March 17, 2009

«በአገሪቱ ለዘመናት ተጠብቆ የቆየውን ተቻችሎ የመኖር ባህልን ለማጠናከር እንሠራለን»

(ቀን፡ 2009/03/14)
በአገሪቱ በተለያዩ የዕምነት ተከታዮች መካከል ለዘመናት ተጠብቆ የቆየው ተቻችሎ የመኖር ባህል የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዚዳንት አስገነዘቡ፡፡
የፕሮቴስታንት የሃይማኖት አባቶች ከመንግሥት ጋር ባካሄዱት የምክክር መድረክ ላይ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳ ንት ቄስ ዶክተር ዋቅስዩም ኢዶሳ ባደረ ጉት ንግግር በኢትዮጵያ በሃይማኖት መካከል የቆየው ተቻችሎ የመኖር ባህል ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንሠራለን ብለ ዋል፡፡ ይህም የቤተክርስቲያኗ አቋም ሆኖ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በሀገሪቷ የሚገኙ ሃይማኖቶች መከ ባበርንና ሰላምን አብሮ ከመኖር ጋር በማ ጣመር ለጋራ ዕድገትና ለሀገር ብልፅግና የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ከግምት ውስጥ ማስገባት ይገባል ያሉት ፕሬዚዳ ንቱ ቤተክርስቲያኗ በዚህ ረገድ ኃላፊነት ዋን እንደምትወጣ አስታውቀዋል፡፡
የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ ከተቀረው ሕዝብ ጋር በጋራ የመኖርን፣ የመተባበርንና የመቻቻል ባሕልን ሊያጠናክር ይገባል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ከዚህ ውጪ የሚመጣ ጉዳይን የሚያስተናግድ ካለ ሃይማኖት ነው ለማለት አያስደፍርም ብለዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶች ተቻችሎ የመ ኖርን ባሕል ለተከታዮቻቸው አጠናክረው እንዲያስተምሩና ለተከታዮቻቸውም ጥሩ ምሳሌ መሆን እንዳለባቸው ቄስ ዋቅስዩም አስገንዝበዋል፡፡ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክር ስቲያን ዋና ፀሐፊ አቶ አገኘሁ ወንድም በበኩላቸው፣ በሀገሪቱ የሃይማኖት እኩ ልነት እስከተረጋገጠ ድረስ አንዱ ከአንዱ የሚበልጥበትም ሆነ የሚያንስበት ሁኔታ እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ በሃይማኖት ዙሪያ የሚነሱ ችግሮ ችን በመንፈሳዊ መልኩ መፍታት አለብን ያሉት አቶ አገኘሁ አልፎ አልፎ ጉዳዩ ከቁጥጥር በላይ ሲሆን፤ የመንግሥት አካላት ተገቢውን ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡

በሃይማኖት ሽፋን ሌላ ጉዳይን የሚያራምዱ አካላትን መከላከልና መቋቋም የሚቻለው የተለያዩ የውይይት መድረኮችን በመፍጠር ስለሆነ በቀጣይም የዚህ ዓይነቱ መድረክ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዋ ደኀንነት አማካሪ ሚኒስትር አቶ ዓባይ ፀሐዬ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት መንግሥት በአገሪቷ የሚገኙ ሁሉንም ሃይማኖቶች በእኩልነት የማስተናገድ ግዴታ አለበት፡፡ አያይዘውም መንግሥት ከአስተዳደራዊ አገልግሎቶች ረገድ ሁሉንም ሃይማኖቶች በአንድ ዓይን የመመልከት ኃላፊነቱን ይወጣል ብለዋል፡፡

መንግሥት በሀገሪቱ የሚወጡ ሕጐችና መመሪያዎች የማስከበር ኃላፊነት እንዳለበት ጠቁመው፤ የእምነት ነፃነት
እንዲኖር እንዲሁመ የመቻቻል ባህሉ እንዲጠናከር ሁሉመ ሃይማኖቶች ኃላፊነት እንዳላባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ሁሉንም
ሃይማኖቶች በሕግም ይሁን በፖሊሲ እኩል ተጠቃሚ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት መንግሥት ይረዳል ያሉት ሚኒስትሩ ከየትኛውም የሃይማኖት አቅጣጫ የሚመጣ ከሕግ ውጪ የተፈጸመ ተግባርን በእኩል ዓይን የማስተናገድና የመዳኘት ኃላፊነት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት በቅድሚያ ራሳቸውን ከሕግ አንፃር ሊቆጣጠሩ እንደሚገባ የገለጹት አቶ ዓባይ መንግሥት ለየትኛውም የሃይማኖት ተቋም ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥም ብቻ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም በበኩላቸው ባደረጉት ገለጻ እንዳስታውቁት፤ በየሃይማኖቱ ያሉትን አሠራሮች ዴሞክራሲያዊና ዘመናዊ ማድረግ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡
የዕምነት ነፃነትና መቻቻል የሚለውን ጉዳይ አጠናክሮ የመቀጠሉ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ የየእምነት ተቋማቱ በተከታዮቻቸው ዘንድ ተጠያቂነት ያለው አሠራር እንዲከተሉ ምዕመናኑም ይህንን ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

መንግሥት ከሃይማኖት አባቶች ጋር ለመወያየት ባዘጋጀው መድረክ በእስካሁነ ሂደቱ ከካቶሊክ፣ ከእስልምናና ከፕሮቴስታንት የሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በነገው ዕለትም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች ጋር እንደሚወያይ ይጠበቃል፡፡

ሪፖርተር፡ አርአያ ጌታቸው
ቀን፡ 2009/03/14

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)