ትናንት ሜይ 2/2008 ነገሩን እምቢልታ የተባለ የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ከጠቆመበት ጊዜ ጀምሮ ትልቅ የመናገሪያ ርዕስ የሆነው የቀድሞው ፓትርያርክ ለዕርቅ መዘጋጀት ጉዳይ ነው፡፡
ደጀ ሰላም ስለ ነገሩ የተረዳችው ሐሙስ ሜይ 1/200 ቢሆንም ዜናው ከርዕስ ያለ የጠነከረ መረጃ ሊገኝበት ባለመቻሉ ለአንባቢ ዕይታ ለማብቃት መታቀብን መርጣለች፡፡ ነገር ግን አንድ ጊዜ ጉዳዩ ይፋ ከሆነ ድርድሩ ይብሰልም አይብሰልም ይህንን ጥሩ ዜና ጥላሸት የሚቀቡ ከመነሣታቸው በፊት ያለንን ለማካፈል ወደድን፡፡
ሁለቱም ፓትርያርኮች ለማስማማት ቀድሞም ብዙ ጥረቶች መደረጋቸው ይታወቃል፡፡ በሊቃነ ጳጳሳት ደረጃ 3 አባቶች የተወከሉበት ቡድን ወደ አሜሪካ መጥቶ የመጣበትን ግብ ሳይመታ የአሜሪካ ድምጽን በመሳሰሉ የሬዲዮ ጣቢያዎችና በሌሎችም መገናኛዎች ሐሳቡን አካፍሎ መመለሱ ይታወሳል፡፡ በስደት ላይ ያሉትን በመወከል ሊቀ ሥልጣናት ሀብተ ማርያም ወርቅነህ ሐሳብ ሲሰጡ ሰምተናል፡፡
ከዚያ በኋላ የተሰማው ዜና የቅንጅት መሪዎችን ሽምግለው አስፈትተዋል የተባሉ የሀገር ሽማግሌዎች ነገሩን መያዛቸውን የሚያስረዳው ነበር፡፡ ብዙም ሳይገፋ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፈቃደኛ አልሆኑም በተባለ ሰበብ ነገሩ ተዳፍኖ ቆይቷል፡፡ አሁን ደግሞ ውሎ አድሮ እነሆ ድርድሩ ፍሬ ለመያዝ የቀረበ የሚመስል ዜና እየተሰማ ነው፡፡
በቤተ ክህነት የሚገኙ የደጀ ሰላም ምንጮች ዜናው ብዙም አየር እንዳልመታው ጠቅሰው ብዙዎችም ለዜናው አዲስ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ጉዳዩ በምስጢር የተያዘ ሆኖ ይሁን ወይም መጀመሪያውኑም ሐሰት ይሁን ነገ ከነገ ወዲያ የሚታወቅ ይሆናል፡፡ የፕሮፌሰር ኤፍሬምና ወዳጆቻቸው ሽምግልና ፍሬ ካስገኘ ግን ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ የምሥራች መሆኑ አይጠረጠርም፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ እንደደረሰን እናስነብባለን፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን፡፡
May 3, 2008
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Blog Archive
-
▼
2008
(151)
-
▼
May
(10)
- Islam: Today's problem to the Church of the resurr...
- Ex-patriarch Aides Reject News
- Archaeologists find Queen of Sheba's palace at Axu...
- Russian Church: E.U. Needs to Do More to Protect C...
- The Last Church Standing in North Cyprus
- With Christ in the Resurrection
- Muslim Rebels Expel Christians in Philipines
- ስለ ቀድሞው ፓትርያርክ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ
- የቀድሞው ፓትርያርክ ወደ አዲስ አበባ ሊያቀኑ ነው ተባለ
- Endless Jihad: The Truth about Islam and Violence
-
▼
May
(10)
No comments:
Post a Comment