January 7, 2009

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ


«በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ ፣ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው» (ኢሳ9፡2)
በሰው ልጅ አዕምሮ ሲመዘኑ ይፈጸማሉ ተብለው የማይገመቱ ነገር ግን የተደረጉ በታሪክ መጻሕፍትም ላይ ሰፍረው የሚገኙ ብዙ ድንቅ ድንቅ ነገሮች አለ<፡፡ በተለይም በዘመናችን በሌላው ዘንድ ለመታወቅ ካላቸው ጥማት የተነሳ አንዳንድ ሰዎች የማይወጡት ዳገት ፣ የማይወርዱት ቁልቁለት ፣ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡


ነገር ግን በመንፈሳዊ ዓለም የተፈጸመውንና በኅሊና ከማመላለስ በልቡናም ከማሰብ በላይ የሆነውን የሥጋዌን (የእግዚአብሔር ሰው መሆን) ምስጢር የሚያህል ግን ተከስቶ አያውቅም፡፡ ወደፊትም አይኖርም፡፡ በዚህም ሰው የመሆን ምስጢር ልቡናቸው የተነካ አበው «እግዚአብሔር ሰውን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ሰውን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል» ብለዋል፡፡

አባ ኤፍሬምም #ይህንን ድንቅ እዩ ፣ ስለተገለጠልንም ምስጢር ምሥጋና አቅርቡ፡፡ ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና ፣ ቃል ተዋሕዷል“ ፣ ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ ፣ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት›› (ውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ) ብሎ ድንቅነቱን ገልጿል፡፡ ይህንን የተዋሕዶ ምስጢር ለማወቅ ልቡናችንን እንክፈት፡፡ በመንፈሳዊ ዓይን በንጹሕ ልቡና ነገረ ልደቱን እንመልከት፡፡ የቅዱሳት መጻሕፍትንም ምስክርነት በጥሞና እንከታተል፡፡

1. ትንቢትና ምሳሌ

እግዚአብሔር ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ በመልካሙ ሥፍራ በኤደን ገነት አኖረው፡፡ በዚህም ሳያበቃ የበለስን ፍሬ እንዳይበላና እንዳይሞት ትእዛዝ የመጠበቅን ሕግ ሰራለት (ዘፍ2፡17)፡፡ ነገር ግን የጠላታችን ዲያቢሎስን ምክር ተቀብለው የእግዚአብሔርን ፍቅርና ትዕዛዝ እምቢ ብለወ< ፣ አማልክት እንሆናል የማለት ስሜት ስላደረባቸው ዕፀበለስን በልተው ፣ ትእዛዙን አፈረሱ፡፡ መርገምም ወደkባቸው፡፡ ምድርም የበረከት ቦታ መሆኗ ቀርቶ የመርገም ሥፍራ ሆነ‹፡፡ እሾህና አሜኬላ በቀለባት (ዘፍ3፡17-19)፡፡ በአዳምና በሔዋን በልጆቻቸው ሁሉ ሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ ፣ ርደተ መቃብር ገሃነም ተፈረደባቸው፡፡ ንስሐ ገብተው ቢለምኑት ኃጢአተኛ መመለሱን እንጅ መጥፋቱን የማይፈልግ እግዚአብሔር አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጻም ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው ቃል ገባለት፡፡ ይህንን የተስፋ ቃል በመጠበቅ አባቶች ሁሉ በጾምና በጸሎƒ ፣ በእንባና በኃዘን ዕድሜአቸውን አሳለñ፡፡

አበ ብዙሃን አብርሃም (በዘርዕከ ይትባረኩ ኰሎሙ አሕዛብ ምድር- በዘርህ አሕዛብይባረካሉ›› (ዘፍ12.3) የሚል የተስፋ ቃል በመያዝ በዘመኑ ሁሉ አምላካዊ ቃል እውን መሆን ሲጠባበp ፣ እግዚአብሔርን ደጅ ሲጠና ቆየ፡፡

ዘመነ አበው ተፈጽሞ ዘSነ መሳፍንት ሲጀምር የእግዚአብሔርን ሰው መሆን በመጠባበቃቸው ገፉበƒ፡፡ ሊቀ ነብያት ሙሴ (ነቢየ ያነሥ ለክሙ እግዚአብሔር እምአኃዊክሙ ዘከማየ ወሎቱ ስምዕዎ- እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ መሃከል እንደኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋM፡፡ እርሱን ስሙƒ›› በማለት አስተምሯል (የሐዋ7፡36፤ ዘዳ 18፡15)፡፡ ምሳሌውን በነበልባልና በሐመልማል አምሳል አይቷልና (ዘጸ3፡1)፡፡ በዘመነ ነገሥትም ነቢየ ልዑል ዳዊት እግዚአብሔር በይሁዳ ወዐብየ እግዚአብሔር በእስራኤል- እግዚአብሔር ታወቀ ስሙም በእስራኤል ከፍ ከፍ አK›› (መዝ 75፡1) ብሎ የዘመናት ግድግዳ ሳይከለክለው የክርስቶስን ምስጢር ተናግሯል፡፡
ልዑለ ባሕርይ አምላክ በቤተልሔም ከተማ በበረትእንደሚወለÉ ፣ በጨርቅም እንደሚጠቀለል ሲያጠይቅ ‹‹ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ ወረከብናሁ ውስተ ዖመ ገዳም- በኤፍራታ ሰማነው በዱር ውስጥም ›ገኘነው›› ብሏል (መዝ 131፡7)፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ዕዝራም ‹‹ወናሁ እሬኢ- ነፋስ ዐቢይ ይወፅእ እምውስተ ባሕር- ታላቅ ነፋስ ከባሕር ሲወጣ አየሀ<›› ብሎ የሥጋዌን ምስጢር ገልጾ አስረድቷል፡፡ ባሕር የእመቤታችን ፣ ነፋስ የጌታ ምሳለ?ዎች ናቸው (ዕዝራ ሱቱኤል 12፡2)፡፡ እነዚህ ደጋግ አበው በምሳሌ ያዩትን ኢሳይያስ ነቢይ አብርቶ አጉልቶ ‹‹ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ፣ ወትሰይሚዮ ስሞ አማኑኤል- እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች›› ብሎ ገልጦ መሰከረ (ኢሳ7፡14)፡፡ የእግዚአብሔር ሰው ሚክያስም መሲሑ የሚወለድበትን ሥፍራ ሲመለከት ‹‹ወአንቲኒ ቤተልሄም ምድረ ኤፍራታ ፣ ኢትሐፅፂ እመሳፍንተ ይሁዳ፤ እስመ እምኔኪ ይወፅዕ ንጉሥ ዘይርዕዮሙ ለሕዝብየ እስራኤል፤ አንቺ ቤተልሄም የኤፍራታ ምድር ፣ ከይሁዳ አለቆች ከቶ አታንሺም ፣ ወገኖቼ እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና›› ብሏል (ሚክ5 ፣ 1-3)፡፡ ትንቢቱ ተነገረ ሱባዔውም ተቆጠረ እግዚአብሔርም አንድያ ልጁን የሚልክበት ወቅት ደረሰ


2. ብሥራት

የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በቤተ መቅደስ ወደምትኖር ወደ ድንግል ማርያም ተላከ፡፡ እመቤታችንንም ‹‹ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ›› ብሎ አበሰራት፡፡ ትህትናዋ የተመሰከረላት እመቤትም ‹‹ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው›› ብላ ራሷን ዝቅ አደረገች፡፡ ‹‹ትጸንሻለሽ›› ሲላትም ‹‹ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል;›› ብላ ንጽህናዋን ገለጠች፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም እንዳያሳዝናት ከፈጣሪው ታዟልና ለማመን በመዘግየቱ ‹‹ድዳ ትሆናለህ›› እንዳለው እንደ ዘካርያስ ሳይሆን የዘመዷን የኤልሳቤጥን ታሪክ በምሳሌነት ጠቅሶ አስረዳት፡፡ ለማረጋገጫም ‹‹እስመ አልቦ ነገር ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር›› ባላት ጊዜ የእምነት እናት ናትና‹‹ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ- እንደ ቃልህ ይሁንልኝ›› ብላ በእምነት ተቀበለች (ሉቃ1 ፣ 26-38)፡፡ ወድያውም ከሦስቱ አካል አንዱ አካል ወልድ ከአብ ከመንፈስ ቅዱሰ አንድነት ሳይለይ ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ በማኅጸኗ አደረ፡፡ እመቤታችን ትሕት“ ፣ ንጽሕና እና እምነት ይዛ እንደተገኘች የርሷ ልጆች ምዕመናንንም ይህንኑ ገንዘብ ልናደርግ ይገባናል፡፡

3. እግዚአብሔር ሰው ሆነ
ወልደ እግዚአብሔር መድኃኔዓለም የሰውን ሥርዓት ይፈጽም ዘንድ በእናቱ ማኅጸን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ተቀመÖ፡፡ ከሁለት አካል አንድ አካል ፣ ከሁለትባሕርይ አንድ ባሕርይ ሆኖ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በዘመነ ሄሮድስ በቤተልሔም ከተማ በከብቶች በረት ፣ በእኩለ ሌሊት ፣ በአጭር ቁመት ፣ በጠባብ ደረት ተወስኖ ተወለደ (ማቴ2፡1፤ ሉቃ 2፡1-7)፡፡ ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ በራእዩ እመቤታችን ጌታን ስለመውለዷ ሲያስረዳ ‹‹አሕዛብን ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ ወለደ‹›› ብሏል (ራእ12፡5)፡፡ ነቢየ ልዑል ኢሳይያስ አስቀድሞ ‹‹ሕፃን ተወልዶልናልና ፣ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል“ ፣ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናልና ፣ ስሙም ድንቅ ፣ መካ` ፣ ኃያል አምላ¡ ፣ የዘላለም አባት ፣ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራM›› ያለው ቃል ተፈጸመ (ኢሳ9፣6)፡፡

ጌታ የተወለደው እንደ ሰው ልማድ ሳይሆን ቃል ከአብ ያለድካም ወጣ ፣ ከድንግልም ያለ ሕማም ተወለደ ፣ በመወለዱም ድንግልናዋን አልለወጠውም ፣ ሰው በመሆኑም አምላክነቱ አልተለወጠም ፣ ይህም ድንቅ የተዋሕዶ ምሥጢር ነው፡፡

4. ስለልደተ ክርስቶስ የአበው ምስክርነት
ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆን ፣ ስለ ጌታችንም በመልእክቱ በሰፊው አስተምሯል፡፡ አባቶቻችን ተስፋ ያደረጉት በማን መሆኑን ሲናገር ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነወ<›› ብሏል (ሮሜ 1፡3-5)፡፡ የገላትያን ምዕመናንንም ሲመክር ‹‹የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ፣ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ›› ብሏል (ገላ1፡4)፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም በመልእክቱ ‹‹ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን ፣ በዓይኖቻችንም ያየውን ፣ የተመለከትነውንም ፣ እጆቻችን የዳሰሱትን እናወራለን›› በማለት በመካከላቸው ስለተመላለስው አብረውት ስለበሉት ስለጌታ በበለጠ ሲያስተምርም ‹‹ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን ፣ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የገለጠውንም የዘላለም ሕይወት እናወራላችኋለን›› ብሏል (1ኛዮሐ1፣1-3)፡፡
የሐዋርያትን መንገድ የተከተሉ አባቶችም በትምህርታቸው ይህንን የተዋሕዶ ትምህርት አስፍተውና አምልተው አስተምረዋል፡፡ ለአብነትም የሐዋርያት ደቀ መዝሙር ፎስጢኖስ ‹‹ክርስቶስ ቅድመ ዓለም የነበረ ሲሆን የሰውን ልደት ተቀበለ›› ሲል የአቴናው ኤጲስ ቆጶስ ዲዮናስዮስም ‹‹በፍጻሜው ዘመን ኢየሱስ ክርስቶስ በድንግል ማርያም ማኅፀን አደረ ድንቅ በሚሆን ምስጢርም ተወለደ›› በማለት ነገረ ልደቱን መስክሯል፡፡ ጎርጎርዮስ ገባሬ ተአምራትም ‹‹ከአባቱ ሳይለይ ከባሕርዩ ሳይለወጥ ከቅድስት ድንግል እመቤታችን ሥጋችንን ነስቶ የለበሰ (ሰው የሆነ) ይህ ነወ<›› ብሏል፡፡

5. ሰው በሆነው አምላክ ያለን እምነት
ኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ መጽሐፍን ቃል እንዳልጠነቀቁ ሰዎች ከብር ይግባውና አምላክ ቅዱሱን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጡር ወይም ከአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ዛሬ የሚማልድ አልያም ሩቅ ብእሲ ብላ አታምንም አታስተምርምም ነገር ግን አባቶቻችን እንዳስተማሩት ቅዱስ መጽሐፍም እንዳረጋገጠው
ሀ. ‹‹ከሰማይ ወርዶ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከእመቤታችን ሥጋን ተዋሕዶ ሰው መሆኑን›› (ሠለስቱ ምዕት)
ለ. ‹‹ቅድመ ዓለም ከአብ ፣ ድኅረ ዓለምም ከእመቤታችን የተወለደ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን›› (ቅ/ አትናቴዎስ)
ሐ. ‹‹ለወልደ እግዚአብሔር ሁለት ልደት እንዳለው ይኽውም ቅድመ ዓለም ከአባት ያለ እናት ድኅረ አለም ከእናት ያለ አባት መወለዱ”›› (ቅዱስ ባስልዮስ )
መ. ‹‹ቃል ሥጋ መሆኑን ነውር በሌለበት ማኅፀን ሥጋን እንደተዋሐደ ዳግመኛም በጌትነቱ የሚኖር እርሱ በጎል (በበረት ) መጣሉን ፣ ሥጋንም ሳይዋሐድ አይዳሰስ የነበረ ወልድ ዛሬ ሥጋን በመዋሐድ መዳሰሱን ፣ የኃጢአትንም ማሠሪያ የሚቆርጥ እርሱ በጨርቅ መጠቅለሉን›› (ቅ/ ዮሐንስ አፈወርቅ)
ሠ. ‹‹ንጽሕት ድንግል ማርያምም እግዚአብሔርን በሥጋ እንደወለደች›› (ቅዱስ ቄርሎስ) እናምናለን፡፡

6. ማጠቃለያ

በአጠቃላይ የልደትን በዓል በምናከብርበት ወቅት ከላይ የጠቀስናቸውን ዋና ዋና ነጥቦች ማጤን እንደሚገባን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ አይሁድ መሲሑ እንደሚመጣ እያወቁ የሚወለድበትንም ቦታ ለሰበዓ ሰገልና ለሄሮድስ እያመለከቱ እነርሱ ግን ከመዳን እንደዘገዩ ሁሉ እኛም በዓሉን በበዓልነቱ ብቻ እያከበርን ከንስሐና ከሥጋ ወደሙ በመራቅ ከሕይወት መንገድ እንዳንወጣ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ይሀንን የተዋሕዶ ምሥጢር ለመረዳት ዘወትር በቤተክርስቲያን በመገኘት ቃለ እግዚአብሔርን መማር ይገባናM፡፡

እግዚአብሔር አምላክ በተዋሕዶ ሃይማኖታችን ፣ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናችን ያጽናን፤ አሜን፡፡No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)