February 11, 2009

መንግሥት በቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና አባቶች ላይ እርምጃ እንዳይወስድ እያሰጋ ነው

መንግሥት በቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና አባቶች ላይ እርምጃ እንዳይወስድ እያሰጋ ነው
አቶ መለስ “ፖለቲከኛ ቄሶች እና ፖለቲከኛ ሼኮች” ያሏቸውን ጎነጡ

መንግሥት በአክራሪ ሙስሊሞች ቆስቋሽነት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመታየት ላይ ያለውን ውጥረት ምንጭ ወደጎን በማለት ቤተ ክርስቲያንንና በአገልግሎት የተሰማሩ መምህራንንና አባቶችን በይፋ መክሰስና ለችግሩ ምንጭ በማድረግ ላይ ይገኛል። በጎንደር የተፈጠረውን አለመግባባትና ጥፋት “ቤተ ክርስቲያን ጨቁናችሁዋለች” በሚል ንግግራቸው ያባባሱት የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪና አዲስ የተቋቋመውና ማስታወቂያ ሚ/ርን የተካው መሥሪያ ቤት የበላይ አቶ በረከት ስምዖን ጥፋታቸውን በመርሳት “እናስራለን፣ እንገርፋለን” ማለት ጀምረዋል።
የደጀ ሰላም ውስጣዊ ምንጮች እንደጠቆሙት የመንግሥትና የአክራሪዎቹ ዒላማ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት ወጣት ሰባክያነ ወንጌል ብቻ ሳይሆኑ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ስለ ጉዳዩ ሲኖዶሱን ለማነጋገር በመጡበት ጊዜም ሳይቀር በድፍረት የተጋፈጧቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጭምር ናቸው ተብሏል። ብፁዕነታቸው “በኢትዮጵያ የሃይማኖት መቻቻል አለን?” የሚል መጽሐፍ በማሳተማቸው የአክራሪዎቹ የጽሑፍ ውርጅብኝ ሲወርድባቸው ከመቆየቱም ባሻገር መንግሥት ስለ ቤተ ክርስቲያን ያለውን የተሳሳተ አመለካከት እንዲያስተካክል በድፍረት በመናገራቸው ጥርስ ውስጥ ሳይገቡ እንዳልቀሩ ተገምቷል።
የበረከት ስምዖን መስመር የሳተ ሐሳብ እርማት ሳይደረግበት ሀገር አቀፍ የወጣቶች ስብበሳ ላይ “በወጣቱ የወደፊት ጥቅምና ሕይወት ዋጋ የሚጠቀሙና የሃይማኖት ግጭት ዓላማቸውን የሚያራምዱ… የራሳቸውን የፖለቲካ ዓላማ ለማራመድ የሚሞክሩ ቄሶችና ሼሖች” መኖራቸውን በመጥቀስ ስላቅ በተሞላበት ንግግር ሀገሪቱ የገባችበትን የአክራሪነት አደጋ ፍፁም ተራ ፖለቲካዊ ገጽታ ብቻ በመስጠት የተናገሩት መለስ ዜናዊ የተሰበሰበውን ወጣት ጭብጨባና ሳቅ ከማግኘታቸው ባለፈ የኢሕአዴግ መንግሥት አደጋውን አርቆ ለመመልከት እንዳልቻለ በተግባር በማሳየት ላይ ይገኛል።
ጠ/ሚኒስትር መለስ “የፖለቲካ ቄሶች” ካሏቸው ውስጥ ምናልባትም ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልንም ለመጨመር ተፈልጎ ይሁን አይሁን የታወቀ ነገር የለም። ብፁዕነታቸው ለሃይማኖታቸውና ለእውነት ያሳዩት ቆራጥነት የሚደነቅ ሲሆን መንግሥት ጉዳዩን ከተራ የፖለቲካ ጨዋታ ባሻገር ሊመለከተው እንደሚገባ ምንጮቻችን ጠቁመዋል። በ2005 ምርጫና ከዚያ በሁዋላ በመጡት ዓመታት “ተራ ቦዘኔ” እየተባለ በምግባረ ብልሹነት ሲነሳ የነበረው ወጣት ሥርዓት ይዞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በተለይም በጥምቀት ሰሞን በማሳየቱ ግራ የተጋቡ የመንግሥት የፖሊስና የጸጥታ ሃይሎች “ዝምታውና ጨዋነቱ ከየት መጣ?” በሚል አባቶችን “አጋልጡ” ማለታቸውና አባቶችም “የምናጋልጠው ሳይሆን የምንገልጠው ቅሬታ በመንግሥት ላይ አለን” ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
መንግሥት በበረከት ስምዖን መመሪያ ሄዶ አባቶችንና መምህራንን ወደ ማሰር የሚሄድ ከሆነ ምናልባት ያልጠበቀው ተቃውሞና በጥይት ሊያቆመው የማይችለው ቀውስ ሊገጥመው እንደሚችል ምንጮቻችን በስጋት ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ማሰርና መግደል በተለይም ከደርግ ዘመን ጀምሮ መንግሥታዊ ስልት እየሆነ እንደመጣ የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ይነግረናል።

2 comments:

Anonymous said...

May the Almighty God give our fathers the strength to fight for the truth.We all know that the government is aganist our church. We Chrisitain must pary every day that is the only solution for us.

Anonymous said...

በተለያየ መድረክ የኦርቶዶክስ አክራሪነታችሁን ፡ሰላም ፈክላጊ አለምሆናችሁን፡ከትናንት ችግር ተምራችሁ ለነገ በጥሩ ሥነ ምግባር አለመዘጋጀታችሁን እያየን እና እየሰማን ነው።
መንግስት የሃገርን ሰላም የመጠበቅ ሃላፊነት እስካለበት ድረስ አጥፊውን አይቀጡ ቅጣት መቅጣት እንዳለበት እምነቴ ነው።
ክርስትና የመንግስት ሃይማኖት መሆኑ ከቀረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ ኦርቶዶክስ እውነታው አልዋጥላት ስላለ ብቻ ጠብ ስታጭር ቆይታለች።ይህንንም በተለያዩ መስኮች ያየነው ሁኔታ ሲሆን' ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት' 'የአባቶቼን እርስት አልሰጥህም' የመሳሰሉ መፈክሮችን ለብሰው በወጡ ማይም ክርስቲያኖች ላይ ነቀፋ ሳይሆን ሙገሳ መቸሯ በራሱ የችግሩ ምንጭ እና ተካፋይ መሆኗን ያረጋግጣል።ከዚህ አይን ያወጣ የኦርቶዶሽ ፈጣጣነት በኋላ መንግስት ምን መስራት እንዳለበት ያውቃል።
እናም ራሳችሁን በድጋሚ ፈትሹ...ከዚያ ውችህ ግን የምታመጡት ወይም የምትፈጥሩት ቅንጣት ታክል ነገር አይኖርም።
በቅሎ ማሰሪያዋን በጠሰች ቢሉት በገዛ እጇ አሳጠረችው አለ ይባላል።
እናንተ የኦርቶዶክስ መሪ ነኝ የምትሉ ሁሉ......
ነፍሳችሁን በድጋሚ መርምሩ።ከሙስሊሞች ጋር በሰላም ለመኖር ሞክሩ.....አክራሪ ሙስሊም የሚባል በኢትዮጵያ ውስጥ የለም።
ነገር ግን አትንኩኝ ፈጣሪየን በነጻ ላምልክበት ፡የመስገጃ ቦታ ይሰጠኝ ስላለ አክራሪ አላችሁት ።
ቁጥሩ ከ65%በላይ የሆነው ሙስሊም አሃዙ ተቀንሶ ተነግሮት እንኳ በሰላም እየኖረ ነው።ከዚህ የበለጠ በደል አለ?ነገር ግን የቃላት ጋጋታ ምድራዊ እውነታን ስለማይቀይር ነው.....ትእግስት ፍርሃት አለመሆኑን ከሙስሊሞች ተማሩ።
ሠላም ስጡን ሰላም ፈላጊዎች ነው።

በአመት 360 ቀን በወር 30 ቀን አመት በአል አድርጋችሁ ሰው እንዳይሰራ የበአል ቀን ነው እያላችሁ ኢትዮጵያን አደኸያችኋት....አይበቃችሁም? ? ?

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)