January 24, 2008

ትግራይ ውስጥ አዲስ ታሪካዊ ስፍራ ተገኘ

The Reporter Newspaper
WEDNESDAY, 23 JANUARY 2008
ምሥራቅ ትግራይ ውቅሮ አካባቢ ጥናታዊ ቅርሶችን የያዘ ስፍራ ማግኘቱን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ከበደ አማረ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት ከወቅሮ ወደ አብርሃ አድብሐ በሚወስደው መንገድ፣ ውቅሮ ቆዳ ፋብሪካ አካባቢ የተገኘው ታሪካዊ ሥፍራ (መካነ ታሪክ) የቅድመ ክርስትና አሻራዎችን የያዘ ነው፡፡ በክልሉ ባለሙያዎች በተከናወነው የአሰሳ ቁፋሮ ከ30 ሴንቲ ሜትር እስከ አንድ ሜትር ባለው ጥልቀት ውስጥ የተገኙት ሦስት ዐበይት ቅርሶች ናቸው፡፡

እንደ ኃላፊው ማብራሪያ አንደኛው ቅርስ የአክሱም ሐውልቶችን ቅርፅ ይዞ የመሠረቱን በርና መስኮት የሚያሳይ ነው፡፡ ሌላኛው ቅርስ ብሔራዊ ሙዝየም ውስጥ ያለውንና የተቀመጠችውን ሴት ሐውልት (ሐውልቲ) የሚመስል ቅርፅ ያለው ቢሆንም ጭንቅላቷ አልተገኘም፡፡ ሦስተኛው ቅርስ ደግሞ የመስዋዕት መሰዊያ በአራት ማዕዘን የተጠረበ ድንጋይ ሲሆን በሁሉም ቅርሶች ላይ በጥንታዊ የሳባ ቋንቋና ፊደል የተፃፈ ጽሑፍ ይታይባቸዋል፡፡ በመሰዊያው ድንጋይ ላይ የመስዋዕቱ ደም ቁልቁል የሚወርድበት ቅርፅ እንዳለውም ታውቋል፡፡

መሰዊያውን በተመለከተ ያለው መላምት ቦታው ከክርስትና እምነት በፊት እንደነበሩት የሃ እና ሌሎች አካባቢዎች ከኦሪት እምነት ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡ አንዳንድ የታሪክ አዋቂዎች እንደሚሉት የሴትየዋ ምስል ከጣኦት ምስል ጋር ሲያያይዙት አክሱም ሐውልት ቅርጽ የሚመስሉት በሮች ወደ እምነት ቦታው ሲገባ ጸሎት ለማድረስ መሰዊያው ቦታ ሰውተው እንደሚገቡ ገና ያልተጣራ መላምት መሆኑን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡
መካነ ታሪኩ ከድሮ ጀምሮ የአርኪዮሎዢ ስፍራ መሆኑ ይታወቅ እንደነበርና በተለይ በአካባቢው ኅብረተሰብ ዘንድ በአፈ ታሪክ የዮዲት መካነ መቃብር ተብሎ እንደሚነገር ኃላፊው አውስተዋል፡፡

ቦታውን የአካባቢው ገበሬዎች ይጠብቁት የነበረ ሲሆን በአካባቢው ምንም ዓይነት ሥራ እንዳይሰራ ይከላከሉ ነበር፡፡ የታሪካዊ ሥፍራውን የወደፊት እጣ ፈንታ አስመለክቶ ኃላፊው እንዳብራሩት የሙከራ ቁፋሮውንና ግኝቱን ቢያካሂዱም ቀጣይና የተጠናከረ ምርምር ለማካሄድ ግን አቅማቸው እንዳልሆነ ገልፀው፣ ተመራማሪዎችና የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ክትትል እንዲያደርጉበት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ትግራይ ውስጥ ጥንታዊ ቅርሶች በትንሽ ቁፋሮ የሚገኙ በመሆናቸው በተቻለ መጠን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉና በኢትዮጵያውያን የሚመሩ ተቋሞች እንደ መቀሌ፣ አዲስ አበባና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ጥናት ቢያደርጉበት ጥሩ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)