January 14, 2009

ቪኦኤ የቤተ ክርስቲያን ወጣቶች በመዝሙር ብቻ ሰርጋችንን እንፈጽም ማለታቸውን ሲተች አመሸ


ታዛቢ (ከቨርጂኒያ)
አዲሱ አበበ እሑድ ጥር 3/2001 ዓ.ም ባዘጋጀውና ከመጋቤ አእላፍ መክብብ አጥናው ጋር ባደረገው ውይይት ወጣቶች በሰርግ ወቅት መዝሙር መዘመራቸው መስመር ያለፈ መሆኑን በመጥቀስ ወጣቶችን ሲተች አምሽቶዋል። ከሐጢአት ተመልሶ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ጋብቻውን ለመፈጸም የሚመጣውን ወጣት ገና ለገና ባህላችንን አልጠበቅህም እያሉ እነርሱ ያላደረጉትን፣ ያልዘሩትን ከሌላው መጠበቅ ትንሽ ያስገርማል።

ቪኦኤ “የፖለቲካውን ለፖለቲካው፣ የቤተ ክርስቲያንን ለቤተ ክርስቲያን” መስጠት መልመድ አለበት። በዚያን ዕለት መርሐ ግብሩ በዲሲና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ዝርያ ያላቸው ወጣቶች አስቀያሚ በሆነ የወንጀል ተግባር ላይ መሠማራታቸው የፈጠረውን ስሜት አንስቶት ነበር። እንዲህ ኢትዮጵያዊው ወጣት አለ እረኛ ተዘልሎ በተቀመጠበት ሁኔታ ከዚያ አምልጠው የመጡትን ለምን ዘመራችሁ ማለት ጭራሹኑ አስቂኝ፣ አናዳጅም ነው። ራሳችን በትውልዳችን ያልሠራነውን ይህ ትውልድ ከሠራው ከቻልን ማመስገን፣ ካልቻልን ላለመተቸት አንደበታችንን መሰብሰብ ጥሩ ይመስለኛል።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)