March 24, 2009

«ኃጢአት በንስሀ፣ እድፍ በውሃ»

ሩቢን አዘሃርዲን /ከሀላባ ቁሊቶ/
(ENA): ዕለቱ የበጋው ]ሐይ ገና ረፋዱ ላይ ግር ብላ የወጣችበት ነው፡፡ ብትወ ጣም ግን ብዙ መፋጀት አልጀመረችም፡፡ በዚህ የአየር ሁኔታ ውስጥ ነው እኔና ጓደኛዬ ሳምንት ሙሉ በሥራ የተጠመድንበትን አዕምሮአችንን ዘና ለማድረግ አላባ ደነቤ ፋማ ወደሚገኘው ሞቅ ያለ ካፌ ጎራ ያልነው፡፡ ካፌዋ በተለይ በዕረ ፍት ቀናት የሚያዘወትራት ስለሚበዛ መሟሟቋ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ አጠገባችን የነበሩ ሰዎች መጀመሪያ ተራ ወሬ የሚያወሩ መስሎን ነበር፡፡ እያደር ግን ክርክርም ንትርክም የሚመስል ነገር ማድመጥ ጀመርን፡፡ የተነሳው መከራከሪያ ጉዳይ አንድ ሁለት እያለ ደርቶ እኛንም ተሳታፊ ያደርገን ጀመር፡፡ ሆኖም ጉዳዩ በተለይ ከሃይማኖት መቻቻል ጋር የተያ ያዘ ስለነበር እኔና ጓደኛዬ የተወሰኑ ሃሳቦች ከሰነዘርንና መሆን የሚገባውን ከተናገርን በኋላ ከውይይቱ መውጣትን መረጥን፡፡ ከውይይቱም ከካፌውም ከወጣንና ወደየቤታችን ከተበታተንን በኋላ ግን የተነሳው ርዕሰ ጉዳይ እያደር ውስጤን ስለከነከነው በጉዳዩ ዙሪያ ለምን የበኩሌን አልልም አልኩኝ፡፡ «የወለዱትን ሲስሙለት» ነውና እነሆ ታነቡት ዘንድ ጀባ ልበላችሁ፡፡

ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ ሰላም በሀገራችን ልማትና ዴሞክራሲን እውን ለማ ድረግ በፍጹም አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሰላም ግን ስለ ተፈለገ ብቻ ሊረጋገጥ አይችልም ፡፡ ሰላም ሊረጋገጥ የሚችለው የግጭት ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን በማስ ወገድ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ሲታይ ሰላም ለዴሞክራሲና ለልማት ያስፈልጋል ብቻ ሳይሆን ለዴሞክራሲና ለልማት እውን መሆን ሰላም እጅግ መሠረታዊ ተፈላጊነት ያለው ምሰሶ ነው፡፡ አገራችን እንደ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ሁሉ በተደጋጋሚ ለውጭ ወራሪ ተጋልጣ በጦርነት ታምሳለች፡፡ ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያውያን ከሌሎች አፍሪ ካውያን ወንድሞቻቸው የሚለያቸው ነገር ቢኖር በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎችና ምክንያቶች ችግር ቢገጥማቸውም ነጻ ነታቸውን ጠብቀው ለመኖር መቻላ ቸው ነው፡፡ ዛሬም ቢሆን ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎች የአፍሪካ አገሮች የውጭ ጥቃት ሰነዘርባቸው እንደሚችል ይገመታል፡፡ ዋናው የሰላም ጠንቅ ግን ከውጭ የሚ መጣ ወራሪ ብቻ አይደለም፡፡ አፍሪካን ከዳርእዳር እያመሰ ያለው ጉዳይ በአንድ ሀገር ህዝብ መካከል የሚፈጠር የእርስ በእርስ ግጭት ነው፡፡ ከውጭ ጥቃት ሊሰነዘርብን የሚ ችለው የውስጣችን ጥንካሬ ሲዳከም ብቻ ነው፡፡በኢትዮጵያ ብሔርብሔረሰቦችና ሃይማኖቶች መካከል በመፈቃቀር ላይ የተመሠረተውን ጠንካራ አንድነት ለማ ፍረስ የውጭ ጠላትና ጥገኛው፣ ሃይማኖቶችን በመከፋፈልና በማጋጨት ማዳ ከም ወይም መበተን እንችላለን ብለው ያምናሉ፡፡

ይሁንና የእምነት ነፃነትና የሃይ ማኖት እኩልነትን ያረጋገጠው ህገ መንግሥታችን ከ]ደቀ ወዲህ በሃይማኖቶች መካከል ያለው መከባበር ተጠናክሯል፡፡ ጥንትም ቢሆን በአገራችን የተለያዩ ሃይማ ኖቶች ለብዙ መቶ ዓመታት አብረው ኖረዋል ወደፊትም ይኖራሉ፡፡ ኢትዮጵያ የክርስትናም ሆነ የእስልምና ሃይማኖትን አስቀድማ የተቀበለች ነች፡፡ በዚሁ መሠ ረት የእስልምናም ሆነ የክርስትና ዕምነ ቶች በእኩል ደረጃ ተከባብረው በፍቅርና በመቻቻል፣ በዋናነት በሰላምና እንደ እምነቱ ባህሪ አንዱ የአንዱን አክብሮ እየኖሩ ናቸው፡፡ ሆኖም የግል የፖለቲካ ፍላጎት ያላ ቸው ኃይሎች የሃይማኖቶች ግጭቶችን ለማነሳሳት ይሞክራሉ- የፖለቲካ ትግላቸ ውን ዓላማ በሽፋን ለማራመድ፡፡ የሀገራ ችን ሃይማኖቶች ተቻችለውና ከዚያም አልፎ ተከባብረው የሚኖሩበት ሁኔታ ሥር እየሰደደ ነው፡፡ ሀገራችን እስልምናና ክርስትና ለመጀመሪያ ጊዜ አብረው የኖ ሩባት ሀገር በመሆኑዋ ለረዥም ጊዜ አብረው ከመኖራቸው ጋር በተያያዘ በተለ ይም በተራው አማኝ አካባቢ ሥር የሰደደ የሃይማኖት መቻቻልና የመከባበር ባህል አለ፡፡ ይህ ባህል እየተጠናከረ ከመሄድ ይልቅ እየተሸረሸረ የሚሄድበት ሁኔታ እንዲፈጠር የጥፋት ኃይሎች የማይፈ ነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡

ይህ ክስተት መነሻው የግል ፍላጎትና በዋናነት በውጭ ተጽዕኖ የሚፈጠር ነው፡፡ አንዳንድ ትምክህተኞች የሁሉንም ሃይማኖት እኩልነት ለማረጋገጥ የሚወ ሰደውን እርምጃ የሌሎች ሃይማኖቶችን ተከታዮች መብትና ክብር የሚነካ አድ ርጎ በማቅረብ ለሌሎች ሃይማኖቶች ክብር ባለመስጠትና መቻቻልን በመቃወም አክራሪነት እንዲሰፍን ይሯሯጣሉ፡፡
በዚህ ዙሪያ ጥቅማቸው የተነካባቸው ያለፈው ሥርዓት ቅሪቶች በግንባር ቀደምትነት በመሰለፍ በአክራሪነት ዙሪያ የሕዝቡን ድጋፍ ለማግኘት ይሞክራሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንዶቹ የሃይማ ኖት እኩልነት መከበር ማለት የሌሎች ሃይማኖቶችን ማንቋሸሽና መበተን፣ ክብራ ቸውን መንካት፣ በመተሳሰብ ሳይሆን በእ ልህ የሃይማኖት እምነትን የመግለጽ ጉዳይ አድርገው በመውሰድ በአክራሪነት የሕዝቡን ድጋፍ ለማግኘት ሲጣጣሩ ይታ ያሉ፡፡

በዚህ መልኩ የሚከሰተውን አክ ራሪነት በዋናነት አማንያንና የሃይማኖት መሪዎች ተገቢውን የማስተካከያ ትም ህርት ሰጥተው ድርሻቸውን በመወጣት ረገድ መታገል ይኖርባቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ሃይማኖትን ሽፋን በማ ድረግ ግጭት የሚቀሰቅሱና ሁከትን የሚ ያነሳሱ ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖችን የሃ ይማኖት አባቶች፣ የየእምነቱ ተከታዮች እና ተቋማቱ ለሕግ አሳልፈው እንዲ ሰጡ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክ ተር ሽፈራው ተክለማርያም ሰሞኑን ጥሪ ያቀረቡት፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፕሮቴስታንትና ከካቶሊክ ዕምነት መሪዎች ጋር ሰሞኑን ሲወያይ ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴንና የአስተዳደሩ ፍትህና ሕግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ]ጋዬ ኃይለ ማርያም እንደተና ገሩት፤ ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ ድርጊቶችን መከ ላከል ከተቋማቱ ይጠበቃል፡፡
እምነትን ሰበብ በማድረግ የሚከ ሰቱትን ድርጊቶች ለመከላከልም የሁሉም የእምነት ተከታዮች ችግሩን ለመመከት የጋራ ግንዛቤ ይዘው ሊንቀሳቀሱ እንደ ሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

ይህ ብቻ አይደለም በኢትዮጵያ ውያን መካከል ለዘመናት ጸንቶ የቆየው ነባር የመቻቻልና የመከባበር ባህል እንዲ ጎድፍ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች እኩይ ዓላማ በኅብረተሰቡ የተቀናጀ ጥረት መና መቅረቱን ከአዲስ አበባ ከተማ የእስልምና እምነት ተከታዮች የተውጣጡ የሃይማ ኖት አባቶችና የአዲስ አበባ ከተማ አስተ ዳደር በተወያዩበት ወቅት ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ እምነት ተከታዮች መካከል ለዘመናት የነበረውን መቻቻል ለማደፍረስ የሚያሴሩ ኃይሎችን በጋራ መከላከል በሚቻልበት ጉዳይ ላይም መክረዋል፡፡

በውይይቱ የተሳተፉ አንዳንድ የሃ ይማኖት አባቶች ለዘመናት የኖረው አብሮ የመኖር ባህላችን ጠንካራና የማይናድ በመሆኑ በሃይማኖት ሽፋን ብጥብጥና ሁከት ለማነሳሳት የሚሞክሩ ኃይሎች ያሰቡትን የጥፋት ተልዕኮ ማክሸፍ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
የሃይማኖት አባቶቹ እንዳሉት እስልምና የመቻቻልና የመደጋገፍ አስተምህሮት እንጂ ግጭትንና ትርምስን አይፈቅድም፡፡
እንዲያም ሆኖ በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን ስም ችግር ለመፍጠር የሚ ንቀሳቀሱ ኃይሎችን ተከታትለው በማጋለጥ መንግሥት አስፈላጊውን የሕግ ማስከበር እርምጃ እንዲወስድ ድጋፍ እንደ ሚያደርጉም አረጋግጠዋል፡፡ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ከአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳሙኤል ጋር በተወያዩበት ወቅት ደግሞ እንዳስታወቁት፤ ሃይማኖት የሰላምና የልማት ማራመጃ ሲሆን ከዚህ ውጪ የሚንቀ ሳቀሱ ኃይሎችን ሁሉም ኅብረተሰብ ሊከላከላቸው ይገባል፡፡
በሕገ መንግሥቱ የ]ደቀውን የሁ ሉም ሃይማኖቶች እኩልነት የማስጠበቅ ኃላፊነት የመንግሥት በመሆኑ ከእምነት ውጪ ሌሎች ዓላማዎችን ለማራመድ የሚጥሩ ኃይሎችን በትዕግስት አይመ ለከታቸውም፡፡

በመሆኑም ኅብረተሰቡና የሃይማኖት ተቋማት ለዘመናት የቆየው አብሮ የመ ኖር፣ የመከባበርና የመቻቻል ባህል
ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተባብረው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል ከንቲባ ኩማ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ ሳሙኤል በበኩላቸው እንዳሉት፤ ሕገ መንግሥቱ ለሁሉም ሃይ ማኖት የሰጠውን እኩልነት በመጠቀም የሌላውን መብት ሳይነኩ እምነትን ማራ መድ ይገባል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም የዕምነት ግጭቶችን መንግሥት ለመቆ ጣጠር የተለያዩ እርምጃዎችን መጀ መሩን ሰሞኑን ለ¬ርላማው ገልጸዋል፡፡ «አንዱ እርምጃ ግንዛቤ ማስረፅ ነው፡፡ ይህ ሥራ ተጠናክሮ የተወሰነ ርቀት ከሄደ በኋላ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት ግን መንግሥት አስፈላጊውን እር ምጃ ይወስዳል፡፡ ሥራው በፖሊስ ብቻ የሚከናወን ባለመሆኑ ኅብረተሰቡ እነ ዚህን ኃይሎች አንቅሮ ሊተፋቸው፣ የሃይ ማኖት መሪዎችም ሊያስታግሷቸው ሲን ቀሳቀሱ ነው ውጤት የሚገኘው» ብለዋል፡፡

ከዚህ በላይ ያሉት ንግግሮች እንዲሁ የተደረጉ አይደሉም፡፡ መጀመሪያ ሕዝቡን ስለሁኔታው ማስረዳት፣ በሕዝቡ አማካይነት እነዚህን ኃይሎች መከላከል፣ ይህ ሁሉ ሆኖ እነዚህ ኃይሎች ማረፍ ካልቻሉ ሕግና ሥርዓትን ማስከበር አስፈላጊ መሆኑን የሚያሰምር ነው፡፡ የሕዝቡን ግንዛቤ የማዳበሩ ጉዳይ ደግሞ በየደ ረጃው ተጀምሯል፡፡ ተጠናክሮም ይቀጥላል፡፡
እዚህ ላይ በመደጋገም ሊሰ መርበት የሚገባው የሃይማኖት እኩልነት በጥብቅ ተግባራዊ መሆን መጀመሩ ሁሉም
ሕዝ ቦች በሰላምና በመፈቃቀር እንዲጠቀሙ የማድረግ እንጂ የማንንም እምነት ክብር የመቀነስ እንዳልሆነ በሁሉም ሃይማኖቶች ተከታዮች ዘንድ የመታወቁ ጉዳይ ነው፡፡

የተለያዩ አስተሳሰብ የሚያራምዱ ወገኖች ከጥቅማቸው በመነሳት ሃይማ ኖትን የጥገኛ ጥቅማቸው መሸፈኛ ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች እንደ ሆኑ ሕዝቡ ተገንዝቦ ሊታገላቸውም ይገባል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በሃይማኖት እኩልነት ረገድ የሚኖሩ ጉድለቶችን ለማስተካከል የሚደረገው ተገቢ ጥረት በእልህ ሳይሆን በመተሳሰብ በጥላቻ ሳይሆን በመቻቻልና በመከባበር ላይ የተመሠረተ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከዚህ አኳያ እልህና ጥላቻ ለማስፋፋት የሚሞክሩ አክራሪዎችን አጀንዳቸው የእምነት ነጻነት የሃይማኖት እኩልነት ማረጋገጥ ሳይሆን በዚሁ ሽፋን ጥገኛ ጥቅማቸውን ለማሳደድ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለዘመናት ያቆ ዩትን ተቻችሎና ተከባብሮ የመኖር አኩሪ ባህላቸውን በጽኑና ዘላቂ መሠረት ለማስቀጠል በጋራ ትግላቸው በተጎናጸፉት ድል ተጠቅመው ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና እንዲያገኙ ማድረግ ችለዋል፡፡ ሕገ መንግሥቱ ባረጋገጠላቸው የሃይማኖት እኩልነትና ነጻነት ተጠቅመው የሁሉም ሃይማኖቶች ተከታዮች ልማታቸውን በማ ፋጠን የሀገራችንን ገጽታ በተሻለ ደረጃ ለመለወጥ ባደረጉት ጥረት ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን በማስመዝገብ ላይ ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተጠናክረውና ዳብረው እንዲቀጥሉ በሃይማኖቶች መካከል የቆየውና የኖረው የመቻቻል ባህል እንዲጠናከር ከምን ጊዜውም በላይ አማኒያንና የሃይማኖት መሪዎች በብቃት መታገልና መመከት አለባቸው፡፡ ከዚህ የዘለለ ነገር ሲያጋጥም ደግሞ መንግሥት ሕግ የማስከበር ኃላ ፊነቱን መወጣት ይጠበቅበታል፡፡ ኃጢ አት በንስሀ፣ እድፍ በውሃ እንዲሉ የጥፋት ኃይሎች፣ በሃይማኖት ሽፋን ትርምስ ለመፍጠር የምትንቀሳቀሱ ኃይሎች ከዚህ ተቻችሎ ከኖረ ሕዝብ እንዲሁም ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት ለማራመድ በፅናት ከቆመ መንግሥት ጋር ከመጣላታችሁ በፊት ከድርጊታችሁ ሰብሰብ በሉ፣ ንስሃ ግቡ፣ በሰላምም ተንቀሳቀሱ ምክሬ ነው፡፡ ሰላም::


No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)