የቀድሞው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ በሀገር ሽማግሌዎች ጥረት ነው በታባለ ሽምግልና ከስምምነት ላይ በመድረስ ወደ አዲስ አበባ ሊሄዱ መሆኑ ተሰማ፡፡
ይህ ገና ያልተረጋገጠው ዜና እንደሚያትተው ከሆነ የቀድሞው ፓትርያርክ ከፓትርያርክ ጳውሎስ ጋር ብቻ ሳይሆን ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር መስማማት ይኖርባቸዋል፡፡
ነገሩ እውነት ከሆነና የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የማይፈልጉ ክፍሎች ካላደናቀፉት በእውነቱ ታላቅ የ፣ምሥራች ይሆናል - ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፡፡ ጽንፈኛ የሆኑና በቤተ ክርስቲያን ተጠልለው የግል ጥቅማቸውን የሚጠብቁ፣ እንጀራቸውን የሚጋግሩ ክፍሎች ግን በቀላሉ ወደ ኋላ እንደማይሉ ይገመታል፡፡ ገና ካሁኑ ኢትዮጵያ ዛሬ (http://www.ethiopiazare.com)የተባለ ድረ ገጽ ዜናውን ሲያወጣው የተጠቀመበት ርዕስ እነዚህ ክፍሎች እንዲህ ዓይነቱን የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እንዴት እንደሚረዱት ያሳያል፡፡ ድረ ገጹ ‹‹ስደተኛው ፓትርያርክ ሊረቱ ነው›› በሚል ዐቢይ ርዕስ ሰፊ ዘገባ አውጥቷል፡፡ ሊረቱ ነው ማለት ምን ማለት ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያን አንድ ብትሆን ለምንድነው የሚቆጨን፡፡ ይህች ታላቅ ቤተ ክርስቲያን አንድ መሆኗ ደስ ሊለን እንጂ ‹‹ተረቱ›› ተሸነፉ እያልን ቡራ ከረዩ ልንል አይገባንም፡፡ አሁንም ቢሆን ዜናው እውነት የሚሆን ከሆነ ሌሎች የልዩነት ቡድኖች እንዳያጨናግፉት ጸሎትም፣ እንቅስቃሴም ያስፈልገዋል፡፡ አንድነትን የሚጠላ ሰይጣን ብቻ ነው፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፡፡
May 2, 2008
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Blog Archive
-
▼
2008
(151)
-
▼
May
(10)
- Islam: Today's problem to the Church of the resurr...
- Ex-patriarch Aides Reject News
- Archaeologists find Queen of Sheba's palace at Axu...
- Russian Church: E.U. Needs to Do More to Protect C...
- The Last Church Standing in North Cyprus
- With Christ in the Resurrection
- Muslim Rebels Expel Christians in Philipines
- ስለ ቀድሞው ፓትርያርክ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ
- የቀድሞው ፓትርያርክ ወደ አዲስ አበባ ሊያቀኑ ነው ተባለ
- Endless Jihad: The Truth about Islam and Violence
-
▼
May
(10)
2 comments:
እውነት በሆነና ጠላት ባፈረ
የእርቅና የሰላም ምሳሌ ይሆኑ ነበር እውነት ቢሆንማ
Post a Comment