February 16, 2009

“ፀሎተ ዲያስፖራ” ??

ለውድ ወ/ሪት (ወ/ሮ)ሰላማዊት አሰፋ
selam23as@yahoo.com
USA

ሰላም ጤና ይስልኝ።
በቅርቡ “ፀሎተ ዲያስፖራ” በሚል ርእስ በአይጋ ፎረም ላይ ያስቀመጡትን ግጥም መሰል መጣጥፍ ተመልክቼዋለሁ። አወራረዱ ክርስቲያኖች የምንጠቀምበትን የጌታን ጸሎት ለማስመሰል በመሞከር የደረሱት ነው።

ምናልባት ገና ጀማሪ ብዕር ጨባጭ ከሆኑ በሚያውቁት መጀመር የተለመደ ስለሆነ ላይፈረድቦት ይችላል። መደበኛ ፀሐፊ ከሆኑ ደግሞ በምዕራባውያን “እግዚአብሔር የለሽነት” (አቴይዝም) ተጠልፈው ስለሚሆን እረዳዎታለሁ። የሚገርመው ግን ብዙ ቁምነገሮች የሚወጡበት አይጋ ፎረም (aiga forum) ይህንን የሰዎችን እምነት የሚደፍር ሚዛን የማይደፋ ጽሑፍ ምንም ሳይመረምር መለጠፉ ነው።

ውድ ወ/ሪት (ወ/ሮ)ሰላማዊት የግል ሐሳብን መግለጽ በሚከበርበት ሀገር ላይ ተቀምጠው ስለሌላው ስሜት መጠንቀቅንም አብረው ሊማሩ ይገባ ነበር። ምናልባትም እርስዎ ራስዎም ክርስቲያን ሊሆኑ ይችላሉ። መጣጥፎ በፈረንጅኛው አፍ “ብላስፌሚ” የሚባለው ዓይነት መሆኑን አልተረዱም ይመስልኛል። በፖለቲካ አመለካከት የሚተቿቸውን ሰዎች ለመንቀፍ ብዙ አማኝ በነጋ በጠባ የሚጸልየውን ክቡር ጸሎት በማይገባ መንገድ መጠቀም መስመር የሳተ አልመሰሎትም? እርሶም አይጋም(aiga forum) ለአንባቢዎቻቸው ስሜት የሚጨነቁ ቢሆን ይህንን ጽሑፍ አውለው አያሳድሩትም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
ሰላመ እግዚአብሔር ይድረስዎ!!
ገብርኤል ሚካኤል
ከአይጋ አንባብያን አንዱ
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)