February 8, 2009

መልእክተ ማኅበረ ቅዱሳን:- "የአክራሪ ሙስሊሞች ን ትንኮሳ ለመግታት ተባብሮ መሥራት ይገባል"

“ሲያመቸው በእስልምናው፣ ሲያመቸው በፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለም እያሳበበ ሰላማዊት ኢትዮጵያን የሚያውከው የአክራሪ እስልምና ትነኰሳ በጊዜ ሊገታ ይገባዋል፡፡ “

አክራሪ ሙስሊሞች በየጊዜው የሚፈጽሟቸው ትንኰሳዎች በእጅጉ እያደጉ መምጣታቸውን ለመረዳት ተጨማሪ ዕውቀትም ሆነ ሌላ ነገር አያስፈልግም፡፡ «ቁርዓናችን ተቀደደ»፣ «እስልምና ተናቀ» ከሚሉ «የተገፋን» ፕሮ¬ጋንዳዎች የተነሣው የትንኰሳ እንቅስቃሴ ቀስ በቀስ እያደገ መጥቶ በአሁኑ ጊዜ ለመስማት የሚዘገንኑ ለማመንም የሚያስቸግሩ ደረጃዎች ላይ ደርሷል፡፡ ቀደም ብሎ በአንዳንድ አካባቢዎች የካህናቱን ሻሽ በማስወለቅ፤ ክርስቲያን ሴቶችን በመድፈር ተነሥቶ፤ የመስቀልና የጥምቀት ቦታዎችን፣ በቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ያሉ ቦታዎችን ለመስጊድነት ካልተሰጠን እስልምና ተንቋል ማለት ነው ወደሚለው ተሸጋገረ፡፡ ይህ ሲፈጸምለትና ትንኰሳው የሚናፍቀውን ግጭት በፈለገው መጠን አልፈጥርለት ሲል ደግሞ ታቦታት ለጥምቀት በሚወርዱት፣ ደመራ ደምረው መስቀል በሚከበርበት ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ላይ ድንጋይ ወደ መወርወርና በዓላቱን ወደ ማወክ ተሸጋገረ፡፡ በእነዚህም ግን ሊያቆም አልቻለም፡፡

በቅርቡ ደግሞ ወደ ክፉ ትንኰሳዎች ተሸጋግሯል፡፡ የክርስቲያኖችን እምነት አያጸድቅም ማለቱንና እስላም ሁኑ ብሎ ማስተማሩን የሚከለክለው አልነበረም፤ ይህ የሃይማኖት መምህራን ተፈጥሮአዊ ጠባይ ነውና፡፡ ነገር ግን ከዚህ አልፎ በጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም በሃይማኖታችን ሥርዓቶች ላይ «ስሕተት ነው» የሚሉትን በጥቅስና በትምህርት ማሳየት ትቶ መሳደብ የ«ጠብ አለኝ በዳቦ» ትንኰሳ ነው፡፡ ከዚያም አልፎ መጽሐፍ ቅዱስን ቀድዶ በሰርግ ዳስ ላይ እንደጉዝጓዝ መበተን እጅግ የከፋ ትንኮሳ ነው፡፡ በዚህም ግን አልተመለሰም፡፡ አክራሪ እስላሞች ሁለት ሦስት እየሆኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመግባት «አላህ አክበር» ማለት፣ ሥዕል ማውረድ፣ ቤተ ክርስቲያኑን «የአላህ ቤት ነው» እያሉ ማወክ ክርስቲያኖቹ አስተዋይና ታጋሽ ባይሆኑ ደም ለማፋሰስ የታለመ ግጭት ለመጫር ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ በጠራራ ፀሐይ በአዲስ አበባ ከተማ ከክርስቲያኖች አንገት ላይ ማተብ ለመበጠስ መሞከር የአክራሪ እስልምና ትንኰሳ ከየት ተነሥቶ የት እንደደረሰ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ከዚህም በላይ ደግሞ «ነገ ምን ሊያደርጉ ይችሉ ይሆን)» የሚለውን ጥያቄ ያስነሣል፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሓላፊነት የማይሰማቸውና ሰብአዊ መብትን እንኳ የማያከብሩ፤ ከራሳቸው እምነትና አስተሳሰብ ውጪ ምንም ለማድረግ የማይመለሱ አካላት በጊዜ ሊገቱ ይገባቸዋል፡፡

አክራሪ እስላሞቹን መግታትም የክርስቲያኖቹ ድርሻ ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡ አደጋነታቸው ለሰላማዊ እስላሞች፣ ለክርስቲያኖች፣ ለመንግሥትና ለሀገር፣ ለሕዝብም ሁሉ ስለሆነ መከላከሉም የጋራ ሊሆን ይገባዋል፡፡ በእኛ እምነት ከሚከተሉት አካላት አፋጣኝ ምላሽ ያስፈልጋል፡፡

1. ከቤተ ክርስቲያን አካላት

የቤተ ክርስቲያን አባቶች መምህራንና ካህናት እንደ እስካሁኑ ሁሉ ሕዝባቸውን ከማስተማርና ከመምከር በላይ የሆነ ሓላፊነት አለባቸው፡፡ የመጀመሪያው በሕግ የቤተ ክርስቲያንን መብት ማስጠበቅ ነው፡፡ ቦታዎቿን፣ ንብረቶቿን፣ ሀብቷን ብቻ ሳይሆን ለክርስቲያን ልጆቿ ስም እየሰጡ እና ጥላሸት እየቀቡ ማሳደድ የሚፈጽሙትን አክራሪዎች በሕግ ማስታገስና የክርስቲያኖችን ሰብአዊ መብት ማስከበር ይጠበቅባቸዋል፡፡ በጅማና ኢሉባቡር፣ በሐረርና በአርሲ አንዳንድ አካባቢዎች ባሉት ክርስቲያኖች ላይ «ነፍጠኞች ውጡ» በማለትና ለጉዳዩ ፖለቲካዊ ጥላ በማበጀት የሚፈጸመውን ግፊት ለመንግሥት አካላት በማስረዳት የሕግ ከለላ እንዲያገኙ ማድረግ ይጠበቃል፡፡ ከዚህም በላይ መንግሥት የሰጣቸውን ሓላፊነት ያለ አግባብ እየተጠቀሙ የራሳቸው ጽንፈኝነት ማራመጃ መሣሪያ ሊያደርጉት የሚሹትን በተጨባጭ ማስረጃ ለከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በማሳወቅ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድባቸው መጠየቅ ይገባል፡፡ በተጨማሪም በሀገራችን ሰላም ሰፍኖ ሁሉም እንደየ እምነቱ በሥርዓት የሚጓዝበ ትን ሁኔታ ለማምጣት ከእስልምናው ሃይማኖት መሪዎች ጋር መመካከርም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ bqR በአንደበት የመንግሥት ደጋፊና የሀገር ጠባቂ መስሎ በውስጡ ከሂዝቦላ ጋር የሚዘምት፤ ከአልሸባብ ጋር የሚዝትብን ጠላት ሳናውቀው ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡ ምእመናንም እንዲህ ያሉትን አካላት ነገራቸውንና ድርጊታቸውን መረዳት ይገባቸዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ሥራቸውን የመንግሥት ለማስመሰል በሚጥሩበት ጊዜ የመንግሥት ትእዛዝ እንዳልሆነ በመረዳት መንግሥትና ሕዝብን ለማቃቃር የሚደረጉ መሆናቸውን መገንዘብና ሐሳባቸውን በተሳሳተ መንገድ እየገለጹና መንግሥትንም የሐሳባቸው ደጋፊ በማስመሰል የሚፈጽሙትን ወንጀል በጊዜው መጠቆም አስፈላጊ ነው፡፡

2. መንግሥትና አስፈጻሚዎቹ

መንግሥት እንደ መንግሥት አክራሪ እስልምናንና የጥፋት ሴራውን እንደማይቀበለው እናምናለን፡፡ ይሁን እንጂ አክራሪው በሰላማውያን እስልምና ተከታዮች ስም የሚያደርጋቸውን ዘመቻዎች በውል እያጠና በማስታገስ ረገድ ሙሉ በሙሉ ተዋጥቶለታል ለማለት ይቸግረናል፡፡ ስለዚህም የአክራሪውን ለምድ በትክክል በማወቅና በማውለቅ ተኩላነቱን አውጥቶ ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡ አሁን ያለው የአክራሪዎቹ አካሔድ እስላሞችንና ክርስቲያኖችን የማጋጨት፣ በመካከሉ የሚናፍቀውን ሁከት የመፍጠርና፤ የዓለም አቀፍ አክራሪዎች መፈንጫ የማድረግ ሕልሙን በእስልምና ስም ሸፍኖ ማቅረብ ነው፡፡ ይህን ሁኔታ በደንብ በመለየት አስፈላጊው ሕጋዊ እርምጃ ሊወስድ ይገባዋል፡፡

በሐረር አካባቢ እየተሠራጩ ያሉት የአክራሪዎቹ ትራክቶች /በራሪ ጽሑፎች/ እንደሚያስረዱትና በዚያም አካባቢ ያሉ ሀገርና ሕዝብ ወዳድ እስላሞች በፍርሃትም ቢሆን እንደሚያስረዱት አክራሪው በሱማሌ ያለውን የግብረ አበሮቹን እንቅስቃሴ በተስፋ ይጠባበቀዋል፡፡ ስለዚህ እነዚህ በክርስቲያኖቹ ላይ የሚፈጸሙት ትንኰሳዎች ሁሉ በሀገሪቱና በሕዝቧ ላይ ላቀዱት ጥፋት ፍንጭ ሰጪዎች ብቻ ሳይሆኑ ተጨባጭ ማስረጃዎችም ናቸው፡፡ ስለዚህም የመንግሥት የደኅንነት ጉዳይ ነገሮቹን ከእስላምና ክርስቲያን ግጭት አልፎ በማየት ፖሊስ ከሚያቀርበው የወንጀል ጉዳይ አልፎ መመልከት ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ጉዳዮቹ ግለሰባዊ አይደሉምና፡፡ ከሀገር ደኅንነት አንጻር ካልታዩና አሁን እንደሚደረገው በተራ ወንጀልነት ብቻ ከታዩ ነገሩ ሃይማኖታዊ ስለሆነ ክርስቲያኑንም ወዳልተፈለገ መንገድ ሊያስገባ ይችላል፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት ከተራ ትንኰሳ ባሻገር በማየት አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ሊወስድ ይገባዋል፡፡

የ¬ሊስ ኃይል ብቻ ሳይሆን ሌሎች እስከ ቀበሌ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላትም ጉዳዮቹን ከማድበስበስ ይልቅ የነገሩን ሥር አጥርቶ ለመፍትሔው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ አክራሪዎቹ ለመስጊድ መሥሪያ በማለት በመብትና በሃይማኖት እኩልነት ሰበብ የሚያቀርቧቸውን የቤተ ክርስቲያን ቦታዎች ጥያቄ ነገሩ ቦታ ከመፈለግ ባሻገር ያለ ትንኰሳ መሆኑንና አለመሆኑን መመርመር ጊዜው የሚጠይቀው ወሳኝ ተግባር ነው፡፡ በችኰላ የጠየቁትን ሁሉ ቦታ ሰጥቶ ሕዝቡን ወደግጭት እንዲያመራ ምክንያት መሆን አይገባም፡፡ ይህ ባልሆነበት በኋላ የሚመጣውን የክርስቲያኖች ጥያቄ በማፈን፣ ካርታ የላችሁም፣ ተቀድማችኋል በማለት ብቻ ማስታገስ ሊያዳግት ይችላል፡፡ ስለዚህም ነገሮችን ቀድሞ ከጠባያቸው አንጻር ማጥናት፣ የሕግ ክፍተቶችን ጥላ አድርጎ የሚሠሩ ተንኮሎች እንዳይሆኑ በውል ማጤን፤ ሓላፊነታቸውን ለፍላጐታቸው መጠቀሚያ የሚያደርጉ ባለሞያዎች የሚፈጽሙትና መንግሥትንም ከሕዝብ ጋር እንዳያጋጩ በጥንቃቄ ማየት ይገባል፡፡ ምክንያቱም እነዚህን ሁኔታዎች የሚያመለክቱ ብዙ ግጭቶችን አሳልፈናልና፡፡

ከዚሁ ጋር መንግሥት እንደመንግሥት ሊያጠናው የሚገባ ነገርም አለ፡፡ አሁን አሁን በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ምእመናን የመንግሥት ሓላፊነታቸውን ተጠቅመው በቤተ ክርስቲያንና በቦታዎቿ እንዲሁም በአማኞቿ ላይ የሚፈጽሟቸው ጭቆናዎች እንዳሉ ይናገራሉ፡፡ መንግሥት እነዚህን ነገሮች ማጣራት፣ መከታተልና እርምጃ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡ ይህ ካልሆነ በመጀመሪያ ደረጃ መንግሥት የሚበድላቸው ይመስላቸዋል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ከፍተኛ ግምት የምንሰጠው ግን እነዚህ በመንግሥት ስም ፈቃዳቸውን የሚፈጽሙ አካላት የተሳሳተ ሥልታቸው የሠራ እየመሰላቸው የባሰ ጥፋት ወደመፈጸም እንዳይሸጋገሩ ከፍተኛ ሥጋት አለን፡፡ ስለዚህ በዚህ በኩል የሚመጣውን አደጋ ለመከላከል የሚቻለው መንግሥትና የሀገር ደኅንነት ለእነዚህ ሥራዎች ትኩረት ሰጥተው መሥራት ሲችሉ መሆኑን እናምናለን፡፡

3. መገናኛ ብዙኃን

አንዳንድ የኅትመትና በአብዛኛው ደግሞ የሬዲዮና የቴሌቭዥን ጋዜጠኞች ሳያውቁት የአክራሪ እስልምና እንቅስቃሴ እንዳይደግፉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ይፋዊ የሆነ የመንግሥት ስታስቲክስ እያለ፣ እንዲሁም ሙያዊ በሆነ መንገድ መገመትና የቦታዎችንም ስፋትና ሊይዙት የሚችለውን የሰው ብዛት በዘመናዊ መንገድ ማወቅ እየተቻለ ተጋንኖ ብቻ ሳይሆን ግርምት የሚፈጥሩ አሃዞችን በዜና ሰምተናል፡፡ ከዚህም በላይ አክራሪዎች ተንኩሰው ተገፋን ሲሉ ነገሩን በውል ሳያጤኑ በተሳሳተ አቅጣጫና እጅግ ከሚገባው በላይ የሚደረጉ ዘገባዎች ሥርዓት ሊይዙ፣ ልክም ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ለአብነት በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ «ቁርዓን ተቀድዷል» ብለው አክራሪዎች ዐመፅ ባነሡበት ወቅት የተደረ ገውን የቀን ሙሉና የሳምንታት ዘገባ ማስታወስ ይቻላል፡፡ ስለዚህ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች አክራሪዎች በእስልምና ሰበብ ከሚያስተጋቡት ወንጀልና የትንኰሳ ተግባር ጋር የሚያደርጓቸውን ዘገባዎችና የዜና እወጃዎች በጥንቃቄ ሊሠሯቸው ይገባል እንላለን፡፡ ለዚህም ማሳያ ማቅረብ ይቻላል፡፡ ቃለ መጠይቅ የሚደረግላት አንዲት አክራሪ እስላም በኢቲቪ የተደረገላትን ቃለ መጠይቅ ተጠቅማ ስድሳ በመቶ ነን ማለቷን ሰምተናል፡፡ ጋዜጠኛው መረጃውን እንኳን አልጠየቃትም፡፡ ወይም ሌላ የስታቲስቲክስ ባለሞያ በማናገር አሃዙን ሳያስተካክል አልፏል፡፡ እነዚህን የመሰሉት ሥራዎች መታረም ይገባቸዋል፡፡

4. ሰላማውያን እስላሞች

አክራሪዎችን ከክፉ ተግባራቸው ለማስታገስም ሆነ ወደ ልባቸው ለመመለስ ኢትዮጵያውያን እስላሞች ሰፊ ድርሻ፣ የተሻለም ዕድል ይኖራቸዋል፡፡ ልጆቻቸውን፣ ወንድሞቻቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውን በመምከር፤ ከእነርሱ የሥውር ሥልጠናና የጥላቻ ቅስቀሳ የመመለስ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ይህም ካልሆነ እንደማንኛችንም ሁሉ አደጋው የጋራችን ነውና ሥራቸውን በማጋለጥና ተንኰላቸውን በማክሸፍ የሀገርን ሰላምና ደኅንነት በመጠበቁ ግንባር ቀደም መሆን ይችላሉ፡፡ በዚህም በሀገራችን ለዘመናት የኖረው የክርስቲያኖችና የእስላሞችን የሰላም የፍቅርና የመግባባት ኑሮ እንዳይጐሽና ወደ መጠራጠርና አለመተማመን እንዳይሔድ መጠበቅ ይቻላል፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያውያን ሰላማውያን እስላሞች ከፍተኛ ታሪካዊ ድርሻችሁን ልትወጡት ይገባል እንላለን፡፡ በቅርቡ የሕንድ እስላሞች ይፋዊ በሆነ መንገድ በታጅ መሐል ሆቴል ላይ ጥፋት ያደረሱትንና እነርሱን መሰሎቹን አለመቀበላቸውንና ማውገዛቸውን ለዓለም ሕዝብ እንደገለጹት ከኢትዮጵያ ነባርና ሰላማዊ እስላሞችም ይህን እንጠብቃለን፡፡

5. ሕዝበ ክርስቲያን

ክርስቲያኑ እስካሁን ያሳየውን ትዕግሥት፣ የዜግነትና ሀገራዊ ሓላፊነት ወደፊትም በተግባር ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ አንደኛ የክርስትናው አስተምህሮ ምንም ዓይነት የማጥቃትና ሰይፍን በሰይፍ የመመለስ አካሔድ አይፈቅድለትም፡፡ ከዚህም በላይ ዋና መሣሪያዎቻችንን ጾምና ጸሎትን በመጠቀም ሰላማችንን ሊያደፈርስ የተነሣውን ረቂቁን የአጋንንት ሠራዊት መበተን ይቻላል፡፡ ትግሉ ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ቅዱስ ጳዉሎስ እንደተናገረው ከጨለማው ገዥዎች ከክፉዎች መናፍስት ጋር ነውና፡፡
በአሁኑ ጊዜ ግን ከዚህም ተጨማሪ ሓላፊነት ተጥሎብናል፡፡ ገዳማትን፣ አብያተ ክርስቲያናትን፣ ሊቃውንትንና አበውን ራሳችንንም የመጠበቅ፡፡ የምናያቸው ትንኰሳዎች አደገኛዎችና ወደአልተፈለገ ግጭት የሚገፋፉ ስለሆነ ቀደም ብሎ ራስንና አብያተ ክርስቲያናትን በመጠበቅ የአክራሪውን ሴራ ማክሸፍ ይቻላል፡፡ ከዚህም ጋር የሚገጥመንንና የምናየውን የአክራሪ እንቅስቃሴ ለሚመለከተው የመንግሥት አካላት በመጠቆም ችግሮቹን እንደ እስካሁኑ በፍጥነት መቆጣጠር ይገባል፡፡

ማጠቃለያ፡-

የአክራሪ እስልምናው ተግዳሮት የዓለም ሁሉ ሆኖአል፡፡ እንቅስቃሴውና መረቡም ሰፊ ነው፡፡ ስለዚህም የሁላችንንም ትብብርና የሓላፊነት ስሜት ይጠይቃል፡፡ ክርስቲያኑና እስላሙ፣ መንግሥትና ሕዝብ፤ ገጠርና ከተሜ፣ ... ሳንል በአንድነት ትንኰሳውን ልንገታ ሴራውንም ልናከሽፍ ይገባናል፡፡ በአንድነትና በትብብር መሥራታችን ውጤታማ የሚያደርገን «አንድነት ኃይል ስለሆነ» ብቻም አይደለም፡፡ የአክራሪው ስልት መጀመሪያውኑ መከፋፈልና መለያየት ስለሆነም ጭምር ነው እንጂ፡፡ ከተለያዩ በኋላ አንድ መሆን ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ደግሞ ሱማሌ ማሳያችን ናት፡፡

ይህም አክራሪ እስልምና ማፍረስ እንጂ መሥራት የማይችል፤ መበጥበጥ እንጂ ሰላም ማምጣት ባሕርዩ ያልሆነ፤ ማወክን እንጂ መምራትን ያልታደለ እንደ ሰይጣን ለጥፋት ብቻ እንደተፈጠረ መገንዘብ ይገባናል፡፡ ሱማሌ ሙሉ በሙሉ እስላማዊት ሀገር ናት፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ሀገር ለመኖር አልተቻላትም፡፡ ይህም አክራሪው ሰላማዊ እስላሞችንና እስላማዊ ሀገሮችንም እንዴት እንደሚጥላቸው ግልጽ ማሳያ ነው፡፡ የፍልስጥኤምን አስተዳደር ተረክቦ የነበረው ሐማስም ወደ መንበረ ሥልጣኑ ከወጣ በኋላ ዐቅም ማነስ ብቻ ሳይሆን ከማሸበር ያለፈ የመሪነት ተግባር የተሳነው መሆኑን በግልጽ አሳይቷል፡፡ ስለዚህ አክራሪ እስልምና ከራሱ አባላት በቀር ሰውን ሁሉ እንደ ጠላት የሚያይ በመሆን ሰይጣናዊ ባሕርዩን ስላሳየ የሃይማኖትና የፖለቲካ ልዩነት ሳይገድበን ተባብረን ተግባሩን ልንታገል ይገባናል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

5 comments:

Anonymous said...

MayGod Bless your work.
I God will give us a leader who thinks peace like U guys one day.

Anonymous said...

Ayiii, mahbere kidusan......yalefebet yeatsewochu astesaseb be addisu zemen ayseram. Ermachun awtu!!! Beterefe mengist ende mahbere erkusan yalu ashebari orthodox christian dirijtochen mela bil sayshal aykerim.
Thnx

Anonymous said...

tx anonymous =2 you got my point iam ethiopian muslim idont have any animosity toward our chirtian nowadays the orthodox iknow changed alot some of them trying to create abig mess to the muslim ethiopians and even to other chiritians like catholic and pentecostal and jhovas it is time for them to repect all citizen and live together

Anonymous said...

almost all oromo christian follwers change to lutheran and muslim thanks god orthodox was teaching as if oromos were sub human calling them galla and not even recognizing their calture and language no more oromo chritians follow your Mehbere saytan theology was any one from this church questionend through whle haile sillasse era for 45years no oromo language was in ethiopian media why those prists didnoy do any thing when afar;somali;english;french ;tigring and amharic were in media ijust want toknow why?????????????

Anonymous said...

almost all oromo christian follwers change to lutheran and muslim thanks god orthodox was teaching as if oromos were sub human calling them galla and not even recognizing their calture and language no more oromo chritians follow your Mehbere saytan theology was any one from this church questionend through whle haile sillasse era for 45years no oromo language was in ethiopian media why those prists didnoy do any thing when afar;somali;english;french ;tigring and amharic were in media ijust want toknow why?????????????

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)