October 30, 2008

የላሊበላ ደብሮች አስተዳደር በ5 ሚሊየን ብር ዘመናዊ ሆቴል አስገነባ

ደሴ፤ ጥቅምት 8/2001/ዋኢማ/ በአማራ ክልል የላሊበላ ደብሮች አስተዳደር በ5 ሚሊየን ብር ወጪ ዘመናዊ ሆቴል አስገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ።
የላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤትና የላሊበላ ደብሮች አስተዳደር ኃላፊ አባ ገብረየሱስ መኮንን ዛሬ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንዳስታወቁት፤ በላሊበላ ከተማ በ1999 ዓ.ም. የካቲት ወር ግንባታው የተጀመረው ዘመናዊና ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል በተያዘው ወር ተጠናቋል።
ሆቴሉ የተገነባው በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትና በዙሪያው የሚገኙ የቱሪስት መስህብ ሃብቶችን ለሚጐበኙ ቱሪስቶች ምቹ የመኝታና የምግብ አገልግሎት ለመስጠት ነው።
ከቤተክርስቲያናቱ ገቢ ተመድቦ ግንባታው የተካሄደው ሆቴል፤ ምቹ አገልግሎት በመስጠት የሃገርን ገጽታ በመልካም ለመገንባት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።ዘመናዊና ባህላዊ ገጽታ በመላበስ የተገነባው ሆቴል አካባቢውን ለመጐብኘት ለሚመጡ ጐብኚዎች የቆይታ ጊዜያቸው ለማራዘም ታስቦ ነው።
ሆቴሉ 56 ዘመናዊ አልጋዎች፣ ልዩ ልዩ የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች ደረጃውን የጠበቀ የመሰብሰቢያ አዳራሽና ለአስተዳደር አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ክፍሎች አሉት።
በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር 45 ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል ለመፍጠር የሚያስችል ነው ያሉት አባ ገብረየሱስ፤ ከቱሪዝም የሚገኘው ገቢ ለአካባቢ ልማት ለማዋልም የተጠናከረ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።
በተጨማሪም በ2 ሚሊየን ብር ወጪ አንድ የሃይማኖታዊ ሙዚየም ለመገንባትም ዝግጅት እያደረጉ መሆኑንም አስታውቀዋል።
የላሊበላ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ኃላፊ አቶ በለጠ ወዳጄ በበኩላቸው፤ ቤተ ክህነት ያስገነባችው ዘመናዊ ሆቴል የውጭና የሃገር ውስጥ ጐብኚዎች ተቀብለው ለማስተናገድ የሚያስችልና የአገልግሎት መስጫዎች እጥረት የሚያቃልል ሲሆን፤ የቱሪዝም ገቢ ከፍተኛ የልማት አቅም መሆኑን የሚያስመሰክር ነው ማለታቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል።

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)