February 2, 2009

በአክራሪዎች ላይ ፖሊስ ሁሉም ዓይነት መረጃ አለው


- በሞባይል መልዕክት የበተኑ ተለይተዋል
(ሪፖርተር):- የኃይማኖትን ስም ተገን በማድረግ ሕብረተሰቡን ለመበረዝ በሚንቀሳቀሱት አክራሪዎች ላይ ፖሊስ ሁሉም ዓይነት መረጃ እንዳለው አስታወቀ፡፡ ከግለሰብ ጀምሮ በቡድን ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያላቸውን ለሕግ እንደሚያቀርብ ተገል..ል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ የሕዝብ ጉዳዮችና ግንኙነት አገልግሎት ኃላፊ ኮማንደር ደምሳሽ ኃይሉ ለሪፖርተር በሰጡት መግለጫ “የኃይማኖት ነፃነት በተከበረበት አገር በሕገወጥ መንገድ ሕብረተሰቡን የማወክ ሥራ ሲሰራ ፖሊስ ዝም ብሎ አይመለከትም፡፡ ችግሩን በእንጭጩ የማስቀረት ሕገመንግሥታዊ አደራ አለበት”፡፡ከሕብረተሰቡ ጋር በሚደረግ ተደጋጋፊነት ያልተለየው ትግል ግለሰቦችና ቡድኖች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነ ኮማንደር ደምሳሽ ተናግረዋል፡፡ በኃይማኖት ስም ልዩነት የሚፈጥሩት አባላት እንዴት እንደሚንቀሳቀሱም አስረድተዋል፡፡

በተለያዩ ኃይማኖቶች እንደሚደረገው ሁሉ እነዚህ አክራሪ ቡድኖችም የስብከት ቅስቀሳ ያካሂዳሉ፣ ለቅስቀሳቸው የተለያዩ መንገዶችን ይከተላሉ፡፡ ፖሊስ እንደደረሰበት በኤስ.ኤም.ኤስ መልዕክት በመላላክ በተለያዩ ካሴቶች፣ በጋዜጣና በመፅሔት የመበረዝ ሥራቸውን እንደሚሰሩ ነው ኮማንደር ደምሳሽ ያስታወቁት፡፡ ኮማንደሩ አጠንክረው እንደገለፁት በሞባይል ስልክ መልዕክት ሲለዋወጡ የነበሩትና የመልዕክቶቹ መነሻ ምንጮች ሙሉ በሙሉ ታውቀዋል፡፡ ይህም በመሆኑ ፖሊስና ሕዝብ ባደረጉት ትብብር አንድም ችግር አልተፈጠረም፡፡

ወንጀል ለመሥራት እስከመደራጀት የደረሱ እንዳሉ የጠቆሙት ኮማንደር ደምሳሽ የሁሉም ዋና አጀንዳ በኃይማኖት ስም ብጥብጥ በመፍጠር የራሳቸውንና የቡድናቸውን የፋይናንስ አቅም ከፍ ማድረግ ብቻ ነው፡፡

ሁሉም የኃይማኖት ተቋማት የሌላውን ኃይማኖት ሳይነኩ የራሳቸውን ኃይማኖት ብቻ መስበክ እንዳለባቸው በኢትዮጵያዊያን ዛሬ የሚሰበክ አዲስ ትምህርት ሳይሆን በልዩነት ተስማምቶ መኖር ልዩ ቅርስ እንደሆነ ኃላፊው ገልፀው፣ ይህንን ልዩ እሴት ለማጥፋት ለሚንቀሳቀሱት ፖሊስ ፊት እንደማይሰጣቸውም አመልክተዋል፡፡

ኮማንደር ደምሳሽ ቁጥራቸውን በውል መግለፅ ባይፈልጉም በወንጀሉ አሉበት የተባሉ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ስለምርመራው ተጠይቀው መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ “በምርመራ ላይ ያለ ጉዳይ በመሆኑ ዝርዝር ጉዳይ ውስጥ አልገባም” ያሉት ኮማንደር ደምሳሽ ከታሰሩት መካከል ታዋቂ ግለሰቦች መኖራቸውን ባያስተባብሉም ይፋ አላደረጉም፡፡

የአንድ ኃይማኖት ተከታይን በሌላው ላይ የሚያነሳሳ ሲዲ፣ ካሴት፣ መፅሔትና መጽሐፍ የሚያሳትሙ ወደ ሕግ እንዲቀርቡ ፖሊስ እያጠናው እንደሆነ ታውቋል፡፡

ቀደም ሲል ራሳቸውን ካዋርጃ በሚል የሚጠሩ በጅማና ቤኒሻንጉም አካባቢ ተደራጅተው ሕዝብ ውስጥ በመግባት ዓላማቸውን ከማሰራጨታቸው በፊት ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት በአንድነት መደምሰሳቸው አይዘነጋም፡፡

ሰሞኑን የተሰማውን የኃይማኖት ልዩነት የመፍጠር ሙከራ ተከትሎ የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች መንግሥትንም እየወቀሱ ነው፡፡

“መንግሥት ለኃይማኖት በዓላት አላስፈላጊ ትኩረት እየሰጠ ነው” የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች “መንግሥትና ኃይማኖት የተለያዩ በመሆናቸው የኃይማኖት በዓላትን በመንግሥት መገናኛዎች ቀኑን ሙሉ ማስተላለፉን ይቃወማሉ”

የኃይማኖት በዓላት ሲከበሩ የቴሌቪዥን ጋዜጠኞች የኃይማኖቱን ልብስ ለብሰው ቀኑን ሙሉ የሚያስተላልፉት ዝግጅት ከጥቅሙ ጉዳቱ ማመዘኑን የጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎች “መንግሥት የኃይማኖት እኩልነትን ለማሳየት እያደረገ ያለው ልዩ እንክብካቤ ቢመረምር የተሻለ ነው” ብለዋል፡፡

ያልተጣሉ፣ ተጣልተው የማያውቁ፣ አብረው የኖሩ፣ አብረው እየኖሩ ያሉና ወደፊትም አብረው የሚኖሩ ሕዝቦችን በየአደባባዩ ፖስተር ላይ በመለጠፍ ሰው የማያስተውለውን ልዩነት በማስታወስ ለገንዘብ ሲሉ ማስታወቂያ በሚሰሩት ላይም መንግሥት ቁጥጥር ሊያደርግ እንደሚገባው አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል፡፡

3 comments:

Anonymous said...

ታዋቂ ግለሰቦች መኖራቸውን ባያስተባብሉም ይፋ አላደረጉም፡፡
Simachew yegeltsi ke-betekirstayan lijochi ke-hone chigeri endememeta bewekut yeshalali

Anonymous said...

awo,eslimina dirom yetesfafaw betorinet new.be egziabiher sim sewun megidel yatsedikal yemil hayimanot eslimina bicha new.be asia,seman africa yetaye yekirb gize tarik new.ye eslimina emnet teketayoch liyasibubet yigebal

Anonymous said...

Aayyi Mahibere Qudusan? tigermialesh!!! Be'wnetu bettaaam naw yedenqegn. Pente siyaqitish wa da eslamochu zorsh? weyy anchhiii.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)