February 12, 2008

እውነተኛ አባቶቻችን የት ሄዱ?

የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ በእሑድ ፌብሩዋሪ 11/2008 ዝግጅቱ የሚገርም ፕሮግራም አቀረበልን፡፡ ፓርትያርካችንን በአዲስ አበባ ‹‹ስለ ድንቅ አገልግሎቸው›› ከሸለሙት ግለሰቦች መካከከል አንደኛውና የዚህ ‹‹ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ታላቅ አስተዋጽዖ›› ያደረጉ የቤተ ክርስቲያን ሰዎችን ለመዘከር የተንቀሳቀሰው ቡድን አባል የሆኑትን አቶ ሙሉጌት አሥራተ ካሣን አነጋግሮ አቀረበልን፡፡ ስለዚህ አነጋጋሪ የሽልማት ጉዳይ ሪፖርተርየዘገበውን ከደጀ ሰላም አስተያየት ጋር አስተባብረን ማቅረባችንን ታስታውሳላችሁ፡፡

መቸም ለቤተ ክርስቲያናችን መልካም ሥራ የሠራ ማንም ሰው በምድር ባይሸለም በሰማይ መሸለሙ ስለማይቀር በምድር ብንሸልመው እንመሰገናለን እንጂ አንነቀፍም፡፡ ነገር ግን የአቡነ ጳውሎስ ሽልማት እንኳን እኛን እርሳቸውንም የሚያሳምን አይመስለንም፡፡ ስለየትኛው አገልግሎታቸው እንሸልማቸው?
1ኛ. ቤተ ክርስቲያን አንድነቷ ተናግቶ ከ2 እንድትከፈል ስላደረጉ?
2ና. የቤተ ክርስቲያን አንጡራ ሀብት የሆኑ ሊቃውንትን መቀመጫ ስላሳጡ?
3ኛ. ዘረኝነቱን ዛሬ አሜሪካ ተሰድጃለሁ ከሚሉት ከነ ሊቀ ሥልጣናት ሀብተ ማርያም ወርቅነህ አስበልጠው በቤተ ክህነቱ ስለተከሉት?
4ኛ. ሹመት በዕውቀት ሳይሆን በጉቦ እንዲሆን ስላደረጉ?
5ኛ. ሊቃውንት እየተሰደዱ፣ ያልተማሩ አፈጮሌ መነኮሳት ከአዲስ አበባ ጀምሮ ያለውን የደብር አስተዳሪነትና የቤተ ክህነት ኃላፊነት እንዲቆጣጠሩት ስላደረጉ?
6ኛ. አክራሪ እስልምና ቤተ ክርስቲያን አንገት ላይ ካራውን አስቀምጦ ከዛሬ ነገ አረድኩሽ በሚልበት ወቅት ቤተ ክርስቲያን እንዳትጮህ አፏን ስላፈኗት?
6ኛ. ከመንግሥት ጋር አብረው ምዕመናን በአባቶቻቸው እንዲያፍሩ ስላደረጉ?ስለየትኛው እንሸልማቸው? ይህ ሁሉ ቀልድ ነው፡፡ ሸላሚዎቹም ቢሆኑ ከቤተ ክርስቲያን እየተዘረፈ ካለው ሀብት ተካፋዮች ከሆኑ መልካም፡፡ በቅንነት ከሆነ ያደረጉት ግን እንዲያው በከንቱ ደከሙ፡፡

ኦርቶዶክሳውያን ግን በዚህ ዓይነቱ አሳፋሪ ተግባር እና አንገት አስደፊ አባት ተስፋ ልንቆርጥ አይገባንም፡፡ ዛሬም ሰማይን ከምድር በጸሎታቸው የሚያስታርቁ ቅዱሳን አባቶች አሉን፡፡ በጸሎታቸው ገቢረ ተዓምራትን የሚያደርጉ፣ በትምህርታቸው ጥራት የተመሰከረላቸው፣ ለሥጋቸው ሳይሆን ለነፍሳቸው የኖሩ አበው አሉን፡፡ ከፓትርያርኮችም ቢሆን እነ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን፣ እነ አቡነ ቴዎፍሎስን ማስታወስ ይገባል፡፡

ከሊቃውቱም እንደነ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ (1885-1962)፣ እንደነ መምህር አካለ ወልድ (1824-1912 ዓ.ም) ያሉትን አስታውሱ፡፡

ይማሯል እንዳካልዬ፣
ይዋጓል እንደ ገብርዬ›
› የተባለላቸው፡፡

ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩ ጊዜ

አፈር መልሱ እንጂ ድንጋይ ለምናችሁ፣
የቀለም ቀንድ ነው ትሰብሩታላችሁ፤
መምህር አካለ ወልድ ቄሱ የት ደረሱ፣
ጎንደር ወረዱ ወይ ሥልጣን ሊመልሱ፣
እስቲ ሰፌድ ስጡኝ አፈሩን ላንፍሰው
ያንን ሁሉ ቀለም ወዴት አፈሰሰው?

ተብሎላቸው ነበር፡፡


በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ታላቁ ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩስ እንዴት ይዘነጋሉ?

በቅርቡ የታተመ (1999ዓ.ም) ‹‹ፍሬ ሊቃውንት፡- ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትና ስብከቶች›› የተሰኘ መጽሐፍ ካገኛችሁ አንብቡት፡፡ ቢያንስ ያለፈውን እያሰብን እንድንጽናና ያደርገናል፡፡

በጵጵስና እና በፕትርክና ደረጃ ስለደረሱ አባቶች ታሪክ ደግሞ ዲ.ን መርሻ አለኸኝ በተባሉ ፀሐፊ በ1997 ዓ.ም የተጻፈ ‹‹ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን›› የተሰኘ መጽሐፍ አንብቡ፡፡

እንዲህ ዓይነቱ ልብን የሚነካ ድርጊት ሲፈጸም እንዲህ ያስብለናል፡፡

ሊቃውንቱ ሁሉ ከወዴት ደረሱ፣
በኃጥኡ በአባሲው ሲፈርስ መቅደሱ፣
ፓትርያርክ ተክልዬ ይምጡ ይናገሩ፣
የፓትርያርክነት ይኸ ነው ወይ ግብሩ?ቸር ወር ያሰማን

1 comment:

Anonymous said...

IN THE NAME OF GOD, we need fathers of quality.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)