January 28, 2009

የአባቶቻችንን ርስት ምን ያህል እንፈልገዋለን?

(በብርሃናዊት)

በዘንድሮው የጥምቀት በዓል ላይ: የተለያዩ ኢትዮጵያውያን "ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት" እና "የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም" የሚሉ ጽሑፎች የታተሙበትን ቲሸርቶች ለብሰው በዚህ ድረ-ገጽ ላይ ሳይ: ሁለት ዓይነት ስሜት ተሰማኝ::

1. የመጀመርያው ሕዝበ-ክርስቲያኑ ለእምነቱና የእምነት ሥርዓቱን በነጻነት ለማካሄዱ ምን ያህል ተቆርቋሪ እንደሆነና: ሙሉ ለሙሉ የእምነቱን ጉዳይ ችላ እንዳላለው: ምናልባትም እንደማይለውም ጭምር የተረዳሁበት ስለሆነ: አዎንታዊ ገጽታው ታይቶኛል::

2. ሁለተኛው ስሜቴ ግን: ሕዝበ-ክርቲያኑ ስሜቱ እንደሻከረና: በትንሹም በትልቁም ሊገነፍል የሚችል ስሜታዊነትን እንዲያዳብር በጽንፈኞች መደረጉን ሳይ የፈጠረኝ ስሜት ነው:: በእውነቱ መልካሙን መንፈሳዊነት የሚያደፈርስና የሚሠርቅ: የጨቅጫቃ መናፍቃንና የተንኳሽ ጽንፈኞች ፍላጻ የኢትዮጵያን ሕዝበ ክርስቲያን ወግቶ እስከዛሬ ሳይገድለው በመቅረቱ ጥበበ-እግዚአብሔርን እንዳደንቅ ተገድጃለሁ:: ሰአሊ ለነ ቅድስት የምንላት ድንግል ማርያም አሁንም በእኛ ተስፋ አልቆረጠችም::

ነገር ግን: አንድ ነገር ታሰበኝ:: ማለትም የአባቶቻችን ርስት ማለት ምን ማለት ነው? የት ነው ያለው? ለመኖር ከእኛ የሚፈልገው ምንድነው? 'ርስቴ ነው' ስንል ምን ማለታችን ነው? 'አልሰጥህም' ስንልስ ማንን ነው? ላለመስጠታችን መገለጫው ምንድነው? የምር አንሰጥም? እንፈልገዋለን?

እዚህ ላይ በዝርዝር እያንዳንዳችን ብንነጋገር ልዩነት ይኖረን ይሆናል::

ከመልስ ይልቅ ጥያቄዎችን ልጻፍና እስቲ በአእምሮዋችን እናመላልሰው?

የአባቶቼ ርስት የት ነው ያለው? ኢትዮጵያ ወንዞችና ተራሮች ላይ? ጋራው ሸንተረሩ ላይ? የቤተክርስቲያን አጥር ውስጥ? የቤተክርስቲያን ቅድስተ-ቅዱሳን ውስጥ? ታቦቱ ላይ? መስቀሉ ላይ? የቄሶቻችን ጥምጥም ላይ? መጻሕፍቶቻችን ውስጥ? የሃይማኖት ዶግማችንን የምንገልጽባቸው ጸሎት መጻሕፍቶች ላይ? የት ነው ያለው?

የአባቶቼ ርስት ለመኖር ምኔን ይፈልጋል? ጡንቻዬን? ብዛቴን? ፖለቲካዊ ኃይሌን? የኢኮኖሚ ዕድገቴን? የወዳጅ ሀገሮችን እርዳታ? ወኔዬን? ከሃይማኖቴ ውጪ ካሉት ሰዎች ጋር ተላትሜ ለክብሬ ስል ለመሞት ያለኝን ቁርጠኝነት? ወይስ ምኔን ይፈልጋል?

የአባቶቼ ርስት የእኔ ርስት የሚሆነው እንዴት ነው? የአባቶቼ ርስት ነው ስላልኩት? አባቶቼ ይኖሩ የነበሩበት ቦታ አዘውትሬ ስለምሄድ? አባቶቼ የተከሉትን አብያተክርስቲያናትና ገዳማት እስካሁን ካሉበት ሳይነቃነቁ አካላዊ ይዘታቸው እንዲጠበቁ በመርዳት? የአባቶቼ ርስት ስል አብርሃም አባት አለን እንደሚሉት አይሁድ ወይስ የአብርሀምን እምነትና ምግባር እየፈጸምኩ?

የአባቶቼን ርስት የማልሰጠውስ ለማነው? ለሌላ ሃይማኖት? ለሌላ ሀገር? የኔ ሃይማኖት ሰዎች የአባቶቼን ርስት ይዘውልኛል? ለእኔስ በትክክል አስረክበውኛል? አባቶቼ እንደአባቶቼ ናቸው? ወይስ እነሱም በየአጋጣሚው እንደአይሁድ አብርሃም አባት አለን እያሉ ነው? የአባቴን ርስት የሚወስዱብኝ ከቤተክርስቲያን ውጪ ያሉት ናቸውን? ጦርና ጎራዴ ይዘው በግዘፍ የሚመጡብኝ ናችውን? ወይስ በረቂቅ የሚመጡ ደግሞ ሌሎች ብዙ አሉ? ስንት ስንት አካፈልኩ ለእያንዳንዳቸው? ለረቂቃኑም ለግዙፋኑም? ለቤት ውስጦቹም: ከቤት ውጪ ላሉትም?

የአባቶቼንስ ርስት በርግጥ እፈልገዋለሁ? ለምን? ልኮራበት? ለቱሪዝም? ለማንነት መገለጫና ለታይታ? ለታሪክ ማሟሟቂያ? ለኢኮኖሚ ዕድገት? በዓመት አንዴ ከአለም የእረፍት ጊዜ ወስጄ ለማሳልፍበት ክብረ በዓል? ወይስ ከእግዚአብሔር ጋር ቀን በቀን: ደቂቃ በደቂቃ ሕይወት አድርጌ ልኖርበት? ለመንግሥቱ ልበቃበት? የርስቱ ርስትነት ለመኖርያ ነው ወይስ ለጊዜያዊ ተያዥነት? ሌላ ትርፍ ለማግኘት የብድር ማስያዣ ነው ወይስ የምበላው የምጠጣው በርሱም የምኖርበት እውነተና ሀብትና ሕይወት?

ሁላችንም አተኩረን ራሳችንን ልንጠይቅ ያስፈልገናል::

በርግጥም የአባቶቻችን ርስት ያስፈልገናል! ላንሰጠውም መሐላችንን ከየራሳችንና ከእግዚአብሔር ጋር ማጽናት አለብን::

ሰላም!

8 comments:

Anonymous said...

ሰ ላ ም የ እ ኔ ን የ አ ባ ቴ ን ም ሆ ነ የ እ ና ቴ ን ር ስ ት ደ ር ግ ሙ ል ጭ አ ድ ር ጎ ወ ስ ዶ ታ ል

Anonymous said...

ma?

Anonymous said...

Ayiiiii

Whatevr you think, you think of what you have in this world, yemotk!!!

Anonymous said...

the ortodox chritian are crying for the place which was given to muslims to build mosque or mesgid they have full right to do so but since fall of derge they are gettig radicalized just like serbian

Anonymous said...

IF yousay that in gonder the muslim youngesters will say no in harer';bale kefa so donot start what youcnnot finish

Anonymous said...

The Land Belongs to God [The self sufficient]

Instead of crying for land,I think if all the Orthodox Churches sell out the "Gold-made Crosses",the money earned could built SEVERAL INDUSTRIES in Ethiopia.
Did you see what Aba Paulos carried on his neck too? that's part of the wealth of the church. The Roman Catholic become enriched through sales of some fabricated pars of the Cross in the name of "buying a passport to Heaven", a few hundred years ago.
If you don't give what you love most to your brother/sister, you're not a believer- both Islam and Christianity preach.
Practically NIL
Every one fails to win its own 'ego'.

Anonymous said...

Ehh ahun gebagn you want to sell the crose to get money way do not you work hard.I know some muslims (like momhamed & missonery) did the same thing years ago to make themselves rich & to destroy history & you have that sprit todays too. But God was is & will be with us & thanks to those who hide all our identity & keeps to these days.
We will do our best to transfer to the next generation.

Anonymous said...

መአበል ከመጣ፡ የሚየቆመው ፡የለም
ኢትዮጵያ፡የክርስቲያን፡ደሴት፡ የሙ ስሊሞች ፡ባሕር፡ ናት!
ጥበብ ይናፍቀኛል፡
ተቻችሎ የሚኖር ሕዝብ የስቀናኛል፡
ድንቁርና ያስፍራኛል፡
ጦርነት የስጠላኛል፡
ከጸጋየ ገ/መ
የሃይማኖት መሪዎች ሀቀኛ ሚና አስፈላጊነት፡ ሀቅኛ መሪዎች ገንቢ ወቀሳን
በጸጋ ይቀበላሉ ከስሀተታችው ይማራሉ፤ ወገንተኝነትን፤ መንደርተኝነትን፤
ጠባብነትንና፤ ትምክህተኝነትን አጥብቀው ይዋጋሉ የወከላቸውንና የመረጣቸውን ህብረተስብ በሀቅ ያገለግላሉ።ፈጣሪን ይፈራሉ ፡መሬት፣ባሕር፡የሰ ው፡ልጅ፡የዱር፡አራዊት፡የመሳሰሉት፡በሙሉ፡የፈጣሪ፡ናቸው፡ብለው፡የምናሉ፡፡
ኢትዮጵያ ለሁሉም ይበቃል!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)