱና አባቶቹ የማይፈቅዱትን ተግባር በግልና በቡድን ለማስፈጸም የሚደረግ እንቅስቃሴን የሚቃወም ብቁ ዜጋ የመፍጠርና መንግሥትና የሃይማኖት አባቶች በተስማሙባቸው ነጥቦች ዙሪያ መሥራትን እንደሚያካትት ዶክተር ሽፈራው አስታውቀዋል፡፡
መንግሥት ከሃይማኖት አባቶች ጋር ያደረገውን ውይይት ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ለመቀጠል ማሰቡንም ዶክተር ሽፈራው አስታውቀዋል፡፡
እስከአሁን ያሉ የተናጠል መድረክ ወደጋራ መድረኮች ይቀየራል ያሉት ሚኒስትሩ፤ በዚህ መድረክ የሚነሱና የጋራ መግባባት የሚደረስባቸው ጉዳዮችን በመያዝ ከወጣቶች፣ ከምሁራን፣ ከታዋቂ ግለሰቦችና ከሽማግሌዎት ጋር ምክክር እንደሚካሄድም ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡
ከአነዚህ የተለያዩ የኅብረሰተብ ክፍሎች ጋር የሚካሄደው የምክክር መድረክ ላይ የሚነሱና የጋራ መግባባት የሚደረስባቸውን ጉዳዮች በመያዝ በቀጣይም ሀገራዊ ኮንፈረንስ እንደሚዘጋጅ አስታውቀዋል፡፡
ሀገራዊ ኮንፈረንስ ከማካሄድ ጐን ለጐን የሃይማኖት አባቶች የጋራ መግባባት በተደረሰባቸው ነጥቦች ዙሪያ የሚጠበቅባቸው ሥራ መኖሩን ዶክተር ሽፈራው ጠቁመው፤ ከዚህ አንፃር የሃይማኖት አባቶች ተከታዮቻቸውን የማብቃት ሥራ ሊሠሩ፣ ከአቅም በላይ የሆነ ጉደዮች ሲያጋጥምም ከመንግሥት ጋር አብሮ የመሥራት ዝንባሌን ሊያሳዩ ይገባል ብለዋል፡፡
አሁን ባለንበት ሁኔታ በኢትዮጵያ በምንም ዓይነት መንገድ ለአክራሪነትም ይሁን ለፅንፈኝነት መነሻ ሊሆን የሚችል አንዳችም ነገር አለመኖሩን ሚኒስትሩ አመልክተዋል፡፡ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት በግልጽ ያስቀመጠውን ጉዳይ ባለመረዳት ፅንፈኞች የሚያካሂዱት አንቅስቃሴ ፈጽሞ የተሳሳተ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የዚህ አጀንዳ አራማጆች ከስህተታቸው ታርመው ሃይማኖች አባቶቻቸው ጋር ቀርበው ሊመካከሩና ለጥቃቄዎቻቸው መልስ ሊያገኙ እንደሚችሉም አስረድተዋል፡፡
በዚህ ከመንግሥት ተወካዮች ጋር ለአራት ቀናት በተካሄደው ተከታታይ የምክክር መድረክ የካቶሊክ፣ የፕሮቴስታንት፣ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት አባቶች ተካፍለዋል፡፡ ውይይቱም ግልጽነትና መግባባት የሰፈነበት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡


No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)