Monday, 23 March 2009
አዲስ አበባ፤መጋቢት14/2001/ዋኢማ/ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ግጭት እንዲፈጠር የሚያደርጉ ግለሰቦችን በማጋለጥ ከመንግስት ጎን ሆነው እንደሚሰሩ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የተለያዩ የዕምነት አባቶች አስታወቁ።
በክፍለ ከተማው የሚገኙ የተለያዩ የዕምነት ተቋማት አባቶች ትናንት በክፍለ ከተማው ቀበሌ 01/05 የመሰብሰቢያ አዳራሽ ባካሄዱት ውይይት ላይ እንዳስታወቁት፤ ሐይማኖትን ሽፋን በማደረግ ዕኩይ ዓላማቸውን ለማሳካት የሚጥሩ ግለሰቦችን ነቅሶ ለማውጣት ይሰራሉ።
የአገር ቅርስ በሆኑ የሀይማኖት ተቋማት ላይ ጥፋት በሚያደርሱ ወንጀለኞች ላይ የሚጣልባቸው ቅጣት ቀላል መሆኑ ቀርቶ ሌሎችን በሚያስተምር መልኩ ሊሆን እንደሚገባውም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የተለያዩ የዕምነት ተከታዮች ለዘመናት ተቻችለውና ተከባብረው የኖሩባትና የሚኖሩባት አገር መሆኗን ጠቁመው፤ በአሁኑ ወቅትም ህገ-መንግስቱ የዕምነት ዕኩልነትንና ነጻነትን በማረጋገጡ የተለያዩ የዕምነት ተከታዮች እምነታቸውን በነጻነት እያራመዱ ናቸው ብለዋል።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት፤ በአገሪቱ ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ሀይሎችን በጋራ በመመከት ለዘመናት የዘለቀውን ተቻችሎ የመኖር እሴት መጠበቅ ይገባል።
መንግስት የዕምነት ግጭት መንስኤ የሚሆኑ ድርጊቶችን በመለየት ከሀይማኖት ተቋማት ውጭ የሚካሄዱ አላስፈላጊ ቅስቀሳዎችን ለመቆጣጠር በሚያደርገው ጥረት ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመሆን አጥፊዎችን መንጥሮ ማውጣት እንደሚኖርበት አቶ ሺሰማ አሳስበዋል።
በውይይቱ ላይ ከተለያዩ የዕምነት ተቋማት የተወከሉ የሀይማኖት አባቶች፣ የተለያዩ ዕምነት ተከታዮችና የክፍለ ከተማው አስተዳደር ካቢኒዎች ተሳታፊ መሆናቸውን የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ማስታወቂያ ፅህፈት ቤት የላከውን ዘገባ ጠቅሶ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል።
March 24, 2009
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Blog Archive
-
▼
2009
(275)
-
▼
March
(20)
- The monastic community of Ethiopia
- የመንግሥት ኃላፊዎችና ሠራተኞች የሃይማኖት ግጭትን በማባባስ ረገድ ሚና ነበራቸው...
- ልብስ እና ምላስ
- Paltalk Jihad on Ethiopia
- «ኃጢአት በንስሀ፣ እድፍ በውሃ»
- በሃይማኖት ሽፋን ግጭት የሚያነሳሱ ግለሰቦችን ለማጋለጥ እንደሚንቀሳቀሱ የዕምነት...
- Gospel singer creating waves
- Who is Intolerant?
- Ethiopia, an Astonishing Christianity on African S...
- Ethiopian Muslims Demonstrate in DC
- ከሃይማኖት አባቶች ጋር የተደረገው ተከታታይ የምክክር መድረክ ውጤታማ እንደነበር...
- መንግስት ሁከት ለመፍጠር የሚንቀሰቀሱ ግለሰቦችን ለመከላከል ከዕምነት ተቋማት ጋ...
- በሃይማኖት ሽፋን አፍራሽ አጀንዳዎችን ይዘው ወደ አደባባይ የሚወጡ ፀረ ሠላም ሃ...
- በመርካቶ አካባቢ ፓለቲካና ሃይማኖት ቀመስ ግጭት ተፈጠረ
- «በአገሪቱ ለዘመናት ተጠብቆ የቆየውን ተቻችሎ የመኖር ባህልን ለማጠናከር እንሠራ...
- Islam and Terrorism
- Negash Mulugeta has this to Say
- The Religion of the Moon "God"
- Ethiopian Muslim Arrested For Sending HIV-Infecte...
- Blogs Accessible in Ethiopia Now
-
▼
March
(20)
1 comment:
dr wedagenehe he is theSERVANTE of GOD HE KNOWS GOD those who spokes evil words agaiste him you need the mercy of GOD please live hime to GOD BECOSE only GOD knows INDETAILE THANKYOU FROM USA
Post a Comment