October 30, 2008

የድሬ ሼከና ሁሴን መስጊድን በዓለም ቅርስነት ለማስመዘገብ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ነው


Saturday, 25 October 2008
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 14/2001/ዋኢማ/ የድሬ ሼከና ሁሴን መስጊድን በተባበሩት መንግስታት የሳይንስና ባህል ድርጅት/ዩኔስኮ/ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ። በቅርሱ አካባቢ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች የሚውል ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ የሚያስችል ቴሌቶን ለማካሄድ ስምምነት ዛሬ ተፈርሟል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሼህ ኤልያስ ሬድማን በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳስታወቁት፤ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ድሬ ሼክ ሁሴና የነጃሺ መስጊድን ጨምሮ ሌሎች እስላማዊ ቅርሶች በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገቡ አዲስ አበባ ከሚገኘው የድርጅቱ ኃላፊዎች ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል።በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተደብቀው የቆዩ ታሪካዊ ቦታዎች፣ መስጊዶችና የእምነቱ ታላላቅ ሰዎች ታሪክ ተገቢ ቦታውን እንዲያገኝና ለአገሪቱ መልካም ገጽታ ግንባታ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የገለጹት ሼህ ኤልያስ፤ ያለፉት እስላማዊ ልምዶችና ተሞክሮዎች የኢትዮጵያውያንን ተቻችሎ አብሮ የመኖር ባህል አጉልቶ እንደሚያሳይ ጠቁመዋል።በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ጃራ ወረዳ የሚገኘውና ጥንታዊ መስጊዶችን፣ ቤተ መጽሃፍትንና እስላማዊ የህንጻ ጥበብ ያረፈባቸው ግንባታዎችን ያካተተው የድሬ ሼክ ሁሴን ቅርስ በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ለቱሪዝም ኢንደስትሪው ጠቃሚ እንደሆነ አመልክተው፤ ቅርሱ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድ ታላላቅ መሻኮዎች መናኸሪያ እንደነበርም አስረድተዋል።ቅርሱን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ በሚደረገው ጥረት አካባቢውን ለጎብኝዎች በሚመች መንገድ በመሰረተ ልማቶች ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የገለጹት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፤ የቱሪስቶች ማረፊያ ሆቴሎች፣ የመንገድ፣ የውሃና የመብራት አገልግሎቶችን ለማስፋፋት በቅርቡ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።ቴሌቶኑ በድሬ ሼክ ሁሴን በሚከበረው የአረፋ በዓል ላይ እንደሚጀመርና ጥር 3 ቀን 2001 በሸራተን አዲስ እንደሚካሄድና ሃምሳ ሚሊየን ብር ለማሰባሰብ መታቀዱን ጠቁመው፤ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በቴሌቶኑ በመሳተፍ የዜግነት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።ምክር ቤቱ ለአካባቢ ነዋሪዎች ማህበራዊ ተቋማትን ደረጃ በደረጃ ለማማላት ጥረት እንደሚያደርግና ተመራማሪዎች በጃራ አካባቢ ለሚያደርጉት ምርምርም ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ሼህ ኤልያስ አስታውቀዋል።የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ አልዪ ዑመር በበኩላቸው፤ የድሬ ሼክ ሁሴን ታሪካዊ ቅርስ በዓለም እውቅና አግኝቶ ተገቢ ጥበቃና እንክብካቤ እንዲደረግለት እየተሰራ ባለው ስራ ቢሮው ተሳታፊ መሆኑን ተናግረዋል።ቅርሱን የማጥናትና ቅርሱ በሚገኝበት አካባቢ አስፈላጊ የልማት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገለጸው፤ የክልሉ መንግስት ቅርሱ ታሪካዊ አሻራውን እንደጠበቀ ለትውልድ እንዲተላለፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።እስላማዊ ቅርሶችን ለማሰባሰብና ለመጠበቅ እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው፤ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ተገቢ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል።የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶኑን ለማዘጋጀት የሚያስችለው ስምምነት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ በኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ሰርቪስ መካከል መፈረሙን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል።

1 comment:

Unknown said...

Yihim ale????????????????????

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)