February 24, 2009

መንግስትና የሀይማኖቶች መቻቻል

አዲስ አበባ የካቲት 14 2001 ( ሬዲዮ ፋና ) መንግስት በሀይማኖቶች መካከል ያለው መቻቻል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከእምነት ተቋማትና ከህብረተሰቡ ጋር ተቀራርቦ እንደሚሰራ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ገለፁ።

ሚኒስትሩ አቶ አባይ ፀሀየ ለሬድዮ ፋና እንደገለፁት በሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሰቀሱ ግጭቶችን አስቀድሞ ለመከላከል መንግስት ከሀይማኖት አባቶችና ከህብረተሰቡ ጋር ተቀራርቦ ይሰራል። የሃይማኖት ተቋማት ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብን እንዲያዳብሩ ለመርዳትም መንግስት የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።

በስነ ዜጋ ትምህርት ውስጥ የሀይማኖት መቻቻል ተካቶ እንዲሰጥ እንደታቀደ መግለፃቸውንም ባልደረባችን ብርሀኑ ወልደሰማያት ዘግቧል።

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)