April 4, 2008

ፖፕ ሽኖዳ ሳልሳዊ በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት ያደርጋሉአዲስ አበባ, መጋቢት 25 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - የእስክንድሪያው ፖፓ እና የመንበረ ቅዱስ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ የሦስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ሚያዝያ 3 ቀን 2000 ዓ.ም አዲስ አበባ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ አስታወቀች፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ ኢትዮጵያንና አብያተ ቤተክርስቲያኗን ለመጎብኘት የሚመጡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት ነው፡፡ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅሕፈት ቤት የውጭ ግኑኝነት የበላይ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያካሂዱ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ቀደም ሲል በ1966 ዓ.ም ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል ።
በ1967 ዓ.ም የተከሠተውን የመንግስት ለውጥ ተከትሎ በቤተክርስቲያኒቱና በሀገሪቱ ላይ በተፈጠረው ችግር ምክንያት የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ግኑኝነት ለ34 ዓመታት ተዳክሞ መቆየቱን ብጹእ አቡነ ገሪማ አስታውሰዋል፡፡
የሁለቱ እኀት አብያተ ክርስትያናት ግኑኝነት መዳከሙን የተመለከቱ የአብያተ ክርስትያናቱ መንፈሳዊ መሪዎች ባደረጉት ጥረት ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ስምምነት ላይ ተደርሷል ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ባደረጉት ጥሪ መሠረት የኢትዮጵያ ኦርተዶክስ ተዋዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከብጹአን ጳጳሳት ጋር በመሆን ባለፈው ዓመት ሐምሌ 1999 ዓ.ም በግብጽ ጉብኝት ማድረጋቸውን አባ ገሪማ አስታውሰዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ግኑኝነታቸው ቀደም ሲል እንደነበረው ለመቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በሠፊው መወያየታቸውንና በተስማሙባቸው ጉዳዮች ላይም መፈራረማቸውን ገልጸዋል፡፡ የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከ330 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1967 ዓ.ም ድረስ የጠበቀ ሰላማዊ ግኑኝነት እንደነበራቸው ተመልክቷል፡፡ ሁለቱ አብያተ ቤተ ክርስቲያናት በዚሁ የረዥም ጊዜ ግኑኝነታቸው በትምህርተ ሃይማኖት፣ በምስጥራተ ቤተክርስቲያን አፈፃጸም፣ ቀኖና ቤተክርስቲያንን ጠብቆ በመኖርና በገዳማዊ ሥርአት አንድ ሁነው የኖሩ መሆናቸውን ብጹእነታቸው ገልጸዋል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ አርብ ሚያዝያ 3 ቀን 2000 ዓ.ም በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያና በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በካህናትና በምእመናን ደማቅ አቀባበል ይደረግላቸዋል፡፡ የተለያዩ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንደሚጎበኙም ተገልጿል።

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)