December 31, 2008

ተዋሕዶ = ኢትዮጵያ: ኢትዮጵያ = ተዋሕዶ

Dear Dejeselamaweyan,
Selam all. Here you have an article contributed by our new blogger Berhanawit. We thank our sister for joining us in blogging for the Church, and about the Church. We invite other children of Tewahedo to join us.
Cher Were Yaseman,
amen.
+++
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማህበረ ቅዱሳንና በሌሎች ድረ-ገጾች ላይ በአክራሪ ሙስሊሞች የተፈጸመውን ቤተክርስቲያን ቅጽረ-ግቢ ጥሶ ገብቶ እስላማዊ አምልኮ ሥርዓት የመፈጸም ድርጊት አብዛኞቻችን አንብበናል: ወይም ከሌሎች ሰምተናል ብዬ እገምታለሁ:: ይህን ጽሁፍ እንድጽፍ ያስገደደኝ በቅርቡ www.cyberethiopia.com/warka4 ላይ በጉዳዩ ዙርያ የተለያዩ ተሳታፊዎች የጻፉትን አስተያየት ሳነብ ነው::

ብዙ የፕሮቴስታንትና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች አስተያየታቸው የሰጡ ሲሆን በፎረሙ ላይ እንደታዘብኩት ኦርቶዶክሳውያን ቤተክርስቲያናቸው ውስጥ እንዲህ ያለ ድርጊት ሲፈጸም ደስ እንደማይላቸው ቢገልጹም 'ለምን ሙስሊሙ ቤተመቅደስ ገብቶ የራሱን አምልኮ ፈጸመ" የሚለው ጥያቄ ግን መነሳቱን በራሱ አልወደዱትም:: ምክንያቱም:

"ጥያቄውን ማንሳትና ለውይይት ማቅረብ በራሱ ተቻችሎ መኖር የለመደውን የኢትዮጵያ ሙስሊምና ክርስቲያን መሀል የሚፈጠር 'ጸብ-ጫሪነት’ ነው”

ነበር ምላሻቸው::

የእስልምና እምነት ተከታዮች ግን በጉዳዩ አስተያየት ከመስጠት የታቀቡ ይመስላል:: ቢሆንም: በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ: በዝምታም ሆነ በቃል: በአክራሪ እስልምና አነሳሽነት የሚፈጸሙ ህገ-ወጥ ድርጊቶችንም ሆነ የሰው ንብረትና ሕይወት ላይ አደጋ የሚያደርሱ ጥቃቶች ላይ ያላቸው አመለካከት እንዲህ የሚል ድምጸት አለው:-

"እንዲህ አይነት ድርጊቶችን የሚያደርገው ከ CIA ጋር እጅና ጓንት የሆነው የክርስቲያኑ መንግሥት ነው:: በአክራሪነት ስም እስልምናን መዋጋት ሲፈልጉና የእስልምና እምነት ተከታዮች ቁጥር በፍጥነት በዓለማችን ላይ እየጨረ መምጣቱን ሲገነዘቡ: ራሳቸው የሆነ ጥቃት ያቀናብሩና 'አክራሪ እስላሞች ፈጸሙት' ብለው ስም ያጠፋሉ"

በማለት ይከሳሉ:: የአርሲንም ሆነ የጅማን: ወይም የሐረርና የጎንደሩን አይነት የሰው ህይወት መጥፋት ደረጃ የደረሰ ግጭት በእስልምና እምነት ተከታዮች መፈጸሙን አስመልክቶ ገፋ ያለ ጥያቄ ሲቀርብላቸው ሁለት ዓይነት ምላሾች የማቅረብ አዝማሚያ ይታይባቸዋል:-

1. እንዲህ ዓይነት ድርጊት ለመፈጸሙ ማስረጃ የለም:: ማስረጃ እስካላየሁ ድረስ አላምንም::

2. (ድርጊቱ መፈጸም አለመፈጸሙን ወደጎን በመተው) ...በታሪክ ውስጥ በሃይማኖት ስም ከፍተኛ እልቂት ያደረሰው ክርስትና ነው እንጂ እስልምና አይደለም:: ምሳሌ- የመስቀል ጦርነት......

በማለት ድርጊቱ እምብዛም ትኩረት ሊሰጠው የማይገባ የ"ክርስቲያን አክራሪዎች" ወይም እየተለየ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ሙስሊሙን ለማስወጋት የሚያደርጉት አድራጎት እንደሆነ ለማሳየት ይሞክራሉ::

በእስልምና እምነት ተከታዮች ይህ አመለካከት ቢያዝ የሚደንቅ አይደለም:: ምክንያቱም የእምነቱ ተከታዮች እንደመሆናቸው መጠን የሃይማኖታቸውን ስም መጠበቅና ክሶቹንም መከላከሉ ላይ ማተኮራቸው የማይቀር ነው:: ከዚህ ወጥቶ ባልተዛባና ባልተንጋደደ አእምሮ ሁሉን መርምሮ ትክክለኛ አስተያየት ለመስጠት እጅግ ብርቱና በራሱ ይሚቆም አእምሮ ያስፈልጋል::

ፕሮቴስታንቶች በድርጊቱ በእጅጉ የተደሰቱ ይመስላል:: ከሚሰጧቸው ምላሾች ብቻ ከተለያዩ ነጥቦች አንጻር ድርጊቱ እንዳስደሰታቸው መመልከት ይቻላል:: ከነዚህ ነጥብች መሃል ጥቂቶቹ:-

1. ድርጊቱ መፈጸሙ ቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ ኃይሏን እንዳጣች ያሳያል::

2. ቤተክርስቲያን እኛ ብቻ ሳንሆን ሌላው ወገንም ጠልቷታል: ስለሆነም ሽንፈቷን አምና መቀበል የምትደርስበት ደረጃ ላይ እየደረሰች ነው::

3. "ለምን ይህ ድርጊት በቅጽሬ ተፈጸመ" ብላ ክስ መመስረቷ በራስ መተማመን እንደጎደላት ያሳያል:: አጋጣሚውን ተጠቅሞ ሙስሊሙን የመስበክ ሥራ አለመሠራቱ የሐዋርያነት አገልግሎት በቤተክርስቲያኒቱ ትኩረት የማይሰጠው መሆኑን ያሳያል::

4. ቦታዬ ላይ መናፍቅ ጉባዔ አያካሂድበትም: አይቀበርበትም ስትል የነበረችው ቤተክርስቲያን አሁን የራሷ ቅጽር ግቢ በሌሎች ሲደፈር "በሠፈሩት ቁና መሠፈር አይቀርም: ለጌታም ጌታ አለው ሆኖባታል" የሚሉ አይነት አስተሳሰቦች ናቸው::


የበለጠ ያስገረመኝ: የሳበኝና እያንዳንዳችን ትኩረት ልንሰጥበትና ልናስብብበት ይገባል ብዬ የማምነው ግን በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችም ይሁን በሌሎች የተሰጡትን አስተያየቶች ሳይሆን mainstream attitude የያዘ በሚመስለው የተማረው ኦርቶዶክሳዊ የሚሰጠው አስተያየት ላይ ነው:: በዚህ ሙስሊሙ በቅጽረ-ቤተክርስቲያን ገብቶ በመስገዱ ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሃይማኖታዊ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ በፎረሙ ከተደረጉ ውይይቶች በመነሳት ይህ ቡድን ያለው አመለካከት ምን እንደሆነ ለመታዘብ ያቅሜን ያህል ሞርክሬያለሁ:: እጅግ በጣም የሚገርመውና እኔንም በግሌ ያሳሰበኝ ጉዳይ ቤተክርስቲያን አዘውትረው ከሚመላለሱ ኦርቶዶክሳውያን ውጪ የሆኑ: ነገር ግን ኦርቶዶክስነታቸው ካልካዱ ብዙ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ያለው አመለካከት ከፕሮቴስታንቶች ጋር አንድ አይነት የመሆን ዝንባሌ ማሳየቱ ነው::

እነዚህ ቡድኖች እነማን ናቸው? የበለጠ ገለጻ የሚያስፈልገው ይመስለኛል:-

1. እነዚህ ወገኖች በአእምሮዋቸው ያለችው ኢትዮጵያ "በነፍጠኛ/ፊዩዳል" አማራ ለረጅም ጊዜ ስትገዛ ቆይታ አሁን "የብሔር ብሔረ-ሰብን መብት አክብራ ነጻ የወጣችው" ኢትዮጵያ ናት:: ስለሆነም በደርግና በኢህአዴግ ዘመን በተቀናበረ መልኩ ስላለፉት የኢትዮጵያ ዘመናት አስከፊነትና ስለሕዝቧም አክራሪ ወግ አጥባቂነትና አላዋቂነት ሲማሩ የኖሩ ናቸው:: በአጭሩ የተሳከረ አካዳሚክስ ሰለባ ናቸው::

2. እነዚህ ወገኖች ከላይ በተጠቀሰው አመለካከታቸው ሳቢያ በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከሌሎች እምነቶች የሚደርስ ማንኛውም የቃላትም ሆነ የድርጊት ጥቃት ባለፉት ዘመናት ቤተክርስቲያኗ በሃገሪቱ ላይ የነበራትን "አላግባብ የሆነ የበላይነት" ማካካሻና የዞረውን ድምር ማብረጃ ሽሮ ፍትፍት ነው:: ስለሆነም ባሁን ጊዜ ከሌሎች የእምነት ድርጅቶች የሚደርስባትን ጥቃት ቤተክርስቲያኗ እንደፍጥርጥሯ ሆና ትወጣው እንጂ ለምን ይህ ሆነ ብላ የሕግ ከለላነትን መጠየቅ የለባትም የሚል አስተሳሰብ አላቸው:: እየደረሰ ያለው ጥቃት ቤተክርስቲያኗ በጨዋታውና በሃይማኖት ማስፋፋት ፉክክሩ ሜዳ ላይ ኳሱን በደንብ ተቆጣጥራ ለመጫወት ያላት የብቃት ማነስ ውጤት ስለሆነ “ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ" አይነት ሁኔታ ላይ ነው ያለችው- ችግሯ ይህ ነው: ብለው ያስባሉ::

3. እነዚህ ወገኖች ርዕዮተ-ዓለማቸው በሚገባ በቅርበት ቢጠናና ቢገመገም አብዛኞቹ የማርክሲዝም ሌኒኒዝም አመለካከት ተከታዮች ናቸው:: በእነዚህ ሰዎች ዘንድ ባህል: ማንነት: እምነት: ሃይማኖት: ወ ዘ ተ.... በቃላት ተከሽነው የሚቀርቡና የኪነጥበብ ማዋዣ የሆኑ ቅመሞች ከመሆን ያለፈ መሬት የሚነካ ትርጉም የላቸውም:: ስለሆነም ለነዚህ ሰዎች ዘለዓለማዊ ሕይወት: ተጋድሎ: ለእምነት የሚከፈል መሥዋዕትነት ወዘተ. በእያንዳንዱ እምነት ውስጥ ባሉ "አክራሪዎች" እና "ወግ አጥባቂዎች" የተፈጠሩ ሕዝብን የማጋጫ አስተሳሰቦች ናቸው:: ለነርሱ የመንፈሳዊነት መለኪያው ከሁሉ እምነቶችና አመለካከቶች ጋር ሊስማማ የሚችል አንድ የግል ፍልስፍና ለራስ አጽድቆ በራስ የሃይማኖት መመርያ በአእምሮአዊ (እውቀታዊ) ብቃት መኖር ነው:: በዚህ መመዘኛ ሲታይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንም ፈተናውን ትወድቃለች (መንፈሳዊት: ሕይወታዊት: አማናዊት እንጂ ሃሳባዊት: ፍልስፍናዊት: ወይም ጊዜውን ተከትላ አስተሳሰቦችን የምትፈጥር ዘመናዊት አይደለችማ?!) ስለሆነም እርሷም አስተሳሰቧን መለወጥ ይገባታል: ሁሉን ያቀፈ ተራማጅ እምነት ልትፈለስፍ ይገባታል- የሚል አስተሳሰብ አዳብረዋል::

4. እነዚህ ወገኖች በአብዛኛው የሚድያና የኪነጥበብና ዝንባሌ ያላቸው ናቸው:: ስለሆነም በሚድያና በኪነ-ጥበብ መልእክቶች ተጽዕኖ ሥር የማይወድቅ ምናልባት በገዳም ብቻውን የሚኖር ካልሆነ በቀር ሌላ ስለሌለ አብዛኛው እንደዕለት-ተለት ሕይወቱ ተዋሕዶን የማይኖረው (Non-practicing) ኦርቶዶክሳዊ ክፍል አስተሳሰቡ ምን እንደሆነ ሊያሳይ የሚያስችል ቡድን ነው:: እንደእኔ እንደእኔ በዚህ የአመለካከት ፈተና እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ screen ብናደርገው ስንት እንዲህ አይነት ቸልተኛ አመለካከት ያልቀላቀሉ ኦርቶዶክሳውያን እናገኛለን? ይህን ያህል ለማለት ይከብደኛል: ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ- ከ43.5% ቢያንስ በግማሽ ያህል እንደሚያንስ:: የቀረው ተግባራዊ መንፈሳዊ ሕይወት የሚኖረው (practicing) ኦርቶዶክሳዊስ በዚህ አመለካከት ተተብትቦ ይሆን መንፈሳዊነቱ አላድግ ያለው?

5. የበለጠ አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ በፖለቲካው መድረክ (በገዢው ፓርቲም ሆነ በተቃዋሚው ዘንድ) ቦታ ይዘው በብዛት የሚንቀሳቀሱት እነዚሁ ዓይነት አመለካከት ያላቸው ወገኖች መሆናቸው ነው:: የዘመኑ ፖለቲካ ከላይ እንደጠቀስነው አይነት ከሁሉ ጋር መስማማት የሚችል አስተሳሰብ ያዘለ አመለካከት ማዳበርን እንደዋንኛ የፖለቲካ ብቃት መገምገሚያ መሥፈርት አድርጎ ይመለከተዋል:: ነገር ግን በዘመናችን ርዕዮተ አለሟን ለሁሉም ሃይማኖቶች ወለል አድርጋ የከፈተች ሀገር አለች? በእውነቱ ሀገር የሁሉም እምነቶችና የሁሉም አይነት ፖለቲካዊ እሳቤዎች ቤት መሆን ትችላለች? ሀገር የማን መሆኗ መጀመርያ ሊበየን አይገባውም? ኢትዮጵያ የማናት? ኢትዮጵያን ማን ሰራት? ለዚህ ደፋር መልስ መስጠት ቤተክርስቲያኒቱ ካልቻለች ጥቂት አሥርት አመታትን አትዘልቅም:: በቤተክርስቲያኗ ጠንከር ያለ የማስተማር: የመረጃ ሥርጭትና የአካሄድ አብዮት ካልተደረገ በቀር በቀጣይነት በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ የምናየው ሥርዓት ከእስካሁኑ ማርክሲሳዊ አስተሳሰብ የተለየ ሆኖ ኢትዮጵያዊና መንፈሳዊ ሊሆን አይችልም:: ያለመንፈሳዊነቷ ኢትዮጵያ ምንም ከለላ የላትም:: ኢትዮጵያ ያለሃይማኖቷ ምንም ናት:: ቤተክርስቲያንን ከኢትዮጵያ: ኢትዮጵያን ከቤተክርስቲያን ነጥሎ መመልከት አደጋው ከላይ እንደጠቀስነው ያለ mainstream የምንፍቅና አስተሳሰብ በኦርቶዶክሳውያን አእምሮ ውስጥ ማሳደግ ነው::

ካሁን በኍላስ ከስህተታችን አንማርም?

ይቆየን!


5 comments:

Warkawit said...

How are you doing Birhanawit? it is nice to see u again. lol! By the way, I can't read the Amaharic part. Is there anything i have to do? I mean I have Amaharic font in my PC. I don't know why it didn't display it. Anyways, I hope we will learn something important and fair from Deje Selam.

Warkawit

Unknown said...

Dear Warkawit,
Nice to see you here at Deje Selam. Please join Birhanawit in blogging here.
Cher Were Yaseman,
Deje Selam

SABALI said...

Hello,
I would really like to read what is written and to participate as well. Unfortunately, I couldn't read the amharic font. Could you tell me how I can view the Ge'ez fonts please?

thanks

Anonymous said...

To read the Amharic fonts, you can download Geez fonts from this website:
http://members.lycos.co.uk/geezunicode/

Unknown said...

Blogger Warkawit said...

How are you doing Birhanawit? it is nice to see u again. lol! By the way, I can't read the Amaharic part. Is there anything i have to do? I mean I have Amaharic font in my PC. I don't know why it didn't display it. Anyways, I hope we will learn something important and fair from Deje Selam.

Warkawit

January 01, 2009
Delete
Blogger ደጀ ሰላም said...

Dear Warkawit,
Nice to see you here at Deje Selam. Please join Birhanawit in blogging here.
Cher Were Yaseman,
Deje Selam

January 01, 2009
Delete
Blogger lonebis said...

Hello,
I would really like to read what is written and to participate as well. Unfortunately, I couldn't read the amharic font. Could you tell me how I can view the Ge'ez fonts please?

thanks

January 01, 2009
Delete
Anonymous Anonymous said...

To read the Amharic fonts, you can download Geez fonts from this website:
http://members.lycos.co.uk/geezunicode/

January 01, 2009

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)