February 12, 2008

ፓትርያርኩ ፎቷቸውን በየቤተ ክርስቲያኑ ቅጽረ ግቢ ማሰቀላቸው አወዛገበ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 5ኛ ፓትርያርክ እንደተለመደው ሌላ አወዛጋቢ ተግባር ፈጽመዋል፡፡ ፎቷቸውን በትልልቅ ቢል ቦርድ መሰል ማስታወቂዎች ላይ በማስለጠፍ በየቤተ ክርስቲያኑ ቅጽረ ግቢ እያሰቀሉ ነው፡፡ ይህንኑ በተመለከተ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ 3 ጽሑፎች የወጡ ሲሆን ሁለቱ ጉዳዩን ይቃወማሉ፣ አንደኛው ደግሞ ይደግፋል፡፡ ውይይቱን የጀመረው የመጀመሪያው ጽሑፍ በጋዜጣው ድረ ገጽ ላይ የለም፡፡ ሁለቱን ግን እዚህ ላይ ያገኟቸዋል፡፡
1. የአመፅ አባት የወለደው የጥፋት ብዕር በወልደ ሥላሴ ዘብሔረ ካኑ

2. ባላደራ ጮኸ ከተራራ! እስከማዕዜኑ ተሐነክሱ!(እስከመቼ ታነክሳላችሁ)ከዮሐንስ አርአያ

. ...አንድ የሃይማኖት አባት ቤተክርስቲያን ሲመርቅ በ60ና 70 ሺህ ብር ከጊዮንና ከዋቢ ሸበሌ ካልተደገሰ አልመጣም? ሲል በየገጠሩ እየፈረሱና እየተበተኑ ያሉትን ቤተክርስቲያናትና ምዕመን አስተውሏል ማለት ይቻላል? እነዚያንስ ካልጠበቀ ኃይማኖት ጠብቋል ማለት ይቻላል? .....

....በገጠር ያሉ ገዳማትና አድባራት በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተዘጉ ባሉበት ወቅት የሕዝብ ገንዘብ ግን ለግለሰቦች ይረጫል፤ ለቀረቡ ሰዎች መሸለሚያ ይሆናል፡፡ ዛሬ ደግሞ እንሸልምዎት በሚሉ “ወዳጆች” አቅራቢነት ልሸለምበት ሲባል ለእምነታችን አያስፈራምን፡፡ ......

..የቤተክርስቲያን የውጭ ግንኙነትም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑ አይሳትም፡፡ ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ጋር በሚደረጉ ጉባኤዎች የኢትዮጵያ ተሳትፎ እስከዝምታ የደረሰ ነው፡፡ የኦሬንታል፣ የምሥራቅ ኦርቶዶክሶችና ካቶሊኮች በጳጳሳት ደረጃ ሲወያዩ ብዙውን ጊዜ የኢትዮጵያ ውክልና ከማኅበረ ካህናት የዘለለ አይደለም፡፡ ለምን? ሲኖዶሱ ያቀፋቸው አብዛኞቹ ጳጳሳት የዕውቀት ደረጃ እምን ድረስ ቢሆን ነው?......

...የኢትዮጵያን ሚሌኒየም አስመልክቶ የተለያዩ የዓለም ሃይማኖት መሪዎችን ጋብዞ ... የተካሄደው ጉባኤ ወደ ዓለማዊነት ያደላ በቤተክርስቲያን፣ በክርስትናና በምእመኖች ላይ እየደረሰ ያለውን ዓለማቀፍ ችግር ላይ ያላተኮረ በመሆኑ ቅሬታን ያስከተለ ነበር፡፡ ከመስኮብና ከአንዳንድ አገራት የመጡት የኦርቶዶክስ ልዑካን በነገረ መለኮት ዙሪያ፣ በአክራሪዎች ሳቢያ በክርስትና ላይ እየደረሰ ባለው ችግር ዙሪያ እንወያይ የሚል አጀንዳ እንዲቀርብ ቢጠይቁ በጎ ምላሽ ባለማግኘታቸው ቅሬታ ማሰማታቸውን አንዳንዶችም ከውይይቱ ማቋረጣቸው ያየነው፣ የሰማነው ጉዳይ ነው፡፡

....በፓትርያርክ ጳውሎስ ዘመን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከምን ጊዜውም የከፋ ችግር አጋጥሟታል፡፡ ፓትርያርኩ 1984 ዓ.ም ላይ ከመንበሩ ሲቀመጡ ያስቀረጹት “ነዋ ወንጌለ መንግሥት” (እነሆ የመንግሥት ወንጌል) ዓርማ ከተግባር ይልቅ መፈክር ሆኖ ለመቅረቱ ብዙ ማስረጃ መደርደር አያስፈልግም፡፡.....

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)