January 10, 2008

በአሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ክርስትና ሃይማኖትን ያንጸባርቃሉ ያላቸውን ወንበሮች በሙሉ ከኤምባሲው አነሣ

በአሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ክርስትና ሃይማኖትን ያንጸባርቃሉ ያላቸውን ወንበሮች በሙሉ ከኤምባሲው አገልግሎት መስጫ አካባቢዎች ማንሣቱ ታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት እየተሠሩ ባህላዊነታቸውን ጠብቀው የአገራችንን ማንነት የሚያስተዋውቁት የታሪክ መገለጫዎች በተለይም በአክራሪ ሙስሊሞች በኩል ነቀፋ እና ተጨቁነናል ለሚሉት አባባላቸው በምሳሌነት የሚጠቅሱት ነበር፡፡ መንግሥት ሙስሊሞችን በማባበል ፖሊሲው በመግፋት በአምባሳደር ሳሙኤል አሰፋ አጋፋሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ባለፈው ሚያዚያ 1999 ዓ.ም ለጻፉት ደብዳቤ መልስ እየሰጠ ይመስላል፡፡ ጉብኝትም ማድረጋቸውን በደብዳቤያቸው ጠቅሰዋል፡፡

ምናልባትም ይህ ኤምባሲው የፈጸመው ድርጊት የመጀመሪያው ትንኮሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገ የሚከተሉ ሌሎች ርምጃዎች መኖራቸውን እናውቃለን፡፡

አንዲት አገር የተለያዩ ሃይማኖታዊ ቅርሦች ይኖሯታል፡፡ ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር ፈቃድ ዓለም ያደነቃቸው ክርስቲያናዊ ሀብቶች ባለቤት ልትሆን ችላለች፡፡ ይህ የማይታበል ሐቅ ነው፡፡ ይህንን የሺህ ዓመታት ታሪክ ለመሰረዝ መነሣት ምን ይባላል? ዛሬ ወንበሮቹን አነሡ ነገ ደግሞ ምን ሊያደርጉ ነው? እኛስ ዝም የምንለው እስከ መቼ ነው፡፡ በእውነቱ መንግሥት ሊያስብበት ይገባል፡፡ ‹‹አክራሪ ዲያስፖራዎች ናቸው›› ብሎ የክርስቲያኖችን ጥያቄና ስሜት ባይገፋው መልካም ነው፡፡

7 comments:

Anonymous said...

The eternal dream of the extremist is to remove Christianity from the mentality, physical evidence and the talk of the people .I think as a Christian we are giving up the joined existence of Ethiopia and Orthodox Christianity.And they are gaining the strength to say Christianity is just a past history read the article on Ethiopian first.
What scares me the most is our zemeta zemmm Abatochem zemm Lejochem zemm

Anonymous said...

You are right my friend. Everybody keeps quiet. especially the Orthodox people are very ignorant of what the fanatics are doing to our Church. Wake up guys, wake uuuuuuuuuuuuuuuuuuuuP!!!!!!

Unknown said...

Thank you dear all.

Anonymous said...

ወንበሮቹ የተነሱት አርጅተው ሊሆን ስለሚችል በቂ መረጃ እስካላመጣህ ድረስ መልእክትህ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት የለውም እንዲሁም የባሰ በህዝቦች መካከል ጥርጣሬና ሁከት መፍጠር እንዳይሆንብህ መጠንቀቅ አለብህ ሀገር የሚያድገው በመቻቻልና በትእግስት ብቻ ነው ::

ለምሳሌ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሶማሊያ የሚገኙ ሙስሊም ወንድሞቻቸው ደም በግፍ በከንቱ እየፈሰሰ በትእግስት ከማሳለፍ በስተቀር ሌላ አማራጭ አልተከተሉም ::

ታድያ ለሙስሊሞች ደም ምንም ደንታ የሌለውን መንግስት ዛሬ አንተ ለሙስሊሞች ያደላል ብለህ በአሮጌ ወንበር ብትወነጅለው አመለካከትህ አርቆ ማስተዋል የተሳነው ጥሬ እንዳይሆንብህ ::

Anonymous said...

Previous Anonymous
See that is the problem.The brotherhood you feel is for muslims only.There are people dying in Ethiopia too.What do you say about that?For you Islam is a nationality not just religion.You would not feel the same for your fellow Ethiopian unless that person is a muslim.But any Ethiopian Christian would consider you a brother and we have seen it.We are well aware of the fact so don't bother to explain

Anonymous said...

It is an Alert!...NIKU
It is one thing, we will see a lot tomorrow if we don't say something now.
According to ethiopian histry, Christianity and Ethiopia have thousands of years corelation(beleive it or not since 340AD). But the embassy is trying to destroy the real image of the country so we need to demonstrate our concern otherwise we will lose the TRUE Ethiopia.
Little John

Anonymous said...

Please Muslim brothers, Prepair your minds for change.Leave unnecessary thoughts.Think about humanities.Life is not relign.But,it's a part of life.Also Orthooxians respect others.Ethiopia is one.Their peopls are one.Stand for revolution.The moment time is the time of change.pls...pls...pls...

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)