February 5, 2009

"ተደራጅተውም ይሁን በተናጠል የአገርን ሰላም ለመበጥበጥ ለሚነሱ ይቅርታ አይኖርም"


"ተደራጅተውም ይሁን በተናጠል የአገርን ሰላም ለመበጥበጥ ለሚነሱ ይቅርታ አይኖርም"
ኮማንደር ደምሳሽ ኃይሉ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ መታየት የጀመረውን የኃይማኖት ልዩነትና ግጭት የማንሳት ሙከራ ፖሊስ በተለያየ መልኩ እየገለፀው ይገኛል፡፡

ፖሊስ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ካስተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ በጉዳዩ ዙሪያ ምን እየሰራ እንደሆነ የፌዴራል ፖሊስ የሕዝብ ጉዳዮች ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ደምሳሽ ኃይሉን አሰግድ ተፈራ አነጋግሯቸዋል፡፡

Bravo commander!!!
Now you are awake. Thank God for that. But the Ethiopian people still needs an honest assessment of the situation in Ethiopia and an urgent action to stop the fanatics from creating further damage. Whatever political stand we have, Ethiopians should stand by EPRDF's side when you are really safeguarding the safety of Ethiopia and Ethiopians. But you may still need to know the danger of the fanatics. If EPRDF's government is to crumble, the danger basically comes from these fanatics who decided and proclaimed openly in their radio shows to control government power. Do you have that information, commander?ሪፖርተር፡- በአክራሪነት የተፈረጁ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ተገልጿል፤

ኮማንደር ደምሳሽ፡- የመፈረጅ ሥራ አልሰራንም፡፡

ሪፖርተር፡- በኃይማኖት መካከል ልዩነት ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በቁጥጥር ሥር ውለዋል?

ኮማንደር ደምሳሽ፡- የተፈረጁ ሳይሆኑ ተጠርጥረው የተያዙና በምርመራ ላይ ያሉ አሉ፡፡ በምርመራ ላይ ያለ ጉዳይ ሳይጠናቀቅና ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶ የጥፋተኛነት ውሳኔ ሳይሰጥ አይፈረጅም፡፡ በዚህም ላይ የኃይማኖት ጉዳይ የእምነት ጉዳይ በመሆኑ ጥንቃቄ ያሻዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ምን ያህል ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል?

ኮማንደር ደምሳሽ፡- ቁጥራቸውን መግለፁ ብዙም አስፈላጊ አይሆንም፡፡ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ አሉ፡፡

ሪፖርተር፡- ከጥርጣሬ የዘለለ መረጃ የላችሁም?

ኮማንደር ደምሳሽ፡- ለመግለፅ የፈለግኩት ሕጋዊ አግባቡን ብቻ ነው፡፡ ፖሊስ በኃይማኖት ዙሪያ ልዩነት በመፍጠር ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ላይ ሁለም ዓይነት መረጃ አለው፡፡ አንዳንዴም ሊደረጉ የታሰቡ ጉዳዮችን አስቀድሞ በማወቅ በእንጭጩ ያከሽፋቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- መረጃ ካላችሁ አሁን በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለው የኃይማኖት ልዩነት የመፍጠር አዝማሚያ ደረጃው የት ነው?

ኮማንደር ደምሳሽ፡- በአየር ላይ ነው ያለው፡፡ ልዩነት ለመፍጠር በተፈለገው መጠን ወደ ታች ወርዶ ሕብረተሰቡ ውስጥ አልዘለቀም፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ በሕዝቡ ተባባሪ አልሆንም ባይነት ነው፡፡ ፖሊስ ችግሩ ወደ ህብረተሰቡ ሳይወርድ እንዲጠፋ የበኩሉን ሁሉ እያደረገ ነው፡፡ ሕብረተሰቡ የሚሰጠው ድጋፍ ከፍተኛ በመሆኑ ተሳክቶልናል፡፡ የኃይማኖት ግጭት ከተጀመረ አደገኛ መሆኑን ማንም ያውቀዋል፡፡

ሪፖርተር፡- በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል በትክክል አክራሪ መሆናቸውን አውቀው የገቡበት አሉ? በምርመራ የተገኘ ምሳሌ ጠቅሰው ቢያስረዱኝ፤

ኮማንደር ደምሳሽ፡- የተለያዩ ዓይነት ተጠርጣሪዎች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ባከረሩ ቁጥር በእምነታቸውና በእምነታቸው ስር ከሚያመልኩት አምላክ ይበልጥ የሚወደዱና የተለየ ስፍራ የሚሰጣቸው የሚመስላቸው አሉ፡፡ እንደነዚህ ዓይነቶቹ እውነቱ ሲነገራቸው "እንደዚህ ነው እንዴ?" ይላሉ፡፡ ከተለያዩ ወገኖች የቤት ሥራ ተቀብለው ተግባር ላይ ለማዋል ኃይማኖቶችን መጠቀም ዋንኛ የትግል መሳሪያቸው ያደረጉም አሉ፡፡ እነዚህ ኃይሎች በኃይማኖት ስም ይገፋሉ፡፡ በስብከት ስም ይቀሰቅሳሉ፡፡ ተከታዮችን በማብዛት ኃይማኖትን ከፊት አድርገው ስውር አጀንዳ ያራምዳሉ፡፡ የፖለቲካ ሥራ ይሰራሉ፡፡ ራሳቸውን በገንዘብ ያደራጃሉ፡፡

ሪፖርተር፡- አክራሪ የሚባሉት ወገኖች ልዩ የገንዘብ ምንጫቸውን ጠቅሰው ሊነግሩኝ ይችላሉ?

ኮማንደር ደምሳሽ፡- የሚታወቅ ነገር እንደሌለ አስቀድሜ ገልጫለሁ፡፡ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጪ አገር ሊሆን ይችላል፡፡

ሪፖርተር፡- ከውጪ አገር እነማን?

ኮማንደር ደምሳሽ፡- ፖሊስ በምርመራ ላይ ባለበት በአሁኑ ሰዓት በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ጉዳይ መናገር በምርመራ ሥራው ላይ ጫና ያሳድራል፡፡

ሪፖርተር፡- ከተጠርጣሪዎች መካከል የፖለቲካ ሹመኞች ይገኙበታል? በተለይም ከፍተኛ ባለሥልጣናት?

ኮማንደር ደምሳሽ፡- ፖሊስ ህገ መንግሥቱን የመጠበቅ አደራ ያለበት በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ትልቅ ትንሽ፣ ባለስልጣን ተራ ዜጋ . . . የሚል መለያየት የለም፡፡ ወደፊት ጉዳዩ ለህግ ሲቀርብ ዝርዝሩ ይታወቃል፡፡ አሁን ሁሉንም ጉዳይ የሚያውቁት ምርመራውን የያዙት አካላት ብቻ ናቸው፡፡

ሪፖርተር፡- ተጠርጣሪዎቹ ክስ መቼ ይመሰረትባቸዋል?

ኮማንደር ደምሳሽ፡- በቅርቡ ክስ ይመሰረትባቸዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ የምርመራ ሥራው . . .

ሪፖርተር፡- ከታሰሩ ቀናትን ያስቆጠሩ አሉ፤ ከመብት አንፃር ጉዳያቸው እንዴት ነው የሚታየው?
ኮማንደር ደምሳሽ፡- ከመብት አንፃር አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር በዋለ በምን ያህል ጊዜ ክስ እንደሚመሰረትበት የተቀመጠ ገደብ አለ፡፡ ከዚህ አንፃር መሰራት እንዳለበት እናምናለን፡፡ እየተሰራም ነው፡፡ ምርመራው ተጠናቆ፣ ክስ ተመስርቶ ውሳኔ ቢሰጥና ሌላው የሕብረተሰብ ክፍል ቢማርበት እንመርጣለን፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ የተከተሉት መንገድ ሁሉ የስህተት እንደሆነ አምነው ወደ ህብረተሰቡ ተመልሰው ምሳሌ እንዲሆኑ ይፈለጋል፡፡

ሪፖርተር፡- ቀደም ባሉት ጊዜያት በተለያዩ የአገሪቱ ግዛቶች ጥፋት ደርሷል፡፡ እርስዎ ፖሊስ ሁለም ዓይነት መረጃ አለው ይላሉ፡፡ እንዴት ይታረቃል?

ኮማንደር ደምሳሽ፡- በተለያዩ ክልሎችና አስተዳደሮች በኃይማኖት ሽፋን ተደራጅተው ጥፋት የፈፀሙ አሉ፡፡ በፍርድ ቤት የተያዙ ጉዳዮች በመሆናቸው ዝርዝር ውስጥ መግባት አይቻልም፡፡ ፖሊስ አስቀድሞ ጥፋቱን ያላከሸፈው ከመረጃ እጥረት ብቻ ነው ሊባል አይችልም፡፡ ታላላቅ የሚባሉትን አገሮች ጨምሮ በዓለም የተለያዩ ክፍሎች እንደሚታየው አሰቃቂ ድንገተኛ አደጋ ይከሰታል፡፡ እኛም አገር ተመሳሳይ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ዋናው ነገር አደጋው በተፈለገው መጠን ሳይሰፋና ሰብአዊና ቁሳዊ ጥፋቱ ሳይበዛ መቆጣጠር መቻሉ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የተሳካ ሥራ የተሰራ ይመስለኛል፡፡ በቀጣይ ትኩረት ያደረግነው ቅድመ መከላከል ሥራ ላይ በመሆኑ አልቀጠለም፡፡

ሪፖርተር፡- የኃይማኖት ፅንፈኞች የሚባሉት የቅስቀሳ መንገዶቻቸው ተለይተዋል? እነዚህ መንገዶችን ለመዘጋትስ ምን ተሰራ?

ኮማንደር ደምሳሽ፡- ካሴት፣ ሲዲ፣ የሕትመት ውጤቶች፣ ኢንተርኔት፣ ኤስ.ኤም.ኤስ፤ እና ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥንና ሌሎች መንገዶችን ይጠቀማሉ፡፡ የመናገርና የመፃፍ ነፃነት ባለበት አገር እንዴት ለይተን እገዳ እንጥላለን? በሚል ዝም ብለናቸው ቆይተናል፡፡ ቢሆንም ግን የሕትመት ውጤቶቹ የሚራቡበት ጉራንጉር ሳይቀር ለፖሊስ የተሰወረ አልነበርም፡፡ የሚያሰራጩትንም ሆነ የሚበትኑት ኃይሎች ምስጢር አልነበሩም፡፡ ከጊዜ ወደጊዜ ይጣራሉ በሚል ትምህርት የተሰጣቸውም ነበሩ፡፡ በሌላ በኩል መዘንጋት የሌለበት ዓለም ጠባለች፡፡ መረጃ ቤት ድረስ ይመጣል፡፡ ቅስቀሳ ጓሮ ድረስ ይደርሳል፡፡ በዓለም አቀፍ ሳተላይቶች የሚተላለፉ መረጃዎች የሚጫወቱት ሚና ቀላል አይደለም፡፡ በሁሉም ዙሪያ ከኃይማኖት አባቶች ጋር መክረናል፡፡

ሪፖርተር፡- በየኃይማኖቱ የተፈጠሩት አክራሪዎች የራሳቸው የሕዝብ ግንኙነት አላቸው ይባላል፤ እንቅስቃሴያቸው እንዴት ነው?

ኮማንደር ደምሳሽ፡- በኃይማኖት ስም አባላትን እንዲያምኑ ማድረግ ዋና አጀንዳቸው ነው፡፡ እንዲያምኑ ከተደረገ በኋላ ለእምነታቸው የበለጠ የቀኑ መስሏቸው የወንጀል ተግባር እንዲፈፅሙ ማድረግ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በኤስ.ኤም.ኤስ መልዕክት መረጃ በመቀያየር ለጥፋት ሲቀሰቅሱ የነበሩ እንዳሉ ታውቋል፡፡ የመልዕክቱ ይዘትና የሕዝቡን ምላሽ ቢገልፁልኝ፤

ኮማንደር ደምሳሽ፡- በሁሉም ኃይማኖቶች ስም ፅንፈኛ ሆኖ የመውጣትና የመደራጀት ነገር የተለመደ ነው፡፡ በአንድ ኃይማኖትና በኃይማኖቱ የእምነት ስርዓት ስር ሆነው በየጊዜው የሚለያዩ፣ በመለያየት የራሳቸውን ቁጥር ለማብዛት በተለያየ መንገድ የሚሰሩ አባላት የሚመለምሉ አሉ፡፡ እነዚህ አካላት በየኃይማኖት የበዓላት ቀንና የእምነት ስርዓት ማካሄጃ ሰዓታት ላይ ከአለባበስ ጀምሮ እንዲህ ዓይነት ልብስ ልበሱ፣ ይህንን ያዙ የሚል መልዕክት ተላልፎ ነበር፡፡ ብዙም አስፈላጊ ስላልሆነ ዝርዝር ውስጥ መግባት ባያስፈልግም አንዳንዶቹ መልዕክቶች ጭር ሲል ቅር የሚላቸው አካላት ከየጫት ቤቱም የሚያሰራጩት ነበር፡፡ በኃይማኖት ብቻ ሳይሆን በሌላውም መንገድ የተወሰነ ነገር ሽው ያለ ሲመስላቸው ቶሎ ቶሎ የማራገብና የማጋጋል ሥራ የሚሰሩ አሉ፡፡ ህብረተሰቡ የፖሊስ ዋንኛ አጋር በመሆኑና ሰላሙን ስለሚፈልግ እንዲፈጠር የተፈለገው ነገር በጅምሩ ይቀጫል፡፡ ለዚህም ነው በአክራሪነት የሚደረገው እንቅስቃሴ ሁሉ ህብረተሰቡ ውስጥ የማይገባው፡፡ ይህም ቢሆን ፖሊስ የህዝብን ሰላም የማስጠበቅ ኃላፊነት ስላለበት፣ ህገ መንግሥታዊ አደራ ስለተቀበለ በሕገ መንግሥቱ ከተቀመጠው ውጪ የሚንቀሳቀሱ ኃይሌችን በዝምታ እንደሚያልፍ ያልገለፀበት አጋጣሚ የለም፡፡

ሪፖርተር፡- የትኛው ኃይማኖት ተከታዮች ናቸው በአብዛኛው ችግር እየፈጠሩ ያሉት?

ኮማንደር ደምሳሽ፡- ይህ አደገኛ አካሄድ ነው፡፡ የመገናኛ ዘዴዎችም ሆኑ ሁሉም ዜጐች ጥንቃቄ ሊወስዱበት የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ የእምነት ነፃነት በተከበረበት አገር ሁሉም እምነቱን ማራመድ ያለበት የሌላውን ሳያንቋሽሽ፣ ዝቅ ሳያደርግ፣ ወይም ማነፃፀሪያ ሳያደርግ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ካለፈና የራስን ከፍ፣ የሌላውን ዝቅ የማድረግ ነገር ካለ ህግን ተላልፋችኋል ተው እንላለን፡፡ ለበላይ ኃላፊዎቻቸው እንነግራለን፡፡ አባባል እያነሱ ሌላውን መቆስቆስ ተገቢ አይደለም፡፡ የሁሉም የሆነችን አገር የአንድ አድርጐ ማሳየትም አግባብ አይሆንም፡፡ አስፈላጊ ወዳልሆነ ነገር ሊያመራ ይችላል፡፡ ሁሉም ሲያስተምር መጠንቀቅ አለበት፡፡ መቻቻልን ባህሉ አድርጐ የኖረን ህዝብ እሴት ለማጥፋት ማሰብ ስህተት ነው፡፡ ለዚህ ነው ጥንቃቄ ያስፈልጋል የምንለው፡፡ የተሳሰርንበትን ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱ ካስቀመጠው ጉዳይ ወጥተን መራመድ ስንጀምር ችግር ይፈጠራል፡፡ የሰዎችን ትኩረት የሚስቡ ነገሮችን ከማድረግ ሁለም ወገኖች ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ በተለይ የመገናኛ ብዙሃን ሊወስዱ የሚገባቸው ጥንቃቄ ከፍተኛ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ይመስላል፤

ኮማንደር ደምሳሽ፡- ማስጠንቀቂያ ሊሆን ይችላል፡፡ ፖሊስ የአንድን እንቅስቃሴ መነሻና መድረሻ ሲያውቅ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፡፡ ፖሊስ ባለበት ሕገ መንግሥታዊ አደራ ቀላል አድርጐ የማያየው፣ አክብዶ የሚያየውና በምንም መልኩ ትዕግሥትን የማያስብበትን ርምጃ ይከተላል፡፡ በዚህ መነሻ ተደራጅተውም ይሁን በተናጠል የህዝብንና የአካባቢን ብሎም የአገርን ሰላም ለመበጥበጥ ለሚነሱ ይቅርታ አይኖርም፡፡ በተለይም አገራችንን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ለመውሰድ የተደረገውንና ሲደረግ የነበረውን የተለያየ ሙከራ ለሚረዱ የህብረተሰብ ክፍሎች መልዕክቱ ግልፅና ግልፅ ነው፡፡ ዛሬስ ለኢትዮጵያ የሚተኙላት አሉ? የሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች ሊጠይቁት የሚገባ ጥያቄ ይሆናል፡፡

3 comments:

Anonymous said...

the muslims are creating problem every where


http://news.bbc.co.uk/2/hi/asia-pacific/7872635.stm

Anonymous said...

ewunetim dem melash,yetechefechefutin ethiopian christianoch dem endemitimelis tesfa alen

Anonymous said...

kkkk Komanderu eko Muslimoch endih aderegu alalum ,hodachun yeqoretachehu negerun slemtawqut new.

Fes yalebet zlay aychlm alu!
Ethiopia teqeyralech ,muslimoch angetachewun qena adrgewal,endedrow bemetachew lay atremamedum.Tegbaban !
dejeselam endehu akrarina tsebachari blog new selamna -teru neger aytebeqm !

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)