January 7, 2008

በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ የነበረው የመዝሙርና የትምህርት ፕሮግራም ተከለከለ

ሪፖርተር ጋዜጣ እንደ ዘገበው
እስራ አመቱን /ሚሌኒየሙን/ ምክንያት በማድረግ በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ የነበረው የመዝሙርና የትምህርት ፕሮግራም ተከለከለ፡፡ ማህበረ ቅዱሳንና ቤተክህንት በመተባበር ትናንት ሊያካሂዱት የነበረው መንፈሳዊ ዝግጅት የተከለከለው ከፖሊስ በመጣ ትዕዛዝ ነው፡፡
የእስራ አመቱ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቄስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም ለሪፖርተር ጋዜጣ የእገዳ ትዕዛዝ መምጣቱ እንቆቅልሽ ሆኖባቸዋል፡፡

ዝግጅቱን ለማካሄድ ኮሚቴው ዝርዝር ጉዳዩን በማሳወቅ ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ፈቃድ ማግኘቱን የገለፁት ቄስ ዶክተር ሙሉጌታ ለዝግጅቱ ከፍተኛ ወጪ ከወጣና ህዝቡ ፕሮግራሙን እንዲከታተል በቴሌቪዥን ማስታወቂያ ከተላላፈ በኋላ በፖሊስ ትዕዛዝ ፕሮግራሙ እንዲሰረዝ መደረጉ ተገቢ አለመሆኑን አመልከተዋል፡፡

ቄስ ዶክተር ሙሉጌታ እንዳሉት ትናንት ከ8፡00 ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ ታስቦ ለነበረው ዝግጅት በመቶ ሺ የሚቆጠር ገንዘብ ወጥቷል፡፡ ለመድረክ ግንባታውም ከ16ሺ ብር በላይ ወጥቷል፡፡

..አሰባሳቢ ኮሚቴው ፕሮግራሙን እንዲሰርዝ የሚገልጽ ደብዳቤ እስከ ትናንት ድረስ አልደረሰውም.. ያሉት የኮሚቴው ሰብሳቢ በመጨረሻ ሰዓት ላይ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊሶች ዝግጅቱ ወደሚካሄድበት ቦታ በመሄድ የመንፈሳዊ ዝግጅቱ በጃን ሜዳ እንዲካሄድ ማዘዛቸው እንዳስገረማቸው ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም ..ፕሮግራሙን የምናካሂደው እኛ ነን፡፡ መቀየር ካስፈለገም ተስማምተንና ተነጋግረን መሆን አለበት፡፡ ልናዘጋጀው ባላሰብንበት ቦታስ ፕሮግራሙን እንዴት ልናካሂድ እንችላለን?.. ብለዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክተን ያነጋገርናቸው የፌደራል ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ደምሳሽ በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ የነበረው መንፈሳዊ ዝግጅት የተከለከለው በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በተፃፈ ደብዳቤ መሰረት መሆኑን ገልፀውልናል፡፡

እንደ ኮማንደር ገለፃ በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ የነበረው ዝግጅት ወደ ጃን ሜዳ እንዲዛወር ተደረገ እንጂ አልታገደም፡፡ ዝግጅቱ በጃን ሜዳ እንዲካሄድ የተወሰነውም ቀደም ሲል በመስቀል አደባባይ እንዲካሄድ የተያዘ ሌላ ዝግጅት በመኖሩና የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት በማሰብ መሆኑን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

መንፈሳዊ ፕሮግራሙ በመስቀል አደባባይ እንዳይካሄድ የሚገልጽ ደብዳቤ በግልባጭ ለፌደራል ፖሊስ እንደተላከ የገለፁት ኮማንደር ደምሳሽ በመስተዳድሩ ውሳኔ የፕሮግራሙ አዘጋጆች መስማማታቸውን ተናግረዋል፡፡

በኃይሌ ሙሉ

3 comments:

Anonymous said...

Thank you for this information. This article/event is another indication that the Tewahedo Christian faith in Ethiopia has decreased in priority in the world of politics, economics and society in general. Please keep the information coming, perhaps it can awaken a Noah, God can do wonders with one person. The question I have is, how long has the program of celebrating Gena in Meskle square been going on? (In years) Egziabher yestelign

Anonymous said...

The meskel square has always been a place(spot) where the EOTC celebrates any kind of festival or ceremony.The church is entitled to use it.Celebration like Meskel is performed each year at the square but I believe this program for Gena is new but still it is not right to stop a program that has already a permission to go on

Anonymous said...

Thanks 'Lom'...yes I agree, if the program was approved it should have been allowed to move on. But this is the way the government has been dealing with events it does not approve off, I am not saying they are anti religious but perhaps the place was the problem, or the event or even both, I have no idea. What can be done about this now or even when planning for the future? From my experience I think we need to really focus on Love to fight our battles. Love towards God, within ourselves and towards others. We can see what love is in 1cor 13. Love is not just holding hands singing 'kumbaya' and passivity. Its mysterious type of action that is not always visible. One Abbat told me, we have no power in our Church because we are not united in Love. Love is the greatest force. We need to work on accepting love to work through us individually, then once it starts to work within us, it will flow out to others, and vice versa. Its God who is love, and God doing the work. We just need to walk in His law for all this to happen...Just some thoughts.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)