January 27, 2009

በጎንደር ለተቀሰቀሰው ግጭት መንግሥት ኃላፊነት አለበት

በጎንደር በጥምቀት ሰሞን የተፈጠረው ግጭት፣ መብረዱ ሲሰማ ውስጥ ውስጡን ግን በሁለቱም ወገኖች በኩል ያለው አለመተማመንና መቃቃር ግን የተዳፈነ እሳት እንዳይሆን እያሰጋ ነው። ለአንድ ሳምንት አህል የተዘጉ ሱቆች እየተከፈቱ ነው። ነገሩን ለማብረድ ፖሊሱንና ፌዴራሉን ያሰማራው መንግሥት መጀመሪያውኑ ችግሩ እንዲባባስ ማድረጉን በቅጡ የተገነዘበው አይመስልም። ይልቁንም በጅምላ መግለጫ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን መክሰሱ ደግሞ ሌላ ትልቅ ጥፋት ሆኗል።

ጎንደር ሐረር አይደለችም፣ ሞቃዲሾም አይደለችም። በተለምዶ “አርባራቱ ታቦት” የሚባለው የታቦት ብዛት የከተመባት፣ ለክርስቲያናዊ ምልክቷ ጽኑዕ አሻራ ያላት ከተማ ናት። ታዲያ እንዲህ ሆና ሳለ እንዴት የአክራሪነት ምልክት መታያና መገለጫ፣ ይባስ ብሎም ወሐቢአዊ እስልምና አንገቱን ቀና ቀና ያደረገባት ሥፍራ ልትሆን ቻለች?

ጎንደር ቁጥሩ ቀላል የማይባል ሙስሊም ኢትዮጵያዊ ይኖርባታል። ሰላማዊ ሙስሊም ስለሆነ ከክርሲቲያኑ ጋር አተካሮም፣ ግጭትም አያውቀውም ነበር። ይሁን እንጂ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ይህ ሰላማዊ ጠባዩ እየተቀየረ “ተንኳሽ”ና “ጸብ ጫሪ” በመሆን ላይ ይገኛል። ነገሩ ሲነሣ በመጀመሪያ “ለቀብር ቦታ ይሰጠን” በሚል የተነሣ እንደሆነ ምንጮች ያለፉትን አሥር ዓመታት በማስታወስ ለደጀ ሰላም ሪፖርተር ገልጸዋል።
ጥያቄያቸው ትክክለኛ ስለነበረ የሚገባቸው ቦታ ተሰጥቷቸው ሲኖሩ ነገሩ ከፈር እንዲለቅ ያደረጉት የአቶ መለስ ዜናዊ የቀኝ እጅ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን መሆናቸውን እነዚሁ ምንጮች ጠቁመዋል። አቶ በረከት ሙስሊሞች በከተማው እንዲሰጣቸው የጠየቁትን ቦታ ሁሉ፣ የከተማው ፕላን ከሚያዘው መስመር በመውጣት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲሰጣቸው በስብሰባ ላይ በቃል ብቻ በሰጡት ትዕዛዝ የተነሣው ፈር የለቀቀ አካሄድ ለሰሞኑ ግጭት ትልቅ አሉታዊ አስተዋጽዖ እንዳደረገ ምንጮቻችን መስክረዋል።
ነገሩ በድብቅ የተደረገ ሳይሆን አቶ በረከት በመሩት ብዙ ሕዝብ የተሰበሰበበት ስብሰባ ላይ የተደረገ ጋጠ ወጥ ውሳኔ ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ ሙስሊሞች “በቤተ ክርስቲያንና በክርስቲያኖች ተጨቁነናል” የሚለውን ስሞታቸውን ሲያቀርቡ ይህንን ፈርጁን ያልለየ አስተያየት በመድገም “አዎን እናንተን የጨቆነችው ቤተ ክርስቲያን ናት” በማለት በይፋ መናገራቸው ተሰብሳቢውን የልብ ልብ እንደሰጠውና ለአሁኑ ግርግርና ረብሻ መሠረት መጣሉ ታውቋል።
ክርስቲያኑ በደፈናው ለሙስሊሞች ቦታ አይሰጣቸው የሚል ችፍን ጥላቻ የለውም። ነገር ግን አሰጣጡ ሥርዓት ያለውና የከልርስቲያኑን ሃይማኖታዊ ማንነት የሚጋፋ መሆን የለበትም። ለምሳሌ የልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥምቀት ሥፍራን ካልጠፋ አካል ለሙስሊም መስጠት ምን ይባላል? በቅ/ገብርኤል አጥቢያስ ቁርዓን ለማስቀራት ሥፍራውን መስጠት ምን ይባላል?

ሙስሊም ወገኖቻችን በተለይም ውጪ ያሉት ይህንን ሁሉ ማገናዘብ አለባቸው። በደፈናው ክርስቲያኑን ለመቃወም መነሣት ምንም አይረባቸውም።

4 comments:

Anonymous said...

Good job now. Here you go and have to push that way not a simple report. And I wish to read the connection of Al Amoudi to the ongoing conflict in that Christian town. I know he secured a big land there to 'invest' but didn't start it yet except constructing the psychology of Muslim Minorities in the town. If you go that way too, you will find how Bereket and co are the catalysts. And do you know that a fanatic muslim was in his last phase of excuting his plan to bombard the Like Likawunt there? I feel guilty when I write this, but what can we do?

Anonymous said...

Open the lik below and listen what is happening on Muslims who lives in Gonder.


http://ethiopiajustice.blogspot.com/2008/12/ethiopia-gonder-muslims-under-siege.html

Anonymous said...

Mikir le denkoro

what ever you write or say you don't feel any responsiblity. actualy when does morons do take responsiblity you are the one. get life rather than propagating this fanatic ideas hear. Ethiopia Is a nation of All people all religion. most of you never read history book you claimed its a christian nation ...bla ...bla... since when it was christian island ? there was judaism befor christianity came as a gust. then islam followed like christianity...then pente who knows who will come tomoro but still called ethiopian religion. oooooo get life dont wast time...

Anonymous said...

IS THIS TRUE

VERY IMPORTANT ... every one should listen to this and...

http://amalethiopia.wordpress.com/

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)