January 29, 2009

የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እና የመንግሥት ባለሥልጣናት ውዝግብ

ጥር 15 ቀን 2001 ዓ.ም ከሠዓት በኋላ በቅዱስ ሲኖዶስ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፤ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ፣ የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር፣ የመንግሥት ኮሚውኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዲኤታና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና፣ ከአዲስ አበባ፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብና ከተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች የመጡ ሊቃነ ጳጳሳትና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከመንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ጠንካራ ውይይት አድርገዋል።
ሪፖርተር ጋዜጣ ቀንጭቦ ያቀረበልን ስብሰባ ጠቅላላውን ውይይት አልጠቀሰም። ባለ ሥልጣናቱ እንደለመዱት አባቶችን ንቀው እንደመጡ ምንም ጥርጥር የለውም። የለመዱት ነው። ፓትርያርኩ የመንግሥት ወገን ናቸው ተብሎ መገመቱ፣ መደምደሙ መቸም አልቀረም። ቤተ ክርስቲያናችን በተለይም በዘመነ ኢህአዴግ ግርማዋን፣ መታፈሯን፣ መከበሯን አጥታለችና እነ “ባለ ሥልጣን” አስፈራርተውም፣ አርፋችሁ ተቀመጡ ብለውም፣ “ወጣቶቹን ቲ-ሸርት ያላበሱትን አጋልጡ” ብለውም ለመሄድ ወስነው እንደመጡ ጥርጥር የለውም።
ውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደሚናገሩት “ወጣቱን በጥምቀት ሰሞን እንደዚያ ሆ! ብሎ እንዲወጣ ያደረገው ማን እንደሆነ አጋልጡ” የተባሉት አባቶች “ወጣቱን ማን እንደዚያ እንዳደረገው አናውቅም፤ እግዚአብሔር ያውቃል” ማለታቸው ተሰምቷል። “የክርስቲያን ደሴት እያሉ የሚጽፉትን ወጣቶች ማን ነው የሚያስተባብራቸው?” የተባሉት አባቶች በቀጥታ መልስ አልሰጡም። ጥያቄውን በጥያቄ የመለሱት ብፁዕ አቡነ ገሪማ “ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ ወዲህ ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት መሆኗን አቁማ ከሆነ ይነገረን” ማለታቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል። ብፁዕነታቸው መቸም እንዲህ ደፍረው መናገር ጀምረው ከሆነመ ቤተ ክርኢስቲያን ቀን እየወጣላት ነው ማለት ይቻላል።
ባለ ሥልጣናቱ ቤተ ክርስቲያንን ለማነጋገር የመጡት ቤተ ክርስቲያን ስለተዋረደች፣ በመቅደሷ ካህናቷ ስለ ታረዱ፣ ምእመናኗ ስለታረዱ አይደለም። ወይም አንድ ህሊናውን የሳተ አክራሪ ከመቅደሷ መጥቶ “አላህ ወአክባር” ስላለም አይደለም፤ የጥምቀት ስፍራዋ በባለጌ ባለሥልጣናት ተወርሶ ለመስጊዳቸውና መድራሳቸው መገንቢያ ስለተሰጠም አይደለም። እነርሱ የመጡት “የጎንደር ምእመን የጥምቀት ቦታቸውን በጉልበት ስልስከበሩ፣ ወጣቶች አርሞኒካቸውን ጥለው እያለቀሱ መዝሙር ሲዘምሩ ስለዋሉ፣ ያለምንም ፖሊስ ርዳታ በዓላቸውን በሥርዓት ስላከበሩ ነው። አባቶች እንደተናገሩት ከመቶ በላይ መጻሕፍት በአክራሪዎች ሲጻፉ ዝም ያለ መንግሥት፣ ለቁጥር የሚታክቱ የስብከትና የስድብ ሲዲዎች ሲበተኑ ዝም ያለ መንግሥት፣ ዐረቦችን አስደሰትኩ ብሎ የጠየቁትን ሁሉ እየሰጠ የልብ ልብ የሰጣቸው መንግሥት አሁን አባቶችን ማስፈራራት መጀመሩ ብዙም የሚገርም አይደለም።
ሪፖርተር እንደዘገበው “ቤተክርስቲያኗ ባስተላለፈችው መግለጫ ላይ፣ ከሕገ መንግስት ድንጋጌና ከሃይማኖታዊ ስነ ምግባር ውጭ በመንቀሳቀስ አንዳንድ ፀረ-ቤተክርስቲያን (አክራሪዎች) ከአዲስ አበባ ከተማ ጀምሮ በየክልሉ ባሉ ዞኖች እየፈፀሙት ያለው ተንኮልና ደባ እየሰፋ፣ እያደገና እየተጠናከረ ከመምጣቱ በፊት ከችግሩ አስከፊነት አንፃር በዳኝነት ታይቶ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስድ የሚያስችል አመራር ይሰጥ ዘንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳለፈውን ውሳኔና ማስረጃ በማያያዝ ጥቅምት 15 ቀን 2001 ዓ.ም ለሚመለከተው አካል አቤት” ስትል ብትቆይም አጥጋቢ ምላሽ አላገኘችም።
አባቶች በትክክልም እንደተናገሩት ለቤተ ክርስቲያን ከዚህ በላይ አስቸጋሪ ጊዜ ሊገጥማት አይችልም። አሁንም ሙሰሊሞችነጅ ባንጠላም አክራሪዎቹን ግን የምናፈቅርበት ምንም ምክንያት የለም። እንደነርሱ ለመግደል ባንነሣም የጎንደር ወጣቶች እንዳሉት “ለሃይማኖታችን ይፈሳል ደማችን”። የመንግሥት ስጋት ምነድነው? ሥልጣናቸው ናት። የሃይማኖት ነገር ከምንም የፖለቲካ ችግር በላይ አደገኛ እንደሆነ የተረዳው አይመስልም። ዛሬም ቅንጅትና አንድነት፣ ኦነግና ኦብነግ፣ ኢህአፓና ደርግ ወዘተ ወዘተ ናቸው ስጋቶቹ።

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)