February 14, 2008

ፓትርያርኮቻችን

ከዚህ ጽሑፍ ቀደም ብለን ባወጣናቸው ጽሑፎች በአሁ ጊዜ ፓትርያካችን ያደረጉትን ነገር አንስተን መጠቃቀሳችን ይታወሳል፡፡ እንዲያው በደፈናው አሁን ያለውን ከመተቸት፣ ለሽልማቱም ቢሆን ማን ምን ሠራ የሚለውን ለማወቅና ለማሳወቅ ስለ ቀደሙት ፓትርያርኮቻችን መጠነኛ ዳሰሳ ለማድረግ ወሰንንን፡፡ መዳሰስ ብቻ ሳይሆን አንባብያን እስካሁን ካሉት አባቶች በሥራቸው ትጋት፣ በአገልግሎታቸው የበለጠ የሚያመሰግኗቸውን እንዲመርጡ የድምጽ መስጫ እናዘጋጃለን፡፡ ከዚያ አስቀድሞ ግን ማንነታቸውንና የሠሩትን ሥራ ማወቅ ስለሚገባ ከዛሬ ጀምሮ አንድ አንድ እያልን እናቀርባለን፡፡

እነዚህም አምስት ፓትርያርኮቻችን የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ (1884-1963 ዓ.ም)


2. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ (1902-1971 ዓ.ም)፣

3. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (1910-1980 ዓ.ም)
4. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ እና
5. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ናቸው፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፡፡

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)