April 5, 2008

ቤተ ክርስቲያኗ ያዘጋጀችው ዐውደ ርዕይ በወልዲያ ከተማ ተከፈተ

ወልዲያ, መጋቢት 26 ቀን 2000 (ወልዲያ) -
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሚሌኒየሙን በዓል አስመልክታ ያዘጋጀችው ዐውደ ርዕይ ዛሬ በወልዲያ ከተማ ተከፈተ፡፡
''መጪው ዘመን እንዳይቀድመን እንነሳ!''በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ዐውደ ርዕይ የቤተ ክርስቲያኗን የ2 ሺህ ዓመታት ጉዞና ለሥነ ጽሁፍ ዕድገት ያበረከተችውን አስተዋጽኦ እንደሚያንጸባርቅ በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኗ በዜማ፣በሥዕል፣በሥነ ሕንጻ በመሳሰሉት ዘርፎች ታዋቂ ሊቃውንት ማበርከቷም ተወስቷል፡፡
ለአምስት ቀናት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ የሚቆየውን ዐውደ ርዕይ የከፈቱት የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቄርሎስና የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ በላቸው ናቸው፡፡

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)