February 9, 2009

ኢሕአፓ ስለ “ሃይማኖት ግጭት” መግለጫ ሰጠ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) “በኢትዮጵያ ውስጥ ስለተከሰተው የሃይማኖት ግጭት” መግለጫ ሰጠ።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሕይወት ውስጥ የማይዘነጋ ሥፍራ ካላቸው ከነመኢሶን፣ ደርግና ኢሕአዴግን ከመሳሰሉት ኮሚኒስታውያን ንቅናቄዎች አንዱ የሆነው ኢሕአፓ በድረ ገጾች ላይ ባስነበበው መግለጫው በቅርቡ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለተከሰተው “የሃይማኖት ግጭት” በሥልጣን ያለውን መንግሥት ተጠያቂ አድርጓል። “ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ወደ ልጣን ከመጣ ወዲህ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በሃይማኖቶች መካከልና በእያንዳንዱ ሃይማኖት ውስጥ መጠነ ሰፊ የሆነ ችግር ፈጥሯል” ያለው መግለጫው መንግሥት “ከሲኖዱ ህግጋት ውጭ ሌላ ፓትርያርክ” በመሾም ሕዝቡ እንዲከፋፈል ማድረጉን ያትታል። መንግሥት “በእስልምና ሃይማኖት ውስጥም እየገባ ፖለቲካዊ አመራር ለመስጠት ሞክሯል” ሲል ገልጿል። “በዚህም ይህ የህወሓት መንግሥት ግጭቶችን ከማብረድ ይልቅ በመቆስቆስና በማፋፋም ሕዝባችንን ወደ ክፉ አደጋና ሊያባራ ወደማይችል የጦርነት አውድማ እየመራ ይገኛል” ብሏል።

የኢሕአፓ መግለጫ “ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አንዳንዴ በገዥው ክፍሎች ‘በኢትዮጵያ የሚገኙ እስላሞች’ እየተባሉ እንደ ባይተዋርና ሁለተኛ ዜጋ የተጠሩበትን፣ የዜግነት መብቶቻቸው ተረግጠው በመሬት ስሪት አድልዖ ይሁን በሥራ ዕድል መነፈግና የተያያዙ ሌሎች በደሎች ይደርሱባቸው እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታዎቻችን ናቸው” ሲል አንዳንድ የኢሕአዴግ ባለሥልጣናትና ግራ ዘመም ኢትዮጵያውያንና እግዚአብሔር የለሽ ኮሚኒስት ኢትዮጵያውያን ላለፉት 40 ዓመታት ሲያስተጋቡት የነበረውን “ቤተ ክርስቲያን ጨቋኝ ናት” ስብከት አስተጋብቷል።
መግለጫው ዓይኑን በጨው ታጥቦ በጅማ በአክራሪዎች የተጨፈጨፉትን ክርስቲያን ዜጎች ዕልቂት በመናቅ “ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች የጠላለቁበት አደገኛ ክስተት” ሲል በሰው ሕይወት ይቀልዳል። ይልቁንም ክርስቲያኖች “ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት” የሚል ቲ-ሸርት መልበሳቸውን እንደ ከባድ ወንጀል በመቁጠር ሲሳለቅ ቆይቶ “ ዛሬ መስኪድ ብዙ ተሠራ፣ ቤተክርስቲያን የተሠራው በሙስሊሞች ቦታ ላይ ነው … ወዘተ በሚል መዘባራት” አይገባም ሲል ለጽሑፍ በማይገባ ስላቅ ክርስቲያኖችን ይኮንናል።
በመጨረሻም መግለጫው “ይህን የሃይማኖት ውዝግብ ለማርገብና በጋራ በኢትዮጵያዊነት ስሜትና መግባባት እንድንኖር ለማድረግ የበለጠ ሃላፊነቱን የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች ትልቁንና ወዋነኛውን ድርሻ ይሸከማሉ” ሲል አጠቃሏል።

የመግለጫውን ሙሉ ቃል እዚህ ያንብቡ።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)