March 6, 2008

Historical Churches RenovatedHistorical Churches older than Lalibela are renovating.

ደሴ የካቲት 27/2000/ዋኢማ/ በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ በላሊበላ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ ታሪካዊና ኃይማኖታዊ ቅርሶች በዝናብና በፀሐይ ከሚደርስባቸው ጉዳት ለመከላከል የሚያስችል እንክብካቤና ጥገና እያደረገ መሆኑን የላሊበላ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ሃብቶች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

በጽሕፈት ቤቱ የቱሪዝም ሀብቶች ማስተባባሪያ ቡድን መሪ አቶ ሀብታሙ ተስፋ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንዳስታወቁት፤ በላሊበላ ከተማ ዙሪያ በገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ ሰባት ጥንታዊና ሀይማኖታዊ ቋሚ ቅርሶች ጥገናና እንክብካቤ እየተደረገላቸው ነው።

ጥገና እየተደረገላቸው ያሉት አብያተ ክርስቲያናትና ቋሚ ቅርሶች በዕድሜ ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የሚቀድሙ መሆናቸውን ቡድን መሪው ገልፀው፣፤ በዝናብ፣ በፀሐይና ነፋስ ከሚደርስባቸው ጉዳት ለመከላከል የሰንበሌጥና እንጨት ክዳኖቻቸውን ታሪካዊነታቸውን እንደጠበቁ የማደስና የማጠናከር ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።

ለአብያተ ክርሰቲያናቱና ታሪካዊ ቅርሶች እድሳትና ማጠናከሪያ የሚውል 153ሺ ብር ከፌዴራል ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን መመደቡን አስታውቀዋል።

ቋሚ ቅርሶቹ በበርካታ የውጭ አገር ቱሪስቶች የሚጐበኙና ከፍተኛ የቱሪዝም ገቢ ምንጭ መሆናቸውም ጠቅሰው፣ ቋሚ ቅርሶቹን ከሰው ሰራሽና ከተፈጥሮ ጉዳት ለመከላከል ከጊዜያዊ መጠለያ በተጨማሪ ዘላቂ መጠለያ እንዲኖራቸው ለማስቻል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑን መሆኑን ገልፀዋል።

እድሳትና እንክብካቤ እየተደረገላቸው ካሉት አብያተ ክርስቲያናት መካከልም ገነተማሪያም፣ አሸተንማሪያም፣ ቀኒት ሚካኤል፣ ካርቲና ሚካኤልና ጊልባና ጊዮርጊስ እንደሚገኙበት ቡድን መሪው መናገራቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል።

The above news is excerpted from the government affiliated news agency Walta.

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)